Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 September 2011 10:12

የትያትር እጥረት ተጠና

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ትያትር ቤቶች የገጠማቸውን የትያትር ጽሑፍ እጥረት አስመልክቶ የጥናት ወረቀት ቀረበ፡፡ አምና ከተደረገ የመስኩ ባለሙያዎች ውይይት በመነሳት የጥናት ወረቀት ያቀረበችው አርቲስት ሕይወት አራጌ ነች፡፡ በጥናቴ መጠይቅ፣ ቃለምልልስ እና የቡድን ውይይት ተጠቅሜአለሁ ስትል ለአዲስ አድማስ ማብራሪያ የሰጠችው አርቲስት ሕይወት የትያትር ጽሑፍ (Script) እጥረት እንዲከሰት ምክንያት ናቸው ያለቻቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች ገልፃለች፡፡

በዚሁም መሠረት የፀሐፌ ተውኔቶች ክፍያ አለመሻሻል፣ ለፀሐፍቱ በቂ ቴክኒካዊ ስልጠና አለመሰጠት፣ የትያትር ጽሑፍ ግምገማ ሂደት አታካች መሆን ለፀሐፌ ተውኔቶች በትያትር ጽሐፍ እንዲወዳደሩ የሚጋብዘው ማስታወቂያ በግልጽ ቦታ አለመለጠፍና በመገናኛ ብዙሃን አለመነገር የትያትር ጽሑፍ እጥረት እንዲኖር ዋነኞቹ መንስዔዎች ናቸው፡፡ ትኩረቷን በአራት የአዲስ አበባ ትያትር ቤቶች ላይ ያደረገችው አጥኚዋ በመፍትሔ ሀሳቧም የክፍያ ሥርአት መሻሻል አለበት፣ ባለሙያዎች በሠልጠና ቢታገዙ፣ ማስታወቂያዎች ግልጽ በሆነ ቦታ እና ብዙ ሰው በሚያያቸው ቦታ ቢለጠፉና በመገናኛ ብዙሃን ቢነገሩ የተሻለ ይሆናል ብላለች፡፡
በትያትሪካል አርት የመጀመያ ዲግሪ ያላት አርቲስት ሕይወት አራጌ በአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ጥናትና ምርምር ኦፊሰር ነች፡፡ አሁን እየታየ ያለው ..ረመጥ.. ትያትርን በአዘጋጅነት እንዲሁም እየታዩ ባሉት በ..ሩብ ጉዳይ..፣ ..ፎርፌ.. እና ..ትዳር ሲታጠን.. ትያትሮች በተዋናይነት እየሠራች ነው፡፡

 

Read 4562 times Last modified on Saturday, 24 September 2011 10:14