Administrator

Administrator

ህገወጥ መድሃኒቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሣሪያ ለጤና ጥበቃ ሚ/ር አበርክቷል
በህክምና፣ በመድሃኒትና በኬሚካል ዘርፍ አዳዲስ ምርቶችን በማቅረብ የሚታወቀውና ዋና መ/ቤቱ በጀርመን አገር የሆነው መርክ የተሰኘው ድርጅት በኢትዮጵያ ሥራ ጀመ፡፡ ይህ በአዲስ አበባ ከተማ የተከፈተው አዲስ ድርጅት ሱዳንን፣ ኢትዮጵያንና ፈረንሳይኛ ተናጋሪ የሆኑ የአፍሪካ አገሮችን የሚየገለግልና በቀጠናው የመጀመሪያው ማዕከል ነው ተብሏል፡፡
ድርጅቱ በትሮፒካል አካባቢዎች እምብዛም ትኩረት ባልተሰጣቸውና እንደ ቢልሀርዚያ ያሉ አደገኛ በሽታዎችን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም የድርጅቱ ሃላፊዎች ከትናንት በስቲያ በሸራተን አዲስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል፡፡
ድርጅቱ በመሠረተው የዓለም አቀፍ ፋርማ ሄልዝ ፈንድ ፕሮግራም ስር ሁለት አነስተኛ ላብራቶሪዎች ለጤና ጥበቃ ሚ/ር ያበረከተ ሲሆን መሣሪያዎቹ ህገወጥና የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ መድሃኒቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡
መርክ በጀርመን አገር በ1968 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰራ በህክምና፣ በመድሃኒትና በኬሚካል ዘርፍ የተሰማራ አንጋፋ ኩባንያ ነው፡፡

Saturday, 10 May 2014 12:32

ውሀና ጠቀሜታዎቹ

ከመተኛትዎ በፊት አንድ ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ፡፡ ስትሮክን እና የልብ ህመምን ለመከላከል ይረዳዎታልና
ጠዋት ከእንቅልፍዎ እንደተነሱ 2 ብርጭቆ ውሃ ከጠጡ ውስጣዊ የሰውነት አካላትዎን ለማነቃቃት ያግዝዎታል፡፡
ሻወር ከመውሰድዎ በፊት አንድ ብርጭቆ ውሃ የሚጠጡ ከሆነ ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመከላከል ይጠቅሞታል፡፡
ከምግብ በፊት አንድ ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ለምግብ መንሸራሸር ይረዳል
ምግብ ከመመገብዎ 30 ደቂቃ በፊት በቂ ውሃ ይጠጡ፡፡ ብዙ ባለመመገብ የሰውነት ክብደትዎን ለመቀነስ እንዲችሉ ያግዞታል፡፡

የጓደኛዎን ወይም የጐረቤትዎን የፌስቡክ “ፓስወርድ” ለማግኘትና ገመናውን ወይም ሚስጥሯን መበርበር ይፈልጋሉ?

ቀላል ነው፡፡ አንድ መስመር በማትሞላ ጽሑፍ የልብዎን ማድረስ ይችላሉ፡፡ አንድ ደቂቃ አይፈጅም፡፡ “ኮፒ” ከዚያ

“ፔስት” ማድረግ ብቻ ነው ከእርስዎ የሚጠበቀው። ከሁለት ሰዓት በኋላ፤ የጓደኛዎ ወይም የጐረቤትዎ ፓስወርድ እጅ

ይገባል…
በኢንተርኔት የተሰራጨው መልዕክት አጭርና ግልጽ ነው፡፡ በዚሁ መልዕክት የተማረኩ ብዙ ህንዳዊያን ወጣቶች በሁለት

አቅጣጫ የሚመነዘር ትርጉም እንዳለው ልብ አላሉትም፡፡ የሰዎችን ፓስወርድ በቀላሉ መስረቅ ትችላለህ - ይሄ አንደኛው

ትርጉም ነው፡፡ ሌሎች ሰዎች ያንተን ፓስወርድ በቀላሉ መስረቅ ይችላሉ፡፡ ይሄንን ሁለተኛ ትርጉም ልብ ለማለት ጊዜና

ፍላጐት ያልነበራቸው በሺ የሚቆጠሩ ህንዳዊያን፤ የጓደኞቻቸውን ወይም የስራ ባልረቦቻቸውን ገመና ለመበርበር

ቸኩለዋል። እውነትም ነገርዬው ቀላል ነው - “ኮፒ - ፔስት”… “ኮፒ - ፔስት”
በእርግጥም፤ ያቺ አንድ መስመር የማትሞላ ፅሁፍ የዋዛ አይደለችም፡፡ ፓስወርድ ለመስረቅ ተብላ የተቀመመች ናት፡፡

ግን…እዚህ ላይ ነው፤ ታሪኩ ድንገት የሚታጠፈው - “ሰርፕራይዝ” እንደሚባለው፡፡
“ኮፒ - ፔስት” ቀላል ቢሆንም፤ ኮምፒዩተራቸው ምን እያደረገ እንደሆነ አያውቁም። ፓስወርድ እየተሰረቀ ቢሆንም፤

ከሌላ ሰው ተሰርቆ እየመጣላቸው አይደለም፡፡ ከሁለት ሰዓት ጥበቃ በኋላ ምን እንደሚፈጠር ለማየት ነው የሚጠብቁት።

የራሳቸው ኮምፒዩተር፤ የራሳቸውን የፌስቡክ ፓስወርድ አፈላልጐ ለማግኘት፤ ከዚያም ያንን ፓስወርድ ወደሌላ ሰው

አድራሻ ለመላክ ትንሽ ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡ ለካ፣ የሌላ ሰው ፓስወርድ ለመስረቅ ሳይሆን፣ የራሳቸው ፓስወርድ እንዲሰረቅ

ነው በፈቃደኝነት የተባበሩት፡፡ “አጭር ምጥን ብላ የተቀመመችና የተራቀቀች ስርቆት” ይሉሃል እንዲህ ነው፡፡ አንድ ሰው

የሆነ ጊዜ ላይ የፈጠራትና ያሰራጫት ዘዴ ናት፡፡ ከዚያ በኋላማ የሆነ ቦታ ሆኖ፣ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ

የፌስቡክ ፓስወርዶች በአድራሻው እየተላኩ ፓስወርዶችን መሰብሰብ ነው፡፡
ከጥቂት ወራት በፊትም በተመሳሳይ የማታለያ ዘዴ የፓስወርድ ስርቆት እንደተካሄደ የገለፀው ገልፍ ኒውስ እንደሚለው፤

100ሺ ያህል የፌስቡክ ደንበኞች ፓስወርድ ተሰርቆባቸዋል፡፡ ቁምነገሩ ግን፤ እበላለሁ ሲሉ መበላት፤ እነጥቃለሁ ሲሉ

መነጠቅ ይኖራልና እንጠንቀቅ የሚል ነው፡፡
ከሰሞኑ ከወደ ፊሊፒንስ የወጣውም ጉድ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡ በፌስቡክ አለም፤ ማን ምን እንደሆነ በእርግጠኛነት

ለማወቅ ያስቸግራል። ለዚያም ነው፤ በእውነተኛው አለም በሰው ፊት የማንናገራቸውና የማናደርጋቸው ነገሮች፤ በፌስቡክ

አለም ለመናገርና ለማድረግ ብዙዎች የሚደፋፈሩት። ስኮትላንዳዊው ታዳጊ፣ በፌስቡክ የአንዲት ቆንጅዬ ፎቶ በማየት

ተማርኮ ነው ጓደኝነት (ግንኙነት) የጀመረው፡፡ ብዙም ሳይቆይ የግል ወሬ ማዘውተር መጣ፡፡ ፎቶዎችን ተራ ፎቶ ሳይሆን

ከላይም ከታችም አጋልጠው የሚያሳዩ ፎቶዎችን ተለዋውጠዋል። መኝታ ቤት ውስጥ በወሲብ ጊዜ የሚያጋጥሙ አይነት

ወሬዎችንም ለምደዋል፡፡
ይሄ ሁሉ የሆነው በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ለታዳጊው ስኮትላንዳዊ ሰማይ ምድሩ የተገለባበጠበትም በአጭር ጊዜ

ውስጥ ነው። “ገንዘብ ካላመጣህ፤ ያ ሁሉ ያወራነውን ነገር በኢንተርኔት በፌስቡክ እለቀዋለሁ” የሚል ማስፈራሪያ

ደረሰው፡፡
“በጓደኝነት የፌስቡክ ግንኙነት የፈጠረው፤ ቆንጅዬ ፎቶ በማየት ከተማረከላት ሴት ጋር አይደለም፡፡ ሰዎችን

በማስፈራራት ገንዘብ ከሚዘርፉ የፌስቡክ ማፍያዎች ወጥመድ ውስጥ አስገብተውታል፡፡
የተጠየቀውን ገንዘብ ቢከፍል እንኳ አይለቁትም። በማፍያዎቹ ወጥመድ ተይዘው በማስፈራሪያ ገንዘብ የከፈሉ በርካታ

የፊሊፒንስ ወጣቶች፤ በአንድ ጊዜ አልተገላገሉም፡፡ እንደገና ገንዘብ እንዲያመጡ ይጠየቃሉ፡፡ ብዙዎቹ ሦስት አራቴ

ከከፈሉ በኋላ ነው፤ ማስፈራሪያው ማብቂያ እንደሌለው ገብቷቸው ለፖሊስ የተናገሩት፡፡ የፊሊፒንስ ፖሊስ ወደ 60

ገደማ የፌስቡክ “ማፊያዎችን” በመያዝ ሰሞኑን ፍ/ቤት አቅርቧል፡፡

የቀን እንጀራቸው 7 ነገሮችን ነካ ነካ ማድረግ ብቻ ሆኗል

ከባድና የተከበረ፣ ህፃናት የሚመኙትና ወላጆች የሚኮሩበት የፓይለት ሙያ፣ ተረት ሆኖ ሊቀር እየተቃረበ ነው።

በእርግጥ፣ የጎበዝና የሰነፍ ፓይለት ልዩነት፣ የበርካታ ሠዎች የሕይወትና የሞት ጉዳይ መሆኑን ከማሌዢያው አደጋ

መመልከት ይቻላል። በዚያ ላይ፣ የትርፍና የኪሳራ ጉዳይም ነው። ሉፍታንዛ በቅርቡ ያጋጠመውን ችግር አላያችሁም?

5500 ፓይለቶች ያሉት ሉፍታንዛ፤ በየእለቱ በ1400 በረራዎች ወደ 150ሺ የሚጠጉ መንገደኞችንና በርካታ ጭነቶችን

በማጓጓዝ ይታወቃል።
ይሄን ሁሉ የሚሠራው በአንድ ቀን ነው። በያዝነው ወር መባቻ ግን፣ ብዙዎቹ ፓይለቶች ለሦስት ቀን የሥራ ማቆም

ለማድረግ በመወሰናቸው፣ ሉፍታንዛ ችግር አጋጠመው።  በሦስት ቀናት ውስጥ ወደ 4ሺ ገደማ በረራዎች ተሰርዘው፣ ወደ

ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ መንገደኞች ሲጉላሉ አስቡት። ታዲያ እንዴት ነው፤ የፓይለት ሙያ ተረት ለመሆን የተቃረበው?
ኒው ኤሌክትሮኒክስ መፅሔት እንደዘገበው፤ አውሮፕላኖች ያለ ፓይለት መንገደኞችን እንዲያጓጉዙ ለማድረግ የሚያስችል

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንደ ልብ ተትረፍርፏል። ቴክኖሎጂዎቹ ሥራ ላይ ውለው በተደጋጋሚ ውጤታማነታቸው

ከመታየቱም በተጨማሪ፣ የመንገደኞች አውሮፕላን ያለ ፓይለት ከለንደን ስኮትላንድ ደርሶ መልስ 800 ኪሎ ሜትር

እንዲያርፍ የተደረገው ሙከራም ስኬታማ ሆኗል። እናም ወደፊት የፓይለት አስፈላጊነት እየተረሳ መምጣቱ አይቀርም።
ዛሬም ቢሆን፣ የፓይለቶች የዘወትር ሥራ እንደድሮው አይደለም። ለአውሮፕላኖችና ለአብራሪዎች የብቃት ማረጋገጫ

በመስጠት ቀዳሚውን የተቆጣጣሪነት ስፍራ የያዘው ኤፍኤኤ እንዳለው፤ ዛሬ ዛሬ የፓይለቶች ስራ ኢምንት እየሆነ ነው።

ከለንደን የተነሳውን አውሮፕላን አትላንቲክ ውቅያኖስን ተሻግሮ፣ እስከ ኒውዮርክ ከተማ ድረስ ከ5ሺ ኪ.ሜ በላይ

ሲጓዝ፣ ፓይለቱ ምን ይሰራል? ወንበሩ ላይ ቁጭ ብሎ ከአጠገቡ የሚገኙ ቁልፎችንና ማርሾችን ስንት ጊዜ ይነካካል? 7

ጊዜ ብቻ! ይሄው ነው፣ የፓይለቱ እለታዊ መደበኛ ሥራ? ለዚህም ነው ሙያው ተረት ለመሆን ተቃርቧል የሚባለው።

እባብና ጊንጥ፣ ነብርና አንበሳ፣ ቀበሮና ጅብ አይስተካከሏትም - በነፍሰ ገዳይነቷ
ቱጃሩ ቢል ጌትስ፣ በትንኝ ላይ ያወጀው ጦርነት ከተሳካ ሚሊዮኖችን ከሞት ያድናል። በቴክኖሎጂ ፈጠራ ከአለማችን

ቁንጮ ሃብታሞች መካከል አንዱ ለመሆን የበቃው ቢል ጌትስ፣ በድሃ አገራት በተለይም በአፍሪካ ጤንነትና ትምህርት

እንዲስፋፋ በርካታ ቢሊዮን ዶላሮችን በመለገስ ዘመቻ ከጀመረ ቆይቷል። ከዘመቻዎቹ አንዱ ትንኝን ከምድረገፅ ማጥፋት

ነው። ለምን? የትንኝን ያህል ብዙ ሰዎችን የጨረሰ ሌላ ፍጥረት የለም።
እባብና አንበሳን፣ ጅብና ቀበሮን ... “እንደ ነብር” ብንፈራቸውም፤ ከትንኝ ጋር ሲነፃፀሩ የሚያስከትሉት አደጋ ትንሽ

ነው። ትንኝ፣ የወባ በሽታን በማሰራጨት በየአመቱ 200 ሚሊዮን ሰዎችን ለበሽታ ትዳርጋለች። የ600ሺ ሰዎችን ሕይወት

ትቀጥፋለች።
ከበረዷማው አንታርቲካ በስተቀር ትንኝ የሌለችበት የአለማችን አካባቢ የለም ማለት ይቻላል። አይነታቸው ብዙ ነው -

3500 ያህል የትንኝ ዝርያዎች አሉ። የመራባት ፍጥነታቸውም ለጉድ ነው። በተለይ፣ እርጥበትና ሙቀት በሚያገኙበት

ወቅት፣ ጠቅላላ የትንኞች ቁጥር በመቶ ትሪሊዮን የሚቆጠር ይሆናል - ለአንድ ሰው ከ15ሺ በላይ ትንኞች ይደርሱታል

ማለት ነው። ትንኝ፣ በቁጥር ብዛት ከጉንዳንና ከምስጥ በመቀጠል ተወዳዳሪ የላትም። ዘ ዊክ እንደዘገበው፣ በመላው

አለም ያሉ ምስጦችች 250 ትሪሊዮን ሲሆን፣ የጉንዳኖች ቁጥር የዚህን አራት እጥፍ ይሆናል - አንድ ኳድሪሊዮን

(ለሁሉም ሰው ብናከፋፍላቸው፣ ለእያንዳንዱ ሰው ከ140ሺ ጉንዳኖች በላይ ይደርሱታል)።

ያስደነግጣል። ከ340ሺ እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር... ከዚያም የሚያልፍ ማለት ነው። ለንግድ፣ “አይን የሆኑ ቦታዎች”

ላይ የቤት ኪራይ አይቀመስም - ከሁሉም በላይ ደግሞ በሆንክኮንግ፣ በኒውዮርክና በፓሪስ። በ64 ሃብታም አገራት ላይ

ጥናት ያካሄደው ኩሽማን ኤንድ ዌክፊልድ እንደሚለው፤ በሆንክኮንግ ሃብታሞች የሚያዘወትሩት የገበያ አካባቢ ላይ፣

ሶስት በአራት ሜትር የሆነች አንዲት ሱቅ በወር 32ሺ ዶላር ትከራያለች (ከ600ሺ ብር በላይ ማለት ነው)። በሁለተኛ

ደረጃ የተጠቀሰው ውድ ኪራይ የሚገኘው፣ በኒውዮርክ ፊቭዝ አቨኑ የሚባለው አካባቢ ነው። ተመሳሳይ አነስተኛ ክፍል

በወር 26ሺ ዶላር ኪራይ ያስከፍላል። ቀጥሎ የሚመጣው ከወደ ፓሪስ ነው - በወር 17ሺ ዶላር የሚከፈልበት።

ተራ ሰዎች የታጠቁትን መሣሪያ ለማነፃፀር እንጂ፣ ሁለቱ መንግስታት የታጠቁትን  ለመቁጠር አይደለም። በአሜሪካ

መሣሪያ የታጠቀ ቤተሰብ ነው የሚበዛው - 58 በመቶ ያህል ቤተሰቦች የመሣሪያ ባለቤት ናቸው። ብዙዎቹም፣ ሦስት እና

አራት የመሣሪያ አይነቶች አሏቸው። የተለመደ ባሕል ወይም እምነት ብቻ አይደለም። የመሣሪያ ባለቤትነት ትልቅ ዋጋ

የተሰጠው መሰረታዊ መብት ከመሆኑ የተነሳ፤ ከ230 ዓመት በፊት የአገሪቱ ሕገመንግስት ሲፀድቅ በማይደፈሩ መብቶች

ዝርዝር ውስጥ እንዲገባ ተደርጓል። ዛሬ፣ በሲቪል አሜሪካዊያን እጅ ውስጥ ያለ የጦር መሣሪያ፣ ከ300 ሚሊዮን በላይ

ነው።
በቻይና፣ የጦር መሣሪያ ባለቤትነት፣ የሚያስቀጣ ወንጀል እንጂ የሚከበር መብት አይደለም። የጦር መሳሪያ ፈልጎ

ማግኘት ያስቸግራል። በሌላው አካባቢ ይቅርና፣ የተቃውሞና የአመፅ አዝማሚያ ይታይበታል በሚባለው ጊዝሆ በተሰኘ

የቻይና ክልልም የጦር መሳሪያ ብርቅ ነው።
በቅርቡ በክልሉ በተካሄደ ሰፊ አሰሳ ግን ብዙ ሕገወጥ መሣሪያ ተገኝቶ ተወርሷል - 12ሺ ሕገወጥ ቢላዋ።

ለራስ፣ ለቤተሰብ፣ ለማህበረሰብ፣ ለአገር፣…. የሚጠቅም ራዕይና ሕልም ይዘው ወደ ት/ቤት ወደ ግል ጉዳይ፣ ወደ ሥራ፣

ወደቤት… ሲሄዱ፣ የመኪና አደጋ ካሰቡበት ሳይደርሱ መንገድ ላይ ያስቀራቸውን ዜጎች ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡ በኮልፌ

የደረሰውን የመኪና አደጋ፣ አባይ በረሃ የተቃጠለውን ስካይ ባስ፣ በቅርቡ እንኳ በሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ … የደረሱትን

የመኪና አደጋዎች ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡
በየዕለቱ፣ በራዲዮ በሚቀርበው የትራፊክ አደጋ፣ የሞት፣ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት… ሲሰማ

“አሽከርካሪዎች ጆሮ የላቸውም ወይ?” ያሰኛል፡፡ ይህ ሁኔታ ሁነኛ መፍትሔ ካልተፈለገለትና በዚሁ የሚቀጥል ሆነ ከ16

ዓመት በኋላ (በ2030 እ.ኤ.አ)፣ የመኪና አደጋ በመላው ዓለም ከመጀመሪያዎቹ 5 የሞት መንስኤዎች አንዱ እንደሚሆን

የዓለም ጤና ድርጅት ተንብዮአል፡፡
ግምቱ ያለምክንያት አይደለም፡፡ በዓለም ላይ በየዓመቱ በመንገድ ላይ (በመኪና) አደጋ 1.24 ሰዎች እንደሚሞቱና 50

ሚሊዮን ያህል እንደሚቆስሉ የድርጅቱ መረጃ ያመለክታል፡፡ ከሟቾቹ ግማሽ ያህሉ፣ እግረኞች፣ ቢስክሌትና የህዝብ

ትራንስፖርት ተጠቃሚ መንገደኞች ናቸው፡፡ ከመቶ ሰዎች 90ዎቹ የሚሞቱት አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች

ሲሆን ከመቶ የመኪና አደጋዎች 62ቱ የሚከሰቱት አገራችንን ጨምሮ በ10 አገሮች ብቻ እንደሆነ የጤና ድርጅቱ ሪፖርት

አመልክቷል፡
ሌላው የሚሊዮኖች ሞት ምክንያት የሥራ ቦታ አደጋና በሽታ ነው፡፡ በሥራ ቦታ አደጋና በሽታ በየ15 ሰከንዱ አንድ

ሰራተኛ ይሞታል፡፡ 160 ሰራተኞች ደግሞ የስራ ቦታ አደጋ ሰለባ ይሆናሉ፡፡ በደሌ (ሄኒከን) ቢራ የዘንድሮውን የዓለም

የደህንነትና የጤና ቀን ባሳለፍነው ሳምንት ባከበረበት ወቅት ለሰራተኞቹ ያሰራጨው በራሪ ወረቀት፣ በዓለም ላይ በየቀኑ

6,300፣ በዓመት 2.3 ሚሊዮን ሰዎች በሥራ ቦታ በሚፈጠር አደጋ እንደሚሞቱና በየዓመቱ 317ሺ የሥራ ቦታ አደጋዎች

እንደሚያጋጥሙ አመልክቷል፡፡
በዕለቱ፣ በደሌ ቢራ የመኪናና የሥራ ላይ አደጋዎች የሚያደርሱትን ጉዳትና መከላከያውን በልዩ ልዩ ዘዴዎች፣

ለከተማዋና ለአካባቢዋ ነዋሪዎች፣ እንዲሁም ለፋብሪካው ሰራተኞች አስተምሯል፡፡ በከተማዋ አደባባይ እግረኞች

ከትራፊክ አደጋ ለመጠበቅ ግራቸውን ይዘው እንዲጓዙ፣ አሽከርካሪዎችም የትራፊክ ሕግ አክብረው እንዲያሽከረክሩ፣

ጉዳዩ በሚመለከታቸው ሰዎች ትምህርት ከመሰጠቱም በላይ የነዋሪውን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ በሁለቱም ፆታ በጎዳና ላይ

ሩጫ ላሸነፉ ተወዳዳሪዎች ሽልማት ሰጥቷል፡፡  በድርጅቱ ግቢ ውስጥ የሥራ ላይ ደህንነትን አስመልክቶ ለሰራተኞች

የተለያዩ የአደጋ ዓይነቶች፣ መንስኤና መከላከያ በተለያዩ ዘዴዎች ከማስተማሩም በላይ በተደረጉ ውድድሮች ላሸነፉ

ሰራተኞች ሽልማት ሰጥቷል፡፡
በሞባይል እያወሩ መኪና ማሽከርከር፣ ሲዲ ወይም ራዲዮ መቀየር፣ መኪና ውስጥ መብላት፣ ወደ ውጪ ሌላ ነገር ማየት፣

ጠጥቶ ማሽከርከር፣ የተለያዩ አደንዛዥ ዕፆች መጠቀም፣ እያሽከረከሩ መዋብና አጎንብሶ ዕቃ ማንሳት፣ በፍጥነትና

በግዴለሽነት መንዳት፣ መጥፎ የአየር ፀባይና የተበላሸ መንገድ ዋነኞቹ የአደጋ መንስኤ ምክንያቶች መሆናቸው

ተገልጿል፡፡
በደሌ ቢራ የሥራ ቦታ ደህንነትን ለመጠበቅና አደጋን ለመከላከል ከሰራተኞቹ ውስጥ የሙያ ደህንነት ጀግና ለመምረጥ፣

የእሳት አደጋ መኪና ለመግዛትና ጥራት ያላቸው የአደጋ መከላከያ ቁሳቁስ ከውጭ ለማስመጣት ማቀዱ ታውቋል፡፡

አንድ የኦሮሞ ተረት እንዲህ ይላል፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሰው ወደ ዘመቻ ይሄድ ኖሮ ቤተሰቡንና ቤት ንብረቱን ሁሉ ለጎረቤቱ አደራ ብሎ፤ ቀዬውን ተሰናብቶ ወደ ጦር ሜዳ ሄደ፡፡
ጦርነቱ ከሁለት ዓመት በላይ ፈጀ፡፡ ብዙ ሰው ከወዲህ ወገን ሞተ፡፡ ከጠላትም በኩል እንደዚሁ ስፍር ቁጥር የሌለው ሰው አለቀ፡፡ ይሄንን ሁሉ አልፎ ያ ዘማች ተርፎ ወደ መንደሩ ተመለሰ፡፡
ገና ወደ ቤቱ ሳይደርስ መንገድ ላይ ያገኘውን ሰው ሁሉ፤
“መንደራችን ሰላም ነው ወይ?” ብሎ ይጠይቃል፡፡
“ሰላም ነው፡፡ ምንም የደረሰ ነገር የለም” ይለዋል አንዱ፡፡
ሙሉ በሙሉ ለማመን ስለሚቸገር ሌላውን ሰው፤
“ጎበዝ፤ መንደራችን እንዴት ነው? ሰዉስ እንዴት ከረመ” ሲል ይጠይቃል፡፡ ሌላውም ሰውዬ፤
“ኧረ አማን ነው፡፡ ምንም የተፈጠረ ችግር የለም” ይለዋል፡፡
እንዲህ እየጠየቀ ሲጓዝ በመጨረሻ ያንን ቤተሰቡንና ቤት ንብረቱን አደራ የሰጠውን ጎረቤቱን አገኘው።
ተቃቅፈው ተሳሳሙ፡፡
“እንዴት ነህ?” አለ ዘማች፡፡
“ደህና!” አለ ጎረቤት፡፡
“ሁሉ አማን፣ ሁሉ ደህና?”
“ሁሉም አማን ነው፡፡ ሰላም ነው!”
“እርግጠኛ ነህ? ምንም ችግር አልገጠማችሁም?”
“ኧረ ምንም፡፡ ያ ያንተ ውሻ ብቻ ከመሞቱ በስተቀር ምንም የሆነ ነገር የለም”
“ውሻዬ እንዴት ሞተ?”
“አጥንት ሲግጥ አንቆት ሞተ”
“የምን አጥንት?”
“አንድ የታረደ በሬ ነበር የሱን አጥንት ሲበላ አንቆት ነው፡፡”
“በሬው ለምን ታረደ?”
“ለባለቤትህ አርባ”
ዘማች ኡኡታውን ለቀቀው፡፡ ጮኸ፡፡ ዕንባው ተንዠቀዠቀ፡፡ ጎረቤትዬው አባብሎ ቀና አደረገውና፤
“እቤት ስትደርስ ያደርስህ የለም ወይ? በቃ ዝም በል” አለውና መንገድ ይጀመራሉ፡፡
ከዚያም መቼም ባል የሚስቱን አሟሟት ማወቅ አለበትና፤
“ለመሆኑ ምን ሆና ሞተች?” አለው ፡፡
“በወሊድ ነው የሞተችው” አለ ጎረቤት፡፡
“በወሊድ?!” አለ ባል፣ በድንጋጤ፡፡
“አዎ በወሊድ ነው”
“ከማን አርግዛ?” አለ ባል፤ ዘመቻ የቆየው ሁለት ዓመት መሆኑን እያሰላሰለ፡፡
“ሰው ካንተ ነው ይለኛል፤ እኔ ግን እኔ አይደለሁም እላለሁ!” አለው፡፡
*       *       *
ዛሬ በሀገራችን፤ ትንሽ መገለቻዎች፣ የትልቁ ስዕል ምልክቶች ናቸው! ማናቸውንም የነገር አካሄድ ሥረ-መሰረቱን ደብቀን የምንጓዝበት ከሆነ፤ ውጤቱ አያምርም፡፡ እያንዳንዱ የተከማቸ ነገር ድንገት አንድ ጊዜ ለመፈንዳት ቅንጣት ሰከንድ ትበቃዋለች፡፡ የTipping Point (ፍንዳታዋ ነጥብ እንደማለት) ደራሲ ነገሩ እየደለበ ይሂድ እንጂ ለመፈረካከስ አንዲት አጋጣሚ ትበቃዋለች ይላል፡፡ ዕውነት ነው፡፡ ውስጥ ውስጡን የተጠራቀመ፣ የተነፋፋ ምሬት በየት እንደሚፈነዳ አይታወቅም፡፡ ምሬት ተጠራቅሞ ወደ አንድ ቦይ ሳይገባ በፊት ካልገደቡት፤ ውሎ አድሮ ለያዥ ለገራዥ የሚያስቸግር ሊሆን ይችላል፡፡
ብዥታና ዳፍንተኝነት አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው፤ ህሊናዊው (subjective) ሁኔታ ሲዘገይና ዕሙናዊው ሁኔታ (objective) እጅግ ሲቀድም ነው፡፡ ካለንበት ሁኔታ ተነስተን ስናስበው፣ ይህ ክስተት የሚመጣው፤ ምሬቱ እጅግ ሲበረክትና መፍትሔው እጅግ ሲዘገይ ነው ማለት ነው፡፡
የአሜሪካው የሲቪል መብቶች ትግል መሪ “እምቢ ብሎ መነሣት፣ ያልተሰሙ ድምፆች ቋንቋ ነው” ይለናል፡፡ ይህን ልብ እንበል፡፡ ትምህርት የረጋ አካባቢ፣ የተቀደሰ መንፈስና ንፁህ ልቦና ይፈልጋል፡፡ ታዋቂው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን፤
“ለእኔ፣ በመርህ ደረጃ፤ ትምህርት፤ ከፍርሃት፣ ከጉልበት እና ከአርቴፊሻል ሥልጣን ጋር የሚሰራ ከሆነ የመጨረሻ አስከፊ ነገር ነው፡፡ ይህ ዓይነት አያያዝ ድምፅን ያኮስሳል፣ ስሜትን ያቀዝዛል፣ ቅንነትንና የተማሪዎችን ሙሉ ልብ (ልበ-ሙሉነት) ያመነምናል፡፡ በዚህ ሁኔታ የምናፈራውም፤ እጁን የሰጠና ተምበርካኪ ትውልድ ነው” ሲል ጠቅልሎ ያስቀምጠዋል፡፡
በክፍል የምንማረውን ያህል ከህይወትም እንማራለን፡፡ ከአካባቢም እንቀስማለን፡፡ ስለሆነም ዕድሜ ልካችንን ተማሪዎች ነን፡፡
ነገር እስኪባባስ፣ እስኪጎመዝዝና እስከሚመር ተብሎ ታይቶ፤ ወደ ፍንዳታ ደረጃ እስከሚደርስ ማየት፤ በኋላን በመካያው ሰበብና ምክን ፈጥሮ “የአብዬን እከክ ወደምዬ ልክክ፤ አያዋጣም፡፡
ሁሉም ተማሪ የሰከነ፣ የተቀነባበረ፣ የበሰለ መልክ መያዝ ይገባዋል፡፡ ሁሉን ነገር በጥሞና መመርመር የመማር ዋንኛው አንጓ ነው፡፡ ግራ ቀኙን ማየት ክፉ ደጉን መለየት የማንኛውም ጉዞ መሰረታዊ መነሻ ነው፡፡ ዊሊያም አስበር የተባለ ካናዳዊ ሐኪም ስሞት መቃብሬ ላይ እንዲፃፍ የምፈልገው፤ ከዚህ በታች ያለው ነው፡-
‹እዚህ ለመድረስ ነው እንደዚያ የተጣደፍነው?!›
ጆርጅ ደብሊዩ ቡሽ በማዕረግ ዲግሪ ለተሸለሙት የዬል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባደረጉት ንግግር፤ “የክብር ተመራቂ፤ ተሸላሚ እና የማዕረግ ተሸላሚ ለሆናችሁ ተማሪዎች እንኳን ለዚህ አበቃችሁ እላለሁ። በ‹ሲ›(ር) የተመረቃችሁም አይዟችሁ፤ እናንተም እንደኔ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለመሆን ትችላላችሁ” ብለዋል፡፡
ለሁሉም ተማሪ አገሪቱ እኩል እድል ትሰጣለች ነው ቁም ነገሩ፡፡ እኛስ? ብሎ መጠየቅ እንግዲህ የእኛ ፋንታ ነው፡፡ በየትም አገር፣ በየትም ጊዜ፤ ለሁሉ በሽታ አንድ ዓይነት መድኃኒት የለም ‹ፓናሲያ› እንዱሉ፡፡ ለሁሉ ችግር አንድ ብቸኛ መፍትሄም የለም፡፡ ሁሉም መንገድ ወደ አንድና አንድ ሰፈር ብቻ አያደርስም። የጉዳዮቻችን አፈራረጅ እንደወቅቱና ሁኔታው ተጢኖ ሳይሆን፤ ሁሉም በተለመደው መንገድ መሆኑ አሳሳቢ፡፡ “ይሄማ በዚህ በዚህ ሰበብ የመጣ ነው”፣ “ይሄማ ከጀርባ ይሄ ይሄ ነገር ቢኖረው ነው፡፡ ይሄማ ከተለመዱት ሰዎች ውጪ አይሆንም” (“Round up the usual suspect” እንዲል፤ ቃለ-ፊልም)፤ እያልን ብዙ መንገድ ለመሄድ አይቻለንም፡፡ በለሆሳስ እናስብ፡፡ ዙሪያ-መለስ ዕሳቤ ይኑረን። አገርና ህዝብ በማይጎዳ ፍትሀዊ ጎዳና እንጓዝ፡፡ አለበለዚያ “ብትናገር ያምናውን፣ ብትፈትል አንድ ልቃቂት” የሚለው የትግሪኛ ተረት እፊታችን ይደቀናል፡፡

Saturday, 10 May 2014 12:13

የወቅቱ ጥቅስ

የፖለቲካ መፈክሩ፤ “የእኛ ተግባር መማር መማር መማር” የሚለው የሌኒን መርህ ነበር፡፡
አንዲት ልጅ የክፍል ፈተና እያለባት “ፎርፋ” የትም ስትዋልግ ትውላለች፡፡
አባት ይሄንን ጉድ ሰሙና አስጠሩዋት፡-
“አንቺ፤ ለምንድነው ከክፍል የቀረሺው? ሌላው ቀርቶ ትምህርት ቤታችሁ ላይ የተለጠፈውን “የእኛ ተግባር መማር መማር መማር” የሚለውን እንኳን አታስታውሺም?” አሏት፡፡
ልጅቱም፤
“አባዬ፤ ሌኒንኮ ተማሩ አለ እንጂ፤ ተፈተኑ አላለም!” አለቻቸው፡፡