Administrator

Administrator

አንዳንድ ዕውነተኛ ክስተቶች ሲቆዩ ተረት ይመስላሉ፡፡ የሚከተለው እንደዚያ ዓይነቱ ነው፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን፣ ከዓመታት በፊት፣ እዚሁ እኛ አገር የቀበሌና የከፍተኛ የሶስት ወር የሂሳብ ሪፖርት፣ ይሰማ ነበር ይባላል፡፡ በዚህ ስብሰባ ምክንያት የታሠሩ አንድ ሰው ለእሥር መዝጋቢው የነገሩት ነው፡፡ እንዲህ አሉ፤ “ሪፖርቱን ይሰማ ዘንድ የቀበሌው ነዋሪ ግዴታ አለበት፡፡”
በዚሁ መሰረት የዚያን ዕለት የቀበሌው ህዝብ ግልብጥ ብሎ ወደቀበሌው አዳራሽ መጥቷል፡፡
ሰብሳቢው -
“እንደለመደው የቀበሌያችንን የፋይናንስ ሪፖርት እናዳምጣለን” አሉ፡፡
ይሄኔ እኔ፤
“ከዚያ በፊት እኔ አንድ አስተያየት አለኝ” አልኩ፡፡
ዕድል ተሰጠኝ፡፡
(በዚያን ዘመን ገዢ የነበረው መንግሥት - “የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ” ነበር የሚባለው፡፡ የሽማግሌው አስተያየት ይህን ስም በተመለከተ ነበር)
“በተሰጠኝ ዕድል በመጠቀም የመንግሥታችን ስም “ጊዜያዊ” የሚለው ልክ አይደለም፡፡ ይሄን ሁሉ ዓመት አስተዳድሮን ዘላቂ የማይሆንበት ምክንያት አይታየኝም፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ “ጊዜያዊ” የሚለውን እንሰርዝና ዘላቂ እናድርገው” አልኩ፡፡
ህዝቡ በሁለት ተከፍሎ ሙግት ገጠመ፡፡ የጠዋቱ ስብሰባ እስከ ከሰዓት ዘለቀ፡፡ ሰብሳቢው ተናደዱና፤
“ስብሰባው ለሌላ ቀን ተዛውሯል” አሉና በተኑት፡፡
ከዚያ እኔም እንደሌላው ሰው ወደ ቤቴ እየሄድኩ ሳለሁ
“ትፈለጋለህ” ብለው ወደ እሥር ቤት አመጡኝ፡፡ ምን አጠፋሁ? ብል፤ “የፋይናንስ ስብሰባ አደናቅፈሃል!” አሉኝ… ካሉ በኋላ ወደ መዝጋቢው ፍርጥም ብለው ዞረው፤ “ይሄውልህ ወዳጄ፤ ይሄ መንግሥት ለምን ዕድሜ ጨመርክልኝ ብሎ አሠረኝ፡፡ ባጭሩ መቀጨት ነው እንዴ የሚፈልገው?” አሉ፡፡
***
ብዙ መንግሥታት የሚበጃቸውን አያውቁም፡፡ የሚጠቅማቸውን ሲመከሩ፣ በግድ ምክሩ ከራሴ ወገን ካልመጣ በሚል ይመስላል፤ አሻፈረኝ፣ አልሰማም ይላሉ፡፡ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ሹም እንዳሉት ነው፡፡ አንድ ጊዜ አንድ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ኃላፊው አልሰማ እያሉ ሲያስቸግሩት፤
“ይሆናል ሲሉዎት አይሆንም
አይሆንም ሲሉዎት ይሆናል፤
የርሶ ነገር ምን ይሻላል?”
ሲል ፃፈላቸው፡፡
ኃላፊው የመለሱለት፤
“ተጣጥሮ መሾም ነው!” የሚል ነበር፡፡
ይህ ዕውነታ ዛሬም የሚከሰት ነው፡፡ ልዩነቱ ዛሬ በግልፅ ሹሞቹ እንቢታቸውን አለመግለፃቸው ነው፡፡ አለመሰማማት ክፉ አባዜ ነው፡፡
የምክሩን ምንነት እንጂ የመካሪውን ማንነት ብቻ ማየት ከጥንት ጀምሮ ጐጂ ባህል ነው፡፡ ምክሩን አውቆና መርምሮ፣ ጠቃሚውንና ጐጂውን መለየትም ያባት ነው፡፡ ሁሉም ነገር ሂደት መሆኑን አለመርሳት ብልህነት ነው፡፡
አዲስ ሃሳብን እንደጠላት ማየት የዋህነት ነው፡፡ ሁሌ በአንድ ሀዲድ ላይ መሄድ ለውጥን ያርቃል እንጂ አያቀርብም፡፡ ፕሮጄክቶች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት፣ ዕቅዶች ከመተግበራቸው በፊት፣ የሚቀርቡ የሥጋት አስተያየቶችን ለእንቅፋትነት የተሰነዘሩ አድርጐ ማየት በተለይ ከተለመደ፤ አደገኛ ነው፡፡ የሚያመላክተውም የአሉታዊነት ኃይልን (Negative Energy) ነው፡፡
አለመቀበልን “እኔ ያልኩት ብቻ ነው ልክ” ማለትን፣ አልፎ ተርፎም ፍርደ ገምድልነትን ነው የሚያመጣው፡፡ ያ ደሞ ፀረ - ዲሞክራሲ ነው፡፡ ሥራዎች ከተሠሩ በኋላ “ይፍረሱ”፣ “እንደገና ይስተካከሉ”፣ “መጀመሪያም ፕላኑ ችግር ነበረበት” ማለት ጊዜን፣ የሰው ኃይልን፣ ገንዘብና ንብረትን ማባከን መሆኑን መቼም ማንም ጅል አይስተውም፡፡  ብዙ ተብሏል፡፡ አልተሰማም፡፡ ሆኖም መንግሥት ባይሰማስ እኛ ምን እናድርግ? ብሎ ማሰብም ደግ ነው፡፡ ሁሌ መንግሥትን በመጠበቅ ህዝብ ተባብሮ መሥራት የሚችለውን ተሳትፏዊ ተግባር አለመፈፀምም ደካማነት ነው፡፡ ለምሳሌ በ1966 ዓ.ም ድርቅ ወቅት የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች፤ ወሎና ትግራይ ድረስ በራሳቸው ወጪ ሄደው ህዝቡን ለመታደግ ጥረዋል፡፡ ዛሬም እንደዚያ ማሰብ ጠቃሚ ነው፡፡ ህዝብ በረሃብ ሲጐዳ እጅን አጣምሮ መቀመጥ፤ “ያንተ ቤት ሲንኳኳ ይሰማል እኔ ቤት” የሚለውን መዘንጋት ነው፡፡ ችግሩ ያገር ነውና አገር መረባረብ አለበት፡፡ ህዝብ የሚቻለውን ማድረግ አለበት፡፡ አለበለዚያ “ሁሉ ፈረስ ላይ ከወጣ ማን መንገድ ያሳያል” ይሆናል፡፡

     በኢንተርኔት ነጻነት ከ12 የአፍሪካ አገራት የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች ቻይና የኢንተርኔት ነጻነት በመገደብ 1ኛ ናት
    የኢንተርኔት ነጻነት በአለማቀፍ ደረጃ ለአምስት ተከታታይ አመታት እያሽቆለቆለ እንደሚገኝና ኢትዮጵያም የኢንተርኔት ነጻነት ከሌለባቸው የአለማችን አገራት አንዷ መሆኗን “ፍሪደም ሃውስ” የተባለው አለማቀፍ ተቋም ሰሞኑን ባወጣው አመታዊ ሪፖርት አስታወቀ፡፡ተቋሙ በ65 የአለማችን አገራት ላይ ያካሄደው የ2015 የኢንተርኔት ነጻነት ጥናት ሪፖርት፣ ከአለማችን አገራት የከፋ የኢንተርኔት ነጻነት የተንሰራፋባት ቻይና መሆኗን ጠቁሞ፣ ጥናቱ ካካተታቸው 12 የአፍሪካ አገራት መካከልም ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ነጻነት የመጨረሻውን ደረጃ ትይዛለች ብሏል፡፡
2.9 በመቶ የኢንተርኔት አገልግሎት ሽፋን ባለባት ኢትዮጵያ፣ የማህበራዊ ድረ ገጾችና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አፕሊኬሽኖች እንዲሁም ፖለቲካዊና ማህበራዊ ይዘት ያላቸው ጽሁፎች ይታገዳሉ፣ ጦማርያንና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ተጠቃሚዎችም ይታሰራሉ፣ ፕሬሱም ነጻ አይደለም ብሏል፡፡
በአገሪቱ የኢንተርኔት አቅርቦትና ተደራሽነት ችግሮች እንዳሉ የጠቆመው ሪፖርቱ፣ የአገልግሎት መቆራረጥና አዝጋሚነት በስፋት እንደሚያጋጥምና በአይሲቲው ዘርፍ ለሚሰማሩ ገለልተኛ ተቋማትና ስራ ፈጣሪዎች የሚሰጠው ዕድልም እጅግ ውስን ነው ብሏል፡፡የ2007 አገራዊ ምርጫ መቃረቡን ተከትሎ በርካታ ተጽዕኖ ፈጣሪ ዜናዎች እንዳይሰራጩ ታግደዋል፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድረገጾችም አገልግሎት እንዳይሰጡ ተደርገዋል ያለው ሪፖርቱ፤ ከ100 በላይ ድረገጾችም አሁንም ድረስ ታግደዋል፤ መንግስት በኢንተርኔትና በሞባይል በሚደረጉ ግንኙነቶች ላይ የሚያደርገውን ክትትልና ስለላ አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል፡፡
መንግሥት በበኩሉ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚሰነዘሩ ተመሳሳይ ትችቶችን ማስተባበሉ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በቅርቡ እንደገለፀው፤ የኢንተርኔት ስርጭትና አጠቃቀምን ለመቆጣጠር የሚያስችል ህግ ይፀድቃል፡፡
ኢትዮጵያ በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ቀዳሚ ከሆኑት የአለማችን አምስት አገራት አንዷ ናት ያለው ሪፖርቱ፣ ከ2014 እስከ 2015 ባለው ጊዜም፣ መንግስት ሃሳባቸውን በገለጹ ጦማርያንና በድረገጽ ጋዜጠኞች ላይ የሚያደርሰውን እንግልትና እስራት አጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ገልጿል፡፡የ2015 የኢንተርኔት ነጻነት ሪፖርት እንደሚለው፤ ጥናት ከተደረገባቸው 65 የአለማችን አገራት መካከል ነጻ የተባሉት 18 ሲሆኑ፣ 28 አገራት የተወሰነ የኢንተርኔት ነጻነት እንዳለባቸው፣ 19 አገራት ደግሞ  የኢንተርኔት ነጻነት እንደሌለባቸው ተረጋግጧል፡፡


“የእህል ምርት፣ ከአምና የበለጠ እንጂ ያነሰ አይሆንም”…ግብርና ሚኒስቴር “እንደ ኢትዮጵያ በድርቅ የተጐዳ የለም፤ 15 ሚሊዮን ሰው ሊራብ ይችላል”…ለጋሾችየዝናቡ መጠን ካለፈው ዓመት በ40 በመቶ ቀንሷል

ባለፉት 30 ዓመታት ባልታየ ከፍተኛ ድርቅ ሳቢያ፣ የተረጂዎች ቁጥር 15 ሚሊዮን ሊደርስ ደሚችል የተገለፀ ሲሆን ግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ፤ የዘንድሮ የእህል ምርት ከአምናው የበለጠ ይሆናል አለ፡፡ በኤሊኖ ምክንያት፣ እንደ ኢትዮጵያ በድርቅ የተጐዳ አገር ካለመኖሩም በተጨማሪ፣ ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የተረጂዎች ቁጥር ከ3 ሚሊዮን ወደ 8 ሚሊዮን እንደጨመረ መንግስትና ለጋሾች በጋራ ገልፀዋል፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላም የተረጂዎች ቁጥር 15 ሚ. ሊደርስ ይችላል ብለዋል - ለጋሾች፡፡ ግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ትናንት በሰጠው መግለጫ፣ ድርቁ ከባድ ቢሆንም፣ ከፍተኛ የእህል አምራች አካባቢዎች ላይ ብዙ ጉዳት አልደረሰም ብሏል፡፡ ዘንድሮ ምን ያህል እህል እንደሚሰበስብ፣ በስታትስቲክስ ኤጀንሲ ጥናት ይካሄዳል ያሉት የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ፤ ጥቅል የሀገሪቱ የእህል ምርት እንደማይቀንስ ግን በጥቅል ዳሰሳ

ለሳተላይት ሥርጭቱ ከ12ሚ. ብር በላይ ዓመታዊ በጀት ጸድቋል

    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ፣ ምእመና ድምፅዋን የምታሰማበትና መረጃ የምትሰጥበት የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት እንድትጀምር ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡
ከጥቅምት 12 ጀምሮ የዓመቱን የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በማካሔድ ላይ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የቴሌቪዥን አገልግሎቱን ለማስጀመር ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ በጀት ከትላንት በስቲያ ማጽደቁ ታውቋል፡፡
በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብዙኃን መገናኛ ድርጅት በሚል ተዋቅሮ ሥራ አስኪያጅ በመሠየምና እስከ 22 ሠራተኞችን በመቅጠር የሚጀምረው አገልግሎቱ፤ ዝግጅቱንና ቀረጻውን በሀገር ውስጥ በማከናወን በሳተላይት እንደሚሠራጭ ተገልጿል፡፡
 በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያ ተልእኮ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ የሚመራውና ዘጠኝ አባላት ያሉት የብዙኃን መገናኛ ቦርድ፣ የሳተላይት ሥርጭት አገልግሎቱን የሚሰጠው የኮሚዩኒኬሽን ኩባንያ በመምረጥ ሥራውን ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡
በሚዲያ ጥቅም፣ አሠራርና የወደፊት አቅጣጫ ለምልአተ ጉባኤው አባላት ማብራሪያ የሰጡት የቦርዱ አመራሮች፤ የሳተላይት ሥርጭቱ መካከለኛው ምሥራቅን፣ ደቡብ አውሮፓን፣ ሰሜንና ምሥራቅ አፍሪቃን እንደሚያካልልና ለተቀረው ዓለም ዝግጅቱን በኢንተርኔት በመጫን እንደሚያስተላልፍ አስረድተዋል፡፡
 በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ከ50 ሚሊዮን ያላነሱ አገልጋዮችና ምእመናን ያሏት ቤተ ክርስቲያኒቱ፣ ተከታዮቿን ለማስተማርና ለመጠበቅ የምትችልበት ተጨማሪ ሚዲያ ካላመቻቸች በተለይም ተረካቢውን ወጣት ትውልድ ለመድረስ እንደሚያስቸግራት፣ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡
 የሚዲያ ጥናት እና የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴውን በማስተባበርና የውጭ ተሞክሮዎችን በመዳሰስ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩት አቡነ ሳሙኤል፣ የቴሌቪዥን አገልግሎቱ ቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረተ እምነቷን፣ ሥርዐቷን፣ ትውፊቷንና ታሪኳን ለማስተማር፤ ቅዱሳት መካናቷንና ቅርሶቿን ለማስተዋወቅ፤ ለጥናትና ምርምር ለማነሣሣት፤ በየአህጉረ ስብከቱ የተሠሩ መልካም ሥራዎችን በማቅረብ የምእመኑን ድጋፍ ለማግኘት እንደሚረዳት “ሚዲያ እና ዓለምአቀፋዊ አስተሳሰብ” በሚል ርእስ ባቀረቡት ጽሑፍ አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዘንድሮና ቢያንስ በ7 በመቶ ያድጋል ተብሏል

     አለማቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ፤ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት የ2015 የኢኮኖሚ ዕድገት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስና ባለፉት ስድስት አመታት ከተመዘገቡት የአካባቢው
የኢኮኖሚ ዕድገቶች ዝቅተኛው እንደሚሆን መተንበዩን ቢቢሲ ዘገበ፡፡ተቋሙ ባለፈው ማክሰኞ ይፋ ባደረገው የአካባቢው የግማሽ አመት የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያ እንዳለው፣ አምና 5 በመቶ የነበረው የኢኮኖሚ ዕድገት ዘንድሮ ወደ 3.75 በመቶ ዝቅ እንደሚል የሚጠበቅ ሲሆን፣ ለኢኮኖሚ ዕድገቱ መቀነስ በምክንያትነት ከተጠቀሱት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከልም የነዳጅና የሸቀጦች ዋጋ መቀነስ እንዲሁም በቻይና ኢኮኖሚ ላይ የታየው መቀዛቀዝ ይገኙበታል፡፡ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራት የዘንድሮ የኢኮኖሚ ዕድገት ከአገር አገር የተለያየ እንደሚሆን የጠቆመው ተቋሙ፤ ኮትዲቯር፣ ኢትዮጵያና ታንዛኒያን የመሳሰሉ አገራት ዘንድሮና በቀጣዩ አመት የ7 በመቶ እና ከዚያ በላይ ዕድገት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል ብሏል፡፡የነዳጅ ዋጋ ከ2014 አጋማሽ ጀምሮ ከግማሽ በላይ መቀነሱ፣ ናይጀሪያ እና አንጎላን የመሳሰሉ የነዳጅ ላኪ አገራትን በተለየ ሁኔታ ተጎጂ አድርጓል ያለው ተቋሙ፤ ዛምቢያ፣ ጋና እና ደቡብ አፍሪካን የመሳሰሉ የሚኒኔራል ላኪ አገራትም በሸቀጦች ዋጋ ቅናሽ ክፉኛ እንደተጎዱ ገልጧል፡፡ከቅርብ አመታት ወዲህ በአለማችን ፈጣን ዕድገት ከሚያስመዘግቡ አካባቢዎች ተርታ መሰለፍ የቻለው ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት መንግስታት፣ የኢኮኖሚ ዕድገት ቅናሹ የሚያስከትላቸውን አሉታዊ ተጽዕኖዎች ለመቋቋም የሚያስችሉ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን እንዲያደርጉም አይ ኤም ኤፍ አሳስቧል፡፡

       የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ጸሃፊ አህመድ ሻሂድ ሰሞኑን ባወጡት ሪፖርት፣ የኢራን መንግስት በዚህ አመት ብቻ ከ1ሺህ በላይ ሰዎችን በስቅላት ለመግደል አቅዷል ማለታቸውን ፎክስ ኒውስ ዘግቧል፡፡
የኢራን መንግስት በተለያዩ ምክንያቶች በስቅላት የሚገድላቸው ሰዎች ቁጥር ባለፈው አመት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ያሉት ሻሂድ፣ የአገሪቱ መንግስት ካለፈው ጥር ወር አንስቶ 700 ያህል ሰዎችን በስቅላት መግደሉን ተናግረዋል፡፡ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ አለማቀፍ ህጎችን በመጣስ፣ ሁለት ወጣት ጥፋተኞችን በስቅላት የገደለው የኢራን መንግስት፤ በሌሎች  ወጣቶች ላይም ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈጸም እየተዘጋጀ መሆኑን የጠቆሙት ሻሂድ፣ ስቅላት የተፈረደባቸው አብዛኞቹ ወጣቶች በሰው ላይ ያደረሱት ጉዳት የለም፤ አደንዛዥ ዕጽ በመጠቀም ስለተወነጀሉ ብቻ ነው ቅጣቱ የተጣለባቸው ብለዋል፡፡የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች፤ ኢራን አለማቀፍ ህጎችን በመጣስ የራሷንና የውጭ አገራትን
ጋዜጠኞች ታንገላታለች በሚል በተደጋጋሚ ሲተቹ መቆየታቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ሻሂድም
ብዙ ጋዜጠኞች አመለካከታቸውን በማንጸባረቃቸውና ዘገባ በመስራታቸው ብቻ በአገሪቱ መንግስት
የከፋ ቅጣት እየተጣለባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በማህበራዊ ድረገጾች፤ ዜናዎችንና የተለያዩ ጽሁፎቻቸውን በማሰራጨታቸው ብቻ የሞት ቅጣት የተጣለባቸው ጋዜጠኞችም እንዳሉ ሻሂድ ገልጸዋል፡፡ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄም፤ ባለፈው የፈረንጆች አመት መጨረሻ ከ30 በላይ ጋዜጠኞች
በኢራን እስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ ማስታወቁን ዘገባው አክሎ ገልጿል፡፡

ለ35 አመታት የዘለቀው የ1 ልጅ ብቻ ፖሊሲ፣
ከ400 ሚ. በላይ ወሊዶችን አስቀርቷ
    ቻይና ዜጎቿ አንድ ልጅ ብቻ እንዲወልዱ የጣለችውንና ከ35 አመታት በላይ የዘለቀውን አስገዳጅ የስነህዝብ ፖሊሲ በማሻሻል፣ ሁለት ልጆችን መውለድ እንደሚችሉ የሚፈቅድ አዲስ ህግ ልታወጣ መወሰኗን ከትናንት በስቲያ ማስታወቋን ቢቢሲ ዘገበ፡፡የአገሪቱን የወሊድ መጠን ለመቀነስና የህዝብ ቁጥር ዕድገቱን ለመግታት ታስቦ የተቀረጸው “የአንድ
ልጅ ብቻ” ውለዱ ብሄራዊ ማዕቀብ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረበት እ.ኤ.አ ከ1979 ጀምሮ ባሉት
አመታት፣ በአገሪቱ ሊከሰቱ ይችሉ የነበሩ 400 ሚሊዮን ያህል ወሊዶች  መምከናቸውን ዘገባው
ጠቁሟል፡፡በአገሪቱ በእድሜ የገፉ ሰዎች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱ፣ ቻይና ተተኪ ትውልድ እንዳታጣ
ስጋት መፍጠሩን ተከትሎ፣ መንግስት የወሊድ ገደቡን እንዲያሻሽልና ዜጎች ተጨማሪ አንድ ልጅ
መውለድ እንደሚችሉ ለመፍቀድ እንዳነሳሳው ተገልጧል፡፡አንድ ልጅ ብቻ ውለዱ የሚለውን ህግ ጥሰው ሌላ ልጅ ጸንሰው የተገኙ ቻይናውያን ሴቶች፤ ጽንሱን እንዲያጨናግፉ ይገደዱ እንደነበር እንዲሁም ከስራቸው ይፈናቀሉና የተለያዩ ቅጣቶች ይጣሉባቸው እንደነበርም ዘገባው አስታውሷል፡፡

   ታዋቂው የኮምፒውተርና ስማርት ፎን አምራች ኩባንያ አፕል፣ ባለፉት 12 ወራት የሸጣቸው አይፎን ስልኮች ቁጥር ክብረ ወሰን ማስመዝገቡንና ይህን ተከትሎም በታሪኩ ከፍተኛ የሆነውን የ53.4 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ እንዳገኘ ማስታወቁን ዘ ቴሌግራፍ ዘገበ፡፡አፕል ባለፉት 12 ወራት ያገኘው አጠቃላይ ገቢ 233.7 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን የጠቆመው ዘገባው፤ ይህም ኩባንያው በሳምንት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ወይም በእያንዳንዷ ሰከንድ ከ1ሺህ 693 ዶላር በላይ ትርፍ ማግኘቱን ያሳያል ብሏል፡፡ኩባንያው እስካለፈው መስከረም ወር በነበሩት ሶስት ወራት ገቢው በ22 በመቶ በማደግ 51.5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ያስታወቀው አፕል ኩባንያ፤ በያዝነው ሩብ አመት ከ75.5 እስከ 77.5 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭ አስመዘግባለሁ ብሎ
እንደሚጠብቅም ገልጿል፡፡ባለፉት ሶስት ወራት 48 ሚሊዮን አይፎን ስልኮችን እንደሸጠ የጠቆመው ኩባንያው፣ በተጠቀሰው ጊዜም ሽያጩ የ22 በመቶ እድገት ማሳየቱን አስታውቋል፡፡

     ለኔፓል ሴቶች መብቶች መከበር ለረጅም አመታት በጽናት መታገላቸው የሚነገርላቸው የኔፓል ዩኒፋይድ ማርክሲስት ሌኒኒስት ኮሙኒስት ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር  ቢደሃያ ዴቪ ባንዳሪ፤ በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘገበ፡፡የአገሪቱን ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ባለፈው ረቡዕ በኔፓል ፓርላማ በተከናወነው የድምጽ አሰጣጥ ውጤት መሰረት፤ የኔፓል ኮሙኒስት ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር የሆኑት ዴቪ ባንዳሪ 327 ድምጽ በማግኘት በፕሬዚዳንትነት ሲመረጡ፤ ተፎካካሪያቸው 214 ድምጽ ማግኘታቸውን ዘገባው ገልጿል፡፡
ዴቪ ባንዳሪ በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ሆነው ቢመረጡም ሆኖ፣ በአገሪቱ ህግ መሰረት የመሪነቱን ሚና የሚጫወተው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመሆኑ ሴትዮዋ እንግዳ ከመቀበል ያለፈ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችሉበት ስልጣን እንደማይኖራቸው ዘገባው አስረድቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ካድጋ ፕራሳድ ኦሊ፤ በዚህ ወር መጀመሪያ የተቋቋመውን የአገሪቱ ጥምር መንግስት እንዲመሩ መመረጣቸውን ያስታወሰው ዘገባው፣ ባለፈው ወር የጸደቀው የኔፓል ህገ መንግስት አዲስ ፕሬዚዳንት መመረጥ እንዳለበት በደነገገው መሰረት፣ ረቡዕ ዕለት በተካሄደው ምርጫ የ54 አመቷ ቢደሃያ ዴቪ ባንዳሪ መመረጣቸውን ገልጿል፡፡
አዲሱ የኔፓል ህገ መንግስት ከፓርላማ አባላት አንድ ሶስተኛ ያህሉ ሴቶች መሆን እንዳለባቸው እንዲሁም ፕሬዚዳንት ወይም ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው የሚመረጡት የፓርላማ አባል፣ ሴት መሆን እንዳለባቸው የሚያስገድድ አንቀጽ እንዳካተተም ዘገባው አስታውሷል

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በድሬደዋ ከተማ ካሉ የግል የህክምና

ተቋማት ጋር በመተባበር ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ ለሚያደርገው ፕሮግራም ቴክኒካል ድጋፍ ይሰጣል፡፡ ስራው ከሚሰራባቸው የግል የህክምና ተቋማት በተወሰኑት ተገኝተን በአሁኑ ወቅት ስላለው የእናቶች እና ሕጻናቱ በቫይረስ የመያዝ ወይንም ነጻ ስለመሆን ጉዳይ የሚደረገውን ክትትል ተመልክተናል፡፡ የህክምና ባለሙያዎቹ የሰጡትን ምስክርነት ለንባብ ብለናል፡፡
ስተር እመቤት እሸቴ በሙያዋ ሚድዋይፍ ነርስ ናት፡፡ በእናቶች እና ህፃናት የህክምና ክፍል ውስጥ
ሀላፊ ሆና እየሰራች ነው፡፡ የሚከተለውን ብላለች፡፡ “...ሚድዋይፍ እንደመሆኔ አብዛኛው ስራዬ በማዋለዱ ላይ የሚያተኩር ቢሆንም ግን የእርግዝና ክትትል፣ የእናቶች እና ህፃናት አጠቃላይ ጤና እና ክትባት እነዚህን የመሳሰሉት ላይም እሰራለሁ፡፡ ከሁለት አመት ወዲህ የትኛዋም እናት ኤችአይቪ ቫይረስ በደሟ ከተገኘ መድሀኒቱን ወዲያውኑ እንድትጀምር እየሰራን ነው ያለነው፡፡ ስለዚህ ማንም እናት ወደ ተቋማችን ከመጣች በማዋለጃ ክፍልም ይሁን በእናቶች እና ህፃናት ክፍል እና በክትባትም ግዜ የሚመጡ እናቶች ከዚህ በፊት ሌላ ቦታ ተመረመሩም አልተመረመሩም እኛ ጋር የምክር አገልግሎት ተሰጥቷቸው እንዲመረመሩ ይደረጋል፡፡ ከተመረመሩ በኋላ ውጤቱ ይነገራቸዋል ውጤቱ ታይቶ ደግሞ ማድረግ ያለብን ነገር ካለ ቀጣዩን እርምጃ እንወስዳለን፡፡ ቀደም ሲል ሁሉም እናቶች ሊባል በሚችል ደረጃ የኤችአይቪ
ምርመራ ለማድረግ እሺ አይሉም ነበር፡፡ አሁን ግን መቶ በመቶ ማለት በሚያስችል ሁኔታ ለመመርመር ፈቃደኛ ናቸው፡፡ በወር ውስጥ 20 /እናቶችን ብናዋልድ ሀያዎቹም እናቶች ምርመራ ያደርጋሉ፡፡ ምርመራ በግዳጅ የሚደረግ ሳይሆን በሚገባ ግንዛቤ እንዲያገኙ አድርገን ጥቅሙ ገብቷቸው እና አምነውበት የሚደረግ ነው፡፡ አንዲት እናት የኤችአይቪ ምርመራ ማድረጓ የሚጠቅመው እራሷን ብቻ ሳይሆን ለልጇም እንደሆነ አብዛኛው የህብረተሰቡ ክፍል ተረድቶታል፡፡ ስለዚህ ምርመራውን የማታደርግ እናት የለችም ከብዛት አንድ ሊያጋጥም ይችላል እንጂ ሁሉም እናት ይመረመራል፡፡ የእርግዝና ክትትል ለማድረግ ወደ እኛ ሲመጡ እና ምርመራ ስናደርግላቸው ቫይረሱ በደማቸው የምናገኝው እናቶች ቁጥር በወር ውስጥ ሁለት ወይም ከዛ በላይ ነበሩ፡፡ አሁን ግን ያን አይነት ቁጥር የለንም፡፡ እና በጣም ትልቅ የሚባል መሻሻል ታይቷል፡፡” በድሬደዋ የግል የህክምና ተቋም ካገኘናቸው የህክምና ባለሙያዎች መካከል ሲስተር ቤተል አሸናፊ አንዱዋ ነች፡፡ ሲስተር ቤተል አሸናፊ የማዋለጃ ክፍል ኃላፊ ሆና ነው የምትሰራው፡፡ ስለአገልግሎቱ የሚከተለውን ገልጻለች፡፡                            
     “...ለእርግዝና ክትትልም ሆነ ለወሊድ አገልግሎት በወር በግምት 30-35 ክትትል የሚያደርጉ እናቶች ይኖሩናል፡፡ የሚወልዱትም በየወሩ ቢለያየም ግን በአማካይ ከ20-25 ይሆናሉ፡፡ ክትትል የሚያደርጉት ሁሉ እዚህ አይወልዱም፡፡ አንዳንዴ እዚህ ከአቅማችን በላይ የሆነ ነገር ሲፈጠር ወይም በሌላ ምክንያት በብዛት ወደ ድል ጮራ ሆስታፒታል እንልካቸዋለን፡፡ ከሌላ ቦታ ለመውለድ ብቻ እዚህ የሚመጡም አሉ፡፡ ምርመራውን እዚህ እኛ ጋር አድርገው ቫይረሱ በደማቸው ከተገኘ ወዲያው መድሀኒቱን እንድትጀምር እና አስፈላጊው ክትትል ሁሉ እንዲደረግላት እናደርጋለን፡፡ ልጁ ከተወለደ በኋላም አመት እስኪያልፈው ድረስ ምርመራም መድሀኒትም በበቂ ሁኔታ እንዲያገኝ እናደርጋለን፡፡ በቫይረሱ የሚያዙ አዲስ እናቶችን በሚመለከት ብዙም አይደለም እንጂ ይኖራሉ፡፡ አሁን ባለፈው ሀምሌ ላይ አንዲት እናት አግኝተናል፡፡ እኔ ይህንን ስራ ስሰራ ወደ ስድስት አመት ሆኖኛል፡፡ ከሁለት አመት በፊት የነበረውን እና አሁን ያለንበት ሁኔታ ሳነጻጽረው አሁን በጣም ብዙ ነገር ተቀያይሯል፡፡ ለምሳሌ አሁን ከቫይረሱ ነፃ የሆነ ልጅ እያዋለድን ነው፡፡ በፊት ይህ አይነቱ ነገር አልነበረም፡፡ አሁን ግን ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ነፃ ሆነው ነው
የሚወለዱት፡፡ ህብረተሰቡ በአሁኑ ሰአት ያለው ግንዛቤም በጣም ስለተቀየረ በዚህ ላይ ብዙ መሻሻሎች አሉ፡፡ አሁን ትንሽ ችግር አለ ብለን የምንለው እርጉዝ ሴቶች ለምርመራ ሲመጡ ባሎቻቸው አብረው ለመመርመር ፈቃደኛ አለመሆናቸው ነው፡፡ በእርግጥ አንዳንዶች ፈቃደኛ ቢሆኑም ብዙዎች ግን በስራ እና በተለያየ ምክንያት ሽፋን እየተሰጣቸው ለምርመራ እሺ ብለው አይመጡም፡፡ በእኛ በኩል ግን አስቀድሞውኑም እሺ ያሉትን ምርመራ እንሰራላቸዋለን፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ሚስቶቻቸው ሲወልዱ ስለሚመጡ በዚያን ጊዜ ምርመራ እንዲያደርግ እናግባባለን፡፡ ምክንያቱም እሱም ተመርምሮ እራሱን ማወቁ በቀጣይ ለሚኖራቸው ህይወት በጣም ጥሩ ስለሚሆን ነው፡፡ በጠቅላላው ግን በአሁኑ ሰአት ከቫይረሱ ነፃ የሆኑ ብዙ ህፃናትን እያገኘን ነው ለማለት እንችላለን፡፡    ዶ/ር ሰናይት ገ/የሱስ በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር የኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ በሚሰራው ፕሮጀክት ሙያዊ ድጋፍ የሚሰጡ ሲሆኑ ይህንን ድጋፍ ከሚያደርጉ ቡድን አባላትም ለተወሰኑት አስተባባሪ ናቸው፡፡ በድሬደዋ ከተማ ቡድኑ እየተዘዋወረ ስራውን ሲከታተል ያለውን ሁኔታ እንዲገልጹ የዚህ አምድ አዘጋጅ አነጋግራቸዋለች፡፡ “...ወደ ምስራቁ የሀገራችን ክፍል የመጣንበት ምክንያት ከኢሶግ ጋር በትብብር የሚሰሩትን የግል የህክምና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ እና መረጃ አሰባሰብን ለመመልት ነው፡፡  ፕግራሙ በትክክለኛው መንገድ እየተሰራበት ነው ወይ?፣ አንዲት እናት ስትመጣ የኤችአይቪ ምርመራ ይደረግላታል ወይ? ምርመራውን አድርጋ ቫይረሱ በደሟ ውስጥ ከተገኘም መድሀኒቱን ወዲያው
እንድትጀምር ይደረጋል ወይ?፣ ከቫይረሱ ነፃ ከሆነችም ይህንን ውጤት ጠብቃ እንድትቆይ የሚያደርግ የምክር አገልግሎት ታገኛለች ወይ? እና ባጠቃላይ ፕሮግራሙ በትክክል እየተሰራበት መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ በተጨማሪም ይህንን በተመለከተ ስልጠና ያልወሰዱ ባለሙያዎች ካሉም እዛው ቦታ ላይ የተወሰኑ ነገሮችን እንዲያገኙ እናደርጋለን ማለት ነው፡፡ በጅግጅጋ እና በሐረርም ቆይታ ያደረግን ሲሆን በአብዛኛው አሰራሩ በቆንጆ ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ለምሳሌ ሀረር ላይ ያሉ ሁለት ሆስፒታሎች ፕሮግራሙን የእራሳቸው አድርገው በጥሩ ሁኔታ እየሰሩ ነው፡፡ ብዙ ቦታ ላይ ችግር እየፈጠረ ያለው ይህ ፕሮግራም የእኛ ስራ አይደለም ተቀጥላ ፕሮግራም ነው የሚለው አስተሳሰብ ነው፡፡ ነገርግን አሁን እዚህ ድሬዳዋም ሀረርም ያየነው ነገር በጣም ጥሩ የሚባል ነው፡፡ በርግጥ ጅግጅጋ ላይ ከቫይረሱ ነፃ የሆኑ ሰዎች ብዙ አላየንም ግን ሁሉም እናቶች ምርመራውን ያደርጋሉ፡ ይሄም በጣም ቆንጆ ነገር ነው፡፡ አንዲት እናት ለመውለድ ወደ ህክምና ተቋም ስትመጣ ማዋለድ ግዴታ እንደሆነ ሁሉ ምርመራ ማድረግም የዛኑ ያህል ግዴታ መሆኑን የጤና ባለሙያዎች መረዳት እና ፕግራሙን እንደ አንድ የእራሳቸው ፕሮግራም ይዘውት መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ እዚህም የተመለከትነው ይሄንኑ ነው፡፡

                                  ***
በስተመጨረሻም በድሬዳዋ ጤና ቢሮ ውስጥ እናቶች እና ሕጻናት ጤና ላይ አስተባባሪ ሆነው
የሚሰሩትን ሲ/ር መሰሉ አጥናፌ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡        “...የኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ የሚያስችለው ህክምና እዚህ የተጀመረው በፈረንጆቹ 2001 ነበር፡፡ በድሬዳዋ ከተማ ከመንግስት የህክምና ተቋማት ውጪ በእናቶች እና ህፃናት  ጤና ላይ የሚሰሩ የግል የሕክምና ተቋማትም አሉ፡፡ በፊት ላይ መንግስታዊ ያልሆኑ የህክምና ተቋማት የእራሳቸው አሰራር ነበራቸው፡፡ አሁን ግን በእናቶች እና ህፃናት ጤና ላይ የሚሰሩት ተቋማት ከእኛ ጋር በትብብር ነው የሚሰሩት፡፡ ስለዚህ ድሬዳዋ ላይ የመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በአንድላይ ነው የምንሰራው፡፡ የመንግስትን ብቻ ተይዞ የሚኬድ ከሆነ ውጤትም አይኖረውም፡፡ ምክንያቱም በአብዛኛው በተለይም ደግሞ በግል የህክምና ተቋማት የሚገለገሉ እናቶች ቁጥር በጣም ከፍተኛ መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎች አቅሙም ፍላጎቱም
ሲኖራቸው ወደ ግል ተቋማት ይሄዳሉ በመንግስት ተቋማትም ይጠቀማሉ፡፡ ያለን ግንኙነት ምንይመስላል የሚለውን ስንመለከት በየጊዜው ኤችአይቪን ወይም የቤተሰብ ምጣኔን የተመለከተ ስልጠና ሲኖር የመንግስት እና ህብረተሰቡን በአግባቡ እያገለገሉ የሚገኙ የግል ተቋማትን ለምሳሌ እንደ ማሪያምወርቅ፣ አርት የመሳሰሉት በአጠቃላይ በግል የሚገኙትን ባለሙያዎች አንድ ላይ አድርገን እናሰለጥናለን፡፡ ስለዚህ እኛ ስናሰለጥን የመንግስት ብቻ ብለን ለይተን አናሰለጥንም ለሱፐርቪዥን ስንወጣም በሁለቱም በኩል ያለውን ነገር እናያለን፡፡ እነሱ ሲመጡም ከአጋሮቻችን አንድ ላይ ሆነን ሁሉም ተቋማት ጋር ያለውን ሁኔታ እናያለን ስለዚህ አሁን ቆንጆ ሁኔታ ነው ያለው በግል ተቋማት ላይ እራሱ በሚገርም ሁኔታ ኤችአይቪም እንበለው የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትም እንበለው ብዙ ግል ገበያ ያሚያስገባ ጉዳይ ቢሆንም እንኩዋን እነርሱ ግን ነፃ አገልግሎት ነው የሚሰጡት፡፡ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትም  የኤችአይቪ መድሀኒቶችም በነፃ ነው የሚሰጡት ከእኛ በላይ ትኩረት ሰጥተው ነው የሚሰሩት፡፡ ስልጠና ላይ የሚሰጡ ግብአቶችንም እንዴት ያገኛሉ ቢባል በድሬዳዋ ውስጥ 17 የህክምና ተቋማት ነው ያሉን ፡፡2 የመንግስት
ሆስፒታል፣ 15 ጤና ጣቢያዎች አሉን የእኛ አንዱ ሳቢያን የሚባል ጤና ጣቢያ የመጀመሪያ ደረጃ
ሆስፒታል ሆኗል፡፡ ስለዚህ ምንድነው የሚሆነው ምርመራ የሚያደርጉበት ግብአት ወይም
መድሀኒቶች ሲፈልጉ በስራቸው ያሉ ጤና ጣቢያዎች ከእነሱ ጋር ነው የሚወስዱት፡፡ ሪፖርታቸውም በእነሱ በኩል ነው የሚደርሰን፡፡ ስለዚህ እነዚህ ተቋማት ሃላፊነት አለባቸው ማለት
ነው፡፡ እያንዳንዱ የመንግስት የሕክምና ተቋማት በአካባቢያቸው ከሚገኙ የግል ተቋማት ጋር አንድ
ላይ ሆነው ነው የሚሰሩት ማለት ነው፡፡ በአሁኑ ሰአት የሚያስፈልገው ግብአት ሁሉ በአግባቡ
እየቀረበ ነው ያለው፡፡  በዚህ ስራ ላይ ለድሬዳዋ ጤና ቢሮ ድጋፍ እየሰጡን ያሉ አካላት እንደ ESOG እና CDC ያሉ ድርጅቶች አሉ እነሱን ስለሚሰጡን ድጋፍ ሁሉ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ ከፌደራል ጤና ጥበቃ
ሚኒስቴር ጋርም በጣም የጠበቀ ግንኙነት አለን፡፡ እነሱም በስራ ላይ ክፍተቶች እንዳይፈጠሩ
አስፈላጊውን ግብአት በማቅረብ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ነው፡፡ ስለዚህ አገልግሎቱ ዛሬ ያለበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የብዙ አካላትን እርብርብ ጠይቋል፡፡ ሁሉም ምስጋና ይገባቸዋል፡፡”  ስለዚህ በፊት ላይ የነበረው የኤችአይቪ የምክር አገልግሎት አንድ ሰው ብቻ ይዘሽ ከሁለታችን ውጪ ይህን የሚያውቅ የለም እያልሽ ማማከር ነው፡፡ ይህ አይነቱ የምክር አሰጣጥ በአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ላይ ከፍተኛ ጭንቀት ይፈጥራል መድሀኒቱም ሊቨራፒን የሚባል በምጥ ሰአት ብቻ የሚሰጥ ነበር፡፡ ቀስ እያለ ግን የምክር አገልግሎት አሰጣጡ መጀመሪያ ተጠቃሚዎችን በቡድን አድርጎ ስለ ኤች አይቪ ማስተማር ሆነ፡፡ ከዛም ለእርግዝና ክትትል የምትመጣ እናት ደግሞ ሌሎች ምርመራዎች እንደሚደረግላት ሁሉ የኤች አይቪ ምርመራ ማድረግ እንዳለባት እና አገልግሎቱም በነፃ የሚሰጥ እንደሆነ በሚገባ ይነገራታል፡፡ በዚህ መንገድ ተጠቃሚዎችን ሳታጨናንቂ በፈቃደኝነት እንዲመረመሩ ታደርጊያለሽ ማለት ነው፡፡ አሁን እንደበፊቱ አይደለም በፊት በቀን

ሁለት ፖዘቲቭ ሰዎች ይገኙ ነበር አሁን ግን ይህን አይነት ቁጥር የምታገኚው በሳምንት ውስጥ

ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ አሁን ፖዘቲቭ ለሆነች እናት ነው ጊዜ የምንሰጠው በፊት ላይ ግን

ፖዘቲቭም ሆነች ኔጌቲቭ ጊዜ ትወስጃለሽ ብዙ ተጠቃሚም ካውንስል አታደርጊም እንደገና ደግሞ

የምክር አሰጣጡ በተጠቃሚዎች ላይ ጭንቀት የሚፈጥር አይነት ነበር፡፡ መድሀኒቱም ደግሞ

እየተሻሻለ መጣ በፊት አንዲት እርጉዝ ሴት 28 ሳምንት ሲሆናት ነበር መድሀኒቱ የሚሰጣት አሁን

ግን Test and treat option B የሚባል መጥቷል ይህ እንግዲህ አንዲት እናት የኤችአይቪ

ምርመራ አድርጋ ፖዘቲቭ ከሆነች ወዲያው መድሀኒት እንድትጀምር የምናደርግበት መንገድ ነው፡፡
ቅድም እንዳልኩት የምክር አገልግሎት አሰጣጡም ተሸሽሏል እናቲቱን ከትዳር አጋሯ ጋር በአንድ ላይ አድርጎ መስጠት ያቻላል ብቻዋንም ብትመጣ አገልግሎቱን ታገኛለች፡፡ ስለዚህ አሁን
በሀገራችን እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል በፊት ግን ምርመራውን ለማድረግ ብቻ ከድሬዳዋ አዲስ አበባ
ድረስ እንልክ ነበር፡፡
መ፡ አሁን ቆኝጆ ሁኔታ ነውያለው እንደ በፊቱ እድሎ እና መገለል የለም፡፡ መሰረት የጣለ ትልቅ
የማስተዋወቅ ስራ ነው የተሰራው፡፡ ህብረተሰቡም ግንዛቤ አግኝቷል እሱም ተጨማሪ ሆኖ ኤችአይቪ ፖዘቲቭ የሆኑ እናቶች ደግሞ በየህክምና ተቋማቱ እራሳቸውን አውቀው አስፈላጊውን ትምህርት ወስደው መድሀኒቱን ይጀምራሉ፡፡ ይህንን የሚያስተባብሩ በየተቋማቱ አራት አራት ባለሙያዎች ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ ትልቅ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል በህብረተሰቡም ዘንድ ግንዛቤ መኖሩ እንዲጠነቀቁ አድጓል፡፡ ህብረተሰቡ ምርመራ አድርጎ እራሱን ያውቃል ከተመረመሩም በኋላ ደግሞ   የሚሰጠውን አገልግሎት እዛው ስለሚያገኙ አልፎ ተርፎ የቤተሰባቸውንም ጤንነት ይጠብቃሉ፡፡ እና የቫይረሱ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መጥቷል አዳዲስ የሚያዙ ሰዎችም ቁጥር ከበፊቱ በጣም ቀንሷል፡፡ ወደፊት ከኤችአይቪ ቫይረስ ነፃ የሆነ ትውልድ በማፍራት እረገድ ደግሞ አሁን ቫይረሱ በደማቸው ለሚገኝ እርጉዝ የሚሰጠው መድሀኒት ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ እና ባጠቃላይ ይህ ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ
የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት እኔ በግሌ ምጣም የረካሁበት ነው፡፡ በፊት ሆስፒታል በምሰራበት ወቅት ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ሆነው የሚወለዱ ህፃናትን ቁጥር የማየት እድሉ ነበረኝ እና አሁን ላይ ሆኜ ሳየው ከቫይረሱ ነፃ ሆኖ የመወለድ እድሉ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ እንግዲህ አስቢው እነዛ ሁሉ በቫይረሱ ቢያዙ ነገ ሀገርን የሚረከብ ትውልድ አይኖረንም ማለት
ነው፡፡ ከአራስነት ጊዜ ጀምሮ እስከ እድሜ ልክ መድሀኒቱን መውሰድ ማለትም በጣም ከባድ ነገር
ነው፡፡ ስለዚህ አሁን እየተሰጠ ያለው ህክምና ይህንን ሁሉ ስጋት በእጅጉ የቀነሰ ነው እኛም በጣም በጥሩ ሁኔታ እየሰራን ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ጥ፡ በመጨረሻ በዚህ ላይ የምትጨምሪው ነገር ካለ እድሉን ልስጥሽ
መ፡ በመጀመሪያ እናንተም እዚህ ድረስ መጥታችው እየተሰራ ያለውን ስራ መመልከታችሁ በጣም ጥሩ ነገር ነው፡፡ ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ ኖሮት እራሱን እንዲጠብቅ አዲስ የሚያዙ ሰዎችም ቁጥር እንዲቀንስ የማድረጉ ስራ ለህክምና ባለሙያዎች ብቻ የተተወ ሳይሆን ሌሎችም አካላት ተሳትፎ ሊያደርጉበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን ድርሻ በጣም ትልቅ የሚባል ነው፡፡ እኛ መርዳት ወይም ማሳወቅ የምንችለው ወደ ተቋማችን የሚመጡትን ብቻ ነው፡፡ ነገርግን የመገናኛ ብዙን ተደራሽነታቸው በጣም ሰፊ በመሆኑ ብዙውን የህብረተሰብ ክፍል ማስተማር እና ማሳወቅ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ እዚህ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ቢሰራበት ጥሩ ነው እላለሁ፡፡