Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 01 October 2011 13:24

የኮልድ ፕሌይ 5ኛ አልበም በጉጉት ይጠበቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከሁለት ሳምንት በኋላ ለገበያ የሚበቃው የኮልድ ፕሌይ አዲስ አልበም “Mylo xyloto” በጉጉት እየተጠበቀ እንደሆነ ዘ ጋርድያን ዘገበ፡፡ ኮልድ ፕሌይ አራት አባላትን ያቀፈ የሮክ የሙዚቃ ባንድ ሲሆን ሰሞኑን በቢቢሲ አድማጮች ምርጫ የዓመቱ ምርጥ የፌስቲቫል ባንድ ተብሏል፡፡ የኮልድ ፕሌይ 5ኛ አልበም የሆነው ማይሎ ዛይሎቶ፤ በገበያው ስኬታማ እንደሚሆን ዘጋርድያን  ዘግቧል፡፡

የሮክ ሙዚቃ ባንዱ የሚሰራቸው ሙዚቃዎች በበርካታ የሆሊዉድ ፊልሞች ማጀቢያነት ተፈላጊ ናቸው፡፡ ኮልድ ፕሌይ ሰባት የግራሚ ሽልማቶችን ያሸነፈ ባንድ ሲሆን አስቀድመው ለገበያ የበቁት የባንዱ አራት የሙዚቃ አልበሞች በዓለም ዙሪያ ከ50 ሚሊዮን በላይ ቅጂ ?¹«êL””
የ..ኮልድ ፕሌይ.. መሪ ዘፋኝ ክሪስ ማርቲን፤ ..ስሞት የቀብር ስነስርዓቴ በመታሰቢያ ኮንሰርት እንዲሆንልኝ እፈልጋለሁ.. ሲል ሰሞኑን ኪው ለተባለ መፅሄት ተናግሯል፡፡ የ35 ዓመቱ ክሪስ ማርቲን ከታዋቂዋ ተዋናይት ጉዌንትዝ ፓልትሮው ጋር ትዳር በመፈፀም ሁለት ልጆችን አፍርቷል፡፡ በ..ኮልድ ፕሌይ.. 5ኛ አልበም ላይ በተካተተው ..ፕሪንሰስ ኦፍ ቻይና.. የተባለ ዘፈን ላይ ሪሃና በተጋባዥ ድምፃዊነት ትሰራለች፡፡

 

Read 4227 times Last modified on Saturday, 01 October 2011 13:27