Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

Monday, 27 June 2011 16:14

ማህበረሰብ እና ግለሰብ

የተከበራችሁ አንባብያንዕ-

ስናስብና ስንናገር እንዲመቸን (በቀላሉ እንዲታሰበን) በጥቅሉ ማህበረሰብ እንላለን እንጂ ይሄ ..ማህበረሰብ.. የምንለው ነገር በተጨባጩ አለም ውስጥ የለም፡፡ እንግዲያው ማን ነው ያለው? ግለሰቦች ናቸው፣ እያንዳንዳቸው መልኩም ባህሪዩም ከማናቸውም የተለየ፣ ራሱን የቻለ Universe.

..ነቄ ተቃዋሚ.. መጠላለፍ የፋራ ነው ይላል. . .

 

የፕሮግራማቸው መመሪያ “positive thinking”  ነው. . .

ተቃውሞው ዕውቀትና ሥልጣኔ ተኮር ነው. . .

 

ተቃውሞው ዕውቀትና ሥልጣኔ ተኮር ነው. . .
እንደተለመደው ፖለቲካዊ ወጋችንን በቀልድ እንጀምረዋ( በነገራችን ላይ አንዳንድ ቀልዶች የሰማችኋቸው ቢሆኑ ግን እኔ ..በአዲስ መልክ.. ስለማቀርበው (ምግብ በአዲስ መልክ ጀምረናል እንደሚባለው) ደግማችሁ ብታነቡት ወይም ብትሰሙት እንኳን እንደ ማይሰለቻችሁ አምናለሁ፡፡ (እንደ አንዳንድ ፓርቲዎች ግን እኔ አውቅላችኋለሁ እያልኩ እንዳልሆነ ተረዱልኝ) አሁን ወደ ቀልዳችን፡፡
በምድር ላይ ሳሉ የተለያዩ የዓለም አገራትን በመሪነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ ዲሞክራትም አምባገነንም መሪዎች (ከአፍሪካም ከአውሮፓም) ሲኦል ውስጥ ሆነው (እላይ ቤት ማለት ነው) ወደ የአገራቶቻቸው ስልክ ይመታሉ፡፡ በመጀመሪያ የደወለው አንድ የአውሮፓ አገር መሪ ነበር፡፡ የአገሩን የመንግሥት ተወካይ አግኝቶ ብዙ ነገር ጠየቀው፡፡ ዋናው ጥያቄ ያተኮረው ግን የአገሩ ሳይንቲስቶች ላይ ነበር፡፡ ..እንዴት እስካሁን ድረስ በሽታን የሚያስቀር መድኃኒት አልሠሩም.. እያለ እምቧ ከረዩ ሲል ቆይቶ ስልኩን ዘጋ፡፡ የስልክ ሂሳብ ሲጠይቅ 40 ዩሮ ተባለና ከፈለ፡፡ ሌላ የአውሮፓ አገር መሪ ተነሳና ወደ አገሩ ስልክ መታ፡፡ ስለ ህዝቡ፣ ስለ ኢኮኖሚ ዕድገት፣ ስለ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ርቀት ሲያወራ ቆየና እሱም በአንድ አጀንዳ ላይ ይከራከር ገባ፡፡ ይኼኛው ደግሞ ..እንዴት አሁን ድረስ ግብር ማስከፈል አልተዋችሁም(.. በማለት ተከራክሮ ስልኩን ዘጋ፡፡
እሱም 42 ዩሮ የስልክ ከፈለ፡፡ ቀጣዩ ተረኛ የአፍሪካ አገር መሪ ነበር፡፡ ገና ሲጀምር በነጐድጉድ ድምፁ ሲኦልን ቀወጣት፡፡ አንድም ጊዜ በቀስታ ሲያወራ አይሰማም፡፡ በምድር የሥልጣን መንበሩ ላይ ያለ ሳይመስለው አልቀረም፡፡
..እኔን 20 ዓመት ገዛ ብለው አስወርደው እነሱ ግን 40 ዓመት ሞላቸው(.. አለ በቁጣ - ምድር ላለው ተወካዩ፡፡
..ኧረ ባክህ. . . አሁንም አመ አልቀረም እንዴ. . . የታባታችሁ የእጃችሁን ነው ያገኛችሁት፡፡ እኔ ብኖር ኖሮ እንኳንስ አመ ህዝብም አይኖርም ነበር. . . አመን ማጥፋት ከምንጩ ነው ብያችሁ ነበር እኮ! ግን አትሰሙም! ቀላል እኮ ነው! ህዝብ ሲጠፋ አመ ይጠፋል(.. የቀድሞው የአፍሪካ አገር አምባገነን መሪ ሲኦል ከመጣ አንስቶ አመን ለማጥፋት አጭሩና ውጤታማው መንገድ ህዝብን ማጥፋት ነው የሚለው ፍልስፍናው ላይ ከምሩ እየተከራከረ ይገኛል፡፡ የአፍሪካው መሪ የናፈቀውን አምባገነናዊ ባህርይ በስልክ መስመር እንደ ጉድ በመጮህና በመፎከር ከተወጣ በኋላ ስልኩን ዘጋና 2 ዶላር ብቻ ከፈለ - ለስልኩ፡፡ ሁለቱ የአውሮፓ መሪዎች ተያዩ፡፡ አፍሪካዊው የእነሱን አጥፍ አውርቶ 2 ዶላር፣ እነሱ 40 ዩሮ ገደማ መክፈላቸው አናዷቸው የሲኦሉን የኮሙኒኬሽን ክፍል አዛዥ ጠየቁት፡፡
..ሲኦልም በዘመድ ይሠራል ማለት ነው. . . አይተኸዋል ስንት ሰዓት እንዳወራ. . . እኛ አውሮፓውያን ደግሞ ሙስና ምናምን አንወድም. . . የልማትና የዕድገት ጠር ነው. . . እና አፍሪካዊው ለምን 2 ዶላር ብቻ እንደከፈለ ይነገረን.. አለ አውሮፓዊው መሪ፡፡ ..ጌታዬ!.. ሲል ጀመረ የሲኦል የኮሙኒኬሽን አዛዥ ..ሲኦል ውስጥ በዝምድና አንሠራም. . . ሙስና የሚለውንም ቃል ዛሬ ገና ከእርስዎ መስማቴ ነው..
ሌላኛው የአውሮፓ መሪ ..ይሄን ያህል የታሪፍ ልዩነት ከየት መጣ ታዲያ?..
የሲኦል የኮሙኒኬሽን አዛዥ ..አፍሪካዊው መሪ የአገር ውስጥ ጥሪ እኮ ነው ያደረገው!..
..ነው እንዴ!!.. ብለው ዝም አሉ - የአውሮፓ አገራቱ መሪዎች!
አያችሁልኝ! ቀልዱ እንኳ ሳይቀር እንዴት አፍሪካ ላይ እንደሚያፌዝ፡፡ ከሲኦል ወደ አፍሪካ መደወል ..የአገር ውስጥ ጥሪ ነው.. እኮ ነው የተባለው፡፡ ወይ ነዶ!!
በንዴት መብገን ብቻውን ግን ምንም ለውጥ አያመጣም፡፡ ባይሆን እንደኔ ፕሮፖዛል መጻፍ ይሻላል፡፡ መፍትሔ ያዘለ ፕሮፖዛል እንጂ የችግር ቋት የሚሆን ፕሮፖዛል ግን አይደለም፡፡ በዚህ ሃሳብ መነሻ ነው አዲሱ የተቃዋሚዎች ፕሮፖዛል የተረቀቀው፡፡
እንደተለመደው የፕሮፖዛሉ መፃፍ ሰበቡ ምን እንደሆነ ባስረዳችሁ ደስ ይለኛል፡፡ እንዲህ የአፍሪካን ነገረ ሥራ በቅጡ ስንመረምረው ለኋላቀርነት፣ ለበሽታ፣ ለረሃብ፣ ለመሃይምነትና ለእርስ በርስ ጦርነት የዳረገን ፖለቲካው ነው፡፡ በአፍሪካ የችግሮች መነሻ በአብዛኛው ፖለቲካና ከፖለቲካ የሚወለደው የሥልጣን ፉክክር ነው፡፡
እናም የፖለቲካውን ሁኔታ ካስተካከልን ሌሎች ነገሮች እየተስተካከሉ ይመጣሉ፡፡ ለዚህ ነው የአዳዲስ ተቃዋሚዎች ፕሮፖዛል የተዘጋጀው፡፡
አዲስ ስታይል የሚከተለው አዲሱ የተቃዋሚ ቡድን ዋና መርሁ ..ፕሥሰዥተዥቨጵ ተሀዥነከዥነገ..  (ቀና አስተሳሰብ) የሚል ሲሆን ጭፍን ጥላቻና መጠላለፍ ሲያልፍም አይነካው፡፡ ኢህአዴግ ስለ አዲሱ ተቃዋሚ ሲሰማ አስቀድሞ የሚያነሳው ጥያቄ ምን መሰላችሁ.....የትግል መሳሪያው ምንድነው?.. እነሆ መልሱ፡፡
የትግል መሳሪያው ዕውቀትና ሥልጣኔ ነው፡፡ የአዲሱ ተቃዋሚ ፓርቲ ግንባር ቀደም ዓላማ ዕውቀትና ሥልጣኔን ማስፋፋት ነው በሃይል ወይም በጉልበት አይደለም፡፡ በፀባይ፣ በማግባባት፣ በማሳመን፡፡ እንደምታውቁት በጠብመንጃ የመጣ ሥልጣኔ ወይም ዕድገት የለም፡፡ በዚያ ላይ መሳሪያና ዕውቀት መቼ ኮከባቸው ገጥሞ ያውቃል? አዲስ የሚመሰረተው ፓርቲ ያወቀና የነቃ ነው - ..የአራዳ ልጅ.. እንደሚባለው፡፡
..የአራዳ ልጅ ፓርቲ.. ሲባል አጉል ብልጣብልጥነት የሚያሳይ ሳይሆን ብልህ ወይም ስማርት ለማለት ነው -ስመቷረተ ፐቷረተየ፡ ብትሉትም ይስማማኛል፡፡
ስለ አዲሱ ፓርቲ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያህል አንዳንድ ዕቅዶቹን ብጠቅስላችሁ ጥሩ ይመስለኛል፡፡ የፖለቲካውን ትግል የሚያካሂድበትን ስልትም ስለሚያሳይ ስለ ፓርቲው የተሻለ ምስል ይፈጥራል ብዬ አስባለሁ፡፡ እንግዲህ ዕውቀትና ሥልጣኔ ተኮር መሆኑን ተነጋግረን የለ!
የፖለቲካ ትግሉን የሚያካሂደው በዚሁ መርህ መሰረት ነው፡፡ ለምሳሌ የህዳሴው ግድብ ሊሠራ ነው የሚል ነገር ሲሰማ ወደ ማውገዝ አይገባም፡፡ ተፈጥሮአዊ ባህርይው ይሄን አይፈቅድለትም፡፡ ይልቁንም ባህር ማዶ ተሻግሮ ከኢትዮጵያውያንም ከተለያዩ መንግስታትም ገንዘብ አሰባስቦ ወደ አገሩ ይመለስና የ100 ሚ ብር ቦንድ ይገዛል፡፡ መቼም ኢህአዴግ አትገዛም አይለውም አይደል! ካለውም እራሱ ላይ ጐል አገባ ማለት ነው - ኢህአዴግ፡፡ አዲሱ ፓርቲ አንድ ነጥብ ሲያስቆጥር ኢህአዴግ አንድ ነጥብ ይቀነስበታል ማለት ነው፡፡
ለዩኒቨርስቲዎች የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ከዓለም ዙሪያ አፈላልጐ ይሰጣል - ለመንግሥትም ለግልም፡፡ አሁንም ኢህአዴግ ከተቃዋሚ አልበቀልም ብሎ ከ..ኮራ.. እሰየው ነው! የእሱ ዋና ዓላማ ግን ዕውቀትና ሥልጣኔ ማስፋፋት ስለሆነ ከዚህ ትግሉ ለሰከንድም ቢሆን አያፈገፍግም፡፡
ይሄ ብቻ አይደለም ከፍተኛ ችሎታ ላላቸው ታዳጊ ተማሪዎች በውጭ አገራት የነጻ ትምህርት (ሰቸሀሥለቷረሰሀዥፐ) ዕድል ያመቻቻል - በዓመት ቢያንስ እስከ 500 ተማሪዎች እንዲማሩ ያደርጋል፡፡ አሁንም ኢህአዴግ ..ለፖለቲካ መሳሪያነት እየተጠቀመበት ነው.. በሚል ዕድሉን ከከለከለ፣ ራሱ ግብ ውስጥ ጐል እያስገባ ስለሆነ ድሉ የማታ ማታ የአዲሱ ተቃዋሚ ፓርቲ ይሆናል፡፡ አያችሁ አዲሱ ፓርቲ ችግር ተኮር ሳይሆን መፍትሔ ተኮር ነው፡፡ የጥላቻ ፓርቲ ሳይሆን የቀና አመለካከት ፓርቲ ነው፡፡ ሥልጣን መያዝ የሚፈልገው ኢህአዴግን በማስጠላት ሳይሆን በቀና አስተሳሰብ በመላቅ ነው፡፡ በዚህ ሂደት የበለጠ ቀና የሆነው ፓርቲ ሥልጣን የሚይዝበት ምቹ ዲሞክራሲያዊ ሁኔታ ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ አዲሱ ፓርቲሰጭረፐረዥሰጵ፡ ማድረግም መለያው ነው፡፡ ድንገት ብድግ ብሎ ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ ጋዜጠኞችን ይጠራና ለባቡር መስመር ዝርጋታው 250ሚ. ብር፣ ለኮንዶሚኒየም ግንባታ 50ሚ. ብር እሰጣለሁ ይላል፡፡ ኢህአዴግ የፖለቲካ ጨዋታውን ነቄ ብሎት ..ያንተን ገንዘብ አንቀበልም.. የሚለው ከሆነ ችግር ላይ የሚወድቀው ራሱ ነው፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ኢህአዴግ ዋና መሰረቴ ነው ወደሚለው አርሶ አደር ይሄድና ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት ገበሬውን በሃሴት ሞልቶት ይመለሳል፡፡ የኢህአዴግ መሠረት አልተሸረሸረም? ግን በክፋት ወይም በተንኮል መንገድ አይደለም፤ በቀና አካሄድ ነው፡፡ ህገ መንግሥቱን አክብሮ ይንቀሳቀሳል፡፡ ህገ መንግሥቱን ገበሬውን አትደግፉ አይልም እኮ! ኢህአዴግ ገበሬው የኔ ብቻ ነው ካለ በፍ/ቤት ይከራከር! የአዲሱ ፓርቲ ሌላው መለያ አገር ወዳድነቱ ነው፡፡ ለዚህ ነው ከሥልጣን በፊት አገሩን የሚያለማው፡፡ ለዚህ ነው ከሥልጣን በፊት በአገሩ ላይ ዕውቀትና ሥልጣኔ እንዲስፋፋ የሚተጋው፡፡ ለዚህ ነው ገዢውን ፓርቲ በጥላቻ ወይም በመሳሪያ የማይታገለው፡፡ ትግሉ ዕውቀትና ስልጣኔ በማስፋፋት ነው፡፡ ትግሉ በነቄነት ነው፡፡ ጠብመንጃ መተኮስ አይደለም መያዝ እንኳ ለነቄው ፓርቲ ..ፋርነት.. ነው - የጥንታዊ ጋርዮሽ ዘመን አስተሳሰብ፡፡ ለአዲሱ ..ሰመቷረተ ፐቷረተየ.. የትጥቅ ትግል ያረጀ ያፈጀ የትግል ሥልት ነው፡፡ የአዲሱ ፓርቲ የትግል ዓላማ ሥልጣን ለመያዝ ቢሆንም ከሥልጣኑ እኩል ኢትዮጵያን ከሲኦል ማውጣት ይፈልጋል፡፡ በዕውቀትና በሥልጣኔ እንድትመጥቅ ይተጋል፡፡ ለአዲሱ ፓርቲ የኢትዮጵያን ገታ መቀየር ማለት ይሄ ነው፡፡
አንባቢያን ፓርቲው ገንዘብ ከየት ያመጣል ሊሉ ይችላሉ፡፡ አዲሱ ፓርቲ በአዕምሮ ኃይል (mind power) ያምናል፡፡ እንኳን ገንዘብ ተዓም እፈጥራለሁ ባይ ነው፡፡ ስለዚህ የገንዘቡ ነገር ብዙም አያሳስብም፡፡ ሌት ተቀን ምንጩን ያነፈንፋል፡፡
..ነቄው ፓርቲ.. በቅርቡ ከምርጫ ቦርድ ፈቃድ የሚያወጣ ሲሆን አባል ለመሆን የምትፈልጉ ግን ከዛሬ ጀምሮ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡ ለጊዜው ታዲያ የፓርቲው ሊቀ መንበር እኔ ነኝ፡፡ ምነው ችግር አለ? የፓርቲው እንጂ የአገሪቱ እኮ አልወጣኝም!

እንደተለመደው ፖለቲካዊ ወጋችንን በቀልድ እንጀምረዋ( በነገራችን ላይ አንዳንድ ቀልዶች የሰማችኋቸው ቢሆኑ ግን እኔ ..በአዲስ መልክ.. ስለማቀርበው (ምግብ በአዲስ መልክ ጀምረናል እንደሚባለው) ደግማችሁ ብታነቡት ወይም ብትሰሙት እንኳን እንደ ማይሰለቻችሁ አምናለሁ፡፡ (እንደ አንዳንድ ፓርቲዎች ግን እኔ አውቅላችኋለሁ እያልኩ እንዳልሆነ ተረዱልኝ) አሁን ወደ ቀልዳችን፡፡

በግል ድርጅት ውስጥ በማሽኒስትነት ትሰራ እንደነበርና ድርጅቱ ምርት ቀንሷል በሚል 20 ሠራተኞች ሲያባርር አብራ እንደተባረረች የተናገረችው ወ/ት ሀና ይልማ፤ የእህልና ሸቀጣሸቀጥ ዋጋ በመናሩ ኑሮው አልተቻለም ትላለች፡፡