Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

የቦብ ማርሌይ ፋውንዴሽን ለኢትዮጵያ 100ሺ ዶላር ለገሰ
በአፍሪካ ቀንድ ባሉ አገራት የሚገኙ 12 ሚሊዮን የረሃብ ተጠቂዎችን ለመታደግ ከ150 በላይ የዓለም ምርጥ አርቲስቶች በኢንተርኔት ሶሻል ሚዲያ የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ መጀመራቸውን የቢልቦርድ መሄት ዘገበ፡፡   ከ60 ዓመታት በኋላ የከፋ ረሃብ በምስራቅ አፍሪካ ከወር በፊት የተከሰተ ሲሆን በተለይ በሶማሊያ ረሀቡ 3.6 ሚሊዮን ህዝብ እንዳጠቃና በኬንያና በኢትዮጵያም ረሃቡ እየተስፋፋ መምጣቱን ያመለከተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ነው፡፡

በ2001 ዓ.ም. ተጀምሮ በአዲስ አበባና በየክልል ከተሞቹ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያን አይዶል ውድድር እነሆ ወደመቋጫው ተቃርቧል፡፡ በስድስት ዙሮች የተካሄደውን የድም ውድድር አሸንፈው ለሰባተኛው ዙር ያለፉት አስር ተወዳዳሪዎችም ተመርጠዋል፡፡ የሐረሯ ተወዳዳሪ ህፃን ሃና ግርማ በልዩ ተወዳዳሪነት ለሰባተኛውና ምርጥ አምስቱ ብቻ ለሚመረጡበት ዙር በማለፍ yተወዳዳ ቁጥር አስራ አንድ አድርሳዋለች፡፡

በየዓመቱ በሺዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን በህጋዊ እና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ የመን ይሰደዳሉ፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ወደ ሳውዲ አረቢያ የገልፍ አገራት የሚሻገሩ ወይም  በስንዓ፣ በኤደንና እና በሌሎች የየመን ከተሞች የሚኖሩ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያውያኑ ኑሮ በየመን የተደላደለ ነው ለማለት ያዳግታል፡፡ ሴቶቹ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥረው የሚሠሩ ናቸው፡፡ በወር ከ150 እስከ 300 ዶላር ያገኛሉ፡፡ ብዙዎቹ ወንዶች ግን ስራ የላቸውም፡፡ በሴቶቹ ገቢ ጥገኛ የሆኑ ወንዶች ቢበዙም አንዳንዶቹ ሙዚቃ ቤት፣ ኤሌክትሮኒክስ መደብር ፣ የገፀበረከት ሱቆች በመክፈት ይነግዳሉ፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ሴቶች ከቤት ሰራተኝነት ሌላ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፉርኖ ዱቄት አይን ያለው ነጭ እንጀራ ጋግረው በመሸጥ አትራፊ ንግድ ይዘዋል፡፡ የመናውያን በስንዴ ፉርኖ ዱቄት የሚጋገረው ይህን የኢትዮጵያ ሴቶች እንጀራ ወደውታል፡፡ በፆም ወቅቶች ይህን እንጀራ የሚሸጡ ሴቶች በወር ከወጭ ቀሪ ከ2500 እስከ 3ሺ ዶላር ያገኙበታል፡፡

Saturday, 13 August 2011 09:50

ሴቶችዓለምን እየመሩነው

ታዋቂዋየሆሊውድየኮሜዲፊልምአክትረስና ረስናበዛሬውጊዜላሉትበርካታእንስትተዋንያንሞዴልበመሆንየምትታወቀውማርሊንሞንሮ፣ከዛሬ40ዓመት    በፊት እንዲህ ብላ ነበር፣ ..ዓለም የወንዶች ናት፤ ሆሊውድ ደግሞ የበለጠ በወንዶች ቁጥጥር ስር ነው.. ነገር ግን ማርሊን ሞንሮ እ.ኤ.አ በ1962 ዓ.ም ከሞተች በኋላ በአሜሪካ ሴቶች መብታቸውንና እኩልነታቸውን ለማግኘት በተለያየ ጊዜያት ባካሄዱት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ለውጦች ተከስተዋል፡፡

በሆሊውድና በአሜሪካ መዝናኛ ኢንዱስትሪ ያሉ ዝነኞችን ገበና በመፈልፈል የሚታወቀው አንቶኒዮ ፔሊካኒ በወህኒም የተለመደ ስራውን እንደገፋበት ኒውስዊክ ገለፀ፡፡ ፔሊካኒ የዝነኞችን ምስጥራዊ ሰነድ በመፈልፈል፤ ስልክ በመጥለፍና የደህንነት መረብን ሰብሮ በመግባት አደገኛነቱ የተመሰከረለት ጉድ ጎልጓይ ጋዜጠኛ ነው፡፡ በሎስአንጀለስ ከተማ በግል መርማሪነት ይሰራ የነበረው ፔሊካኒ ከ3 ዓመት በፊት ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘባቸው 76 ወንጀሎች የ15 ዓመት ኑ እስራት ተፈርዶበት በወህኒ ቤት ይገኛል፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ክንዱ ላይ ክርኑን በጣም ያመውና ለጓደኛው ..ምን ባደርግ ይሻለኛል?.. ይልና ይጠይቀዋል፡፡ ጓደኛውም ..አንድ ዋሻ ውስጥ የሚኖር አዋቂ ሰው አለ፡፡ እሱ ጋ ሄደህ ችግርህን ብታስረዳው መፍትሔ ይፈልግልሃል.. አለው፡፡
..ስንት ያስከፍለኛል?..
..አስር ብር ብቻ፡፡..
..ምን ምን ዓይነት ምርመራ ያደርግልኛል?.. ሲል ጠየቀ ታማሚው፡፡
..የሽንት ምርመራ ብቻ ነው የሚያደርግልህ፡፡ ዋሻው በራፍ ላይ በዕቃ ሽንትህን ታስቀምጣለህ፡፡ እሱ ይደግምበታል፡፡ ይመሰጥበታል፡፡ ከዚያ መድኃኒቱን ይነግርሃል፡፡ አለቀ፡፡..

  • ..እንኳን አደረሳችሁ..  ይሻላል ወይስ ..መልካም አዲስ አመት..
  • የወርቅ ፍርፋሪ ብንጠጣም አረማመዳችን አልፈጠነም

የሰዎችን አረማመድና ፍጥነት በማየት፤ ስለ ባህላቸውና አኗኗራቸው ማወቅ፣ ስለባህሪያቸውና አስተሳሰባቸው መናገር ይቻላል? አራት ጋዜጠኞች ሆነን ከሳምንት በፊት የፖላንድ ከተሞችን ስንጎበኝ ነው ጥያቄውን የፈጠርኩት... የተፈጠረብኝ ሳይሆን የፈጠርኩት፡፡ የአስጎብኚዎቻችን እርምጃና ፍጥነት ራሱ... በቀስታ ወደ ኋላ እየቀረንባቸው ምን ያህል ትእግስታቸውን እንደተፈታተንነው! በአገሪቱ ደቡብ ጫፍ ታሪካዊቷን ክራኮ ከተማ ያስጎበኘችን ዶምኒክ የተገናኘን እለት፤ በጉዞ ደክሞን ሊሆን እንደሚችል ነበር የገመተችው፡፡ ግን በማግስቱም ፈጣን አልሆንም፡፡

Monday, 08 August 2011 14:06

የ..ሐምሌ ስንኞች..

ባለፈው እሁድ በቢሾፍቱ ሲኒማ አዳራሽ ኪነጥበባዊ ዝግጅቱን ያቀረበው ..ሆራ ቡላ.. ታዋቂዋን አርቲስትና የማስታወቂያ ባለሙያ ሙሉ ዓለም ታደሰና በ..ሰው ለሰው.. ተከታታይ የቴሌቭዢን ድራማ ልጇ ብሩክን ሆኖ የሚሠራውና የድራማው አዘጋጅ አርቲስት ሰለሞን አለሙ ፈለቀን የክብር እንግዶች በማድረግ የጋበዘ ሲሆን አርቲስቶቹ ልምድና እውቀታቸውን ለደብረ ዘይት ወጣቶች አጋርተዋል፡፡

addis admassበ1ኛው የሚዲያና የኪነጥበብ ባለሙያዎች የእግር ኳስ ውድድር አዲስ አድማስ ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዚን ድርጅት ጋር ለዋንጫ ተጋጥሞ 1ለ0 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ የአዲስ አድማስ ቡድን ተጨዋቾች የዋንጫው መታሰቢያነት ለአሰፋ ጐሳዬ ይሁን ብለዋል፡፡ አዲስ አድማስ በዚሁ ዓመት በታላቁ ሩጫ ተዘጋጅቶ በነበረው የ12 ኪሎሜትር የዱላ ቅብብል ሩጫ ከስምንት ሚዲያዎች መካከል አሸናፊ እንደነበር ሲታወስ፤ በ2003 በሩጫና በእግር ኳስ ከአገሪቱ ሚዲያዎች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ አድናቆት አትርፏል፡፡

በእንግሊዝ እግር ኳስ የ2011 -12 የውድድር ዘመን የሊጉ ሻምፒዮን ማን. ዩናይትድ ከኤፍ ኤካፕ  ሻምፒዮኑ ማን. ሲቲ ጋር ነገ በዌምብሌይ በሚያደርጉት የኮሙኒቲ ሺልድ የዋንጫ ጨዋታ ሊከፈት ነው፡፡ በሌላ በኩል የላቀ የሻምፒዮናነነት ፉክክር እንደሚደረግበት የሚጠበቀው 20ኛው ፕሪሚዬር ሊግ ከሳምንት በኋላ ይጀመራል፡፡ በፕሪሚዬር ሊጉ የ20 ዓመታት ታሪክ ማን. ዩናይትድ ለኮምኒቲ ሺልድ ዋንጫ 14 ጊዜ የተጫወተ ሲሆን ማን ሲቲ በበኩሉ ከ38 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡