Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

አበሻ የባህል ማዕከል እና የስዕል ጋለሪ ከባታ ጫማ አምራች ኩባንያ ጋር በመዋዋል የባታ ምርት የሆኑትን ጫማዎች ለአገራችን ገበያ ከዛሬ ጀምሮ ያቀርባል፡፡ በአለማችን ከአምስት ሺህ በላይ የሚሆኑ ወኪል ሱቆች ያሉት የባታ ጫማ አምራች ኩባንያ የሴትና የወንድ የህፃናት እና የአዋቂ ጫማዎችን ከ80 ብር እስከ 1800 ብር በሚደርስ ዋጋ ለአገራችን ገበያ ለማቅረብ ከአበሻ ጋለሪ ጋር በወኪልነት መፈራረሙን የጋለሪው ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ በድሩ ሙዘይን ተናግረዋል፡፡

Saturday, 01 December 2012 15:01

በዋልያዎቹ ስጋት

በንስሮቹ ጫና፣ በመደብ ጥይቶቹ ጉራ በፈረሰኞቹ ዝምታ ሰፍኗል
መላው ኢትዮጵያዊ በከፍተኛ ጉጉትና ተስፋ በደቡብ አፍሪካ የሚስተናገደውን 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል ብሔራዊ ቡድኑ ከ31 ዓመታት በኋላ ባገኘው የተሳትፎ እድል በተለያዩ ምክንያቶች አጓጉል እንዳይሆን ስጋቶች ተፈጥረዋል፡፡
29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀመር ስድስት ሳምንታት ቀርተዋል፡፡ በምድብ 3 ከተደለደሉ አገሮች ሶስቱ ናይጄርያ፤ ዛምቢያ እና ቡርኪናፋሶ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ተጨዋቾችን በማሰባሰብ እና ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች በመጓዝ የአቋም መፈተሻ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ሲያደርጉ ኢትዮጵያ እስካሁን ዝግጅቷን በይፋ አልጀመረችም፡፡

Saturday, 01 December 2012 14:42

ጋዜጠኛ ብርሐኑ ሰሙ ተሸለመ

በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በተለይ የአዲስ አበባን ታሪካዊ ስፍራዎች አመሠራረት በመዘገብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ብርሃኑ ሰሙ፤ በከተማው አስተዳደር ተሸለመ፡፡ አዲስ አበባ የተመሠረተችበት 125ኛ ዓመት ክብረበአል ሲጠቃለል ጋዜጠኛውን ለሽልማት ያበቁት ስለ ከተማዋ ታሪካዊ ዳራዎች ያደረጋቸው ጥናቶችና ያጠናቀራቸው ጽሑፎች እንዲሁም ያሰባሰባቸው የፎቶግራፍ መረጃዎች ናቸው፡፡ የከተማዋን ልደት አስመልክቶ ከሕዳር 11 እስከ ሕዳር 17 ቀን 2005 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማእከል ተዘጋጅቶ በነበረው አውደርእይ በግል ለመካፈል ጥያቄ አቅርቦ ተቀባይነት ያገኘው ብርሃኑ ሰው ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ባደረገለት ድጋፍ በአውደርእዩ ላይ በነፃ ማሳያ ቦታ ተሰጥቶት ተሳትፏል፡፡

“ሮማን የወረረ ጀግና” በሚል ርዕስ ባለፈው ዓመት በትዕኩ ባህታ ተተርጉሞ ለንባብ የበቃው መፅሃፍ ነገ ከቀኑ በ8 ሰዓት በብሄራዊ ቤተመዘክር አዳራሽ ውይይት እንደሚደረግበት ሚዩዚክ ሜይዴይ አስታወቀ፡፡ ውይይቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ መምህር አቶ ሰለሞን ተሰማ ይመሩታል፡፡

በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው “አዲስ ፎቶ ፌስት” የፎቶግራፍ አውደርእይ የፊታችን ሰኞ በጣይቱ ሆቴል እንደሚቀርብ አዘጋጆች ገለፁ፡፡ ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓና ከአሜሪካ የመጡ 42 የፎቶ ጋዜጠኞች ሥራዎች በአውደርዕዩ ላይ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ በጣይቱ ሆቴል የሚከናወነው የመክፈቻ ሥነ ስርዓት በጥሪ ወረቀት ብቻ የሚገባ ቢሆንም ከዚያ በኋላ በዚሁ ሆቴል፣ በአልያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ፣ በጎተ የጀርመን ባህል ተቋም፣ በጣሊያን የባህል ተቋም፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር፣ በአፍሪካ ሕብረት አዲሱ አዳራሽ እና በሥነ ጥበባት ትምህርት ቤት በነፃ መታደም እንደሚቻል አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

በጋዜጠኛ፣ ደራሲና ሃያሲ ደረጄ በላይነህ የዛሬ አምስት ዓመት በመጽሐፍ ታትሞ የነበረው “የዲያስፖራና የአገር ቤት ልጅ ፍቅር” የፍቅር ምልልስ መጽሐፍ በትረካ መልክ በሲዲ ታትሞ ቀረበ፡፡ ተራኪዎች “የኢትዮ ሊትሬቸር ፖል ቶክ” ወንድ እና ሴት ጋዜጠኞች ናቸው፡፡ “የዲያስፖራና የሀገር ቤት ልጅ ፍቅር” በ2000 ዓ.ም “የናፍቆት ጥላዎች” በሚል ርእስ ታትሞ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በጃዕፈር መጽሐፍት ቤት እና በሌሎችም መደብሮች ለሽያጭ የቀረበው የትረካ ሲዲ በ18ብር እየተሸጠ ነው፡፡ ደራሲው ካሁን ቀደም ስድስት መፃሕፍት አሳትሞ ለንባብ አብቅቷል፡፡

በጋዜጠኛ ሰለሞን ታደሰ የተዘጋጀው “ቦሌ ፒኮክ ጋ ጠብቂኝ” መጽሐፍ ነገ በሌላ በኩል አቶ ተስፋሚካኤል ምንዳዬ የፃፉት “ጥቁር ሰው” የግጥም መጽሐፍ ዛሬ ከጧቱ ሦስት እንደሚመረቅ አዘጋጁ አስታወቁ፡፡

Saturday, 01 December 2012 14:31

የሳቅ ቀን ይከበራል

በ “ላፍተር ጄኔሬሽን ቱ ኦል” እየተዘጋጀ በየዓመቱ የሚቀርበው የሳቅ ቀን ታህሳስ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ለ10ኛ ጊዜ እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ ገለፁ፡፡ በዘንድሮ ዝግጅት አዘጋጆቹ በአፍሪካ የመጀመሪያው ነው ያሉት የሳቅ ትምህርት ቤት የሳቅ ቴራፒ ተማሪዎች ይመረቃሉ፡፡ ምርቃቱን አስመልክቶ አቢሲኒያ የበረራ አገልግሎት የአውሮፕላን ትርኢት ያሳያል፡፡

በብስራት ገመቹ ተፅፎ የተዘጋጀውና በራሷ ፕሮዲዩስ የተደረገው “መልሕቅ” ፊልም ሰኞ እንደሚመረቅ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር የሚመረቀው ፊልም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለሕዝብ መቅረብ ጀምሯል፡፡
በፊልሙ በ “ሰው ለሰው” የቴሌቪዥን ድራማ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ትተውን የነበረችው ብስራት በ “መልሕቅ” እየተወነች ሲሆን በዚሁ ድራማ የሚተውነው ዝናህብዙ ፀጋዬ፣ እንዲሁም ዳንኤል ገበየሁ፣ ኤርምያስ ሀብታሙ፣ አለባቸው መኮንን፣ መንገሻ ተሰማ፣ መክሊት ገብረየስ፣ እንድርያስ አስናቀው እና ሌሎችም ተውነዋል፡፡ የ110 ደቂቃ ፊልሙን ሠርቶ ለማጠናቀቅ 11 ወራት ፈጅቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በቅርብ ዓመታት ካስገነባቻቸው ካቴድራሎች (ደብሮች) አንዱ የሆነው የቦሌ ደብረሳሌም መድሃኒዓለም፣ መጥምቁ ዮሐንስና አቡነ አረጋዊ ካቴድራል የቱሪስት መስሕብነቱን ያሰበበት መሆኑን አስታወቀ፡፡ ካቴድራሉ በአዲስ አበባ ካሉ አብያተክርስትያናት ትልቁ ነው፡፡ ውጭ ሀገራት በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ዜጎች ዘወትር እየተጎበኘ ያለው ቤተክርስትያን የቱሪስት መስህብነቱን በማጠናከር ዘመናዊ ፏፏቴ (ፋውንቴን) አሰርቷል፡፡ የቀብር አገልግሎት የማይሰጠው ቤተክርስትያን ፏፏቴውን በመጪው ማክሰኞ ብፁአን ሊቃነጳጳስ እና ሌሎች እንግዶች በሚገኙበት እንደሚያስመርቅ የቤተክርስትያኑ ጽሕፈት ቤት ከላከልን መግለጫ መረዳት ተችሏል፡፡ በቦሌ መድሃኔዓለም ከሚጎበኙ ስፍራዎች መካከል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ በመሠራቱ አወዛጋቢ የነበረው ሐውልት ይገኝበታል፡፡

Page 10 of 163