
Administrator
Monday, 14 July 2025 20:05
ከ200 ሺ ብር እስከ 100 ሺ ብር የሚያሸልም የወጣቶች ውድድር!!
የወጣቶች አግሮኢኮሎጂ ስታርትአፕ ውድድር (Youth in Agroecology Startup Competition) ምንድነው?
ኢትዮጵያን ሰስተኔብል ፉድ ሲስተምስ ኤንድ አግሮኢኮሎጂ ኮንሶርቲየም (ESFSAC) ከአፍሪካን ፉድ ሶቨርኒቲ አሊያንስ (AFSA) ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ለሆኑ ወጣቶች ያዘጋጀው ውድድር ነው። ዓላማውም ለምግብ ሉዓላዊነት፣ ለዘላቂነት (sustainability) እና ለማህበረሰብ ደህንነት ሀገር-በቀል መፍትሔዎችን ማበርከትና ወጣቶች አግሮኢኮሎጂን እና አገር በቀል ምግቦችን በማስተዋወቅ ረገድ የመሪነትን ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል ነው።
ሁለት የመወዳደሪያ ጭብጦች ተቀምጠዋል፦ የመጀመሪያው አግሮኢኮሎጂካል እርሻ እና ፈጠራ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጤናማ እና የሀገር በቀል ምግቦች ላይ በመስራት እና በማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ነው። ከሁለቱ በአንዱ ላይ የተሰማሩ (startup) የአዲስ አበባ ነዋሪ ወጣቶች መወዳደር ይችላሉ።
ይህ ውድድር የ“My Food is African / My Food is Ethiopian” ዘመቻ አካል ነው።
ማመልከት የሚችለው ማነው?
በአዲስ አበባ የሚገኙ እድሜያቸው ከ18-35 ዓመት የሆኑ፣ አግሮኢኮሎጂን ወይም ጤናማ እና የሀገር በቀል ምግብ ሥርዓቶችን የማሳደግ ተነሳሽነትን የሚደግፉ ሥራዎችን እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች ማመልከት ይችላሉ።
ከአሁን በፊት በተመሳሳይ ውድድር ተሳትፈው ያላሸነፉ ወጣቶች በዚህ ውድድር ማመልከትና መወዳደር ይችላሉ። ነገር ግን በሌላ ውድድር ላይ አሸናፊ የነበሩ ወጣቶች በዚህ ውድድር መሳተፍ አይችሉም።
ከሴቶች እና በቂ ውክልና ከሌላቸው ማህበረሰብ አባላት የሚቀርቡ ማመልከቻዎችን አጥብቀን እናበረታታለን።
ከማመልከቻዎ ጋር ስራዎን ወይም የምርት ናሙናዎን የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ አያይዞ ማቅረብ ይኖርብዎታል።
የምዝገባ ቀን መቼ ነው?
ከሐምሌ 14-25/2017 (ጁላይ 21 - ኦገስት 1, 2025)።
ይመዝገቡ፣ ይወዳደሩ፣ይሸለሙ።
ሽልማቱ ምንድነው?
በዳኞች ለተመረጡት አስር ተወዳዳሪዎች ለውድድሩ ጠቃሚ የሆኑ ሥልጠናዎችን ያገኛሉ፤ የአያንዳንዳቸውን ሥራዎች (በቪዲዮ፣ በፎቶ እና በጽሁፍ) ለሌሎች የሥራ አጋሮቻችን በማጋራት ሥራዎቻቸውን እና እራሳቸውን አንዲያስተዋውቁ ይደረጋል። በተጨማሪም አብረው መስራት ከሚፈልጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ጋር እናገናኛቸዋለን።
አንደኛ ለምትወጣው/ለሚወጣው 200,000 ብር
ሁለተኛ ለምትወጣው/ለሚወጣው 150,000 ብር
ሦስተኛ ለምትወጣው/ለሚወጣው 100,000 ብር
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እና ለመመዝገብ የሚከተለውን ሊንክ ይከተሉ:-
እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የESFSAC ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ፦
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 14 July 2025 20:03
በማሳቹሴትስ በአፓርትመንት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በማሳቹሴትስ ግዛት በፎል ሪቨር ከተማ ባለ 3 ፎቅ የመኖሪያ አፓርትመንት ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት ለሲኤንኤን ተናግረዋል።
በአደጋው ከሟቾች በተጨማሪ በ30 በሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ የአደጋው መንስዔ በመጣራት ላይ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።
እሳቱ በመኖሪያ አፓርትመንቱ መግቢያ መውጢያ ላይ በመበርታቱ ምክንያት አብዛኞቹ ተጎጂዎች ከእሳቱ ለማምለጥ በመስኮት ለመዝለል መሞከራቸው አደጋውን አባብሶታል ተብሏል።
የከተማዋ አስተዳደር በደረሰው አደጋ ማዘኑን ገልጾ፤ አባሎቻቸውን በሞት ላጡ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝቷል።

Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 14 July 2025 20:01
"ከዩክሬን ጋር ስምምነት ካልተደረሰ አሜሪካ
በሩሲያ ላይ ሁለተኛ ደረጃ ማዕቀብ ትጥላለች"
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኔቶ ሃላፊ ማርክ ሩተ ጋር በዛሬው ዕለት በዋይት ሃውስ ተገናኝተው በተለያዩ ዓለማቀፍ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ዓለማቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ ስፑትኒክ ከውይይቱ የተጨመቁ ቁልፍ ነጥቦችን እንደሚከተለው አጠናክሯቸዋል፡፡






የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 14 July 2025 20:00
ሩሲያ በማዕከላዊ አፍሪካ የአልማዝ ማዕድን ለማውጣት ተፈቀደላት
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ የሩሲያ ኩባንያዎች የአልማዝ ማዕድን እንዲያወጡ ፈቃድ መስጠቷን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
ባለፈው ዓመት የአልማዝ የወጪ ንግድ እገዳ ሙሉ በሙሉ መነሳቱ ለማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው፤ የሀገሪቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቴሪ ፓትሪክ አኮሎዛ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
"ምክንያቱም ያለ ማዕቀብ ሀገሪቱ የማልማትና የማዕድን ምርቶቿን በመሸጥ ጥሩ ገቢ የማግኘት እድል አላት” በማለት አዲሱ ነጻነት የሚሰጠውን ኢኮኖሚያዊ አቅም አጉልተው ማሳየታቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
እ.ኤ.አ ሕዳር 21 ቀን 2024 ዓ.ም ለአልማዝ ንግድ ዓለም አቀፍ እውቅና የሚሰጠውና ተቆጣጣሪ አካል የሆነው ‘የኪምበርሊ ሂደት’ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ አልማዝ ወደ ውጭ እንዳትልክ ጥሎ የነበረውን እገዳ አንስቷል፡፡ እቀባው በግጭት ስጋት ምክንያት መጀመሪያ የተጣለባት በፈረንጆቹ 2013 ነበር፡፡
በ2016 እግዱ በከፊል መነሳቱን ተከትሎ ከግጭት ነጻ ከተባሉ አምስት ቀጠናዎች አልማዝ ወደ ውጭ እንድትልክ አስችሏታል፡፡ የማዕቀቡ ሙሉ በሙሉ መነሳት ደግሞ ለሰፊ የማዕድን ሥራዎችና ለዓለም አቀፍ አጋርነት መንገድ ከፍቷል ተብሏል።
የሩሲያ የማዕድን ኩባንያዎች በተመሳሳይ በሳኡዲ አረቢያ ማዕድን በማውጣት ሥራ እንዲሰማሩ ፈቃድ ማግኘታቸው ሰሞኑን ተዘግቧል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Friday, 11 July 2025 08:06
ግብፅ ከኢትዮጵያ የጽሁፍ ማረጋገጫ ጠየቀች
"ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ የሰጠቻቸው የቃል
ማረጋገጫዎች በጽሑፍ ስምምነት ይደራጁ"
ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ የሰጠቻቸውን የቃል ማረጋገጫዎች በጽሑፍ ስምምነት እንድትደግፍ ግብፅ ጠየቀች። ይህ ጥያቄ የመጣው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግድቡ በመስከረም ወር እንደሚመረቅ ከገለጹ በኋላ ነው።
የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ፣ በቅርቡ ብራዚል ውስጥ በተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ጎን ለጎን ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር መነጋገራቸውን ጠቁመዋል።
በብሪክስ ስብሰባ ወቅት፣ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ፣ ግድቡን “ግብፅንና ሱዳንን ሳይጎዳ” የማጠናቀቅና ትብብርን የመቀጠል ፍላጎታቸውን ገልጸው ነበር። ይሁን እንጂ ማድቡሊ፣ እነዚህ የቃል ማረጋገጫዎች በሁለቱ ሀገራት ወይም በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ያለውን የወደፊት ግንኙነት በሚያደራጅ የጽሑፍ ሰነድ ውስጥ መተርጎም አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።
የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “የግብፅ አቋም በፍጹም አልተለወጠም፤ በአባይ ውሃ ድርሻዋ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዲደርስ አትፈቅድም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። ግብፅ የልማት ተቃዋሚ ባትሆንም፣ በአባይ ውሃ ላይ ያላትን ህጋዊ መብት እንደምትጠብቅም አስረድተዋል።
ጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በሰጡት ማብራሪያ ፤ ግድቡ በመስከረም ወር እንደሚመረቅና፣ ፕሮጀክቱ ለቀጠናው ትብብር “ዕድል” እንጂ “አደጋ” እንደማይሆን በመጥቀስ፣ ከግብፅ ጋር ውይይት ለመቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Friday, 11 July 2025 07:49
አየር መንገዱ ወደ ቬትናም አዲስ በረራ ጀመረ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቬትናም መዲና ሀኖይ አዲስ በረራ መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን፤ በረራው 28ኛው የእስያ መዳረሻ ነው ተብሏል፡፡
አየር መንገዱ ዛሬ ወደ ቬይትናም የጀመረው የበረራ አገልግሎት በእስያ 20ኛው መዳረሻ መሆኑን የተናገሩት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፤ ከአፍሪካና ከእስያ ጋር በንግድና በቱሪዝም ጠንካራ ግንኙነትን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።
አዲስ የተጀመረው የበረራ መስመር የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚያግዝም ተጠቁሟል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Friday, 30 May 2025 20:04
ኦቪድ ሪል እስቴት ለገቢዎችና ጉምሩክ ሰራተኞች ቤቶችን ሊገነባ ነው
ኦቪድ ሪል እስቴት ለገቢዎች ሚኒስቴርና ለጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ ከ5ሺህ በላይ የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት ግንቦት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከተቋማቱ አመራሮች ጋር ተፈራርሟል።
የኦቪድ ሆልዲንግ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ ታደሰ፣ ኦቪድ ሪል ስቴትን በመወከል የመግባቢያ ስምምነቱን ከገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ እና ከጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቀበታ ጋር የተፈራረሙ ሲሆን፣ ስምምነቱ የተቋማቱ ሰራተኞች ከኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በአማራጭ እንዲገዙ ያስችላል።
በኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ የሽያጭ ማዕከል በተካሄደው የፊርማ ስነስርአት ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኦቪድ ሆልዲንግ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ ታደሰ፤ የሁለቱም ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ኦቪድን በመምረጣቸውና እምነት በመጣላቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ስምምነቱ ኦቪድ የመኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የመንግስት ሰራተኞችን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይና ሁሉም የኦቪድ እህት ኩባንያዎች ተባብረው ቤቶቹን በጥራትና በፍጥነት ገንብተው እንደሚያስረክቡም ቃል ገብተዋል።
የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው፤ የመኖሪያ ቤቶች አቅርቦት በመንግስት ጥረት ብቻ ሊሟላ የማይችል ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው፣ ኦቪድ ሪል ስቴት እያከናወናቸው የሚገኙ የቤት ልማት ስራዎች በአብነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን አመልክተዋል። ሰራተኞች ይህን ዕድል በአግባቡ እንዲጠቀሙና ገንዘባቸውን ከወዲሁ በመቆጠብ የቤት ባለቤት እንዲሆኑም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
Published in
ዜና
Tagged under
Friday, 30 May 2025 20:01
የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሰረት ደፋርን ያካተተ ቡድን ድሬዳዋ ገባ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሰረት ደፋርን ያካተተ ልዑክ ቡድን አራተኛ ቀኑን በያዘው በ13ኛው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታችና 4ኛው ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለመታደም ድሬዳዋ ገብቷል።
ከምክትል ፕሬዚዳንትዋ በተጨማሪ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ሌተናል ኮሎኔል አትሌት የማነ ፀጋይና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ /ቤት ኃላፊ አቶ ዮሀንስ እንግዳ ድሬዳዋ ገብተዋል።
ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የድሬዳዋ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ዮናስ በትሩ፣ የድሬዳዋ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አህመድ አብዱና የድሬዳዋ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ፅዮን በለጠ ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የፌደሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
የፌስቡክ ገጻችንን ፎሎው በማድረግ የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…https://t.me/AdissAdmas



Published in
ዜና
Tagged under
Friday, 30 May 2025 19:55
ሪያል ማድሪድ አሌክሳንደር አርኖልድን አስፈረመ
የስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ትሬንት፣ አሌክሳንደር አርኖልድን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
አሌክሳንደር አርኖልድ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከልጅነት ክለቡ ሊቨርፑል ለመልቀቅ መወሰኑን ከሣምንታት በፊት ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
በወቅቱም፤ ራሱን በአዲስ ክለብና በተለየ ቦታ ለመፈተሽ በመፈለጉ ከሊቨርፑል ለመልቀቅ መወሰኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል፡፡
ወደ አዲስ ክለብ መሄዱም ያለውን ሙሉ አቅም አውጥቶ እንዲጠቀም እንደሚያስችለው መግለጹ ይታወቃል፡፡
(ኤፍ ኤም ሲ)
የፌስቡክ ገጻችንን ፎሎው በማድረግ የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ስፖርት አድማስ
Tagged under
Friday, 30 May 2025 19:51
አምባሳደር መለስ ዓለም አዲስ ሹመት ማግኘታቸውን አስመልክቶ ምን አሉ?
"የተከበራችሁ ወዳጆቼና ጓደኞቼ፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ጄነራል በመሆን አዲስ ኃላፊነት ተሰጥቶኛል። በቃል አቀባይነት ኃላፊነቴ ወቅት ላደረጋችሁልኝ ድጋፍ አመሰግናለሁ።
የረዥም ጊዜ እረፍት ወስጄ በኢጋድ በኃላፊነት እንድሰራ በተለይ ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ለሰጡኝ ዕድልና እና ባልደረቦቼ ላሳዩኝ ፍቅር ከልብ አመሰግናለሁ። በቆይታዬ ብዙ ነገር ተምሬአለሁ።
ህይወት እንደ መጽሐፍ ነው። ብዙ ምዕራፎች አሉት። እኔም አዲስ ምዕራፍ በፈጣሪዬ ፈቃድ ጀምሬያለሁ፡፡ ከባልደረቦቼ ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላት የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲጠናከር እንሰራለን። መልካም የሳምንት መጨረሻ ይሁንልን። አመሰግናለሁ።"
የፌስቡክ ገጻችንን ፎሎው በማድረግ የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under