Administrator

Administrator

 ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ ነገ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቤተ መፃሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ በ “አንቀፅ 39” መጽሐፍ ላይ ውይይት እንደሚያካሂድ ገለፀ፡፡ የመጽሐፉ ደራሲ አቶ ውብሸት ሙላት፤ ለውይይቱ መነሻ ሃሳብ እንደሚያቀርቡ የጠቆመው ሚዩዚክ ሜይዴይ፤ የመጽሐፍት አፍቃሪያን በውይይቱ ላይ እንዲታደሙ ጋብዟል፡፡

በወጣት ቴዎድሮስ አበራ የተደረሰው “ሀገርህን ጥላት ልጄ እና ሌሎች ልቦለዳዊ ትረካዎች” ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡ መጽሐፉ አራት ታሪካዊ ልቦለዶችን ያካተተ ሲሆን በሃገርና ፖለቲካ እንዲሁም ባለፈውና በመጪው ትውልድ ዙሪያ ይሞግታል ተብሏል፡፡ በ214 ገፆች የተመጠነው መጽሐፉ፤ በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Saturday, 03 October 2015 10:39

የኪነት ጥግ

  (ስለ አርትኦት)
ህይወቴ አርትኦት (editing) ይፈልጋል፡፡
ምርት ሳህል
አርትኦት ያስጠላኛል፡፡ መፃፍ ደስ ይለኛል፤ ፅሁፌን መላልሶ ማንበብ፣ መከለስ ግን አልወድም፡፡
ባሪ ሃናህ
አርትኦት እወዳለሁ፡፡ ከፊልም ስራ የምወደው አንዱ  ክፍል ነው፡፡
ስቲቨን ስፒልበርግ
አርትኦት ለብቻ የሚሰሩት ዓይነት ሥራ ነው፡፡
ጆ ዳንቴ
ከምፅፋቸው እያንዳንዱ አራት ቃላት ውስጥ ሦስቱን እሰርዛለሁ፡፡
ኒኮላስ ቦይሉዩ
መሰረዝ መደለዝ የፈጠራ ምልክት ነው፡፡
ሜላኒ ሰርክል
የሚሰርዝ እጅ ብቻ ነው እውነተኛውን ነገር መፃፍ የሚችለው፡፡
ሜይስተር ጆሃን ኢክሃርት
ማንም ደራሲ ያለመታተምን የሚጠላውን ያህል አርትኦትን አይጠላም፡፡
ጄ.ራስል ላይንስ
ሌሎች በአንድ ሙሉ መፅሐፍ ያሉትን ነገር በአስር ዓ.ነገሮች መግለፅ ምኞቴ ነው፡፡
ፍሬድሪክ ኒቼ
ይሄን ደብዳቤ ያስረዘምኩት ለማሳጠር ጊዜ ስላልነበረኝ ነው፡፡
ብሌይዝ ፓስካል
ብዙ ድግግሞሽ፣ መላልሶ በማንበብና በአርትኦት ሊወገድ ይችላል፡፡
ዊሊያም ሳፋየር
ተገቢ ያልሆኑ ቃላትን አስወግድ፡፡
ዊሊያም ስትራንክ ጄአር
ባዶ ገፅን ልትከልሰው አትችልም፡፡
ሊኦናርድ ዎልፍ
በኪነጥበብ ቁጥብነት ሁልጊዜ ውበት ነው፡፡

Saturday, 03 October 2015 10:38

የዝነኞች ጥግ

ሌላውን መምሰል የለባችሁም፤ ማንነታችሁን ውደዱት፡፡
ሊ ሚሼል
ገንዘብ ማሳደዱን ትታችሁ፣ ከልባችሁ የምትወዱትን ነገር ማሳደድ ጀምሩ፡፡
Tony hsieh
ግብ፤ ቀነ-ገደብ የተቀመጠለት ህልም ነው፡፡
ናፖሊዮን ሂል
ሥራችሁን ለማሻሻል ከፈለጋችሁ የማይቻለውን ለመስራት ሞክሩ፡፡
ብሪያን ትሬሲ
መሞከራችሁን እስክታቆሙ ድረስ ተሸናፊዎች አይደላችሁም፡፡
ማይክ ዲትካ
እንደ ቢራቢሮ ተንሳፈፉ፤ እንደ ንብ ተናደፉ፡፡
ሙሃመድ አሊ
የምንቀጥረው በዓለም ላይ ምርጥ ነገሮችን ለመስራት የሚፈልጉ ሰዎችን ነው፡፡
ስቲቭ ጆብስ
ማለም ከቻላችሁ መስራት አያቅታችሁም፡፡
ዋልት ዲዝኒ
ተመሳሳይ ስኬቶችን መድገም አልወድም፤ ወደ ሌሎች ነገሮች ደግሞ መሻገር እሻለሁ፡፡
ዋልት ዲዝኒ
አመለካከት፤ ትልቅ ልዩነት የሚፈጥር ትንሽ ነገር ነው፡፡
ዊንስተን ቸርችል
እግራችሁን በትክክለኛው ቦታ ማኖራችሁን አረጋግጡ፤ ከዚያ ሳትበገሩ ቁሙ፡፡
አብርሃም ሊንከን
በሌላው ሰው ደመና ላይ ቀስተደመና ለመሆን ጣሩ፡፡
ማያ አንጄሎ

     በአፍሪካም ሆነ በኢትዮጵያ በቴኳንዶ ሙያ ኮሪያ ድረስ ሄዶ ቴኳንዶ የተማረ ብቸኛው አፍሪካዊ ኢትዮጵያዊ ብቸኛው የማስተር ማዕረግ ያለው አሰልጣኝ ነው - ማስተር አብዲ ከድር፡፡ ባለፈው ነሐሴ ወር በቡልጋሪያ ሶፊያ ዓለም አቀፉ-የቴኳንዶ ፌዴሬሽን (ITF) የተመሰረተበትን 60ኛ ዓመት ሲያከብር ለሙያው ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ የወርቅ ሽልማት ተበርክቶለታል”” የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ በህይወቱና በቴኳLዶ ሙያው ዙሪያ ከማስተር አብዲ ከድር ጋር ተከታዩን ቃለምልልስ አድርጋለች፡፡

    አንድ ሰው በቴኳንዶ ምን ደረጃ ላይ ሲደርስ ነው “ማስተር” የሚለውን ማዕረግ የሚያገኘው?
በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ ማስተር ለመባል የራሱ እርከን አለው፡፡ አንድ የቴኳንዶ ተማሪ ትምህርቱን ሲጀምር ከቢጫ ቀበቶ እስከ ጥቁር ቀበቶ ድረስ የራሱ ሂደቶች አሉት፡፡ ከጥቁር ቀበቶ በኋላ ፈርስት ዳን፣ ሰከንድ ዳን፣ ፎርዝ ዳን፣ እያለ ሲክዝ ዳን (6ኛ ዳን) ላይ ሲደርስ ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር የሚል ማዕረግ ያገኛል፡፡ ሰባተኛ ዳን ላይ ሲደርስ ማስተር የሚለውን ማዕረግ ያገኛል ማለት ነው፡፡ እኔም በዚሁ ሂደት ውስጥ አልፌ ነው ማስተር የሚለውን ማዕረግ ያገኘሁት፡፡
በቴኳንዶ ሙያ ለምን ያህል ጊዜ ሰራህ?
ላለፉት 40 ዓመታት ህይወቴ ከቴኳንዶ ጋር ተቆራኝቶ ነው ያለው፡፡ አላህ ከፈቀደ ወደፊትም በሚሰጠኝ ዕድሜ በዚሁ ሙያ እቀጥላለሁ፡፡
በእነዚህ 40 ዓመታት ውስጥ በሙያው ያደረግሃቸውን አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች እስኪ አስረዳኝ…
በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ ራሴ ከመማር አልፌ በኢትዮጵያና በአፍሪካ እንዲሁም በሌላው የዓለም ክፍል እየተዘዋወርኩ አስተምሬአለሁ፡፡ ኮሪያ ድረስ ሄጄ በከፍተኛ ማዕረግ የተማርኩ የመጀመሪያው አፍሪካዊና ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ በሙያው ያሳለፍኩት ውጣ ውረድ ከፍተኛ ነው፤ በተለይም በደርግ ጊዜ ፈተናው ከባድ ነበር፡፡ ዘርፉ እንዳሁኑ በመንግስት እውቅና ተሰጥቶት በይፋ ሊሰራ ቀርቶ እኛም እየተደበቅን ነበር የምንሰራው፡፡ ያ ሁሉ አልፎ በአሁኑ ሰዓት አገራችን በአሶሴሽን ደረጃ ተቋቁሞ የዓለም አቀፉ የቴኳንዶ ፌዴሬሽን አባል ለመሆን በቅተናል፤ እስካሁን ልጆች በማስተማር ክለቦችን በማቋቋም፣ አሶሴሽኑን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡ በአፍሪካም ሆነ በኢትዮጵያ ብቸኛው 7ኛ ዳን ያለኝ ነኝ፤ በዚህ በጣም ደስ ይለኛል፡፡
ከ7ኛ ዳን ወይም ማስተር ከሚለው ማዕረግ በላይስ ሌላ ማዕረግ አለ? ካለስ ወደዚያ ደረጃ ለማደግ ምን አይነት እንቅስቃሴ እያደረግህ ትገኛለህ?
በጣም ጥሩ! ከ7ኛ ዳን ቀጥሎ ያለው 8ኛ ዳን ነው፡፡ ቀደም ብዬ እንደነገርኩሽ 7ኛ ዳን ላይ ሲደረስ “ማስተር” እንደሚባል ሁሉ፣ 8ኛ ዳን ላይ ሲደረስ “ሲኒየር ማስተር” የተሰኘ ማዕረግ ይሰጣል፡፡ እኔም አላህ ፈቃዱ ሆኖ ከደረስኩ (እንደምደርስ ተስፋ አለኝ) ከስድስት ወራት በኋላ 8ኛ ዳን በማግኘት ደረጃዬን ወደ ሲኒየር ማስተርነት አሳድጋለሁ፡፡
ወደቴኳንዶ እንዴት ነው የገባኸው?
ቴኳንዶን የጀመርኩት ገና የአምስት ዓመት ልጅ ሆኜ ነው፡፡ እንዴት ጀመርክ ላልሺው ከአባቴ የወረስኩት ነው፡፡ አባቴ የቴኳንዶ ባለሙያ ነበር፡፡ እንግዲህ የአላህ ስጦታ ሆኖ እድሜዬን ሙሉ በስፖርቱ አሳልፌያለሁ፡፡ ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚቀጥለው ጥቅምት 1 60ኛ ዓመቴን አከብራለሁ፡፡ ከአምስት ዓመቴ ጀምሮ ከስፖርቱ ጋር ነኝ፤ እንደነገርኩሽ በከፍተኛ ደረጃ እየሰራሁ እየተማርኩ፣ በዓለምና በአፍሪካ እየተዘዋወርኩ 40 ዓመታትን አሳልፌያለሁ ማለት ነው፡፡
አሁን 60 ዓመትህ ነው ማለት ነው፤ ግን የ30 ዓመት ወጣት ነው የምትመስለው…
የማልደብቅሽ ነገር ስፖርቱ በራሱ ለአሁኑ የሰውነት አቋሜ የራሱን ሚና ተጫውቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እጅግ የማከብራት፣ የምወዳትና የማፈቅራት ሰላም የሆነች ሚስት አላህ ሰጥቶኛል፤ በኑሮዬ ደስተኛ ነኝ፡፡ ፈጣሪ፤ ሚስት የምትሰራው ከግራ ጎን ነው ይላል አይደል፤ የኔ ሚስት ግን ከሁሉም ጎኔ ነው የተሰራችው፡፡ እህቴም፣ ሚስቴም፣ እናቴም፣ አማካሪዬም… ብቻ ሁሉም ነገሬ ናት፡፡ ከእሷ የማገኘው ድጋፍ፣ እንክብካቤና ፍቅርም በራሱ ከእድሜዬ በታች ወጣት መስዬ ኧረ እንዲያውም ሆኜ እንድታይ ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል፡፡
በትዳር ምን ያህል ጊዜ ቆያችሁ? ልጆችስ አፍርታችኋል?
ላለፉት 31 ዓመታት አብረን በትዳር እየኖር ነው፡፡ በእድሜ ከእኔ በጣም ታንሳለች፤ ገንዬን አሳድጌያታለሁ ማለት ይቻላል፡፡ ልጆች አልወለድንም፤ ወደተለያዩ የውጭ አገራት ሄደን ምርመራ አድርገን፣ መውለድ ትችላላችሁ ተብለናል፡፡ አንድ ቀን ልጅ እንደሚኖረን ተስፋ አለን፡፡ ሆኖም በአሁን ሰዓት የልጅ ጉዳይ በኑሯችን ውስጥ እንደ እንከን ተጠቅሶ አያውቅም፡፡ በዙሪያችን ያሉ የማስተምራቸው ልጆች ሁሉ ልጆቼ ናቸው፡፡ አንድም ቀን በዚህ ቅር ተሰኝቼ፣ በትዳሬና በፍቅሬ ላይ እንቅፋት ሆኖብኝ አያውቅም፡፡ ገኒ ለእኔ ልጄም ጭምር ናት፤ እንዴት እድለኛ እንደሆንኩ አልነግርሽም፡፡
እስኪ ቡልጋሪያ ላይ ባለፈው ነሐሴ ወር ስላገኘኸው ሽልማት ንገረኝ…
ባለፈው ኦገስት በተካሄደው የኢንተርናሽናል የቴኳንዶ ፌደሬሽን 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቴኳንዶ ከፍተኛ እንቅስቃሴና አስተዋፅኦ ያበረከቱ 60 ሰዎች ተሸልመው ነበር፡፡ በዚህ ሽልማት ዝግጅት ላይ ተሳታፊ ብሆንም እንደምሸለምና እጩ እንደነበርኩ ግን አላውቅም ነበር፡፡ የኢትዮ ዮናይትድ ቴኳንዶ አሶሴሽን ፕሬዚዳንት እንደመሆኔ፣ 60ኛ ዓመት በዓሉን ለማክበር ወደ ቡልጋሪያ ሶፊያ ከተማ ሄጄ ነበር፡፡ ሽልማቱ ሲካሄድ ግን ብቸኛው አፍሪካ ኢትዮጵያዊ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆኔን ድንገት ሰማሁኝ፡፡ ይሄ እንግዲህ ለኢትዮጵያም ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ትልቅ ሽልማትና ኩራት ነው ማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ለዚህ ሽልማት ወደ 180 ያህል የዓለም አገራት ተሳታፊ ሆነውበት፣ ከነዚህ ሁሉ አገራት ነው ብቸኛው አፍሪካ ኢትዮጵያዊ የወርቅ ተሸላሚ የሆንኩት፡፡ ፈረንጆቹ ተሳሳቱ የምለው ሽልማቱን ለሚስቴ ለገነት ሀብተማሪያም ባለመስጠታቸው ብቻ ነው፡፡
እንዴት ማለት?
እኔ በጣም ተደባዳቢ፣ አስቸጋሪ ባህሪ የነበረኝና የማልረባ ሰው ነበርኩ፤ እርሷ ናት ለዚህ ማንነት ያበቃችኝ፤ የለወጠችኝ፡፡ በዚያ ላይ እርሷ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ስትሆን እኔ ሙስሊም ነኝ፡፡ የእርሷን ፆም እፆማለሁ፤ የእኔን ፆም ትፆማለች፡፡ የመቻቻል የመፋቀር ተምሳሌቶችም ነን፡፡ አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ ተባብለን ነው ከ30 ዓመት በላይ የዘለቅነው፡፡ የእርሷ ድጋፍና ፍቅር ገና ለብዙ ሽልማቶች ያበቃኛል፡፡ አንድ ነገር ልንገርሽ፤ 35ኛ የጋብቻ በዓላችን ላይ እንደገና ሰርግ ደግሰን ለመጋባትና ትዳራችንን ለማደስ እቅድ ይዘናል፤ አላህ ይርዳን፡፡
ኮሪያ ሄዶ ከፍተኛ የቴኳንዶ ትምህርት በመማር የመጀመሪያው አፍሪካዊ ኢትዮጵያዊ ነህ፡፡ ከኮሪያ ውጭ የት የት ተምረሃል?
ከዚያ በኋላ ያልሄድኩበትና ኮርስ ያልወሰድኩበት የዓለም ክፍል የለም፡፡ ለምሳሌ ጀርመን፤ እንግሊዝ፣ ስውዲንና ሌሎችም አገሮች ሄጄ በዘርፉ አሉ የተባሉ ኮርሶችን በመውሰድ እውቀቴን አዳብሬያለሁ፡፡ ሌላው ህንድ አገር በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ፊዚካል ኢጁኬሽን ተምሬአለሁ፡፡
በአሁኑ ወቅት ቴኳንዶ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለበት ደረጃ ምን ይመስላል?
ዘርፉ በደርግ ጊዜ የነበረበትን ሁኔታ ነግሬሻለሁ፤ በመንግስት አካላትና በተፈቀደላቸው ወገኖች ብቻ በገደብ የሚሰጥ ትምህርት ነበር፡፡ ቴኳንዶ በአሁኑ ሰዓት ጥሩ እውቅና አለው፡፡ ከመንግስትም በኩል እገዛ ይደረጋል፤ ነገር ግን እገዛው በቂ አይደለም፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ በቴኳንዶ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በማርሻል አርት በከፍተኛ ደረጃ ላይ ናት፡፡ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በክልሎችም በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ዩናይትድ ቴኳንዶ አሶሴሽን ስር ምን ያህል ተማሪዎች አሉ?
በአሶሴሽናችን ስር ብቻ 37 ሺህ ሰልጣኞች ይገኛሉ፡፡ ወደ 200 ያህል ክለቦችም እናስተዳድራለን፡፡
እስኪ ስለቴኳንዶ ሳይንስና ዲሲፕሊን በአጭሩ ንገረኝ…
በአጠቃላይ ቴኳንዶ ማለት ህይወት ነው፤ ሰዎች ስለቴኳንዶ ሲያስቡ እግርና እጅ ማወናጨፍ ብቻ ነው ብለው ካሰቡ በጣም ተሳስተዋል፡፡ ነገር ግን ሰው ከእግርና እጅ እንቅስቃሴ በፊት በመልካም ስነ ምግባርና ጥሩ ሰብዕና ጭንቅላቱ ይገነባል፡፡ ታጋሽ፣ ሰው አክባሪ፣ ማህበራዊ ኑሮ አዋቂ፣ በጎ አድራጊ… በአጠቃላይ የጥሩ ስብዕና ባለቤት እንዲሆን ተደርጎ ይቀረፃል፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ወደ አካላዊ እንቅስቃሴ የሚገባው፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት የስብዕና መሰረቶች ውጭ ሆኖ የቴኳንዶ ባለሙያ ነኝ የሚል ካለ፣ ጨርሶ የቴኳንዶን ሳይንስም ሆነ ዲሲፕሊን አያውቀውም ማለት ነው፡፡ ቴኳንዶ ማለት እጅ እግርና አዕምሮ የተቀናጁበት ጥበብ ማለት ነው፡፡ ቴኳንዶ፡- ሰላም፣ ፍቅር አንድነት ነው፡፡ እነዚህ ናቸው በቴኳንዶ ውስጥ ያሉት መሰረታዊ ነገሮች፡፡
በአገራችን በተለይም በመዲናችን በተለያዩ ቦታዎች በርካታ የቴኳንዶ ማሰልጠኛዎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ማሰልጠኛዎች ቃኝተሃቸው ታውቃለህ? ማሰልጠኛዎቹ ምን ያህል ትክክለኛውን የቴኳንዶ ስልጠና እየሰጡ ነው ትላለህ?
 የቴኳንዶ ትምህርት የሚያልቅ አይደለም፡፡ በሂደቱ ውስጥ ብዙ ስህተቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በሂደትም ይስተካከላሉ፡፡ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ዋነኛ ዓላማቸው መልካም ዜጋን ማፍራት ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ከሞላ ጎደል ትምህርቱን እየሰጡ ይገኛሉ፤ በዚያው መጠን ግን ችግር ያለባቸው የሉም ማለት አይቻልም፡፡ ግን በሂደት ሊቀረፉ ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ፡፡ አሁን በየቦታው ለዘርፉ ፈቃድ እየተሰጠ ነው፤ በዚያው መጠን ያሉባቸውን ችግሮች እንዲቀርፉ ማስጠንቀቂያዎችም ይሰጣሉ፡፡
ቴኳንዶ በጥበብና በዲሲፕሊን ካልተሰራ፣ ጋንግስተሮችን የምናፈራበትና ፈቃድ የሌለው መሳሪያ የምናስታጥቅበት ይሆናል፡፡ ቴኳንዶ ደግሞ ጋንግስተሮችን የምናፈራበት ሳይሆን ጋንግስተሮችን የምናጠፋበት ነው መሆን ያለበት፡
ቴኳንዶ በከፍተኛ የትምህርት ተቋም ደረጃ ስለሚሰጥበት ሁኔታ የታሰበ ነገር አለ?
ትምህርቱ በመንግስት በኩል በመምህራን ኮሌጅ ደረጃ እየተሰጠ ነው፡፡
 ዩኒቨርሲቲ ውስጥም እንደ አርት ትምህርት እየተሰጠ ነው፡፡ ወደፊት ራሱን የቻለ ዩኒቨርሲቲ እንዲኖረው ከውጭዎቹ ጋር በመነጋገር ላይ ነን፡፡ ይህ የሚሳካ ይመስለኛል፡፡
በርከት ያሉ የቴኳንዶ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዳሉህ ሰምቻለሁ፡፡ ምን ያህል ናቸው? የት የት ነው የሚገኙት?
በርካታ ተቋማት አሉኝ፡፡ ለምሳሌ አፍሪካ ህብረት ውስጥ፣ ኢሲኤ፣ ጁቬንቱስ ጣሊያን ክለብ ውስጥ፣ ሳር ቤት አዳምስ ፓቪሊዮን ህንፃ እንዲሁም፣ ፍፁም በላይ ሆቴል ውስጥ የማሰልጠኛ ተቋማት አሉኝ፡፡
በኢትዮ ዮናይትድ ቴኳንዶ አሶሴሽን ስር ደግሞ እንደ ፕሬዚደንትነቴ በስሬ ወደ 200 ያህል ክለቦች ይገኛሉ፡፡ እነዚህን እኔ ነኝ የምመራቸው፡፡
እነዚህ ክለቦች ተምረው ከፍተኛ ደረጃ ሲደርሱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉትን ቀበቶዎች (ዳኖች) ፈርሜ ከውጭ የማስመጣቸው እኔ ነኝ፡፡ ዳኖቹ የሚመጡት ከዋና ጽ/ቤታችን ከኦስትሪያ ቪዬና ነው፡፡
እስኪ ማርሻል አርት በሚባሉት እነካራቴ ጁዶ፣ ውሹ ቴኳንዶና ሌሎችም ስፖርቶች መካከል ስላለው አንድነትና ልዩነት በአጭሩ ንገረኝ?
ማርሻል አርቶች በኢንተርናሽናልና በወርልድ ቴኳንዶዎች የተከፋፈሉ ናቸው፡፡ የሚገርመው የነዚህ ማርሻል አርቶች ልዩነት የእንቅስቃሴ ልዩነት ነው፡፡ ውሹ የቻይና ስፖርት ሲሆን በብዛት በአክሮባትና ሰውነትን እንደልብ በማዘዝ (Flexibility) ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ በብዛት ታይገር ስታይል፣ ስኔክ ስታይል በማለት በእንስሳት እንቅስቃሴ ይከፋፍሏቸዋል፡፡ ካራቴ የምንለው የጃፓንና የፈረንሳይ ስፖርት ነው፡፡ ጃፓኖች እንቅስቃሴውን ልዩ አድርገው ስለቀመሩት ከቴኳንዶ ትንሽ ይለያል፡፡ ጁዶ ደግሞ በመያዝና በመጣል እንደ ትግል አይነት ስፖርት ሲሆን ብዙ ጊዜ ወታደሮች የሚያዘወትሩት ነው፡፡
በመጨረሻ የምታክለው ይኖርሃል?
የሚገርመውና ልጨምርልሽ የምፈልገው እስከዛሬ በኦሎምፒክ ውስጥ ወርልድ ቴኳንዶ ነበር ለውድድር የሚቀርበው፡፡
አሁን ግን በ2016 ሪዮ ዲጄነሪዮ በሚካሄደው 31ኛው ኦሎምፒክ ላይ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ከወርልድ ቴኳንዶ ጋር በጋራ ለውድድር ይቀርባል፡
በዚህም ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ወክለው የሚቀርቡ በመሆኑ በጣም ደስተኞች ነን፡፡ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ ትልቅ የምስራች ነውና እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡

  •    ሳዑዲ አረቢያና አጋሮቿ፣ ዘመቻውን አውግዘዋል።
  •    አሜሪካና አጋሮቿ፣ ዘመቻውን ተቃውመዋል።
  •     ኢራንና ኢራቅ፣ በደስታ ድጋፋቸውን ገልፀዋል።

   በሶሪያ ጠረፍ፣ አሮጌው የራሺያ የባህር ሃይል ሰፈር፣ እንደገና ሕይወት ዘርቷል። የሶሪያ ቀውስ ሳቢያ፣ የራሺያ ወታደሮች ከቦታው በመልቀቃቸው፣ አራት የጥበቃ ሰራተኞች ነበር የቀሩት። እነሱም፣ የዛሬ ሁለት አመት፣ ወጥተዋል። ኦናውን የቀረው የባህር ሃይል ሰፈር፣ እንደገና ነፍስ የዘራው፣ ካለፈው ወር ወዲህ ነው።
ዛሬ፣ የራሺያ የጦር መርከቦች የሚመላለሱበት ወደብ ሆኗል። የራሺያ መደበኛ ወታደሮችና የልዩ ሃይል አባላትም ይርመሰመሱበት ጀምረዋል። ይህም ብቻ አይደለም። ወደ ሰሜን በኩል የሚገኝ የአውሮፕላን ማረፊያ፣ የራሺያ አየር ሃይል ካምፕ ሆኗል። ከእነ ‘ሱ24’፣ እስከ ዘመናዊው ‘ሱ34’ ድረስ፣ ከሰላሳ በላይ የራሺያ የጦር አውሮፕላኖች፣ እንዲሁም ከደርዘን በላይ የጦር ሄሊኮፕተሮች ተሰማርተውበታል። ደግሞስ ወከባው!
የራሺያ ራዳር እና የአየር መከላከያ ሚሳዬሎች በየቦታው የተተከሉት፤... የማዘዣ ጣቢያ የተገነባውና ሰፊ የወታደሮች መጠለያ የተሰራው በጥድፊያ ነው። ካምፑን ለመጠበቅ ከመጡት ሁለት ሺ ያህል ወታደሮች ጋር፣ በርካታ ታንኮችና ብረት ለበስ መኪኖችም የካምፑ እንግዶች ሆነዋል።
ካምፑ እየሰፋ በእንቅስቃሴ ሲሟሟቅ፣ የየእለቱን ለውጥ፣ ከሳተላይት ምስል ማየት ይቻላል። በአውሮፕላን መንደርደሪያው ዳርና ዳር፣ የተሰለፉት አውሮፕላኖችም፣ ቁጥራቸው ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ እንደመጣ፣ ከሳተላይ የተነሱ ፎቶዎች ይመሰክራሉ። ሄሊኮፕተሮቹንም፣ አንድ ሁለት፣ ብሎ መቁጠር ይቻላል።
ምናለፋችሁ? የራሺያ አዲስ ዘመቻ፣ ገና ከጀምሩ፣ በጭራሽ ድብቅ ሚስጥር አልነበረም። እንዲያውም፣ ጉዳዩ ያሳሰባቸው የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት፣ “የራሺያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ምን ሊያደርጉ አስበው ነው?” በማለት ሲጠይቁ ቆይተዋል። እንዲያው፣ የሚያደርጉት ነገር ቢጨንቃቸው እንጂ፣ የነገሩ አካሄድ ወዴት እንደሆነ ጠፍቷቸው አይደለም። ቢቢሲ እንዳለው፣ የራሺያ አውሮፕላኖች ወደ ሶሪያ ያቀኑት፣ “ለበረራ ልምምድ” አይደለም። ለሽርሽርም ሊሆን አይችልም። የራሺያ መንግስት፣ የሶሪያ ጦርነት ውስጥ፣ ሙሉ ለሙሉ ለመግባት ወስኗል ማለት ነው።
እንዲያም ሆኖ፣ በቀጥታ፣ ከራሱ ከራሺያ መንግስት ጠይቆ መስማት ሳይሻል ይቀራል? የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ ይህንኑን ነው ያደረጉት። ሰኞ እለት፣ በዩኤን ጉባኤ ላይ፣ ከፑቲን ጋር በኒውዬርክ ተገናኝተው ተወያይተዋል። ፑቲን፣ ብዙም አዲስ ነገር አላወሩም።። ያው...
“አንደኛ፣ የሶሪያ ጣጣ፣ ብዙ አገራትን የሚነካ ነው። ሁለተኛ፣ ሶሪያ ውስጥ የሚዋጉ አክራሪዎችና አሸባሪዎች፣ ከብዙ አገራት የተውጣጡ ናቸው - ከራሺያም ጭምር። አሸባሪዎቹ፣ ወደ ራሺያ ተመልሰው ሽብር መፍጠራቸው ስለማይቀር፣ ከወዲሁ መዋጋት ያስፈልጋል...”
ፑቲን ይህን ከተናገሩ በኋላ፣ ኦባማ ምን አሉ? “በሶሪያ ዘላቂ መፍትሄ ዙሪያ፣ የሃሳብ ልዩነት ቢኖረንም፣ አሸባሪነት መዋጋት አስፈላጊ መሆኑ ግን ያግባባናል ብለዋል” ብለዋል - ኦባማ። ሰላም ይመስላል፤ አይደለም?
ግን አስቡት። አሜሪካና በርካታ የአረብ አገራት፣ በየእለቱ በአይሲስ ላይ የአየር ጥቃት ለመፈፀም፣ አውሮፕላኖቻቸውን እያሰማሩ ነው። ለተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች ደግሞ፣ ድጋፍ ይሰጣሉ። እና፣ የራሺያ ጦር፣ ጥቃት ለመፈፀም ሲነሳ፣ ከአሜሪካ አውሮፕላኖች ጋር ግጭት እንዳይፈጠር ምን አስቧል? ጥቃት የሚፈፅመውስ፣ በየትኛው ታጣቂ ቡድን ላይ ነው?
እነዚህ ጥያቄዎች፣ ፈፅሞ አልተነሱም። ራሺያ፣ የጦር አውሮፕላኖቿን ብታሰልፍም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአየር ጥቃት ትጀምራለች የሚል ግምት አልነበረም። ትልቅ ስህተት!
የ60 ደቂቃ ማስጠንቀቂያ
ረቡዕ እለት ነው፣ ስልክ የተደወለው። ቦታው፣ ኢራቅ፣ ባግዳድ። ከራሺያ ኤምባሲ፣ ወደ አሜሪካ ኤምባሲ ተደወለ። “የምንነግራችሁ አንዳች ቁም ነገር አለ” ... ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት የራሺያ ዲፕሎማት፣ ከፍተኛ የጦር ጄነራል ናቸው።
ዛሬ ነገ፣ ቀጠሮ ምንትስ አልተባለም። ጄነራሉ፣ አስደናቂውን ወሬ ለማድረስ፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ጋ ከች አሉ። ወታደራዊ ጉዳዮችን የሚከታተል የአሜሪካ ዲፕሎማት ጋር ነው መገናኘት የፈለጉት። ተገናኙ። እሺ፣ ምንድነው አጣዳፊውና አስደናቂው ነገር?
“በአንድ ሰዓት ውስጥ፣ የአየር ጥቃት እናካሂዳለን። ያሰማራችሁት አውሮፕላንና ወታደራዊ ሃይል ካለ፣ ገለል አድርጉ”...
ራሺያዊው ጄነራል፣ ይህን መልእክት እንዳደረሱ፣ ከ60 ደቂቃ በኋላ፣ የራሺያ አውሮፕላኖች ሚሳዬል ማስወንጨፍ ጀምረዋል ብሏል ቢቢሲ። የራሺያ ጦር ቃል አቀባይም፣ በአይሲስ እና በአሸባሪዎች ላይ የአየር ጥቃት ማካሄድ ጀምረናል በማለት መግለጫ ሰጡ።
አስገራሚው ነገር፣ አይሲስ የተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ላይ አንድም ፍንዳታ አልደረሰም። አንድም የራሺያ ሚሳኤል አልተተኮሰም። በተቃራኒው፤ በአሜሪካ የሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች፣ በራሺያ አውሮፕላኖች ጥቃት ሳይደርስባቸው አልቀረም የሚል ዘገባ ወዲያውኑ ተሰራጨ - ለዚያውም  በኒውዮርክ ታይምስ እና በዎልስትሪት ጆርናል ጋዜጦች። እና የአሜሪካ መንግስት ምን ምላሽ ሰጠ? ምንም! ምንም?
ጩኸት ከአለም ዙሪያ - አራምባ እና ቆቦ
አዎ፤ የአሜሪካ ባለስልጣናት፣ በራሺያ የተጀመረውን የአየር ጥቃት ተቃውመዋል። ጉዳት እንጂ ጥቅም የለውም ብለዋል - ባለስልጣናቱ። ነገር ግን፣ በአሜሪካ መንግስት የሚደገፉ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት መድረስ አለመድረሱን ለመናገር ፈቃደኛ አልሆኑም። የአውሮፓ መንግስታት አቋምም ተመሳሳይ ነው - ስጋት፣ ቅሬታ፣ ተቃውሞ። ከዚህ ያለፈ አይደለም።
ይልቅስ፣ በራሺያ ላይ፣ ከተቃውሞ ያለፈ ውግዘት የተሰነዘረው፣ ከሳዑዲ አረቢያ ባለስልጣናት ነው። የሳዑዲ አጋሮችም፣ ተቆጥተዋል - እነ ኳታር፣ እነ ባህሬን።
ግብፅና ዮርዳኖስ የመሳሰሉት ደግሞ፣ ዝምታን መርጠዋል።
ኢራን ግን ደስተኛ ናት። የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትርም እንዲሁ፣ ድጋፋቸውን በይፋ ገልፀዋል። እንዲያውም፣ የራሺያ አውሮፕላኖች፣ ኢራቅ ውስጥ፣ አሸባሪዎችን እንዲደበድቡልን እንፈልጋለን ብለዋል - ጠ/ሚሩ።
የአሜሪካና የአውሮፓ መንግስታት ቅሬታ፣ የሳዑዲና የኳታር ቁጣ፣ የግብፅና የዮርዳኖስ ዝምታ፣ የኢራንና የኢራቅ መንግስታት ደስታ... ይሄ ሁሉ ውጥንቅጥ፣ አለምክንያትና በድንገት የመጣ ጉዳይ አይደለም። የሶሪያ ጦርነት፣ ምንኛ እንደተወሳሰበም ያሳያል።
የመንግስት ጦርና በየቦታው የተሰማሩ በርካታ የመንግስት ደጋፊ የሚሊሺያ ቡድኖች... እንዲሁም ከመቶ በላይ አማፂ ወይም አሸባሪ ቡድኖች የሚጨፋጨፉበት ነው - የሶሪያ ጦርነት። በዚያ ላይ ከደርዘን በላይ መንግስታት፣ የጦር ሃይል አሰማርተውበታል። ውስብስብነት ሲያንሰው ነው።
ራሺያ በጀመረችው የአየር ጥቃት ላይ፣ ከየአቅጣጫው የተሰነዘረው ብዙ አይነት ምላሽ፣ አራምባ እና ቆቦ የሚሆንብንም በዚሁ ምክንያት ነው። ለሶሪያው ክፉ ጦርነት እልባት የሚሰጥ፣ አንዳችም መፍትሄ... አንዳችም የመፍትሄ ፍንጭ፣ ለጊዜው እንደሌለም ከዚህ መረዳት ይቻላል።
አንገትን የሚያስደፋ የ“አረቦች አብዮት”
የሶሪያው ቀውስ አጀማመር፣ አሁን አሁን እየተረሳ ቢመጣ አይገርምም። “አምባገነንነትን አስወግዶ፣ የነፃነት ለውጥን ያስገኛል” የሚል ተስፋ የተጣለበት የአረብ አገራት አብዮት ነው መነሻው። የዛሬ አራት አመት፣ የአለም ትልቁ መነጋገሪያ ነበረው “የአረብ አገራት አብዮት”፣ ዛሬ አገንትን የሚስደፋ ጉዳይ ሆኗል።
ኮሎኔል ሆስኒ ሙባረክን ከስልጣን የተባረሩበት የግብፅ አብዮት፣ ምን አይነት ለውጥ እንዳስገኘ ይታወቅ የለ? ብዙም ሳይቆይ ነው፤ “በዲሞክራሲያዊ ምርጫ”፣ የሃይማኖት አክራሪው ቡድን (ሙስሊም ብራዘርሁድ) ስልጣን ይዞ፣ ግብፅን ወደ ባሰ ጨለማ መንዳት የጀመረው። “ዲሞክራሲ” እና “ምርጫ”፣ በስልጡን ፖለቲካና በግለሰብ ነፃነት ላይ ካልተመሰረተ፣ በጎ ውጤት አያስገኝም።
ግብፅ፣ ጠቅልላ በጨለማ እንዳትዋጥ የሚከላከል፣ ከወታደራዊ አምባገነንነት የተሻለ ሌላ መፍትሄ አልተገኘም። ጄነራል አልሲሲ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ላይ ወጡ። ያው፣ የግብፅ አብዮት፣ ኮሎኔል ሙባረክን በጄነራል አልሲሲ በመተካት ነው የተጠናቀቀው። አንገትን ያስደፋል? የሌሎቹን ውድቀት ብታዩ፣ እንደዚህ አትሉም።
የመንንና ሊቢያን ተመልከቱ። መንግስት አልባ፣ የታጣቂ ቡድኖች መጫወቻ፣ የእልቂትና የስደት መናኸሪያ ሆነዋል። የሶሪያው ደግሞ ከሁሉም ይብሳል።
በአራት አመታት ውስጥ፣ የ250ሺ ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል። አንድ ሚሊዮን ሰዎች ቆስለዋል፣ አካላቸው አካላቸውን አጥተዋል። ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች፣ አገር ጥለው ተሰደዋል። 11 ሚሊዮን ሰው (ከአገሪቱ ህዝብ ግማሽ ያህሉ)፣ ከኑሮው ተፈናቅሏል።
ከተሞቻቸው እንዴት እንደፈራረሱ ስትመለከቱ፣ ጦርነቱ ምንኛ ክፋ እንደሆነ ሙሉ ለሙሉ ለመገንዘብ እንደሚያስቸግር ይገባችኋል። አሳዛኙ ነገር፣ ጦርነቱ ገና የተጀመረ እንጂ የተጋመሰ እንኳ አይመስልም።
በስተምስራቅ፣ “የኩርድ ቡድኖች” እና አይሲስ
በመቶ ከሚቆጠሩት፣ የመንግስት ተቃዋሚ ቡድኖች መካከል ትልቁ፣ አይሲስ ነው። በታጣቂዎች ቁጥር ብቻ አይደለም፤ ትልቅነቱ። የተቆጣጠረው ግዛትም ሰፊ ነው።
በእርግጥ፣ ወደ ቱርክ ድንበር አቅራቢያ፣ በኩርድ ተወላጆች የተመሰረቱ ታጣቂ ቡድኖች፣ የተወሰኑ የሶሪያ አካባቢዎችን ይዘዋል። ነገር ግን፣ የአገሪቱን ግማሽ ያህል ግዛት፣... ከቱርክ ድንበር ጀምሮ፣ የሶሪያ ምስራቃዊ ክፍል፣ በአይሲስ የተያዘ ነው። (“ሱኒ ሙሲሊም” በሚል የተቧደነው፣ ከሁሉም በላይ “ሺዓ ሙስሊሞች፣ መናፍቃንና ከሃዲዎች ናቸው” ብሎ በጠላትነት የሚፈርጅና የሚፈጅ መሆኑን አስታውሱ)።
በስተምዕራብ፣ የአሳድ መንግስትና ሄዝቦላ                   
በመንግስት ስር የሚገኘው የሶሪያ ክፍል፣ በስተምዕራብ አካባቢ ነው። በኢራን የሚደገፈው፣ የሊባኖሱ አሸባሪ ቡድን ሄዝቦላም፣ የአሳድ መንግስትን ለመደገፍ 3ሺ ያህል ተዋጊዎቹን፣ በዚሁ አካባቢ አሰማርቷል። ሌሎች የአሳድ ደጋፊ ታጣቂ ቡድኖችም እንዲሁ፣ በዚሁ የምዕራብ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ናቸው። (ሂዝቦላን ጨምሮ፣ አብዛኞቹ የአሳድ መንግስት ደጋፊዎች፣ “ሺዓ ሙስሊም” በሚል የተቧደኑና ከኢራን ድጋፍ የሚያገኙ ታጣቂዎች መሆናቸውን ልብ በሉ)።
ከመሃል፤ መቶ ታጣቂ ቡድኖች (አማፂዎችና አሸባሪዎች)
በስተምስራቅ፣ በመንግስት ጦርና በአጋሮቹ፣ የተያዘ ግዛት አለ። በስተምዕራብ ደግሞ፣ በአብዛኛው በአሸባሪው አይሲስ የተወረረ ግዛት አለ።
ከእነዚህ መሃል፣ ከላይ እስከ ታች፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከመቶ ያላነሱ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች፣ ተሰማርተዋል። ከመንግስት ጋር ይዋጋሉ። ከአይሲስ ጋር ይጨፋጨፋሉ። እርስበርስ ይተጋተጋሉ። አንዳንዴ ደግሞ፣ ሁለት ሶስት እየሆኑ፣ ወይም ደርዘን ያህሉ እየተሰበሰቡ፣ ህብረት ይፈጥራሉ። አይሲስ ሲበረታባቸው። ወይም የመንግስት ጦር ሲያይልባቸው። አንዳንዴ ደግሞ፣ በውጭ መንግስታት ግፊት (በተለይም በሳዑዲና በኳታር ግፊት) እየተሰባሰቡ፣ የጋራ ግንባር ፈጥረናል ይላሉ - የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት።
በየጊዜው የሚፈጠሩት ህብረቶች ብዙ ናቸው። የምር... ከሠላሳ ይበልጣሉ። ከእነዚህ ህብረቶች መካከል አንዱ፣ ‘Army of Conquest’ በመባል የሚጠራው ነው - ‘አስገባሪ ጦር’፣ ‘አስገባሪ ሰራዊት’... ልንለው እንችላለን።
አስገባሪ ሰራዊት... አሸባሪዎች የገነኑበት ሕብረት
ከሳዑዲና ከኳታር፣ የቢሊዮን ዶላሮች ድጋፍ የሚያገኙ ቡድኖችን ያካተተው ይሄው ‘አስገባሪ ሰራዊት’፣ ባለፉት ጥቂት ወራት፣ ከባባድ ዘመቻዎችን ሲያካሂድ ከርሟል። ደግሞም፣ የመንግስትን ጦር እያሸነፉ፣ በብዙ ቦታዎችን ተቆጣጥረዋል። በዚሁ ከቀጠሉ፣ ወደ ዋና ከተማዋ ወደ ደማስቆ እየተቃረቡ መሄዳቸው፣ አይቀርም። ለአሳድ መንግስት፣ እጅግ ከፍተኛ ስጋት ሆኗል።  
(በኳታርና በሳዑዲ ድጋፍ የሚደረግላቸውና “ሱኒ ሙስሊም” በሚል የተቧደኑ ታጣቂ ድርጅቶችን ያካተተ ‘ህብረት’ እንደሆነ አትርሱ። ከሁሉም በላይ፣ ኢራንን አምርሮ ይጠላል - ‘አስገባሪ ሰራዊት’።)
አስገራሚው ነገር፣ በ‘አስገባሪ ሰራዊት’ ውስጥ ከተካተቱት ቡድኖች መካከል ትልቁ፣ አልኑስራ የተሰኘው የታጣቂዎች ቡድን ነው። የአልቃይዳ የሶሪያ ቅርንጫፍ ማለት ነው። ማለትም... በይፋ በአሸባሪነት የተፈረጀ ቡድን ነው። ሁለተኛው ትልቁ ቡድን ደግሞ፣ በሶሪያ፣ የአክራሪው የሙስሊም ብራዘርሁድ ቅርንጫፍ ነው። ሦስተኛው ትልቅ ቡድንም፣ ሌላ አክራሪ ቡድን ነው። በእርግጥ፣ ‘አስገባሪ ሰራዊት’ ውስጥ የተካተቱ ሌሎች በርካታ ትናንሽ ቡድኖችም አሉ።
እንግዲህ፣ የሰሞኑ የራሺያ አየር ጥቃት ዋና ኢላማም፣ ይሄው ‘አስገባሪ ሰራዊት’ ነው።
ታዲያ፣ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት፣ መቆጣቱና ውግዘት መሰንዘሩ ይገርማል? የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብደል አልጁቤር፣ የራሺያን እርምጃ በመቃወም፣ በአፋጣኝ ጥቃቱ እንዲቆም ጠይቀዋል። ‘የሶሪያ መንግስት አሸባሪ ነው’ በማለት የተናገሩት አልጁቤር፣ ራሺያ አሸባሪዎችን እየተዋጋች ሳይሆን አሸባሪዎችን እየደገፈች ነው ብለዋል።
በእርግጥም፣ የአሳድ መንግስት አሸባሪ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን፣ በራሺያ አውሮፕላኖች፣ የአየር ጥቃት የደረሰባቸው የ‘አስገባሪ ሰራዊት’ ቡድኖችም፣ በአብዛኛው አሸባሪዎች ናቸው - የአልቃይዳ ቅርንጫፍን ጨምሮ።
የአሜሪካ መንግስትስ? ተስፋ አስቆራጭ የሶሪያ ሙከራ!
በሳዑዲ የሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች፣ የራሺያ ኢላማ ሆነዋል። በአሜሪካ የሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖችስ? አስቸጋሪ ጥያቄ ነው። አንደኛ ነገር፣ “በአሜሪካ የሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች” የሉም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ የአሜሪካ ድጋፍ፣ በአንድ ታጣቂ ቡድን ላይ ያተኮረ ሆኗል። ከመቶዎቹ ታጣቂ ቡድኖች መካከል፣ የትኛው ከአክራሪነት የፀዳ እንደሆነ ለመለየት አስቸጋሪ ነው። እናም፣ ለታጣቂ ቡድኖች ድጋፍ የመስጠት ፍላጎት፣ በአሜሪካ መንግስት ዘንድ ብዙ አይታይም። የለም።
ለነገሩ፣ ሌሎች አገራትም... ዮርዳኖስና የአረብ ኤምሬትስ እንኳ፣ ለሶሪያ ታጣቂ ቡድኖች የሚሰጡትን ድጋፍ ለማቋረጥ ወስነዋል። ከአክራሪነትና ከአሸባሪነት የራቀ፣ የሚታመን ቡድን ጠፍቷል። ግብፅም እንዲሁ፣ በሶሪያ ጣጣ ውስጥ እጇን ከማስገባት ተቆጥባለች። የግብፅ እጆች፣ በራሷ አገር ጣጣ እና በሊቢያው ቀውስ ውስጥ ተጠምደዋል።
የአሜሪካ መንግስትም፣ ለታጣቂ ቡድኖች ድጋፍ ከመስጠት ይልቅ፣ “ከአክራሪነት የፀዱ ናቸው” የሚባልላቸውን ሰዎች በማሰባሰብ ለማሰልጠን ነው የሞከረው። ግን ብዙ አይደለም። አንድ መቶ ታጣቂዎችን በዮርዳኖስ እንዲሰለጥኑ ተደርገዋል። አብዛኞቹ፣ የት እንደደረሱ አይታወቅም። ቱርክ ውስጥ በአሜሪካ የሰለጠኑትስ? ባለፈው ወር፣ 54 ሰዎች ስልጠናቸውን ጨርሰው  ሶሪያ ሲሰማሩ፣ አብዛኞቹ በአልቃይዳው ቅርንጫፍ (በአልኑስራ) ተገድለዋል። አራት ብቻ ናቸው ቀሩት።
ከሳምንት በፊት ደግሞ፣ እንደገና 75 ታጣቂዎች፣ በ12 ፒክአፕ መኪኖች ከነትጥቃው ወደ ሶሪያ ሲገቡ፣ እንደገና ከሽፎባቸዋል። የመዋጋት አቅም ስላልነበራቸው፣ ግማሽ ያህል ትጥቃቸውን በማስረከብ ነው ህይወታቸውን ያተረፉት ብሏል ቢቢሲ። በአሜሪካ የሚደገፍ የታጣቂ ቡድን ይሄው - (ማለትም፣ ከቁጥር የሚገባ አይደለም)።  
“ከአሜሪካ፣ ድጋፍ ያገኛል” የተባለለት ቡድን፣ በአጠቃላይ ከሰማኒያ በላይ ወታደሮች እንደሌሉት ይጠቅሳል - ዋሺንግተን ፖስት። እና፣ እነዚህ ታጣቂዎች ላይ፣ በራሺያ ጥቃት ተፈፅሟል? የአሜሪካ ወታደራዊ ሃይል ቃል አቀባይ ኮሎኔል ስቲቭ ዋረን፣ ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጡም። “በእርግጠኝነት የምንናገረው የራሺያ ጥቃት በአይሲስ ላይ አለመሆኑን ነው” ብለዋል - ኮሎኔሉ።
ጥቃቱ የተፈፀመው፣ ‘አስገባሪ ሰራዊት’ ላይ ነው። በተለይም በአልኑስራ ቡድን ላይ። “በአልኑስራ ላይ፣ ለምን ጥቃት ተፈፀመ?” ብሎ በግልፅ መከራከር ደግሞ አይቻልም። አሸባሪ፣ የአልቃይዳ ቅርንጫፍ ነው።   

ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የ2015 የአፍሪካ ሆቴሎች ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የሸራተን ሆቴሎች ባለቤት ኩባንያ የሆነው ስታር ውድ ሆቴል እና ሪዞርትን ጨምሮ ራዲሰን ብሉ፣ ሞቪንፒክ ሆቴል እና የስብሰባ ማዕከል እንዲሁም ሌሎች ዝነኛ አለማቀፍ ሆቴሎች በአፍሪካ ሆቴሎችንና ሪዞርቶችን ለመገንባት ስምምነት ፈጽመዋል፡፡የሸራተን መለያ ስም ባለቤት የሆነው ስታርውድ ኩባንያ፤ በ5 የአፍሪካ ሀገሮች ተጨማሪ 7 ሆቴሎችን ለመክፈት ተስማምቷል፡፡
በግብፅ፣ በማሊ፣ በናይጄሪያ 2፣ በኬንያ፣ በሴኔጋል ሆቴሎቹ በመጪው አመት ይከፈታሉ ተብሏል፡፡ ራዲሰን ብሉ ሆቴልና ማረፊያ በበኩሉ፤ በአሁን ወቅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በ27 የአፍሪካ ሀገራት 65 ሆቴሎችን እንደሚያስተዳድር ጠቁሞ በዚህ አመት መጨረሻ በኬንያ እና በሌሎች 5 የአፍሪካ ሀገራት አዳዲስ ሆቴሎች እንደሚከፍት አስታውቋል፡፡
 በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆቴል ስራውን በናይጄሪያ ለመጀመር ማቀዱን የጠቆመው ሞቪንፒክ ሆቴልና የስብሰባ ማዕከል በ4 አመት ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የሚችል ሆቴል እገነባለሁ ብሏል፡፡ከናይጀሪያ ቀጥሎ በሞሮኮም ሆቴል መገንባቱን እንደሚቀጥል ጠቁሟል፡፡

      የካንሰር አይነቶች በርካታ ቢሆኑም ሁሉም ካንሰሮች ግን መነሻ ምክንያታቸው በሰውነታችን ሴሎች ላይ የሚከሰተው ያልተለመደ የሴሎች እድገትና መራባት ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ሴሎች ከተለመደውና ተፈጥሮአዊ ከሆነው መንገድ ውጪ ለቁጥጥር በሚያዳግት መጠን እየተባዙ ይመጣሉ፡፡ በዚህ መንገድ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች መካከል የጡት ካንሰር አንዱ ነው፡፡ የጡት ካንሰር ከተፈጥሮአዊ ሁኔታዎች፣ ከጡት ሴሎችና ቲሹዎች መብዛት አንፃር በሴቶች ላይ በስፋት የሚታይ በሽታ ቢሆንም ወንዶችም በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡አራት አይነት የወንዶች ጡት ካንሰር በሽታዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከልም ኢንቫሰይቭ ዳክታል ካርሲኖማ የተባለው ወንዶች ላይ በስፋት የሚታይና የጡትን ውጫዊ ክፍል የሚወር ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት በጡት ካንሰር በሽታ የሚያዙ ወንዶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንና በሽታው በተለይ እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆናቸው ወንዶች ላይ በስፋት መታየቱን Journal of Health በቅርቡ ለህትመት ያበቃው መረጃ አመልክቷል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ በዚህ በሽታ የሚያዙ ህሙማን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ይኸው መረጃ ጠቁሟል፡፡ በአሜሪካ በ2013 ብቻ ከአንድ ሺህ በላይ ወንዶች በበሽታው መሞታቸውንም ገልጿል፡፡
በአገራችን በካንሰር በሽታ ላይ የተደረጉ የተለያዩ ጥናቶች ቢኖሩም በተለይ በወንዶች ጡት ካንሰር በሽታ ላይ የተደረጉና በሽታው አሁን ያለበትን ደረጃ የሚያመለክቱ መረጃዎች የሉም፡፡ ይሁን እንጂ በአገራችንም በዚህ በሽታ ተይዘው ለህክምና ወደ ሆስፒታሎች የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጠቅላላ ሃኪም የሆኑት ዶክተር አብርሃም ተስፋዬ ይገልፃሉ፡፡
በወንዶች ጡት ካንሰር በሽታ ተይዘው፣ ወደ ሆስፒታሉ ከሚመጡ ከአስር ህሙማን መካከል ሁለቱ በሽታቸው የጡት ካንሰር መሆኑን ሳያውቁ፣ ለዓመታት ሲሰቃዩ የቆዩና ህክምና በወቅቱ ለማግኘት ባለመቻላቸው ምክንያትም ህይወታቸውን የሚያጡ መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡
ከወንዶች ጡት ካንሰር በሽታ አይነቶች መካከል ኢንቫሲይቭ ዳክታል ካርሲኖማ የተባለው በሽታ በአገራችንም በስፋት የሚታይ መሆኑን እኒሁ ዶክተር ተናግረዋል፡፡
የወንዶች ጡት በተፈጥሮው አነስተኛ እና ወተት አምራች ክፍል የሌለው ቢሆንም ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው በአራቱ አይነት የጡት ካንሰር በሽታዎች ይጠቃል፡፡ እነዚህ አራት የጡት ካንሰር አይነቶች ምን ምንድናቸው? መነሻ ምክንያታቸውስ? እስቲ በአጭሩ እንያቸው፡፡
1. ኢንቫሲይቭ ዳክታል ካርሲኖማ
ይህ የጡት ካንሰር የጡት ውጫዊውን አካል በመውረር በከፍተኛ መጠን የሚባዛና በስፋት የሚከሰት የጡት ካንሰር ነው፡፡ ከ80-90% የሚደርሰው የወንዶች ጡት ካንሰርም የዚህ አይነቱ ነው፡፡
2. ኔፓል ፓጌት ዲዝዝ
ከጡት የውስጠኛው ሴል አካባቢ ተነስቶ ወደ ጡት ጫፍ በመውጣት፣ በጡት ጫፍ አካባቢ ራሱን ለማባዛት የሚሰራጭ ነው፡፡ እየበዛ ሲመጣም ጠፍጣፋና ጠቆር ወዳለው የጡት ክፍል ይዛመታል፡፡ ይህ የካንሰር አይነት ከሴቶች ይልቅ በብዛት የሚያጠቃው ወንዶችን ነው፡፡
3. ዳክታል ካርሲኖማ
ይህ የካንሰር አይነት ፈሳሽ ሊያስተላልፍ የሚችለውን የጡት አካል የሚያጠቃ ሲሆን ወደ ውጪኛው ክፍል መጥቶ የመባዛት ሁኔታው ዝቅተኛ ነው፡፡ ይህ አይነቱ የጡት ካንሰር እንደ ኢንቫሲይቭ ዳክታል ካርሲኖማ እና እንደ ኔፓል ፓጌት ዲዝዝ በብዛት የሚከሰት አይደለም፡፡ ከአስር የወንዶች ጡት ካንሰር ህሙማን መካከል አንዱ ብቻ በዚህ አይነቱ የጡት ካንሰር ህመም ተጠቂ ይሆናል፡፡ ይህ የካንሰር አይነት በቀዶ ጥገና የመዳን እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡
4. ኢንሼሲይቭ ሎብላር ካርሲኖሚ
እጅግ አነስተኛ በሆነ መጠን የሚታይ የጡት ካንሰር ነው፡፡ በሴቶች ጡት ላይ ወተት የሚያመርቱ ክፍሎችን የሚያጠቃ የጡት ካንሰር አይነት ሲሆን በወንዶች ላይ የመከሰት እድሉ እጅ አነስተኛ ነው፡፡ 2% የሚሆኑት የጡት ካንሰር ታማሚ ወንዶች፤ በዚህኛው አይነት የጡት ካንሰር የተጠቁ ናቸው፡፡
የወንዶች የጡት ካንሰር እንደማንኛውም የካንሰር ህመም መነሻ ምክንያታቸው በግልፅ የሚታወቅ ባይሆንም ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁት ነገሮች ለበሽታው መከሰት መነሻ ምክንያት ይሆናሉ ተብለው እንደሚገመት ዶ/ር አብርሃም ገልፀዋል፡፡
የእድሜ መግፋት
እድሜ እየጨመረና እየገፋ ሲሄድ በጡት ካንሰር በሽታ የመያዝ እድልም እየጨመረ ይሄዳል፡፡
በውልደት ጊዜ የX እና Yክሮሞዘሞች ተዛብቶ መገኘት
አንድ ወንድ ልጅ ሲወለድ ከአንድ በላይ የX እና አንድ የY ክሮሞዞም ይዞ መገኘት፡፡ ይህም ከፍተኛ የኤስትሮጅንና አነስተኛ የአንድሮጅን ሆርሞኖችን እንዲያመርት ያደርገዋል፡፡ ሆኖም ከአንድ ሺ ወንዶች መካከል በአንዱ ላይ ብቻ የሚከሰት ነው፡፡
የጡት ካንሰር ያለበት የቤተሰብ ታሪክ መኖር
በቤተሰቡ ውስጥ በጡት ካንሰር ህመም የተያዘ ሰው ካለ፣ ለቀጣዩ ትውልድ የካንሰር ሴል ጅኖችን የማስተላለፍ እድሉ ከፍ ያለ ነው፡፡
ለአደገኛ ጨረሮች መጋለጥ
በደረት አካባቢ በሚሰጡ የጨረር ህክምናዎች ሳቢያ አሊያም በማንኛውም የሥራ ፀባይ በጡት አካባቢ ለጨረር የመጋለጥ እድል ካለ፣ በጡት ካንሰር የመያዝ እድሉ ከፍ ያለ ይሆናል፡፡
ወንዶች በጡት ካንሰር በሽታ ሲያዙ ስለሚያሳዩአቸው ምልክቶችና ምልክቶቹ በሚታዩ ጊዜ ማድረግ ስለሚገባቸው ነገር ሃኪሙ ሲናገሩ፤
የጡት ጫፍ አካባቢ በጣም ጠጣርና ወፍራም ሲሆን የጡት ጫፍ የቅርፅ ለውጥ ሲያደርግ፣ በጡት አካባቢ ያለው ቆዳችንን ስንጫነው ጐድጐድ ብሎ የመቅረት ባህርይ ካለው፣ በጡት ጫፍና በጡት አካባቢ መሰነጣጠቅ ከታየ፤ የመቅላት፣ የማሳከክና የማቃጠል ስሜት ካመጣና አልፎ አልፎ የመድማት ወይም ፈሳሽ የማውጣት ሁኔታ ከታየበት አስቸኳይ ምርመራና ህክምና ማድረግ ይገባል፡፡ ይህም በሽታው ስር ሳይሰድ ለመግታት ይረዳል፡፡  

ከእነዚህ የነጭ ሽንኩርት ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን እነሆ፡-
ነጭ ሽንኩርት በውስጡ ከያዘው     የሰልፈር     ማዕድን የተሰሩ አለይን     እና አሊሲይን የተባሉ ኬሚካሎች         በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የቅባት     ክምችት ይቀንሳሉ፡፡
የምግብ መፍጨት ሂደቱ የተቀላጠፈ     እንዲሆን ያደርጋል
የደም ውስጥ ኮሌስትሮልን ይቀንሳል
የደም ግፊትን ያስተካክላል
የልብ በሽታን ይከላከላል  
ስትሮክና የልብ ሴሎች መጐዳት እንዳይከሰቱ ያደርጋል
 መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች
ነጭ ሽንኩርት በተፈጥሮው የደም ፍሰትን የመጨመር ባህርይ ስላለው ከፍተኛ       የደም መፍሰስ ችግር ያለባቸው ሰዎች ሊመገቡት አይገባም፡፡
የጥርስ፣ የድድ መድማት ችግሮች እና የጨጓራ ቁስለት ያለባቸው ሰዎች እንዲመገቡት አይመከርም፡፡
ከ2 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት፣ነፍሰ ጡር ሴቶችና ጡት የሚያጠቡ እናቶች ነጭ     ሽንኩርትን ባይመገቡት ይመረጣል፡፡
እንደ አስፕሪን፣ ዋርፋሪን፣ ትራይ ሶፒዲን የመሳሰሉ መድሃኒቶችን የሚጠቀሙ ሰዎች ነጭ ሽንኩርትን መመገብ         የለባቸውም፡፡
አብዝቶ መጠቀም ለከፋ ጉዳት ሊዳርግ ስለሚችል፣ነጭ ሽንኩርትን በምንመገብ ጊዜ በአነስተኛ መጠን ሊሆን ይገባል፡፡ በተቻለ መጠን ነጭ ሽንኩርትን ሳናበስል መጠቀም ይኖርብናል፡፡  
ምክንያቱም በውስጡ የሚገኘው ጠቃሚ ነገር በእሳት ሊጠፋ ይችላል፡፡ እናም ሁልጊዜ ነጭ ሽንኩርትን በጥሬው ይመገቡ፡፡

በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የሚገኘው (EGCG) ኢ.ጂ.ሲ.ጂ የተባለው ንጥረ ነገር ለካንሰር ህዋሳት እድገት ወሳኝ የሆነውን ዳይ አይድሮ ፎሊት ርዳክቴዝ የተባለውን ኢንዛይም በማገድ ካንሰር በሰውነታችን ውስጥ እንዳይሰራጭ በማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይሰጣል፡፡ አብዛኛዎቹ የካንሰር ህመም መድሃኒቶችም ከዚሁ ከአረንጓዴ ሻይ የሚሰሩ ናቸው፡፡
 ይሁን እንጂ የእንግሊዝና የስፔን ተመራማሪዎች በቅርቡ ይፋ ያደረጉት የጥናት ውጤት እንደሚያመለክተው፤ አረንጓዴ ሻይ በእናት ማህፀን ውስጥ የሚገኘውን ፅንስ ህብለ ሰረሰር በመሰንጠቅ ከፍ ያለ የአካልጉዳት በፅንሱ ላይ ያደርሳል፡፡
 ይህንን ሻይ መጠጣት የሚያዘወትሩ ነፍሰጡር እናቶችም፣ የአካል ጉዳት ያለበት ህፃን የመውለድ እድላቸው እጅግ ከፍ ያለ ነው ተብሏል፡፡