Administrator

Administrator

Saturday, 24 August 2019 14:35

የተፈጥሮ ጥግ


 • የአየር ንብረት ለውጥ በአብዛኛው ሰው ሰራሽ ነው፡፡
ፖፕ ፍራንሲስ
• የአየር ንብረት ለውጥ ላይ መከራከር፣ ምድር ጠፍጣፋ ናት ብሎ እንደ መከራከር ነው፡፡
ቢል ማሄር
• የአየር ንብረት ለውጥ፤ የፖለቲካ ምርጫ ነው::
ማይክ ስሚዝ
• ተልዕኮአችን አንድ ነው፡-ፕላኔቷን መጠበቅና ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ፡፡
ፍራንሶይስ ሆላንዴ
• በዚህ ምድር፣ በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ የማይጎዳ የለም፡፡
ራጄንድራ ኬ.ፓቻዩሪ
• ለአፍሪካ ዕድገት ትልቁ አደጋ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ነው፡፡
ፖል ፓልማን
• የአየር ንብረት ለውጥ፣ የምጽአት ቀን ትንቢት መሆኑ አክትሟል፤ ተጨባጭ እውነታ ነው፡፡
አስትሪድ ኖክልብዬ
• በዚህ ምድር ላይ ያለ እያንዳንዱ ሰው፣ ዓለምን የመለወጥ አቅም አለው፡፡
ኢማ ቶምፕሰን
• የአየር ንብረት ለውጥ፤ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ አይደለም፤ ከደህንነትና ኢኮኖሚ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው፡፡
ጆንቶን ፔሪት
• ለፕላኔታችን ትልቁ አደጋ፣ ሌላው ይታደጋታል የሚለው እምነት ነው፡፡
ሮበርት ስዋን
• የአየር ንብረት ለውጥ ችግርን ካልፈታን፣ ድህነትን ፈጽሞ አናጠፋም፡፡
ጂም ዮንግ ኪም
• የአየር ንብረት ለውጥ፣ ለመጪው ትውልድ ሊተው የሚችል ችግር አይደለም፡፡
ፖፕ ፍራንሲስ

Saturday, 24 August 2019 14:32

አገራዊ አባባል

(ስለ እውነት)
• ዋሾዎች ጥሩ የማስታወስ ችሎታ ያስፈልጋቸዋል፡፡
የፈረንሳዮች አባባል
• እውነትን መናገር አደገኛ ነው፤ እውነትን መስማትም አሰልቺ ነው፡፡
የዳኒሽ አባባል
• እውነቱን ተናገር፤ ነገር ግን ከአካባቢው በፍጥነት ልቀቅ፡፡
የስሎቬንያ አባባል
• ገንዘብ ሲናገር፤ እውነት ዝም ትላለች፡፡
የሩሲያውያን አባባል
• የእውነት ወዳጅ ጠላቱ ብዙ ነው፡፡
የታሚል አባባል
• የእውነት ባሪያ፣ እሱ፣ ነፃ ሰው ነው፡፡
የአረቦች አባባል
• ሦስት ነገሮች ለረዥም ጊዜ መደበቅ አይችሉም፡- ፀሐይ፣ ጨረቃና እውነት፡፡
ቡድሃ
• ያለ ጊዜው የተነገረ እውነት አደገኛ ነው፡፡
የግሪኮች አባባል
• ስለ ራስህ እውነቱን መስማት ከፈለግህ፣ ጎረቤትህን አብሽቀው፡፡
የቼኮች አባባል
• እውነትን በድምፁ ትለየዋለህ፡፡
የሂብሩ አባባል
• እውነት የ ትም ይ ወስድሃል - ወ ህኒ ቤ ትም ጭምር፡፡
የፖላንዶች አባባል
• እውነት ቅርንጫፎች የሉትም፡፡
የህንዶች አባባል
• እውነት ብዙ ቃላት አይፈልግም፡፡
የሩሲያውያን አባባል
• ግማሽ እውነት፣ ሙሉ ውሸት ነው፡፡
የአይሁዶች አባባል
• እውነቱን የሚናገር ወዳጆች የሉትም፡፡
የአፍሪካውያን አባባል
• እውነቱን ተናግረህ፣ ሰይጣንን አሳፍረው፡፡
ጥንታዊ አባባል
• የወይን ጠጅና ሕጻናት እውነቱን ይናገራሉ፡፡
የሮማውያን አባባል

Saturday, 24 August 2019 14:27

የዘላለም ጥግ


 • ተስፋ በጨለማ ውስጥም ሆኖ ብርሃንን ማየት ነው፡፡
(Live purposefully now)
• አንድ ጊዜ፣ ተስፋ ማድረግን ከመረጥክ፣ ሁሉም ነገር ይቻላል፡፡
ክሪስቶፈር ሪቭ
• ተስፋ የነቃ ህልም ነው፡፡
አሪስቶትል
• አስቸጋሪ መንገዶች፣ ብዙውን ጊዜ፣ ወደ አስደሳች መዳረሻዎች ይመራሉ፡፡
ያልታወቀ ሰው
• ምርጫዎችህ፤ተስፋህን እንጂ ፍርሃትህን ማንፀባረቅ የለባቸውም፡፡
ኔልሰን ማንዴላ
• ህይወት ባለበት ሁሉ ተስፋ አለ፡፡
JRR Tolkien
• ከፍርሃት ይልቅ ተስፋን ለመምረጥ ድፍረት ይጠይቃል፡፡
ማርክ ዙከርበርግ
• ክዋክብትን ማየት የምትችለው በጨለማ ውስጥ ብቻ ነው፡፡
ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄአር
• ተስፋ ማድረግንና ደስተኛ መሆንን አትዘንጋ፡፡
ጆን ማክሊዎድ
• ተስፋ በሌለበት ተስፋን መፍጠር ግዴታችን ነው፡፡
አልበርት ካሙ
• ተስፋ ማድረግ፤ የሚያስወጣው ነገር የለም፡፡
ኮሊቴ
• ተስፋ የደፋር ምርጫ ነው፡፡
ቴሪ ጉይሌሜትስ
• ተስፋ፤ ማርን ያለ አበቦች የሚሰራ ብቸኛው ንብ ነው፡፡
ሮበርት ኢንገርሶል
• በእምነት እንጂ በፍርሃት መኖር የለብንም፡፡
ኤልደር ኪውንቴን ኤል.ኩክ
• ያለ ተስፋ መኖር፣ ከህይወት መፋታት ነው፡፡
ፍዮዶር ዶስቶይቭስኪ
• የፀሐይ መውጣትን ወይም ተስፋን ማሸነፍ የሚችል ጨለማ ወይም ችግር የለም፡፡
በርናርድ ዊሊያምስ


Saturday, 24 August 2019 14:05

ሃሳብዎን በነፃነት ይስጡ!

 ውድ አንባቢያን፡- ከዚህ በታች የቀረቡት መጠይቆች ከመስከረም 2011 ዓ.ም አንስቶ እስካሁን ባሉት ጊዜያት የተፈፀሙ ወይም የተከናወኑ ጉ ልህ አገራዊ ሁነቶችን የሚመለከቱ ናቸው፡፡ ዓላማውም የአዲስ አድማስ አንባቢያን የዓመቱን ምርጥ፣ ተወዳጅ፣ አሳዛኝና አስደንጋጭ ክስተቶች በተመለከተ ሀሳባቸውን ወይም አስተያየታቸውን መሰብሰብ ነው፡፡ ምላሽ በመስጠት የተለመደ ትብብራችሁን ታደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን፡፡ እናመሰግናለን፡፡


1. የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክልል ፕሬዚዳንት
2. የዓመቱ ስኬታማ የመንግስት ተቋም
3. የዓመቱ አሳፋሪ የመንግስት ተቋም
4. የዓመቱ ተስፋ የሚጣልበት የዲሞክራሲ
ተቋም
5. የዓመቱ አስደማሚ የመንግስት ስኬት
6. የዓመቱ ስኬታማ አገራዊ ንቅናቄ
7. የዓመቱ አስደንጋጭ ክስተት
8. የዓመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ አክቲቪስት
9. የዓመቱ ምርጥ የፖለቲካ (የመንግስት)
መሪ
10. የዓመቱ ተወዳጅ የቴሌቪዥን ጣቢያ
11. የዓመቱ ተወዳጅ የሬዲዮ ጣቢያ
12. የዓመቱ ምርጥ ኢ-ል ብወለድ መጽሐፍ
13. የዓመቱ ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ምሽት
14. የዓመቱ የሰላምና የፍቅር አርአያ
15. የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ድራማ
16. የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም
17. የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ
18. የዓመቱ አሳፋሪ የፖለቲካ ውዝግብ
19. የዓመቱ ምርጥ የበጎ አድራጎት ድጋፍ

   ዕድሜ------------------------- ፆታ ------------------------ የትምህርት ደረጃ -------------------------
 በፖ.ሳ.ቁ 12324 ልትልኩልን ወይም ዝግጅት ክፍላችን ድረስ በመምጣት በአካል
ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
       አድራሻ፡- ግቢ ገብርኤል፣ ፓላስ ኮሜርሻል ሴንተር፤ 6ኛ ፎቅ
       ለተጨማሪ መረጃ፡- በ0911 201357 ይደውሉ


          ከዕለታት አንድ ቀን የዱር አራዊቶች ሁሉ ተሰባስበው፤
 “እንዴት ነው ነገሩ? የምንበላው ጠፋ፡፡ ሁሉም የሚታደን እንስሳ እየሸሸ ጐረቤት አገር ገባ፡፡ ተጨማሪ እንዳንፈልግ ጫካውም ሥራ ፈትቶ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ጥረን ተጣጥረን ለረዥም ጊዜ የሚያገለግለንን ምግብ ገዝተን ማከማቸት አለብን፡፡ ለዚህ ገበያ ስምሪት የሚላክ ተወካይ ያስፈልገናል፡፡ ማን ቢሆን ይሻላል?”
“ነብር ይሁን!” አለ አንዱ እጁን አውጥቶ፡፡
 ብዙዎቹ ተቃወሙ፤ በተለይ ጦጢት፡፡
“አያ ነብሮ፣ ምግባችንን ቧጦ ቧጦ ከጨረሰብን፣ ሙልጫችንን መቅረታችን ነው፡፡ አለቀልን ማለት ነው፡፡”
“እሺ ሌላ የዱር አራዊት ጠቁሙ?”
“አያ አንበሳ ቢሆንስ?” አለ ዝንጀሮ፡፡
“አያ አንበሳ አይሆንም፤ እሱ ጉልበተኛ ስለሆነ ሁሉንም ጠቅልሎ ይበላብናል፡፡”
“እሺ ሌላስ?”
“ግስላ ቢሆን?”
“ግስላማ በፍፁም አይሆንም”
“እሺ ሌላ እጩ አምጡዋ?”
“ቀበሮስ ብትሆን?”
“ቀበሮም አትሆንም፡፡ ሰውን ማመን ከንቱ ነው እያለች ምኗ ይታመናል!”
“ታዲያ ማንን እናድርግ?”
“ኤሊ ትሁን” አለ ዝሆን
ሁሉም፤
“ኤሊ ጥሩ ናት፤ ኤሊ ታማኝ ናት…እሷ ትሁንልን” አሉ፡፡
ኤሊ ተመረጠችና፤
 “በይ ቶሎ ሸማምተሽ ነይ” ተባለች፡፡
ኤሊ ወጣች፡፡ ግን በጣም ቆየች፡፡ ሀሜት ተጀመረ፡፡
“ዱሮውኑስ ኤሊን መላክ ለምን አስፈለገ”
‹‹ዕውነት ነው፡፡ ቀርፋፋ መሆኗን እያወቅን፣ ምን አቅብጦን ነው እሷን የመረጥነው?››
“ሁለተኛ እሷን አንልክም!”
አጥብቀው ተቃወሙ፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ በሩ ተከፈተና ኤሊ አንገቷን ብቅ አደረገች፡፡
“እኔ እንደዚህ የምታሙኝ ከሆነ አልሄድም” አለች፡፡
***
በማናቸውም ሰዓት መንቀርፈፍ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ወይ መጀመሪያውኑ ሲመረጡ፣ “ፈቃደኛ አይደለሁም” ማለት ነው፡፡ ከፈቀዱ መከራውን መቻል እንጂ ማማረር አይገባም::  ዕድል ከጊዜ ጋር ቁርኝት አላት፡፡ ዕድል ከጊዜ ጋር ስትቀናጅ ተራማጅ እግር አላት፡፡ ስለዚህ እግር እንስጣት፡፡ በእኛ እግር ትራመድና ቀጥላ እርሷኑ ታራምድ፡፡
ግባችን ሩቅ ነው፡፡ መንገዱ መራራ ነው፤ ስንቁም ብርቱ ትጥቅ ይጠይቃል፡፡ ጉዞው ከባድ የመሆኑን ያህል፣ ከባድ መስዋዕትነትን ይሻል፡፡ ያለዚህ መስዋዕትነት አጭር ነው ያልነው መርዘሙ፣ አቃለልነው ያልነው መክበዱ አይቀሬ ነው፡፡
ከቶም የተስፋችን አበባው ሳይረግፍ
ዕምቡጥ ሳይፈነዳ ህይወት ሳይታቀፍ
የዕውነት ዜማ ሳይታቀፍ
የዕውነት ዜማ ሳይጠፍ
የዓለም ሃይሏ ሳይሰንፍ
ልብ፣ ቧንቧ ሳይዘጋ
እስትንፋስ ሳይቆልፍ
መንፈሳችን ሳያድፍ
ማነው መላ መቺ
ህዝቡን የሚታደግ
መፍትሔ የሚያፋልግ     
መንገዱን የሚጠርግ
በነጠላ ጫማ በአንቺ አረማመድ
እንዴት ያልቅልሻል ይህ ሁሉ መንገድ
የሚባለው ለዚሁ ነው!  

Saturday, 17 August 2019 14:28

የዘላለም ጥግ

 (ስለ ሞትና ውልደት)

• ሞት እንደ ውልደት ሁሉ የተፈጥሮ ምስጢር ነው፡፡
ማርክስ አዩሬሊዩ
• ከሞትክ በኋላ ከውልደትህ በፊት የነበርከውን ትሆናለህ፡፡
አርተር ሾፐንሃወር
• ውልደት የሞት መጀመሪያ ነው፡፡ ቶማስ ፉለር
• የውልደት ቀንህ፤ ወደ ሞትም ወደ ሕይወትም ይመራሃል፡፡
ሚሼል ደ ሞንታዥ
• ለሰዎች ማልቀስ ያለብን ሲወለዱ እንጂ ሲሞቱ አይደለም፡፡
ቻርለስ ደ ሞንቴስኪው
• ሕይወት ተቃራኒ የለውም፡፡ የሞት ተቃራኒ ውልደት ነው፡፡ ሕይወት ዘላለማዊ ነው፡፡
ኢክሃርት ቶሌ
• ሕይወታቸውን በጥልቀት የሚኖሩ ሰዎች፤ የሞት ፍርሃት የለባቸውም፡፡
አናይስ ኒን
• ሁሉም መንግስተ ሰማያት መግባት ይፈልጋል፤ ማንም ግን መሞት አይፈልግም፡፡
ያልታወቀ ሰው
• ሞት፤ ለወጣት የሩቅ አሉባልታ ነው፡፡
አንድሪው ኤ.ሩኔይ
• በእያንዳንዱ ማታ፣ ወደ መኝታዬ ስሄድ እሞታለሁ፤ ከእንቅልፌ ስነቃ ዳግም እወለዳለሁ፡፡
ማሃትማ ጋንዲ
• ትርጉም የለሽ ሕይወት ከመኖር ይልቅ፣ ትርጉም ያለው ሞትን እመርጣለሁ፡፡
ኮራዞን አኩይኖ
• ሕይወትን አጣጥም፡፡ ለመሞት በቂ ጊዜ አለ፡፡
ሃንስ ክሪስትያን አንደርሰን
• መሞት ቀላል ነው፤ አስቸጋሪው መኖር ነው፡፡
ፍሬድሪክ ሌንዝ
• ሞት ቅጣት ሳይሆን ሕግ ነው፡፡
ዣን ዱቦስ

Saturday, 17 August 2019 14:27

ከአዋቂዎች አንደበት


• ኢሕአዴግን ማፍረስ አገር ማፍረስ ከሆነ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡… ለሀገር ስንል ስሱ መሆን አለብን፡፡
አቶ የሺዋስ አሰፋ (የኢዜማ ሊ/መንበር)
• --የትግራይ ሕዝብ መገንጠል አይፈልግም፤ ከማን ነው የሚገነጠለው? ፍላጎቱ የህወሐት ነው፡፡---
ሙሉጌታ አረጋዊ (የሕግ መምህር- ለኢትዮ ታይምስ)
• የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚወቀስበት ነገር ካለ፣ መከራን ፀጥ ብሎ የሚሸከምበት ጀርባ ጽናቱ ነው… ያ ነው መወቀስም መፈተሽም ያለበት፡፡
ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ (የሕግ ምሁር-ለኢሳት)
• … የአባቶቻችን ደም ውስጣችን አለ፤ ዛሬ በአሜሪካን አገርና በአውሮፓ፣ ሌላው አፍሪካዊ አቀርቅሮ ሲሄድ ኢትዮጵያውያን ቀና ብለው የሚሄዱት፣ ያ ደም በውስጣቸው ስላለ ነው፡፡ አድዋ ላይ ድል
የሰራ ደም ነው፤ እያንዳንዱን የሚያፀና ደም::…
መምህር ዘነበ (አንዳፍታ ዩቲዩብ)
• …ቃል ጉልበት አለው፤ይተክላል፣ ይነቅላል:: ትውልድ ይፈጥራል፣ ትውልድ ያጠፋል:: ፍቅር ይዘራል፣ ጥላቻን ይዘራል፡፡ በቃል ውስጥ ብዙ መማር ብቻ ሳይሆን አገር መስራት ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ የተሰራችውም የፈረሰችውም በቃል ነው፡፡…
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ  (በ‹‹ማይንድሴት›› መድረክ)
• …መንጋና መንግስት ናቸው ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገባው፡፡ በዓለም ላይ ሰፊ የህይወት ጥፋት የፈፀሙት መንግስትና መንጋ ናቸው፡፡
ዶ/ር ኤርሴዶ ለንደቦ (አንዳፍታ ዩቲዩብ)
• … ምርጫን በተመለከተ እንደ ኢዜማ የተዘጋጀ ፓርቲ ያለ አይመስለኝም፡፡ ነገ ቢካሄድ 400 ወረዳዎች ላይ እጩ ማቅረብ ይችላል፤ ታዛቢ አለው፤ ሁሉ ነገር አለው:: 16 የፖሊሲ ሰነዶች ከሳምንት በፊት በምሁራን ያዘጋጀ ፓርቲ ነው። ግን ይሄ ሁሉ ሆኖ፣ ኢዜማ አገርን ነው የሚያስቀድመው::
አገር መኖር፣ መቀጠል አለበት፡፡ ሕዝብ፣ ከዚህ በላይ መሰቃየት የለበትም ብሎ ያስባል፡፡…
አቶ የሺዋስ አሰፋ (የኢዜማ ሊ/መንበር፤ ለአንዳፍታ)
• …በቀና ንግግርና በቀና ሃሳብ ብቻ አገር የትም አይደርስም፡፡ ቀና ንግግር እያወራን፣ ቅን ሃሳብ ባላቸው መሪዎች እየተመራን፣ ሲኦል ልንወርድ እንችላለን፡፡ እሱ ነው እኔ ግድ የሚለኝ፡፡ ፖለቲካው መሬት መያዝ አለበት፡፡--
ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ (የሕግ ምሁር፤ ለኢሳት)

Saturday, 17 August 2019 14:25

የፀሃፍት ጥግ

 • ሥነ ጽሑፍ የሚያሰላስሉ ሰዎች ሃሳብ ነው፡፡
ቶማስ ካርሎሌ
• የሥነ ጽሑፍ ዘውድ ግጥም ነው፡፡
ደብሊው ሶመርሴት ሞም
• ሁሉም ሥነ ጽሑፍ ሃሜት ነው፡፡
ትሩማን ካፖቴ
• መጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና አይደለም ሥነ ጽሑፍ ነው፡፡
ጆርጅ ሳንታያና
• ሃሜት ከሥነ ጽሑፍ የበለጠ ተወዳጅ ነው፡፡
ሁግ ሊዮናርድ
• የሥነ ጽሑፍ ታሪክ፤ የሰው ልጅ አዕምሮ ታሪክ ነው፡፡
ዊሊያም ሂክሊንግ ፕሪስኮት
• ሥነ ጽሑፍ የራሱን ሕጎች ይፈጥራል፡፡
ጆሴፍ ብሮድስኪ
• ሙዚቃ ሌላ ዓይነት ሥነ ጽሑፍ ይመስለኛል፡፡
ኬቪን ያንግ
• ድንቅ ንግግር ሥነ ጽሑፍ ነው፡፡
ፔጊ ኑናን
• ሳይንስና ሥነ ጽሑፍ መልሶችን ይሰጡኛል:: ፈጽሞ የማልመልሳቸው ጥያቄዎችም ያቀርቡልኛል፡፡
ማርክ ሃዶን
• ሕክምና ህጋዊ ሚስቴ ናት፤ ሥነ ጽሑፍ ደግሞ ውሽማዬ፤ አንዳቸው ሲሰለቹኝ ሌሊቱን ከሌላኛቸው ጋር አሳልፋለሁ፡፡
አንቶን ቼክኾቭ
• ያለ ሥነ ጽሑፍ ሕይወት ሲኦል ነው፡፡
ቻርለስ ቡኮውስኪ
• የሥነ ጽሑፍ ዓላማ ደምን ወደ ቀለም መለወጥ ነው፡፡
ቲ.ኤስ ኢሊዬት
• ሥነ ጽሑፍ፤ የሕይወት ምስጢራዊ ትርጉም ነው፡፡
አና ማርያ ማቱቴ
• ሥነ ጽሑፍ መስተዋት ብቻ አይደለም፤ ካርታ ነው፤ የአዕምሮ ጂኦግራፊ፡፡
ማርጋሬት አትውድ
• ሥነ ጽሑፍ ሕይወትን፣ አዕምሮንና ልብን የመለወጥ አቅም አለው፡፡
  ካሜሮን

Saturday, 17 August 2019 14:24

የተፈጥሮ ጥግ


 • ተፈጥሮን ተመልክቼ፣ ያየሁትን እንደ መሳል የሚያስደስተኝ ነገር የለም፡፡
ሄነሪ ሩሶ
• በእያንዳንዱ ተራራ ላይ መንገድ አለ፤ ከሸለቆው ሆኖ ላይታይ ቢችልም፡፡
ቲዎዶሮ ሮችኬ
• ተራሮች እየተጣሩ ነው፤ስለዚህ ወደዚያው መሄድ አለብኝ፡፡
ጆን ሙይር
• ቀለማት የተፈጥሮ ፈገግታዎች ናቸው፡፡
ሌይን ሃንት
• ተፈጥሮ፤ የወደዳትን ልብ ፈጽሞ አትከዳም፡፡
ዊሊያም ዎርድስ ዎርዝ
• ማር ፍለጋ ስትሄድ፣ በንቦች እንደምትነደፍ መገመት አለብህ፡፡
ጆሴፍ ጆበርት
• በእናት ተፈጥሮ የማትደነቅ ከሆነ፣ አንዳች ችግር አለብህ ማለት ነው፡፡
አሌክስ ትሬቤክ
• ተፈጥሮ፤ የእግዚአብሔር ጥበብ ናት፡፡
ዳንቴ ኢሊግሂሪ
• ምድር በአበቦች ውስጥ ትስቃለች፡፡
ራልፍ ዋልዶ ኢመርሰን
• ምድርን ከአያቶቻችን አልወረስነውም፤ ከልጆቻችን ነው የተዋስነው፡፡
የአሜሪካውያን አባባል
• በተፈጥሮ ሁሉም ነገር የሚከናወነው በዕድል ሳይሆን በሕግ ነው፡፡
ራልፍ ዋልዶ ኢመርሰን
• ሃቀኛ ሁን፤ ከሃቅ ጋር የምትወግን ተፈጥሮ ብቻ ናት፡፡
አዶልፍ ሉስ
• ምድርን ስንፈውስ፣ ራሳችንን እንፈውሳለን፡፡
ዴቪድ ኦር
• ከአንገቴ ላይ አልማዝ ይልቅ፣ የጠረጴዛዬን
ጽጌረዳ አበባ እመ


Saturday, 17 August 2019 14:22

የግጥም ጥግ

              የቁመራ ኑሮ

 ሁለት ገጽታ
ያንድ ሳንቲም
አንበሳና ሰው
አይገናኝም፡፡
አንበሳና ሰው
መለያየቱን
ጠይቅ በቁማር
የተበሉቱን፡፡
ይልቅ አብሮነት
አንድነት ካሉ
በይና ተበይ
አንድ ይሆናሉ፡፡
ሁሉም ገበያ፣
ሁሉም መርካቶ፣ ይሻገራሉ፡፡
ምን አለሽ ተራ
ምን ነካሽ ተራ
ምን ሰማሽ ተራ
ምን ሠራሽ ተራ
ምን አየሽ ተራ
ምን ገዛሽ ተራ
አለቅነ በሠበራ ሽጉጥ
              መዘክር ግርማ
           “ወደ መንገድ ሰዎች”


Page 9 of 449