Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

Saturday, 08 October 2011 09:35

ከታሪክ መማር ብልህነት ነው

በ930 ዓ.ዓ (ቅድመ ልደት ክርስቶስ) የአንዲት የቀጣናዋ ልዕለ - ሃያል የነበረች ሀገር ሕዝቦች፤ ለአርባ አመታት (ከ970 ዓ.ዓ - 930 ዓ.ዓ) የምድሪቱ ንጉስ የነበረውንና በሞት የተለየውን አባቱን ተክቶ የንግስና ዘውዱን ሊደፋ ተገቢ ሆኖ የተገኘው ልጁ የአባቱ አልጋ ወራሽ ሆኖ ወደ ዙፋኑ ለመምጣት በተዘጋጀበት ወቅት፣ ለበዓለ ሲመቱ በመረጧት ሴኬም በተባለች ከተማ በነቂስ ወጥተው ተሰበሰቡ፡፡

አንድ ፓርቲ የገነነበት ፓርላማአሉታዊ፡- ፓርላማው በገዢ ፓርቲና ለስልጣናት የተዘጋጁ ህጎችን ብቻ    ያፀድቃል፤ ሁሌም። ፓርላማ ለምን አስፈለገ?” ያሰኛል። አወንታዊ፡- በአለም ህዝብ ፊት “ፓርላማ የሌለው ኋላቀር አገር” ከምንባል ይሻላል።ቴሌ የመንግስት መሆኑአሉታዊ፡- ቴሌ በከፍተኛ ወጪ የተከላቸው የመንገድ ስልኮች በአብዛኛው አይሰሩም። የባከነው ከፍተኛ ገንዘብም ይቆጫል። አወንታዊ፡- የተተከሉት “የስልክ ቤቶች” ባይሰሩም ለመጠለያነት እያገለገሉ ነው።የቢፒአር ነገርለአመታት ብዙ መቶ ሚ. ብሮችን  የፈጀ  የቢፒአር ሪፎርም፤ ዘላቂ ለውጥ  አላመጣም ሲባል ያስደነግጣል። የባከነው ጊዜና ገንዘብስ?

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን “የሁለት ምርጫዎች (የ1997-2000 ዓ.ም ወግ”) በሚል ርእስ የጻፉት መጽሐፍ በኬንያ በሕትመት ላይ እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን እና ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ገበያ ላይ እንደሚውል ምንጮች ጠቆሙ፡፡

በሰሜን ምስራቅ አማራ ክልል፣ ኦሮሚያ ዞን ጨፋ ሮቢት ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች በአብዛኛው ከቤተሰባቸው ውስጥ አንዱን በበረሃ ጉዞ ወይም በባህር እንዳጡ ይናገራሉ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይ ወጣቱ በየመን በኩል ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመሻገር ሁሌም ልባቸው እንደቆመ ነው፡፡ ያለምክንያት ግን አይደለም፡፡ የሚያውቁት የአካባቢያቸው ወጣት ከሳዑዲ አረቢያና ከየመን በሚልከው ገንዘብ የቤተሰቡን የሳር ጐጆ ወደ ቆርቆሮ ቤት አሻሽሎ ስለሚመለከቱ የእነሱንም ቤተሰቦች ኑሮ እንደ ጓደኞቻቸው ለመቀየር ያልማሉ፡፡ ምኞታቸውን አንግበው የሚገጥማቸውን ሁሉ ተጋፍጠው ባህር በመሻገር  በተገኘው ሥራ ተሰማርተው የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ህይወት ማሻሻልና መለወጥ ይፈልጋሉ፡፡ ክፋቱ ግን አይሳካም፡፡ አብዛኞቹ መንገድ ይቀራሉ፡፡ ከህልማቸውም ይሰናከላሉ፡፡

Saturday, 01 October 2011 13:30

ብራድ ፒት ለኦስካር ታጨ

7 ዓመቱ ብራድ ፒት ለዘንድሮ ኦስካር ሽልማት በእጩነት ከሚቀርቡ ተዋናዮች ተርታ እንደተመደበ የተለያዩ ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ በዋርነር ብሮስ የተሰራውና ለእይታ ከበቃ ሳምንት የሆነው የብራድ ፒት አዲስ ፊልም ..መኒ ቦል.. ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ 20.26 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቶበት ከ..ላዮን ኪንግ.. ቀጥሎ በቦክስ ኦፊስ 2ኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡ በፊልም ስራዎች የሚገኝ የገቢ ስኬት ብዙም ኢምፓየር ለተባለ መፅሄት ሰሞኑን የተናገረው ብራድ ፒት፤ ገቢው ጥሩ ፊልም መሠራቱን የሚያረጋግጥ አይደለም ብሏል፡፡

.በኢየሩሳሌም አማረ የተፃፉ የግጥም ስብስቦችን የያ “ምህላ ሲዘገይ” የተሰኘ መድበል የታተመ ሲሆን በነገው ዕለት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በዮፍታሄ ሲኒማ እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡
የግጥም መድበሉን የሚያስመርቀው ዜማ ብዕር ኢትዮጵያ የሴቶች የሥነጽሑፍ ማህበር ሲሆን ገጣሚዋ የማህበሩ አባል እንደሆነች ታውቋል፡፡

ስለአበባዎችም ያውቃል.. ብሩናይ
የፈረንሳይ ቀዳማይ እመቤት ካሮል ብሩናይ ከፕሬዝዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ጋር ትዳር የመሰረተችው በአበባዎች ላይ ባላቸው እውቀት ተማርካ መሆኑን ገለፀች፡፡ ካሮል ብሩናይ ሰሞኑን ከፕሬዝዳንት ሳርኮዚ የመጀመርያ ልጇን መፀነሷን አስታውቃለች፡፡ ይህንኑ በተመለከተ ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቃለምምልስ፤ የ43 ዓመቱ ኒኮላስ ሳርኮዚ ፕሬዝዳንት ብቻ ሳይሆን በአበባዎችም እንደኤክስፐርት የላቀ እውቀት ያለው ሰው መሆኑ ያኮራኛል ስትል ካሮል ብሩናይ ተናግራለች፡፡

ከሁለት ሳምንት በኋላ ለገበያ የሚበቃው የኮልድ ፕሌይ አዲስ አልበም “Mylo xyloto” በጉጉት እየተጠበቀ እንደሆነ ዘ ጋርድያን ዘገበ፡፡ ኮልድ ፕሌይ አራት አባላትን ያቀፈ የሮክ የሙዚቃ ባንድ ሲሆን ሰሞኑን በቢቢሲ አድማጮች ምርጫ የዓመቱ ምርጥ የፌስቲቫል ባንድ ተብሏል፡፡ የኮልድ ፕሌይ 5ኛ አልበም የሆነው ማይሎ ዛይሎቶ፤ በገበያው ስኬታማ እንደሚሆን ዘጋርድያን  ዘግቧል፡፡

አቶ ግርማና አቶ ሰይፉ በልብስ ስፌት ሙያ ላይ ተሰማርተው አንድ ሱቅ በጋራ በመክፈት ለብዙ ዓመታት አብረው ሰርተዋል፡፡ አቶ ግርማ የጉራጌ ብሔረሰብ ተወላጅ ሲሆኑ አቶ ሰይፉ ደግሞ አማራ ናቸው፡፡ በ1990 ዓ.ም አቶ ግርማ ለመስቀል በዓል ወደ ትውልድ አገራቸው ሲሄዱ ጓደኛው አቶ ሰይፉንም ጋብዘው አብረው ይሄዳሉ፡፡ አቶ ሰይፉ ስለዚህ ጉዟቸው ሁልጊዜም በመገረም የሚያነሱት ጥያቄ አለ፡፡ ..የጉራጌ ሴቶች ክትፎን የሚሰሩት ከጥሬ ሥጋና ከቅቤ ብቻ ሳይሆን የመብላት ፍላጎትን የሚጨምር፣ የጥጋብ ስሜት እንዳይሰማ የሚያደርግ ቅመም የሚጨምሩበት ይመስለኛል፡፡ እንደዚያ ባይሆን በሰዓታት ልዩነት የቀረበልንን ያን ሁሉ ክትፎ መብላት እንዴት ተቻለን?.. እያሉ አሁንም ይጠይቃሉ፡፡

ህይወታችን ..ሆረር..፤ ፊልማችን ..ኮሜዲ!..
መቼም እንኳንስ ለእንደኛ አገሩ ህዝብ ቀርቶ በዕድገት ለገሰገሱትም ሆነ በሃብት ለመጠቁት የዓለማችን ህዝቦችም ቢሆን አንዳንድ የማይፈቱ ችግሮችና እንቆቅልሾች አንዳንዴ አይጠፉም፡፡  የእኛን ትንሽ አሳሳቢ የሚያደርገው ኑሮአችን ሁሉ በችግሮችና በእንቆቅልሾች የተበተበ መሆኑ ነው - አንዳንዴ ሳይሆን ሁልጊዜ፡፡ እናም ሁሌም ጥያቄዎች አሉን - መልስ የሚሹ፡፡ ሁሌም ችግሮች እንደተጋረጡብን  ነው - መፍትሔ የሚፈልጉ፡፡ ሁሌም ..እንቆቅልሽ ምናውቅልሽ.. እንደተባባልን ነው፡፡ እንቆቅልሹን የሚፈታልን ግን የለም፡፡ የቱንም ያህል ስንጠያየቅ ብንውል እንቆቅልሻችን ሳይፈታ ነው የሚያድረው፡፡