Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 01 October 2011 13:13

ጥሬ ስጋ መብላት እንዴት ተጀመረ?

Written by 
Rate this item
(2 votes)

አቶ ግርማና አቶ ሰይፉ በልብስ ስፌት ሙያ ላይ ተሰማርተው አንድ ሱቅ በጋራ በመክፈት ለብዙ ዓመታት አብረው ሰርተዋል፡፡ አቶ ግርማ የጉራጌ ብሔረሰብ ተወላጅ ሲሆኑ አቶ ሰይፉ ደግሞ አማራ ናቸው፡፡ በ1990 ዓ.ም አቶ ግርማ ለመስቀል በዓል ወደ ትውልድ አገራቸው ሲሄዱ ጓደኛው አቶ ሰይፉንም ጋብዘው አብረው ይሄዳሉ፡፡ አቶ ሰይፉ ስለዚህ ጉዟቸው ሁልጊዜም በመገረም የሚያነሱት ጥያቄ አለ፡፡ ..የጉራጌ ሴቶች ክትፎን የሚሰሩት ከጥሬ ሥጋና ከቅቤ ብቻ ሳይሆን የመብላት ፍላጎትን የሚጨምር፣ የጥጋብ ስሜት እንዳይሰማ የሚያደርግ ቅመም የሚጨምሩበት ይመስለኛል፡፡ እንደዚያ ባይሆን በሰዓታት ልዩነት የቀረበልንን ያን ሁሉ ክትፎ መብላት እንዴት ተቻለን?.. እያሉ አሁንም ይጠይቃሉ፡፡

ለመሆኑ ጥሬ ሥጋ /በተለያዩ መልኩ/ መብላት በአገራችን መች ተጀመረ? ደራሲ አለማየሁ ነሪ ..ኢትዮጵያ ሲሳይ.. በሚል ርዕስ በ1998 ዓ.ም ባሰሙት መጽሐፍ ለዚህ ጥያቄ የሚከተለውን መልስ አኑረዋል፡-  
..ከክርስቶስ ልደት 29 ዓመት በፊት የሮማው ንጉሥ አውግስቶስ ቄሣራ አገራችን ኢትዮጵያን በሰሜኑ በኩል በጦር ወርሮ ለመግባት የጦር እንደራሴው የነበረ ጄኔራል ከመላኩ በፊት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጥሬ ሥጋ ቢበላ እንደነውር ይቆጠርበት፣ የነበረ ብቻ ሳይሆን በፍፁም የተከለከለም እንደ ነበር ይታወቃል፡፡ በጦርነቱ ወቅትም ዘማች ሠራዊት ምግቡን ለማብሰል እሳት በሚያነድበት ስፍራ የሚወጣውን ጭስ በመመልከት የጠላት ሠራዊት አስከፊ አደጋ እያደረሰ በወገን ላይ ጉዳት ማመዘኑ፣ የወቅቱ  ኢትዮጵያውያን የጦር መሪዎች ደረሱበት፡፡ በጭሱ ሳቢያ የሚደርሰው ሽንፈትም እጅግ ስለበዛ ሥጋ ለማብሰያ እሳት እንዳይቀጣጠል፣ ጭስ እንዲቀር፣ የኢትዮጵያ ጦርም ጥሬ ሥጋ እንዲበላ እንደታዘዘ፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ጥሬ ሥጋ መብላት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ ባህል ሆኖ መለመዱን.. የዕድሜ ባለፀጎች ይናገራሉ፡፡
ጥሬ ሥጋን መብላት በአገራችን በዚህ መልኩ ከተጀመረ በኋላ በተለይ ከጉራጌ ብሔረሰብ ባህላዊ ምግቦች አንዱ ከመሆን አልፎ በኢትዮጵያ የባህል ምግቦች ውስጥ ቀድመው ከሚጠሩት መሐል የሚገኘው ክትፎ፤ በተለይ በመስቀል በዓል ወቅት በጉራጌዎች ቤት እንደ ምግብ ይበላል ሳይሆን እንደ ውሃ ይጠጣል በማለት የሚገልፀው ጋዜጠኛና ደራሲ ዘነበ ወላ ነው፡፡  
ምንጭ - (የዴንጌሳት በዓልን አስመልክቶ በ2004 ዓ.ም ከወጣው ..ዴንጌሳት መስቀል በጉራጌ.. የተሰኘ አነስተኛ መሄት ኤዲት ተደርጐ የተወደሰ)

 

Read 10768 times Last modified on Saturday, 01 October 2011 13:17