Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

የተራበው- ፈረሱ የሳቀው የዶ/ር አቡሽን የኳንተም ሜካኒክስ መጽሐፍ አንብቦ ነው፡፡ ...በመጽሐፉ ማንም ሰው ..ኳንተም.. የሚባል ነገርን እስከሆነ ድረስ፤ በህይወት ላይ ያሉ ችግሮቹን መፍታት... አንድ ቦታ ብቻ ሳይሆን አርባ የተለያየ ቦታ በአንድ ቅበት መገኘት ይችላል፡፡ ፈረሱ ሳቀ፤ ኳንተም መሆን ብቻ ነው ያለበት፡፡ ሞገድ ሆኖ ከዛሬ ተወርውሮ ትናንት ላይ ለማረፍ... የማይቻል ነገር የለም፡፡

መቅድመ ነገር
የአምስት ሺ ዘመን ታሪክ ለኢትዮጵያ የቆጠራላት ጋዜጠኛ ፍሥሐ ያዜ ያቀረበውን መጽሐፍ ለመተቸት ዓለማየሁ ገላጋይ በአዲስ አድማስ ያቀረበውን ጽሑፍ ደግሜ ደጋግሜ አነበብሁት፡፡ ይህን ያህል ማንበቤ በርካታ የሚነቀሱ ነጥቦች በውስጡ ስለተመለከትሁ እነሱን በዓይነት በዓይነታቸው አውጥቼ በያንዳንዱ ረገድ መባል የሚገባቸውን ለመሰንዘር ስል ነበር፡፡ በሚያስገርም መጠን እያንዳንዱ ራሱን የቻለ ርዕስ እስኪሆን ድረስ የሚሄድ ሆነ፡፡ እንዲህ የሆነውን ደግሞ በጋዜጣ ገጽ እንዴት ማቅረብ ይቻላል? ሁሉንም እንዳሉ ከመተው ግን አንድ ሁለቱን ልምረጥ አልኩ፡፡ ስለኖኅ አና ስለንግሥተ ሳባ፣ ዓለማየሁ ያቀረባቸውን ማንሳትን ሊተውት የሚገባ አይሆንም፡፡ሌሎችን ነጥቦች ግን እንዲሁ በጥቆማና በጥያቄዎች በማንሳት ነጥቦቹ እንዲታሰቡ ሳያደርጉ ማለፍን ልቤ እሺ አላለኝምና እነዚያን አነጣጥቤ፣ በዚህ ጽሑፍ ቅድሚያ ከሰጠሁቸው አንዱንና የሚቀድመውን የኖኅ ህልውና እንደ አዲስ እንዲፈተሽ የተጠየቀበትን ነገር እይዛለሁ፡፡

..ባለመዶሻ፤ ያየው ችግር ሁሉ ሚስማር ይመስለዋል..   ማርክ ትዌይን
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሰው የታመመ ጓደኛውን ሊጠይቅ ወደ ሆስፒታል ይሄዳል፡፡ ጓደኛው የመጨረሻው የሞት አፋፍ ላይ ነበር ይባላል፡፡ ኦክሲጂን በላስቲክ ቱቦ ተገጥሞለት ነው የሚተነፍሰው፡፡
ጠያቂው ወደሚያጣጥረው ጓደኛው ቀረብ ብሎ ሲያየው ታማሚው በጣም ባሰበትና እየተወራጨ በሚያቃስት
..እባክህ የምጽፍበት ወረቀትና እርሳስ አቀብለኝ.. አለ፡፡
ጠያቂው በፍጥነት ወረቀትና እርሳስ እያቀበለው፤
..አይዞህ የፈለግኸውን ጻፍ፡፡ በርታ.. አለው፡፡

በ2011-12 የውድድር ዘመን ለሚቀጥለው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ የምድብ ድልድል ወጣ፡፡ በሌላ በኩል የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደው የአውሮፓ ኮከብ ተጨዋች ምርጫን ሊዮኔል ሜሲ ዣቪ ኧርናንዴዝና ክርስትያኖ ሮናልዶን አሸንፎ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ሐሙስ ዕለት በወጣው የሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ የሆነው ማንቸስተር ሲቲ ከ3 የአውሮፓ ታላላቅ ሊጐች ከተወከሉ ጠንካራ ክለቦች ጋር መገናኘቱ ትኩረት ስቧል፡፡

Saturday, 27 August 2011 13:42

የአባቱ ልጅ

የዜማና ግጥም ደራሲ፣ የሙዚቃ መሣሪያዎች ተጫዋችና ድምፃዊ ከነበረው አባቱ ተፈራ ካሣናከተወዛዋዥ
እናቱ ወ/ሮ አረጋሽ ኩምቴሳ መወለዱ ገና በልጅነት  ዕድሜው ስሜቱ ለሙዚቃ እንዲያዳላ ምክንያት እንደሆነው ይናገራል፡፡ ተወልዶ ያደገበት ፈረንሳይ ለጋሲዮን ለበርካታ የጥበብ ሰዎች መፍለቂያ የሆነና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሙያዎች የከተሙበት አካባቢ መሆኑ ደግሞ ስሜቱ የበለጠ ከሙዚቃ ጋር እንዲተሳሰር አደረገው፡፡ ጐረቤታቸው የነበረው አንጋፋው ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠና ወላጅ አባቱ ተፈራ ካሣ የሙዚቃ ሥራ ልምምድ ሲያደርጉ ሁሌም ከሥራቸው አይጠፋም ነበር፡፡

ለሦስት አስርት ዓመታት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውና እውቅ ባለሙያዎች ያፈራው ራስ ቴአትር በአዲስ መልክ ሊገነባ ነው፡፡ አሮጌው አዳራሽ የመጨረሻ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቱን ነገ ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች በማቅረብ በይፋ ይዘጋል፡፡ ይኸው የዓመት በዓል ልዩ ዝግጅት ባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃ እንዲሁም ውውት ያካተተ ሲሆን ለእንቁጣጣሽ በኢትዮጵያ ሬዲዮናቴሌቬን ለሕዝብ ይቀርባል ተብሏል፡፡

..አይኑማ.. በሚለው ዜማው የሚታወቀው ድምፃዊ እያዩ ማንያዘዋል ከ15 ዓመት በኋላ አዲስ አልበም አወጣ፡፡ ..አሞናል.. የሚለው አዲስ አልበም 10 ዘፈኖች ያሉት ሲሆን በካሴት እና በሲዲ ተዘጋጅቷል፡፡ግጥሙን አቤል መልካሙ ያዘጋጀው አዲስ አልበም ከሕዝብ ከተወሰዱ ዜማዎች በተጨማሪ አበበ ብርሃኔ እና እንዳለ አድምቄ ዜማውን የሰሩ ሲሆን አቀናባሪው ስንታየሁ ክብረት ነው፡፡ለበርካታ አመታት ከመድረክ ርቆ የነበረው ድምፃዊ እያዩ ..አቤል መልካሙ ለአምስት ዓመታት ከጐተጐተኝ በኋላ ተመልሻለሁ.. ሲል ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር በየወሩ የሚያካሂደውን ኪነጥበባዊ ዝግጅት በመጪው ረቡዕ የሚያቀርብ ሲሆን ዝግጅቱ እንቁጣጣሽን የተመለከተ እንደሚሆን አስታወቀ፡፡ ..ጥበብ እንቃመስ.. በሚል ርእስ በሩስያ ሳይንስና ባህል ማእከል በሚቀርበው ዝግጅት 16 የተመረጡ እንቁጣጣሽ ተኮር ግጥሞች፣ አጭር ድራማና ሌሎች ጥበባዊ ዝግጅቶችም ለዕድምተኞች ይቀርባሉ፡፡

የተለመዱ የልጆች ጨዋታ ላይ በመመስረት የተሰራው ..የኢትዮጵያ ልጆች ጨዋታ.. ዛሬ ኤድናሞል ማቲ ሲኒማ ይመረቃል፡፡ አቢሲኒያ ሥነጥበብ ተቋም፣ ማስተር ፊልም ፕሮዳክሽን፣ የኢትዮጵያ ልጆች ኢንተርቴይመንት እና ኪኪ ፕሮሞሽን ባዘጋጁትና በሲዲና በዲቪዲ በተሰራው የልጆች ጨዋታ ላይ 120 ልጆች ተሳትፈዋል፡፡

የሊዮ ቶልስቶይ ድርሰት የሆነውና በተመሳሳይ ርእስ አቶ ወጋየሁ በለው ወደ አማርኛ የተተረጐመው ..አና ካሬኒና.. ረዥም ልቦለድ መሐፍ ለውይይት እንደሚቀርብ የሚዩዚክ ሜይ ዴይ ኢትዮጵያ የመፃህፍት ንባብና የውይይት ክበብ አስታወቀ፡፡ ውይይቱ ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በአምስት ኪሎው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዘክር አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ የመነሻ ሃሳብ በማቅረብ የሚያወያዩት አቶ አለማየሁ አሊ ናቸው፡፡