“24”ን በአንድ ፊልም አጠቃልሎ ለመስራት ስለተያዘው ፕሮጀክት አስተያየቱን የሰጠው ኪፈር፤ ስክሪፕቱን ለማዘጋጀት ብዙ መልፋቱን ገልፆ፤ ለስምንት ዓመት የታየውን የቴሌቭዥን ፊልም በ2 ሰዓት አጠቃሎ መስራት ቀላል እንዳልሆነ ተናግሯል፡፡ በዜግነቱ ካናዳዊ የሆነውና በእንግሊዝ የተወለደው ኪፈር ሰዘርላንድ፤ ከ70 በላይ ፊልሞች ላይ የተወነ ሲሆን ፕሮዱዩሰርና ዲያሬክተርም በመሆን ሰርቷል፡፡ ዘንድሮ “ሜላንኮሊ” በተባለ ሳይንሳዊ ልቦለድ ፊልም ላይ የተወነው ኪፈር ሰዘርላንድ፤ በአራት ፊልሞች ላይ በፕሮዲዩሰርነት ተሳትፏል ፡፡ “ 24” አንድ ወጥ ፊልም ሆኖ ለዕይታ የሚበቃው በመጪው የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንደሆነ ዴይሊ ቴሌግራፍ ጠቁሟል፡፡