Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 15 October 2011 12:16

የአይዶል አሸናፊዎች በደሴ እና ከሚሴ ተሸለሙ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያን አይዶል የዘንድሮ አሸናፊዎቹ በደሴና በከሚሴ ከተሞች የማበረታቻ ሽልማት እንደተደረገላቸው ድርጅቱ አስታወቀ፡፡ የድርጅቱ ዋና አስተባባሪ አቶ አብይ ሳህሌ እንደገለፁት፤ አሸናፊዎቹና 16 የድርጅቱ ሠራተኞች ሽልማትና ስጦታ አግኝተዋል፡፡ በዚህም መሠረት አንደኛ የወጣው ተመስገን ታፈሰ (የከሚሴ ተወዳዳሪ) ከከሚሴ ከተማ አስተዳደር የቤት መስሪያ መሬትና 60ሺህ ብር፣ ከደሴ ከተማ አስተዳደር 10ሺህ ብር፣ ሁለተኛ የወጣው የደሴው ሀሰን አራጋው ከከሚሴ 10ሺህ ብር፣ ከደሴ 10ሺህ ብር፣ ሦስተኛ የሆነው የባህርዳሩ ማስተዋል እያዩ ከከሚሴ 10ሺህ ብር፣ ከደሴ 10ሺህ ብር ሲያገኙ በደረጃ አምስተኛ የነበረው የአዲስ አበባው ይድነቃቸው ገለታ ተክለፃድቅ ከሁለቱ ከተሞች አምስት አምስት ሺህ ብር አግኝቷል፡፡ 16 የውድድሩ አዘጋጆች እያንዳንዳቸው ከከሚሴ የአካባቢውን የባህል ልብስ፤ በደሴ ጋቢ ተበርክቶላቸዋል፡፡Read 3174 times