Administrator

Administrator

   በሸካ አካባቢ የሚኖሩ ብሔር ብሄረሰቦችን ባህላዊ ትውፊትና የአካባቢውን ተፈጥሮአዊ ውበት የሚያሳየውና የ22 ደቂቃ ርዝመት ያለው “ድብቁ የሸካ ደን ውበት” ዘጋቢ ፊልም ትላንት ምሽት በልዑል ሲኒማ ተመረቀ፡፡ የሸካ ዞን አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ መልካ ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት ሲቪል ሶሳይቲ ፈንድ በመተባበር የሰሩትን ይህን ፊልም፤ አርቲስት ዮሃንስ ፈለቀ ያዘጋጀው ሲሆን በብሉ ሚዲያ ፊልም ፕሮዳክሽን ተሰርቶ ቀርቧል፡፡ በምርቃቱ ላይ የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች፣ የሸካ ዞን ኃላፊዎች፣ የመልካ ኢትዮጵያ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል፡፡

   22 አይነት የአገር ውስጥና የውጭ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው በሚናገሩት አቶ ካሱ ሰቦቃ የተዘጋጀውና “ሳንታ ማሪያ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የመዝሙር ቪሲዲ ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አዳራሽ ይመረቃል፡፡ አቶ ካሱ በኦሮምኛ፣ በአማርኛ፣ በግዕዝ፣ በስፓኒሽ በፈረንሳይኛ፣ በጀርመንኛ፣ በግሪክ፣ በቻይንኛ፣ በአረብኛና በጣልያንኛ 11 መዝሙሮችን ያዘጋጁ ሲሆን 12ኛው መዝሙር 11ዱን በምልክት ቋንቋ የሚያሳይ እንደሆነ ታውቋል፡፡ “የቅዱስ ዳዊት በገና ከቅድስት ኢትዮጵያ በዓለም ቋንቋ ሲገለፅ” በሚል መርህ የተዘጋጀው የዚህ ቪሲዲ ዋና አላማው የቅዱስ ዳዊትን በገና ለዓለም ለማስተዋወቅና የኢትዮጵያን የቱሪዝም መስህብነት ለማሳየት እንደሆነ ዘማሪው ተናግረዋል፡፡ በቪሲዲው ምርቃት ላይ ሚኒስትሮች፣ የኤምባሲ ተወካዮች፣ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች፣ አትሌቶችና አርቲስቶች እንደሚገኙም ተነግሯል፡፡ አቶ ካሱ አስተርጓሚ ከመሆናቸውም ባሻገር ታዋቂ ሼፍና አስጎብኚም እንደሆኑም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የታዋቂው የሬጌ አቀንቃኝ የቦብ ማርሊ 71ኛ ዓመት የልደት በአል የዛሬ ሳምንት አርብና ቅዳሜ በተለያዩ የሙዚቃ ድግሶች በሻሸመኔ ከተማ እንደሚከበር አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡
በሙዚቃ ድግሱ ላይ ሲድኒ ሰልማንና ራስ ጃኒን ጨምሮ ከዛምቢያ፣ ሴራሊዮን፣ አሜሪካና ሌሎች አገራት የተውጣጡ 14 አርቲስቶችና ዲጄዎች እንደሚሳተፉበት ታውቋል፡፡
የቦብ ማርሊን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ የሚቀርበው የሙዚቃ ድግስ ዋና ዓላማው፤ በስሙ የተሰየመውን ትምህርት ቤት ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ለማገዝ የሚያስችል ገቢ ለማሳሰብ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በአሉን አለምአቀፍ ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረግን ነው ያሉት አዘጋጆቹ፤ የሬጌ አድናቂው ማህበረሰብ በድግሱ ላይ እንዲታደም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

Saturday, 30 January 2016 12:06

የኪነት ጥግ

(ስለ ማስታወቂያ)
የማስታወቂያ ኤጀንሲ 85% ማደናገርና 15% ኮሚሽን ነው፡፡
ፍሬድ አለን
ሸማቾችን እንዲገዙ ወይም እንዳይገዙ የሚወስነው የማስታወቂያህ ይዘት እንጂ ቅርጽ አይደለም፡፡
ዴቪድ ኦጊልቪ
ፊል ናይት እባላለሁ፡፡ በማስታወቂያ አላምንም፡፡
ፊል ናይት
መጽሔት ሰዎች ማስታወቂያ እንዲያነቡ የመገፋፊያ መሳሪያ ነው፡፡
ጄምስ ኮሊንስ
ማስታወቂያ የንግድ የደም ሥር ነው፡፡
ካልቪን ኩሊጅ
በኪነጥበብ ውስጥ ኃያሲው ብቸኛው ነፃ የመረጃ ምንጭ ነው፡፡ የቀረው ማስታወቂያ ነው፡፡
ፖሊን ካኤል
ማስታወቂያ ሃጢያት የሚሆነው መጥፎ ነገሮችን ሲያስተዋውቅ ብቻ ነው፡፡
ዴቪድ ኦጊልቪ
ማስታወቂያ ህጋዊ የሆነ  ውሸት ነው፡፡
ኤች ጂ ዌልስ
ማንም ያስተላለፍከውን ማስታወቂያ የሚቆጥር የለም፤ ሰዎች የሚያስታውሱት የፈጠርክባቸውን ስሜት ነው፡፡
ቢል በርንባች
ስለማስታወቂያ ግድ የሚሰጣቸው በማስታወቂያ ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡
ጆርጅ ፓርከር
ጥራትን ስጣቸው፡፡ ያ ነው ምርጡ የማስታወቂያ ዓይነት፡፡
ሚልተን ሄርሼይ
ማስታወቂያ የቢዝነስ ልሳን ነው፡፡
ጄምስ አር .አዳምስ
ራስህን የማታስተዋውቅ ከሆነ በሚወዱህ ጠላቶችህ ትተዋወቃለህ፡፡
አልበርት ሁባርድ
በማስታወቂያ የተዋጣለት ለመሆን ማስታወቂያ እንዴት እንደሚሰራ ማወቅ አያስፈልግም፡፡
ዊንስተን ፍሌቸር

  - በ48 ሰዓታት ለ50 ሚሊዮን፣ በ87 ቀናት ለ1 ቢሊዮን ጊዜያት ታይቷል

      እንግሊዛዊቷ አቀንቃኝ አዴል ባለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ የለቀቀችው “ሄሎ” የተሰኘ የሙዚቃ ቪዲዮ በዩ ቲዩብ ድረገጽ በአጭር ጊዜ ውስጥ በበርካታ ሰዎች በመታየት ረገድ “ጋንጋም ስታይል” በሚለው የደቡብ ኮርያዊው የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ፒኤስዋይ ተወዳጅ ዜማ ተይዞ የቆየውን ክብረወሰን መስበሩ ተዘገበ፡፡
ዩ ቲዩብ ላይ በተለቀቀ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለ50 ሚሊዮን ጊዜያት ያህል የታየው የአዴል “ሄሎ”፣ በ87ኛው ቀን  ላይም አንድ ቢሊዮን ተመልካቾች እንዳዩት የዘገበው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፤በ2012 የተለቀቀው “ጋንጋም ስታይል” በበኩሉ ይህን ያህል ተመልካች ሊያገኝ የቻለው በ160 ቀናት ጊዜ ውስጥ እንደነበር አስታውሷል፡፡
የአስር ጊዜያት የግራሚ ተሸላሚዋ አዴል፤ነጠላ ዜማውን ያካተተችበትና ባለፈው ወር ለገበያ ያበቃችው “25” የተሰኘ የሙዚቃ አልበሟም፣ በአሜሪካና በእንግሊዝ የሙዚቃ አልበም ሽያጭ ታሪክ በፍጥነት በብዛት በመሸጥ ክብረወሰን መያዙን ዘገባው አመልክቷል፡፡
በአለማችን የሙዚቃ ቪዲዮ ታሪክ በዩ ቲዩብ ድረገጽ ተለቅቀው ለአንድ ቢሊዮን ጊዜያት ያህል መታየት የቻሉት የሙዚቃ ቪዲዮዎች 18 ብቻ እንደሆኑም ተጠቁሟል፡፡

Saturday, 30 January 2016 11:59

የጸሃፍት ጥግ

(ስለ ክዋክብት)

- ምሽት ደስ ይለኛል፤ ጨለማ ከሌለ ክዋክብትን
ፈፅሞ ማየት አንችልም፡፡
ስቲፌኒ ሜዬር
- ድቅድቅ ያለ ጨለማ ሲሆን ክዋክብትን ማየት
ትችላላችሁ፡፡
ራልፍ ዋልዶ ኢመርሰን
- ክዋክብትን በተመለከተ የምናየው ሁሉ የድሮ
ፎቶግራፋቸውን ነው፡፡
አላን ሙር
- እጣፈንታችን ያለው በክዋክብቱ ውስጥ
አይደለም፤ በራሳችን ውስጥ እንጂ፡፡
ሊሳ ማንትቼቭ
- እያንዳንዱ ኮከብ በውስጥህ ያለውን እውነት
የሚያንፀባርቅ መስተዋት ነው፡፡
አበርጅሃኒ
- ክዋክብት የዩኒቨርስ ጠባሳዎች ናቸው፡፡
ሪኪ ማዬ
- ማታ ማታ እዚያ ላይ የሚታዩት ክዋክብት
ከምታስቡት የበለጠ ቅርብ ናቸው፡፡
ዶውግ ዲሎን
- ጨረቃን አትጠይቁ! ክዋክብት አሉልን!
ኦሊቭ ሂጊንስ ፕሮውቲ
- ጨረቃ ሙሉ በማትሆን ጊዜ ክዋክብት ይበልጥ
ደምቀው ያበራሉ፡፡
ምንጩ ያልታወቀ
- ጉድጓድን አልሞ ከመምታት ይልቅ ጨረቃን
አልሞ መሳት ይሻላል፡፡
ምንጩ ያልታወቀ
- ክዋክብት የዘላለም የጎዳና መብራቶች ናቸው፡፡
ሃሪት ቱብማን
- ለክዋክብት አልም፤ ሰማይን ልትነካ ትችላለህ፡፡
ኦኪው ማንዲኖ
- ሁላችንም ክዋክብት ልንሆን አንችልም፤
ሁላችንም ግን ብልጭ ማለት እንችላለን፡፡
ሔነሪ ዋድስዎርዝ ሎንግ ፌሎው

Saturday, 30 January 2016 11:55

የዘላለም ጥግ

• ጥያቄ የሚጠይቁ ሰዎች አያስፈሩኝም፡፡ እኔን
የሚያስፈሩኝ መልስ ለመስጠት አሻፈረን
የሚሉት ናቸው፡፡
ጃሶን ባቼታ
- ዓለም አገሬ ናት፤ የሰው ልጆች በሙሉ ወንድሞቼ
ናቸው፤ በጎ መስራት ሃይማኖቴ ነው፡፡
ቶማስ ፓይኔ
- የልጆቼን አይስክሬም 38 በመቶ እየበላሁባቸው
ስለግብር ምንነት አስተምሬአቸዋለሁ፡፡
ኮናን ኦ’ብሪን
- የጣልያን ምግብ የመብላት ችግሩ ከአምስት
ወይም ከስድስት ቀን በኋላ እንደገና ይርብሃል፡፡
ጆርጅ ሚለር
- በድጋሚ ሚስት ከማግባት ይልቅ የማልወዳትን
ሴት ፈልጌ አንድ የመኖሪያ ቤት እሰጣታለሁ፡፡
ሮድ ስቲዋርት
- ምንጊዜም ከጨለምተኛ ሰው ገንዘብ ተበደር፡፡
ገንዘቡ ይመለስልኛል ብሎ አይጠብቅም፡፡
ኦስካር ዋይልድ
- ችግሮችህን ፈፅሞ ለማንም አትንገር፡፡ 20 በመቶ
ያህሉ ግድ የላቸውም፤ 80 በመቶው ደግሞ
በችግር በመጠመድህ ደስተኞች ናቸው፡፡
ሎዮ ሆልትዝ
- ትዳር ከመያዜ በፊት ስለልጆች አስተዳደግ
ስድስት ኃልዮቶች ነበሩኝ፤ አሁን ስድስት ልጆች
አሉኝ፤ ነገር ግን ምንም ኃልዮት የለኝም፡፡
ጆን ዊልሞት
- የሰውን አዕምሮ ከመልሶቹ ይልቅ በጥያቄዎቹ
መመዘን ይቀላል፡፡
ፒሬ ማርክ
- ሁሉንም ውደድ፤ ጥ ቂቶችን እመን፤ ማ ንም ላ ይ
መጥፎ አታድርግ፡፡
ዊሊያም ሼክስፒር
- ሃቁን የምትናገር ከሆነ ምንም ነገር ማስታወስ
የለብህም፡፡
ማርክ ትዌይን
- ዘመዶቻችንን እግዚአብሔር ሰጥቶናል፤
እግዚአብሔር ይመስገን ጓደኞቻችንን መምረጥ
እንችላለን፡፡
ኢቴል ሙምፎርድ
- ጋራዥ ውስጥ መቆም መኪና እንደማያሰኝህ ሁሉ
ቤተክርስቲያን መሄድም ክርስቲያን አያሰኝህም፡፡
ቢሊ ሰንዴይ

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ አባት ክፉኛ ይታመምና የአልጋ ቁራኛ ይሆናል፡፡ ባለቤቱ ቀደም ብሎ ህይወቷ አልፏል፡፡ ያለው አንድ ልጅ ብቻ ነው፡፡ የሚያስታምመውም እሱ ነው፡፡
በሰፈሩ በየምሽቱ የሚመላለስና በረት የሚያጠቃ አንድ ነባር ጅብ አለ፡፡ ሰው ሁሉ ይሄንን ጅብ ለመግደል ብርቱ ጥረት ያደርጋል፡፡ ሆኖም ሊገድለው የሞከረ ሰው ሁሉ በውጤቱ የሚናገረው አንድ ቃል ብቻ ነው፡፡
“እህ አያ እገሌ ያን ጅብ እንዴት አደረግኸው?” ይላል መንደሬው፡፡
አዳኙም፣
“አዬ! አድፍጬ አድፍጬ አመለጠኝ ባክህ!”
እንዲህ እንዲህ እየተባለ ያ ጅብ ግን በየማታው ከየበረቱ አንድ አንድ አህያና አንዳንድ ጊደር እየመነተፈ ጉልበቱ እየጠነከረ መጣ፡፡
ታማሚው አባትና ልጅም የዚሁ ጅብ ሰለባ እየሆኑ፣ ብዙ ከብት ከበረታቸው ተበልቶባቸዋል፡፡
አንድ ቀን አባትዬው ልጁን ጠርቶ፤
“ልጄ ሆይ”
“አቤት አባባ”
“የዚህን የጅብ ነገር አንድ መላ መምታት አለብን”
“ምን ዓይነት መላ አባዬ?”
“ወጥመድ ሰርተን እንይዘዋለን”
“ምን አይነት ወጥመድ?”
“ሄደህ ከመንደር ሙዳ ስጋ ገዝተህ ትመጣለህ”
“እሺ፤ ከዛስ?”
“ያንን ሙዳ ሥጋ በጠመንጃችን አፈ - ሙዝ ላይ ታስረዋለህ”
“እሺ፤ ከዛስ”
“ሙዳውን ያሰርክበትን ገመድ ጫፍ ጠመንጃው ቃታ ላይ ታስረዋለህ”
“ከዛስ?”
“በቃ ያንን ወስደህ በረታችን ፊት ለፊት ታስቀምጥለታለህ፡፡ አጅሬ ሥጋውን አገኘሁ ብሎ ሲጎትት ቃታውን ይስበዋል፡፡ ጥይቱ ባፉ ይገባና ድብን ያደርገዋል”
“እሺ አባዬ ዛሬ ማታ ያልከኝን አደርጋለሁ፤ ይሄ ከተሳካኮ የመንደሩ ህዝብ ነው የሚገላገለው፡፡ ለእኛም ጥሩ ስም ያተርፍልናል፡፡”
ልጅ በቃሉ መሰረት ሥጋውን ገዝቶ፣ ጠመንጃው ላይ አስሮ በረቱ ደጃፍ ላይ አስቀምጦ ይጠባበቅ ጀመር፡፡
ከሰዓታት በኋላ ልጁ ወደ አባቱ ሲሮጥ ይመጣል፡፡
“አባዬ አባዬ፤ ጉድ ሆነናል”
“ምነው? ምን ተፈጠረ” አለ አባት በድንጋጤ፡፡
“አባዬ፤ ጅቡ ጠመንጃውን በሰደፉ በኩል ነክሶ ሥጋውን ከነጠመንጃው ይዞት ሄደ፡፡”
አባትየውም፤
“ወይ ጉድ! እንኳን ጠመንጃ ሰጥተኸው እንዲሁም አልቻልነው!”
*          *          *
እንዲህ ያለ የሠለጠነ ጅብ አያድርስ ነው፡፡ ዛሬ በሀገራችን አያሌ የሰለጠነ ጅብ አለ፡፡ የሰለጠነ ጅብ መኖሩ ብቻ ሳይሆን የጅቦች ማሰልጠኛ ያለ ይመስል በርካታ ጅቦች መኖራቸው የበለጠ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ እጅግ የከፋው ነገር ደግሞ የጅቦች የተጠላለፈ መረብ፣ በሜዳ ስሙ “ኔትዎርክ” የሚባል መኖሩ ነው፡፡ ጅብ ለማጥመድ የሚሞክሩት ጥቂት ናቸው፡፡ ስለሆነም በመረቡ ተጠልፈው ራሳቸው ይያዛሉ፡፡ የሙስናን ነገር ለመፍታት እጅግ አዳጋች ያደረገው ይሄ ነው፡፡ ከላይ ነገሩን ይከላከላሉ፣ እርምጃ ይወስዳሉ የተባሉት አካላት ጉዳዩ ውስጥ ካሉበት ነገሩ ሁሉ የግብር ይውጣ እንደሚሆን ግልፅ ነው፡፡ “ስለገብስ አታውራ፡፡ ፈረሱ እንዳይሰማ” ሆኗል ችግሩ፡፡ የምናጠምደው ወጥመድ ሁሉ ጠመንጃ የሚያስነጥቀን ከሆነ ገንዘቡ፣ ሀብቱ፣ መሬቱ ወዴት እንደሚሄድ ያለጥርጥር መናገር ይቻላል፡፡ ፈረንጆች who guards the guards ይላሉ፡፡ ተቆጣጣሪዎቹን ማን ይቆጣጠራቸዋል፤ ጠባቂዎቹንስ ማን ሃይ ይላቸዋል፡፡ እንደማለት ነው፡፡ የቢሮክራሲው፣ የሥራ አስፈፃሚውና የነጋዴው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ዛሬ “ቢዝነስ” የሚባለው ቃል የተራው ዜጋ፣ የተራው ሟች (average mortal) ቋንቋ ሆኗል፡፡ የካፒታሊዝምን ሥርዓት መቀበል፤ “ነፃ ገበያ”፣ “የግል  ሀብት”፣ “የዲሞክራሲ ሥርዓት”፣ “የኢንዱስትሪ መስፋፋት”… እንደምንለው ቃለ-ተውኔት የቀለለ አይደለም፡፡
የካፒታሊዝምን ሥርዓት መቀበል “መሳም ወደሽ ጢም ጠልተሽ” ማሰኘቱ አይቀሬ ነው፡፡ የባህል ወረራው ታላቅ አደጋ ነው፡፡ In God we trust (በእግዚአብሔር እናምናለን) ከሚለው ዶላሩ ላይ ከተፃፈው መራሄ-ቃል ጀምረን (እንዲህ እያልሽ ውቴልሽን ሽጪ ይላሉ ወሎዎች) እስከ ታላላቅ የንግድ መቆጣጠሪያ ኮርፖሬት ኃይሎች ድረስ የተዘረጋ መረብ እንዳለ ማስተዋል አለብን፡፡ በዚህ መረብ ውስጥ የማይጠመደው ጅብ አለ፡፡ በምንም መልኩ ሰው ገለህም ቢሆን፤ ገንዘብ ያዝ የሚለው መርህ አለ፡፡ ከጋሪ እስከ መርከብ ነግደህ አትርፍ (እያጎ እንደሚለው “ገንዝብ ሰብስብ በተቻለ”) የሚለው አለ፡፡ ጉዳዩ ግን የአስርቱ ቃላት ግልባጭ ስብከት፣ ነው፡፡ ማለትም “ሥረቅ”፣ አመንዝር”፣ “የጓደኛህን ሚስት ተመኝ”፣ “ጎረቤትህን እንደራስህ አድርገህ ጥላ” ወዘተ ማለት ነው፡፡ የመንታፊዎች፣ የወሮበሎች፣ የመንገድ ላይ ጉልቤዎች፣ የታጣቂ ሰራቂዎች፣ የቁጭ በሉዎች፣ የምሁራዊ ሌቦች፣ የልማታዊ ቀማኞች፣ የአዛኝ - ቅቤ - አንጓች ዘራፊዎች፣ የረቂቅ አገር - ቦርቧሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ጨረታ በዝባዦች፣ የባንክና የኢንሹራንስ መዝባሪዎች ወዘተ መፈልፈያ ነው ካፒታሊዝም፡፡ ታዲያ እነዚህ ፍልፍሎች እንደቃላት መጠሪያቸው የረከሱ አይደሉም፡፡ የክርስትና ስምም፣ የማዕረግ ጥምም፣ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያገኘ ስምም፣ የቢዝነስ ስምም፤ ያላቸው  የተከበሩ  ሥራዎች ናቸው። እንደኛ የተደላደለ ኢኮኖሚ በሌላቸው አገሮች ላይ እንግዲህ በእንቅርት ላይ ጆሮ  ደግፍ፣ በቡሃ ላይ ቆረቆር ማለት ነው፤ ካፒታሊዝም፡፡ ገንዘብና ገንዘብ እንጂ ሌላ ነገር  አታስቡ፡፡ እነሆ አምላካችሁ እሱና እሱ ብቻ ነው! ይላል መጽሐፈ - ንዋይ! ዕውቀት ባልበለፀገበት፣ ሃይማኖት በገንዘብ እየተሸረሸረ ባለበት፣ ባህልና ቅርስ ካንገት በላይ እየታሰበ ባለበት፣ አገም ጠቀም ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ የሚያኮራ በሚመስልበት፣ የሚከበሩ በዓላት ሁሉ  የኛም እየመሰሉ በሚታዩበት፣ መሰረታዊ የሚባሉት ቤት፣ ውሃ፣ መብራት እንኳ በቅጡ በማይገኝበት አገር የካፒታሊዝም አባዜ ሲጨመርበት “እንኳን ጠመንጃ ሰጥተኸው እንዲሁም አልቻልነው” የሚያሰኝ ነው፡፡ ከዚህ ይሰውረን!   

• የግብጽና ሱዳን ሚኒስትሮች ልዩ ዝግጅት ለማድረግ መክረዋል
• የሶስቱ አገራት መሪዎች በአ/አ በግድቡ ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል

    የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በታችኛው የተፋሰሱ አገራት የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በማጥናት ላይ የሚገኙት አለማቀፍ አማካሪ ተቋማት፤ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ የቴክኒክ ሃሳቦቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅና የግብጽ የመስኖና የውሃ ሃብቶች ሚኒስትር ሆሳም ሞጋዚና የሱዳኑ አቻቸው ሞአታዝ ሙሳም፣ አገራቱ አማካሪዎቹ ለሚያቀርቧቸው ሃሳቦች ማድረግ የሚገባቸውን ልዩ ዝግጅቶች በተመለከተ መምከራቸውን የግብጽ መንግስት የኢንፎርሜሽን አገልግሎት ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡
ሁለቱ ሚኒስትሮች በቀጣዩ የሁለቱ አገራት የጋራ ከፍተኛ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ይፈረማል ተብሎ በሚጠበቀው የአገራቱ የውሃ ሃብቶች ትብብር የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ መወያየታቸውን የጠቆመው መረጃው፣ የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በሚመለከቱ ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውንም ገልጧል፡፡ የግብጹ አሃራም ድረገጽ በበኩሉ፤  የግብጽ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በዛሬው እለት በተጀመረው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸውን ጠቁሞ፣ በግድቡ ዙሪያ ከኢትዮጵና ከሱዳን አቻቸው ጋር ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘግቧል፡፡




-    የኩሪፍቱ ሪዞርት ቅርንጫቾች 9 ደርሰዋል
-    3 አዳዲስ ቅርንጫቾች በመገንባት ላይ ናቸው
-    በጅቡቲም በ150 ሚ. ብር ሪዞርት እየተሰራ ነው
በዓለም ላይ ያሉ ታዋቂ ሆቴሎች፣ ኤርፖርቶችና ከቀረጥ ነፃ (ዲዩቲ ፍሪ) ሱቆች፣ በዓለም የተሰራጩ የኢትዮጵያውያን ሬስቶራንቶች፣ … በኢትዮጵያውያን ቪሌጅ ውስጥ ኮርነር ወይም መደብር ሊኖራቸው ይችላል፡፡
ሀሳቡ የተጠነሰሰው ከ6 ዓመት በፊት ነው፡፡ ኢትዮጵያን ቪሌጅ፣ የኢትዮጵያ ቻምፒዮን (ምርጥ) ምርቶች የሚሸጡበት ማዕከል ነው፡፡ ምርቶቹን መሸጥ ብቻ ሳይሆን የምርት ሂደታቸውም  የሚታይበት ሥፍራ ነው፡፡ ጥጥ ሲፈተል፣ ሲደወር፣ ሲሸመን…፤ብረት ሲግል፣ ሲቀጠቀጥ፣ ሲቀልጥ … ፤የሸክላ ሥራው፣ አፈሩ ሲነፋ፣ ሲቦካ፣ ሲሰራ፣ በእሳት ሲቃጠል … በመጨረሻም የሁሉም ምርቶች የሚቀርብበት ማዕከል ነው - ኢትዮጵያን ቪሌጅ፡፡
የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭቃዎች አሰራር ለትውልድና ለልጅ ልጆቻችን የምናስተላልፍበት፣ የባህል ማዕከል ሆኖ የውጭ አገር ሰዎችና (ቱሪስቶች) ትልልቅ ማርኬተሮች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ፣ የአገራችንን ባህላዊ የወግ ዕቃዎችና የሚፈልጉትን ዓይነት ምርቶች ከአንድ ስፍራ የሚገዙበት የኤክስፖርት ማርኬት ለመጀመሪያ ጊዜ “የራሳችን ምርት ማዕከል” ሰፈር ወይም መንደር የምንለው የገበያና የማሳያ ቦታ በቢሾፍቱ (ኩሪፍቱ) በ74 ካ.ሜ ቦታ ላይ እየተገነባ ነው፡፡
በባልትና የተካኑ ታዋቂ አምራቾች፣ በአሁኑ ወቅት ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ እየላኩ ያሉ ታላላቅ ኩባንያዎች ከእኛ ጋር ለመሥራት ተመዝግበው የግንባታው ስራ እየተካሄደ ነው፡፡ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት የተለያዩ የኢትዮጵያ ምርጥ (ሻምፒዮን) ምርቶችን ሱቅ እየከፈትን፣ የኢትዮጵያን የቱሪዝም፣ የባህልና የኤክስፖርት ማዕከል፣ አዲሲቱን ኢትዮጵያ በግልጽ ለዓለም ማሳየት እንጀምራለን፡፡ የሚገነቡት ሱቆች ብቻ አይደሉም፤200 ያህል የኮንፈረንስና የቱሪስቶች ማረፊያ ክፍሎች ስለሚሰሩ ወጪው 400 ሚሊዮን ብር ይሆናል፡፡
በሪዞርት ደረጃም በኢትዮጵያ ትልቁን ስፍራ ይይዛል ብዬ አስባለሁ፡፡ አሁን 100 ክፍሎች አሉን፡፡ 200 ክፍሎች ሲጨመሩ 300 ክፍሎች ይኖሩናል፡፡ በአንድ ጊዜ 300 ያህል ሰዎች እናስተናግዳለን ማለት ነው፡፡ ግንባታው ሲጠናቀቅ በርካታ የኮንፈረንስ ክፍሎች ይኖሩናል፡፡ አሁን 1,000 ሰዎች መያዝ የሚችል አዳራሽ አለን፡፡ አዲሶቹ ሲጨመሩ ደግ ከ1,500 - 2,000 ሰዎች የሚያስተናግድ አዳራሽና ፋሲሊቲ ይኖረናል፡፡ በዚህ ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በዓይነቱም፣ በትልቅነቱም፣ በስፋቱም የመጀመሪያው ይሆናል ----- በማለት የኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ታዲዎስ ጌታቸው በለጠ፣ በግንባታ ላይ ስላለው አዲሱ የኢትዮጵያ ቪሌጅ ገልጸዋል፡፡
አቶ ታዲዎስ አርሲ ውስጥ በትንሽ መንደር ተወልደው፣ ደሴና አዲስ አበባ ነው ያደጉት፡፡ በ1973 ዓ.ም ወደ ሱዳን ገብተው፣ ለ3 ዓመት ከቆዩ በኋላ በስደተኝነት አሜሪካ ገቡ፡፡ እዚያም ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን የራሳቸው ፀጉር ቤት፣ የራሳቸው ሬስቶራንት ከፍተው ይሰሩ ነበር፡፡ ክለቦችንም ፕሮሞት በማድረግ ሰርተዋል፡፡ በዚህ ዓይነት እየሰሩ ድርጅቶቹ ወደ ሁለት አድገው ነበር፡፡
ከ20 ዓመት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ፣ በ1994 ዓ.ም በአገራቸው ኢንቨስት ለማድረግ ጓደኞቻቸውን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ፡፡ በመጀመሪያ በቦሌ መንገድ የሚገኘውን ቦስተን ህንፃ በ37 ሚ. ብር ገንብተው በቦስተን ስፓ ጀመሩ፡፡ ቦስተን ስፓ የአዲስ አበባና የአካባቢዋ ሴቶች ለሰርግና ለልዩ ዝግጅቶች የሚዋቡበት ምርጥ ስፓ ነው፡፡ በመቀጠልም በቢሾፍቱ ኩሪፍቱ ሪዞርት ተከፈተ፡፡ የሪዞርቱ ሥራ እያደገና እየሰፋ ሄዶ፣ ባህርዳር ኩሪፍቱ፣ አዳማ ኩሪፍቱ፣ ዝዋይ ኩሪፍቱ፣ … እያለ የኩሪፍቱ ቅርንጫፎች ብዛት 9 ደርሷል፡፡ አቶ ታዲዎስ በዚህ ብቻ አልረኩም፡፡ ሌሎች አዳዲስ ሪዞርቶች በቡራዩ ------------------፣ በጅቡቲ እያስገነቡ ነው፡፡
ኩሪፍቱ ሪዞርት ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶና አድጎ ወደ ውጭ የወጣ የመጀመሪያው ሪዞርት ነው፡፡ ጂቡቲ የተመረጠችበት የራሷ ምክንያቶች አሏት፡፡ ሁለቱም አገሮች የቱሪዝም ደጋፊ ከመሆናቸውም በላይ ጂቡቲ በዕድገት እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ፍላጎት አላት፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ጂቡቲ፣ ኢትዮጵያ የሌላትን ሰማያዊ ውሃ፣ ነጭ የባህር ዳርቻ አሸዋ፣ በርካታ የባህር ምግቦች፣ … ስላላት ነው፡፡ ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ ከኢትዮጵያ ከ40 ወይም 45 ደቂቃ የአውሮፕላን በረራ በኋላ የሚደረስባት መሆኗ ነው ያስመረጣት፡፡
ሌሎች ምክንያቶችም አሉ፡፡ የጂቡቲ ወደብ ከምስራቅ አፍሪካ ለየት ያለና በጣም ውብ ነው፡፡ ከዚህም በላይ 250 ሺህ ካ.ሜ ሰው ሰራሽ ደን አሉት፡፡ ኢትዮጵያውያን የጫጉላ ሽርሽርና ክብረ በዓላቸውን ጂቡቲ እየሄዱ እንደሚያሳልፉ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ የራሳቸው የሆነ የተሻለ ምርጫ ቢያገኙ በጣም ይደሰታሉ በማለት ኩሪፍቱ ቁጥር 2 በጅቡቲ እየተሰራ መሆኑን አቶ ታዲዎስ ገልጸዋል፡፡
የመጀመሪያው ምዕራፍ የጂቡቲ ኩሪፍቱ ፕሮጀክት 150 ሚሊዮን ብር ወይም 7 ሚሊዮን ዶላር ይፈጃል፡፡ ሪዞርቱ እየተስፋፋ ሲሄድ ወጪው ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል መናገር ይከብደኛል ይላሉ አቶ ጌታቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ሪዞርት፣ ለኢትዮጵያውያን አንድ መውጪያ አማራጭና መዝናኛ እንደሚሆን በእርግጠኝነት ተናግረዋል፡፡
በቱሪዝም በኩል ኢትዮጵያ በሰሜን ያላት እሴቶች፡- ላሊበላ፣ አክሱም፣ ጎንደር፣ ባህርዳር እንዲሁም በደቡብ ያሉ ሰፊ የሆኑ ሞዛይክ ባህላችንን እናስተዋውቅበታለን፡፡ ጂቡቲ ደግሞ ሰማያዊ ውሃዋን፣ የባህር ዳርቻዋን፣ የባህር ምግቦቿን፣ ሻርኮቿን፣ … በማስተዋወቅ ሁለቱም አገሮች ይጠቀሙበታል፡፡
ጂቡቲ በዓለም የሌለ ልዩ የሆነ የአሳ ነባሪ ጉብኝት፣ እንደጨው ባህር በአፍሪካ ዝቅተኛ ሥፍራ ላካሰን የተባለ ንፁህ የጨው ቦታ፣ የተፈጥሮ የሆኑ የተለያዩ የባህር ውስጥ እንስሳት (አኳሪየም) አሏት፡፡ እነዚህን ነገሮች አንድ ላይ ሲቀናጁ ጂቡቲ የመጣ ቱሪስት ወደ ኢትዮጵያ ጎራ ብሎ ይጎበኛል፡፡ እዚህ የመጣ ጎብኚ ደግሞ ወደ ጅቡቲ ሄዶ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት ያያል፡፡ በዚህ አይነት ሁለቱ አገሮች ዓለም አቀፍ እውቅና አግኝተው ቱሪዝማቸውን ያሳድጋሉ፡፡    
የጅቡቲው ኩሪፍቱ ግንባታው የተጀመረ ሲሆን በመጀመሪያው ምዕራፍ 64 ክፍሎች ይኖሩታል፡፡ የተለያዩ አገራት ሬስቶራንቶች፣ ስፓ፣ የተለያዩ የውሃ ላይ መዝናኛዎች፣ የዶልፊንና የሻርኮች ትርዒት፣ የተለያዩ የተፈጥሮ የውሃ ውስጥ እንስሳት መመልከቻ ጀልባዎች፣ … ለየት ባለ መልኩ የኢትዮጵያና የዓለም ቱሪስቶች ይስተናገዱበታል፡፡
ኩሪፍቱ ዕድገቱ እየተስፋፋ፣ ቅርንጫፎቹ እየበረከቱ ነው፡፡ እነዚህን ሁሉ ቅርንጫፎች በአንድ ዓይነት አስተዳደር ማናጅመንት መምራት የጥራት ደረጃው ተመሳሳይ የሆነ አገልግሎት መስጠት … ሊከብድ ይችላል፡፡ አቶ ታዲዎስ እነዚህን ጉዳዮች እንዴት ተወጥተዋቸው ይሆን?
እኛ ስንጀምርም ኢትዮጵያዊ ሆኖ ወደ ሌሎች አፍሪካ አገሮች ሊሻገር የሚችል፣ ኢትዮጵያዊ ዲዛይን ያለው፣ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የሰሩትና የሚመሩት (ካስፈለገ አፍሪካውያን የሚመሩትና የሚያስተዳድሩት) የኢትዮጵያንና የአፍሪካን ሬነሳስ ለዓለም ህዝብ የምናስተዋውቅበት ኮርፖሬት ማኔጅመንት አለን፡፡ እያንዳንዱ ቅርንጫፍ ደግሞ፣ የየራሱ አመራር አለው፡፡ ሰራተኞቻችንን የምንቀጥረው አሰልጥነንና ፈትነን ነው፡፡ ከጊዜው አሰራር ጋር እንዲተዋወቁና እንዲላመዱ የሥራ ላይ ሥልጠና ይሰጣቸዋል፡፡
ስለዚህ መቶ ቅርንጫፎች ቢኖሩንም አሰራርና ማኔጅመንታችን አንድና ተመሳሳይ ነው፡፡ ኩሪፍቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በብራንድ ደረጃ እያደገና እየሰፋ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ሰራተኞቻችንም ከጊዜ ወደ ጊዜ በአገልግሎት አሰጣጣቸው ልምድና ክህሎታቸውን እያገለበቱ ስለሆነ እኛ ኢትዮጵያውያን ለዓለም ህዝብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንሰጣለን በሚል ኩራት ይቀጥላሉ ብዬ አምናለሁ ብለዋል፡፡
 ኩሪፍቱ በየቦታው ቅርንጫፎቹን የሚከፍተው በትርፍ ቢንበሸበሽ ነው ወይስ ትርፉን መልሶ ኢንቨስት እያደረገ ነው? ጥያቄውን ለባለቤቱ አቀረብኩ፡፡ “የበለፀገችና ያደገች፣ የተለወጠች ኢትዮጵያን የማየት ዓላማና ፅናት ነው እንጂ በትርፍ ተንበሽብሸን አይደለም” አሉ፤ፍርጥም ብለው፡፡
እኛ የምናገኘውን ትርፍ ሁሉ ድንጋይና ሲሚንቶ ላይ ነው የምናውለው፡፡ እዚህ ደረጃ መድረስ የቻልነው በዓላማና በቁርጠኝነት፣ በማደግና በመለወጥ ላይ ያለችውን አገራችንን በምንችለው አቅም እንደግፍ ብለን፣ ፍላጎታችንን እየገታንና በየፕሮጀክቱ ከተባባሪ አካላት ጋር ጠንክረን በመስራት ነው በማለት አስረድተዋል፡፡
 
በአሁኑ ወቅት ካፒታላችሁ ምን ያህል ነው? አልኳቸው
አቶ ታዲዎስ ዝም ብለው መስራት እንጂ ካፒታላቸው ምን ያህል እንደሆነ አያውቁም፡፡ “በእውነት ነው የምልህ፣ ምን ያህል እንደሆነ አላወቀውም፡፡ አሁን እየበዛ ስለመጣ ቁጭ ብለንም ካልኩሌት አድርገነው አናውቅም ዕድገታችን ግን በግልፅ የሚታይ ነው፡፡ በቀጣይ እንመጣበታለን ብዬ አስባለሁ፡፡
አቶ ታዲዎስ ሲጀምሩ ራዕይ ነበራቸው፡፡ ራዕዩም ከአፍሪካ 100 ምርጥ ሪዞርቶች አንዱ መሆን የሚል ነበር፡፡ አሁን ያን ሕልማቸውን ምን ያህል እያሳኩ ይሆን? ይደረስበታል ብዬ አምናለሁ፡፡ ባለፉት 13 ዓመታት ባደረግነው ጠንካራ የቡድን ሥራ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ከዚህ በኋላ ያለው ሥራ ይከብደናል ብዬ ስለማላምን፣ በአፍሪካ በመጀመሪያ ተርታ ከሚሰለፉ ሪዞርቶች አንዱ፣ የኢትዮጵያን ስም የሚያስጠናራ ተወዳዳሪ የሚሆን ሪዞርት ይሆናል ብየየ አምናለሁ፡፡
ኩሪፍቱ፣ እንደሚገመተው ውድ አይደለም፡፡ የውጭ አተር ዜጎችና ዲያስፖራዎች ቢኖሩም አብዛኞቹ ደንበኞች ኢትዮጵውያን እንደሆኑ ባለቤቱ ይናገራል፡፡ “ዝም ብሎ የሚመጣ ነገር የለም፡፡ እኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፕሮሞት እናደርጋለን፡፡ “ኩሪፍቱ” የሚለው የብራንድ ስማችንም “ሂልተን፣ ሸራተን፣ …” እንደሚለው እየተለመደና እየታወቀ ስለሆነ ሥራችን በቋሚነትና በተከታታይነት እያደገ ነው የመጣው፡፡
እንደማንኛውም ሆቴል እንደየጊዜው የሚለዋወት ዋጋ አለን በእኛ ክረምት ሰኔ፣ ሐምሌና ነሐሴ የሚመጣ ቱሪስት የለም፡፡ በእነዚህ ሦስት ወራት ጎረቤት አገሮች ጂቡቲ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኩዌት ሌሎቹንም አገሮች የምናግባበት የተለየ ፓኬጆች አሉን፡፡ በዚያን ጊዜ ከተለያየ የዓለም ክፍሎች ልጆቻቸውን ይዘው የሚመጡ ኢትዮጵያውያን እናቶች አሉ፡፡ ጊዜውን እያየን ስለምንሰራና ፕሮሞት ስለምናደርግ አልጋችን ይያዛል፡፡
ኩሪፍቱ በአሁኑ ጊዜ ለ2000 ቋሚና ጊዜያዊ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ የኢትዮጵያውያኒ ቪለ፤ጅ ሥራ ሲጀምር 1,000 ወጣት ሴቶች ይቀጠራሉ፡፡ በመጪው ዓመት መጨረሻ በኩሪፍቱ ሪዞርት የሚሰሩ ዜጎች ቁጥር 3, 000 ይደርሳል ብለዋል፡፡