መክሊት ሐደሮ አዲስ አልበም እየሠራች ነው
ኢትዮጵያዊቷ የሶል እና ጃዝ ሙዚቀኛ መክሊት ሃደሮ፤ ሰሞኑን በጉግል የሳምንቱ ምርጥ አርቲስት የተባለች ሲሆን 3ኛውን አዲስ የሙዚቃ አልበሟን እየሰራች መሆኑን ሳንፍራንሲስኮ ክሮኒል ዘገበ፡፡
ከሳምንት በፊት በአሜሪካዋ የናቫዳ ግዛት በሚገኘው ሴንተር ፎር አርትስ፣ የሙዚቃ ሥራዎቿን ያቀረበችው መክሊት፤ በድምፃዊነትና በዘፈን ግጥም ደራሲነቷ በካሊፎርንያ እየተወደሰች መሆኗንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሩት ነጋ በፊልም አየርላንድን
የ29 ዓመቷ ሩት ነጋ በፊልም ተዋናይነት በአየርላንድ ስኬታማ እየሆነችና በተለያዩ መድረኮች አገሪቱን እያስጠራች መምጣቷን የተለያዩ ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ በቅርቡም በታዋቂዋ እንግሊዛዊ ድምፃዊት ሼሪሊ ቤሲ የህይወት ታሪክ ላይ የሚሰራውን ፊልም ሩት ነጋ በመሪ ተዋናይነት እንደምትሠራ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ሙዚቃ የዓለም ገበያን እየተቀላቀለ ነው
አዲስ አኩስቲክ የሙዚቃ ቡድን ትውስታ (Remembrance) የተሰኘውን አዲስ የሙዚቃ አልበም ለገበያ ማብቃቱ ታወቀ፡፡ ከኢትዮጲክስ ተከታታይ የሙዚቃ አልበሞች ስኬታማ ገበያ b|§ ተሻሽለውና በአዲስ መልክ ተቀናብረው ለዓለም ገበያ የቀረቡ ኢትዮጵያዊ ዘፈኖች በዓለም አቀፍ ደረጃ ፋሽን እየሆኑ መምጣታቸውን ዘ ጋርድያን ሰሞኑን ዘግቦታል፡፡ በዓለም ዙሪያ ከ30 በላይ የሙዚቃ ባንዶች በድሮ የኢትዮጵያ ዘፈኖች ዜማ ሙዚቃዎቻቻውን እየሠሩ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
ዜማ ብእር.. ነገ ዝግጅቱን ያቀርባል
ዜማ ብእር የሴት ደራሲያን ማህበር ነገ ጧት ..እናትና ጥበብ.. በሚል ርስ የእንቁጣጣሽ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቱን ቦሌ በሚገኘው ..ፀሐይና ልጆቿ.. ሕንጻ ያቀርባል፡፡ በዝግጅቱ የማህበሩ አባላትና ሌሎች እድምተኞች ኪነጥበባዊ ዝግጅቶቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
እሹሩሩ.. ቪሲዲ ዛሬ፤ ..የትሮይ ፈረስ.. ሰኞ ይመረቃሉ
በመላኩ ኢንተርቴይመንት የተዘጋጀው ..እሹሩሩ.. የተሰኘ የኮሜዲ ቪሲዲ ዛሬ ከቀኑ 7፡30 በአዲስ አበባ ባህልና ትያትር አዳራሽ ይመረቃል፡፡ መላኩ ገብሩ ጽፎ ፕሮዲዩስ ያደረገውን የአንድ ሰዓት ኮሜዲ ቪሲዲ ያዘጋጀው ታደሰ ንጉሥ (አቡ) ነው፡፡በፊልሙ ፋንቱ ማንዶዬ፣ ፍቅርተ ጌታሁን፣ ተመስገን መላኩ፣ ፀጋዬ ዘርፉ፣ ሰብለ ተፈራ፣ ወንድወሰን ብርሃኑና ሌሎችም ተውነዋል፡፡በሌላም በኩል በአሳምነው ባረጋ ልቦለድ ድርሰት ላይ ተንተርሶ የተሠራው ..የትሮይ ፈረስ.. ፊልም ሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ይመረቃል፡፡
ደራሲ ማሞ ውድነህ መከሩ
አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ማሞ ውድነህ ፊልሞች በተናጠል ከሚሠሩ ይልቅ በአንድ ኩባንያ ቢሠሩ የተሻለ እድገት ይመጣል ሲሉ የፊልም ባለሙያዎችን መከሩ፡፡ ..አንናገርም.. የተሰኘው ፊልም በእንቢልታ ሲኒማ ከትናንት ወዲያ ሲመረቅ የክብር እንግዳ የነበሩት ደራሲ ማሞ ውድነህ፤ በወጣት ጋዜጠኝነት ዘመናቸው ኤርትራ ውስጥ ከሆሊውዱ ትዌንቲዝ ሲንቸሪ ፎክስ ስቱዲዮ ጋር መሥራታቸውን አስታውሰው፣ ለአሜሪካ ፊልም ከፍተኛ ገቢ እያመጣ ነው፤ ኢትዮጵያም እንዲያ ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡
..ፖየቲክ ጃዝ.. በሸበሌ ይቀርባል
የግጥም ሥራዎች ከጃዝ ሙዚቃ ጋር ተዋህደው የሚቀርቡበት ..ፖየቲክ ጃዝ.. የፊታችን ረቡዕ ጳጉሜ 2/2003 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ጀምሮ በሸበሌ ሆቴል እንደተዘጋጀ ተገለፀ፡፡በዝግጅቱ ላይ ገጣሚና ጋዜጠኛ አበባው መላኩ፣ ገጣሚና ሰዓሊ ቸርነት ወ/ገብርኤል፣ ገጣሚ ምስራቅ ተረፈና ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ ከመለከት ባንድ ጋር የግጥም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ የአሁኑ ዝግጅት ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን የጠቆሙት አዘጋጆቹ፤ ፕሮግራሙን በየወሩ ለማቅረብ ከሸበሌ ሆቴል ባለቤት ፈቃድ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ ሥነሑፍ አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ተቀበሉ
ኮድ ኢትዮጵያ ባስተባበረውና ኮድ ካናዳ ድጋፍ ያደረገለት በርት የአፍሪካ ሥነ ሑፍ ሽልማት አሸናፊዎች ባለፈው እሁድ ሽልማታቸውን የካናዳ ኤምባሲ አንደኛ ፀሃፊ ሚስ ማጋን ካየርስ ባሉበት ከትምህርት ሚኒስትር ዳኤታ አቶ ፉአድ ኢብራሂም እጅ ተቀበሉ፡፡ በውድድሩ አንደኛ የወጣው |Young Crusaders´ የሚል መሐፍ የፃፈው ጋዜጠኛና መምህር ሰለሞን ኃይለማርያም ሁለት መቶ ሰባት ሺህ ሃምሳ አራት ብር፣ ሁለተኛ የወጣው የ |Escape´ ፀሃፊ ደራሲ ገበየሁ አየለ አንድ መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ሃያ ሰባት ብር፣ ሦስተኛ የወጣው ሜሮን ተክለብርሃን የፃፈችው |The Letter´ መሐፍ ሃምሳ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ሦስት ብር ከሃምሣ ሳንቲም ተሸልሟል፡፡
ሚዩዚክ ሜይዴይ የውይይት ቦታ ይቀይራል
በየ15 ቀን አንድ ጊዜ የመፃሕፍት ንባብ ውይይት በማድረግ ላይ የሚገኘው ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ፣ የመፃሕፍት የመወያያ ቦታ ሊቀይር መሆኑን ገለፀ፡፡ የሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ የመፃሕፍት ንባብና ውይይት ክበብ ሃላፊ አቶ በፍቃዱ አባይ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፣ የእድምተኞች ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የተሻለ ስፋት ያለው መሠብሠቢያ አዳራሽ ያስፈለጋቸው ሲሆን ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አመቺ ሥፍራ እየፈለጉ መሆናቸውን እንዲሁም የተሳታፊ ቁጥር በ2004 ዓ.ም ይበልጥ ለማብዛት መዘጋታቸውን ገልፀዋል፡፡
ራስ ትያትር እስከ መስከረም 30 ይፈርሳል
ቀድሞ ከነበረበት የእህል መጋዘንነት ወደ ትያትር ቤትነት የተለወጠው ራስ ትያትር ከ32 ዓመት አገልግሎት በኋላ ሥራ ያቆመ ሲሆን በአዲስ መልክ ከመገንባቱ በፊት ማፍረሱ እስከ መስከረም 30 ይጠናቀቃል፡፡ አሮጌው ትያትር ቤት የመጨረሻ ዝግጅቱን ባለፈው እሁድ ያቀረበ ሲሆን ከዚሁ ዝግጅት ከፊሉ ለእንቁጣጣሽ በኢትዮጵያ ሬዲየና እንደሚቀርብ ባለፈው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ሐምሌ 29 1971 ዓመተ ምህረት የመንግስቱ ለማን የትርጉም ትያትር በማሳየት ሥራ እንደጀመረ የተገኘው ማስረጃ ይጠቁማል፡፡ በእሁዱ ዝግጅት የመሰናበቻ መግቢያ ንግግር ያደረገው የትያትር ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አርቲስት ኩባራቸው ደነቀ፤ አዲሱን ግንባታ አስመልክቶ ሲናገር ..በርካታ ችግሮች ያሉበት የአዲስ አበባ ካቢኔ ለራስ ትያትር ቅድሚያ መስጠቱ ያስመሠግነዋል.. በማለት 24 ሚሊየን ብር መነሻ በጀት ለአዲሱ ሕንፃ ግንባታ የመደበውን አስተዳደር አመስግኖዋል፡፡