Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

አርሰን ቬንገር አርሰናል ከፕሪሚዬር ሊግ የዋንጫ ፉክክር አለመውጣቱን ተናገሩ፡፡ አርሰናል ከመሪው ማን ዩናይትድ በ11 ነጥብ ርቆ በ17ኛ ደረጃ ላይ መገኘቱ ያሳስበኛል ያሉት አሰልጣኙ ከዋንጫ ፉክክር ውጭ ሆኗል ለማለት ግን ጊዜው ገና ነው ብለዋል ሲል ዘ ሰን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ አርሰን ቬንገር ላለፉት ሁለት ወራት በክለባቸው ለታየው ውድቀት ተጠያቂ በመደረግ ሃላፊነታቸው አጣብቂኝ ውስጥ ቢገባም ለሚደርስባቸው ትችት አልበገር ማለታቸውን የተለያዩ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡  በተለይ ለ6 ዓመታት ከዋንጫ ድል ርቆ የቆየው አርሰናል ዘንድሮ በፕሪሚዬር ሊጉ ከ58 ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ግዜ ባጋጠመ መጥፎ አጀማመር ማሳየቱ የቬንገርን ቆይታ ጥያቄ ውስጥ ከቶታል፡፡

መሐመድ ለ800 ሜ ሪኮርድ ሰባሪነት ታጨ
አትሌት ኢማና መርጋ በዳይመንድ ሊግ በ5ሺ ሜትር  በተከታታይ ዓመት ለሁለተኛ ጊዜ አሸነፈ፡፡ ከኬንያውያን አትሌቶችና ከታላላቆቹ የረጅም ርቀት አትሌቶች ሞ ፋራህና በርናንድ ላጋት ጉሮሮ ለጉሮሮ በመተናነቅ የሚታወቀው አትሌት ኢማና በዳይመንድ ሊጉ በ5ሺ ሜትር በአንደኛ ደረጃ በማጠናቀቁ 40ሺ ዶላር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በዘንድሮው የዳይመንድ ሊግ በ5ሺ ሜ በተለያዩ 5 ከተሞች ከተካሄዱ ውድድሮች ሁለቴ በአንደኛነት፤ አንድ አንድ ጊዜ ደግሞ ሁለተኛ፣ ሶስተኛና አራተኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡

ታላቁ ሩጫ ከኮካ ኮላ በመተባበር ያዘጋጀው  የ7 ኪ.ሜ ተከታታይ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከሳምንት በፊት በተሳካ ሁኔታ መጀመሩን አዘጋጆቹ ገለፁ፡፡ በኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ውድድሮች በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ለሰአት መቆጣጣርያ የሚሆን ቺፕ በተገጠመላቸው የመሮጫ ጫማዎች ውድድሩ ተካሂዷል፡፡ 1ኛው የኮካኮላ ሲሬዬስ የ7 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ከሳምንት በፊት ሲካሄድ 3ሺ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈው በወንዶች ምድብ መወሰነት ገረመው በ21 ደቂቃ 46 ሴኮንዶች እንዲሁም በሴቶች ምድብ እቴነሽ ድሪባ በ25 ደቂቃ ከ52 ሴኮንዶች ርቀቱን በመሸፈን አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ሕጻናት በኤችአይቪ ቫይረስ ከተያዙ እናቶች ከተወለዱ uºL ሊደረግላቸው የሚገባውን የክብካቤና ድጋፍ አገልግሎት ለማመቻቸት አስቀድሞ ሕጻናቱ በቫይረሱ መያዝ አለመያዛቸው በግልጽ መታወቅ አለበት፡፡ Linkage ማለትም በኤችኤቪ ቫይረስ ከተያዙ እናቶች የተወለዱ ሕጻናት የጤና ክትትልን የሚመለከተው አሰራራር በአሁኑ c›ƒ በየሆስፒታሉ በምን መልክ እየተካሄደ ነው? የህክምና ባለሙያዎች እና የህክምና ተቋማቱ አሰራራር እና የህብረተሰቡ ግንዛቤ ምን መምሰል አለበት? የሚለውን በዚህ እትም ለንባብ ብለናል፡፡

Saturday, 24 September 2011 10:24

ባህላዊ ምግቦች

የጉራጌ ብሔረሰብ የኢኮኖሚ መሰረት ግብርና ቢሆንም ለአትክልት፣ ለአዝርዕትና ጥራጥሬ እንዲሁም ለእንስሳት እርባታ ምቹ የሆነው የእርሻ መሬቱ በፊውዳል ባለስልጣናትና ባለጉልት በመነጠቁ አብዛኛው የብሔረሰቡ አባላት መሬት አልባ ሆነው መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ከተዛባው የፊውዳሉ የመሬት ስሪት በተጨማሪ ህዝቡ ሰፍሮ የሚገኝበት መሬት አብዛኛው ክፍል ለሰብል እርሻ የማይመች ጠባብና ዳገታማ በመሆኑ በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ይተዳደሩ የነበሩት የብሔረሰቡ አባላት ከእርሻቸው ተፈናቅለው ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ከተማዎች በመፍለስ በንግድና በቅጥር ስራ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡

Saturday, 24 September 2011 10:16

መስቀልን የሚዘክሩ ዝግጅቶች

ዛሬና ነገ ይቀርባሉ  
የደንጌሳት ምሽት ሐሙስ ቀረበ  
የጉራጌ ብሔረሰብን ባህላዊ የመስቀል አከባበር የሚዘክሩ ዝግጅቶች በእምድብር ከተማ እና በአዲስ አበባ ዛሬ እና ነገ ይቀርባሉ፡፡ ..ጉራጌ ልማ.. በእምድብር ከተማ ዛሬ ከጧቱ 3ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት በሚዘልቅ ዝግጅት የጉራጌ መስቀል አከባበርን ሞዴል በአንድ ቀን ማሳየት የሚል ዓላማ ያለው ሲሆን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በመስቀል በዓል ልዩ ዝግጅት የሁለት ሰዓት ተኩል የአየር ሽፋን እንደሚሰጠው የጉራጌ ልማት ሕፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ፈቃደ ተክለማርያም ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡ እንደ እሳቸው ገለፃ ዝግጅቱ ከመዝናኛነቱ ባሻገር የጉራጌ ሕዝብ ተደራጅቶ የማልማት ሰፊ ልምዱን ለመላው ኢትዮጵያ ያሳይበታል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ወላጆች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መማሪያ መፃሕፍት ማግኘት አልቻልንም ብለዋል፡፡ አስተያየታቸውን ለዝግጅት ክፍላችን የሰጡ ወላጆች በእጥረቱ የልጆቻችን ትምህርት አቀባበል ተጽእጸኖ ውስጥ ወድቋል ብለዋል፡፡ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ወላጆች በበኩላቸው መፃሕፍቱ የሚሸጡት በጥቂት ቦታ በመሆኑ በወረፋ እየተጉላሉ መሆናቸውን ነግረውናል፡፡

Saturday, 24 September 2011 10:12

የትያትር እጥረት ተጠና

ትያትር ቤቶች የገጠማቸውን የትያትር ጽሑፍ እጥረት አስመልክቶ የጥናት ወረቀት ቀረበ፡፡ አምና ከተደረገ የመስኩ ባለሙያዎች ውይይት በመነሳት የጥናት ወረቀት ያቀረበችው አርቲስት ሕይወት አራጌ ነች፡፡ በጥናቴ መጠይቅ፣ ቃለምልልስ እና የቡድን ውይይት ተጠቅሜአለሁ ስትል ለአዲስ አድማስ ማብራሪያ የሰጠችው አርቲስት ሕይወት የትያትር ጽሑፍ (Script) እጥረት እንዲከሰት ምክንያት ናቸው ያለቻቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች ገልፃለች፡፡

Saturday, 24 September 2011 10:09

ሹገር ማሚ.. ፊልም ይመረቃል

የአንጋፋውን ድምፃዊ ክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ ልደት በመጪው ረቡዕ ስምንት ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር የሚዘከር ሲሆን የግብዣ ጥሪ ከሚደርሳቸው እንግዶች ውጭ ያሉት አድናቂዎቹና ሌሎች ተመልካቾች የትያትር ቤቱን የመስቀል የዓውዳመት ዝግጅት ለመታደም የመግቢያ ዋጋ እንደሚከፍሉ ታወቀ፡፡

..ሁለት ደቂቃ በባግዳድ.. እየተሸጠ ነው
ኤኬ ካአማስ ያዘጋጀው መጽሐፍ ..የብቃት መንገዶች.. በሚል የአማርኛ ርዕስ ለንባብ በቃ፡፡ ደምሰው ከበደ የተረጐመው መጽሐፍ 140 ገፆች አለት፡፡ ዋጋው 25 ብር ነው፡፡ በሌላም በኩል የኢራቅን የዛሬ ሃያ ዓመት ወቅታዊ ሁኔታ የሚያስቃኝ ..ሁለት ደቂቃ በባግዳድ.. የተሰኘውን የአሞስ ፔርመተር፣ አሪባር ዮሴፍ እና ሚካኤል ሀንድል የእንግሊዝኛ መሐፍ ሻምበል ተስፋዬ ርስቴ ወደ አማርኛ መልሰውታል፡፡ 169 ገጽ ያለው መጽሐፍ በ28 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ የትርጉም መጽሐፉ በተርጓሚው የግል ችግር በሁለት አስርት ዓመታት ዘግይቶ መውጣቱም በመሐፉ መግቢያ ተጠቅሷል፡፡