Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 29 October 2011 15:08

ላናድህ ያለ እሳት ሲጭር፣ እሳት ፍለጋ አትሂድ፡፡ ማገዶውን አርጥብ፡፡

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ንጉሥ ሶስት ልጆቹን ጠርቶ፣
“በጣም ከማርጀቴ በፊት ካለኝ ነገር ሁሉ የምትመርጡትን ላወርሳችሁ እፈልጋለሁና ምርጫችሁን አሳውቁኝ፡፡ በኋላ ግን የወረሳችሁትን ነገር የት እንዳደረሳችሁት ትነግሩኛላችሁ” ይላቸዋል፡፡የመጀመሪያው ልጅ፤“አባቴ ሆይ፤ ለእኔ ገንዘብ ስጠኝ፡፡ በሀገሬ ላይ ትልቁ ባለፀጋ ሰው ተብዬ መኖር ነው የሚያስደስተኝ፡፡ ከዚያ ሌላ ምንም የምጠይቅህ ነገር አይኖርም” ይላል፡፡

ንጉሡም፤ በርካታ ገንዘብ አውጥቶ ይሰጠዋል፡፡
ቀጥሎ ሁለተኛው ልጅ ወደ ንጉሡ ይቀርባል፡፡ እሱም፤
“አባቴ ሆይ፤ እኔ የምፈልገው ዕውቀት ነው፡፡ ያንን ከሰጠኸኝ በምንም በሌላ ነገር አላስቸግርህም፡፡ በሀገሬ ላይ ሊቅ ተብዬ እንደመኖር የሚያስደስተኝ ነገር የለም” ሲል ምርጫውን አሳወቀው፡፡
ንጉሡም ዕውቀት (ትምህርት) እንዲያገኝ ያደርገዋል፡፡ በመጨረሻ ሶስተኛው ልጅ ወደ ንጉሡ ይቀርብና፤
“አባቴ ሆይ፤ እኔ ሌላ ምንም የማስቸግርህ ነገር የለም፡፡ ጥበብ (wisdom) እንድትሰጠኝ ብቻ ነው የምፈልገው፡፡ ምክንያቱም ጥበብ ብስለትን፣ ልምድን፣ ዕድሜን፣ ብልሀትን… ሁሉ ያስጨብጠኛል” ሲል ይጠይቀዋል፡፡
ንጉሡም ልጁን ጠቢብ የሚያደርጉት ነገሮች ሁሉ እንዲሟሉለት ያደርጋል፡፡
ከዚህ በኋላ “በሉ በየፊናችሁ በሀገራችሁ ላይ የፈለጋችሁትን እያደረጋችሁ ኑሩ፡፡ አንድ ቀን እጎበኛችኋለሁ” ሲል ያሰናብታቸዋል፡፡
በጥቂት ዓመታት ውስጥ ሶስቱም ልጆች ዝናቸው የገነነ ሆነ፡፡
የመጀመሪያው ልጅ - ያ ሀብታሙ ሰውዬ፤ ያ ዲታው አለፈ ይባላል መንገድ ላይ ሲታይ፡፡ ይህ ልጅ በጣም ይዝናና ጀመር፡፡ ሁለተኛው ልጅ ያ ጢቅ ያለ ዕውቀት ያለው ምሁር አለፈ ይባላል፡፡ ቆይቶ ይህ ልጅ እጅግ ይኩራራ ጀመር፡፡ በሄደበት ሁሉ ስለምሁርነቱ ያወራል፡፡ ሶስተኛው ልጅ ጠቢቡ ሰውዬ መጣ ይባላል፡፡ በጣም ትሁት፣ በጣም አስተዋይ፣ በጣም ተወዳጅ ሆነ፡፡
ዓመታት እየገፉ ሲሄዱ ከዕለታት አንድ ቀን ንጉሡ ተራ በተራ ልጆቹን ሊያይ ከቤተ መንግሥቱ ወጥቶ ይመጣል፡፡ የመጀመሪያውን ልጅ ያገኘዋል፡፡ በጣም ተጎሰቋቁሏል፡፡
“እህስ ምን ደረስክ” ይለዋል ንጉሡ፡፡
ልጁም፤ “አባቴ ሆይ፤ የሰጠኸኝን ገንዘብ እየተዝናናሁ ጨረስኩት፡፡ አሁን ባዶ እጄን በመሆኔ አንተን ማስቸገር ስላፈርኩ ከሰዎች ልበደር ሞከርኩ፤ ማንም አልሰጥ አለኝ፡፡ ስለዚህ ለመስረቅ ሞከርኩ፡፡ ተይዤ ታሰርኩ፡፡ ሰሞኑን ነው የተፈታሁት” አለው፡፡
ንጉሡ ወደ ሁለተኛው ልጅ ይሄድና “አንተስ ምን ደረስክ?” ሲል ይጠይቀዋል፡፡
ሁለተኛው ልጅም፤
“በሰጠኸኝ ዕውቀት ዝነኛና ስመ-ጥር ለመሆን ችያለሁ፡፡ ነገር ግን ዕውቀቱን ምን አድርጌ ወደ ገንዘብ እንደምለውጠው ባለማወቄ ደህይቻለሁ፡፡ ወደ አንተም እንዳልመጣ ከዕውቀት ሌላ ምንም አልፈልግም ብዬሀለሁ፡፡ ወደ ሌሎች ሄጄ ገንዘብ ስጡኝ እንዳልል ‘ኩራትህ እራትህ ይሁንህ’ እያሉ ተሳለቁብኝ” ሲል ሁኔታውን አስረዳ፡፡
በመጨረሻ ንጉሡ ወደ ሶስተኛው ልጅ ይሄድና፤
“አንተስ እምን ደረስክ?” ይለዋል፡፡
ሦስተኛው ልጅም፤
“አባቴ ሆይ፤ በጣም አመሰግንሀለሁ፡፡ የሰጠኸኝ ጥበብ ብዙ ብልሀት አሳይቶኛል፡፡ ዕውቀት ስፈልግ ወደ ት/ቤት ገባሁኝ፡፡ ገንዘብ ስፈልግ ስራ ፈጠርኩኝ፡፡ ከሰዎች ለመኖር መልካም ስነ ምግባርን ያዝኩኝ፡፡ በጣም በደስታ ሀብት አፍርቼ እየኖርኩ ነው!” አለው፡፡
ንጉሡም፤
“እግዚሀር ይባርክህ! ባንተ ውስጥ ሶስት ልጆች አሉኝ - ገንዘብ፣ ዕውቀት እና ጥበብ፡፡ አገሬን ማስተዳደር ያለብህ አንተ ነህ፡፡ ስለዚህ መንግሥቴን አውርሼሀሉ!” ብሎ ዙፋኑን አስረከበው፡፡

* * *
ገንዘብ፣ ዕውቀትና ጥበብ ከተዋሃዱ ዕድገትን ማምጣት መቻላቸው አይጠረጠሬ ነው፡፡ የፋይናንስ ተቋማትን በዕውቀትና በጥበብ መምራት ከፍተኛ ክህሎትን ይጠይቃል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ስርቆትንና ኢ-ተዓማኒነትን ለማስወገድ የራስን እጅ ፅዳት ይፈልጋል፡፡ እጅን መታጠብ ግን እንደ ጲላጦስ ከደሙ ንፁህ ነኝ ማለት አይደለም፡፡ ንፁህነትን በተግባር ማረጋገጥ እንጂ፡፡ ተቃዋሚዎቻችንን በብልሃትና ብልጫን በማሳየት እንጂ በሌላ ጉልበታዊ መንገድ እናሸንፍ ካልን የሁልጊዜና የሚያዋጣ መንገድ ይዘናል ለማለት አያስደፍርም፡፡
“በዙሪያችን ባላንጣዎች ከሌሉን ሰነፍ እንሆናለን” ይላሉ ፀሀፍት፡፡ ምቀኛ አታሳጣኝ የሚለው ነው አበሻ፡፡ የተቃዋሚዎች መኖር፤ የዲሞክራሲ መኖር ማረጋገጫ ነው የሚሉትም ለዚሁ ነው፡፡ ሞኝ ከጓደኞቹ ከሚያገኘው ይልቅ ብልጥ ከጠላቶቹ የሚያተርፈው ይበልጣል - ዋናው ከብልጥነት ይልቅ ብልህነት ላይ ማተኮር ነው፡፡
ከቮልቴር ጋር:-
“አምላኬ ሆይ!” ከወዳጆቼ ጠብቀኝ፡፡ ከጠላቶቼ እኔ ራሴን እጠብቃለሁ” ማለትንም አለመርሳት ነው፡፡
በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ ተፎካካሪን እንደ ጠላት ማየት ዓይነተኛ አመለካከት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ በእርግጥ ጤናማ ተፎካካሪነትም ገና በእንጭጩ ያለና አነጋጋሪ ተግባር ነው፡፡ የት ድረስ በጋራ እንጓዛለን፤ የት ድረስስ በየግል ተለይተን እንሄዳለን ብሎ መጠየቅና መስመሮቹን በቁጥር ማስመር የፖለቲካ ብልህነት ማስረገጫ ነው፡፡ “እኔ ብቻዬን ያልቃኘሁት ክራር ዘፈን አይሆንም” ብሎ ማሰብም ሆነ “እኛ ከሌለንበት ምንም ነገር ትክክል አይሆንም፡፡ የሚለው እሳቤ አገር አያለማም፡፡ ይህንን እሳቤ መገላገልም መስዋዕትነትና የፖለቲካ ብልህነት ይጠይቃል፡፡
ጥበብን መካንና ብልህነትን ማወቅ በፖለቲካም፣ በዲፕሎማሲም ውስጥ የረቀቀ ቦታ ያለው ፍሬ ጉዳይ ነው፡፡
አብርሃም ሊንከለን በአሜሪካው የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት ባደረገው ንግግር፤ ደቡቦቹ ተሳስተው ነው እንጂ ወንድሞቻችን ናቸው የሚል አመለካከት ነበረው፡፡ ታዲያ አንዲት አሮጊት “የማንታረቃቸው ጠላቶች ናቸውና መደምሰስ አለባቸው” ማለት ነበረብህ ስትል ትወቅሰዋለች፡፡ “የለም እመቤቴ” አለ ሊንከለን፣ “ጠላቶቼን ወዳጅ ሳደርጋቸው ደመሰስኳቸው ማለት አይደለምን?” ሲል አንድምታውን በጥያቄ ደምድሟል፡፡ እንኳንስ የፖለቲካ ተፎካካሪን ጠላትንም መርታት የሚቻልባቸው ብልሃቶች እንዳሉ የሚያመላክቱን ብዙ ታሪካዊ አስተምህሮቶች እንዳሉ ልብ እንበል፡፡
ጊዜ ሳያልፍ ቀና ቀናውን በማሰብ አገርን ከድህነት፣ ከብዝበዛ፣ ከኢፍትሃዊነት፣ ከማንአለብኝነት፣ ከግብዝነትና ከምሁራዊ - ተዓብዮ መገላገል አለብን፡፡ “የተወሰደብንን ቦታ ማስመለስ እንችላለን፤ የጠፋብንን ጊዜ ግን መመለስ አንችልም” ይለናል ናፖሊዮን ቦናፖርት፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ወዳጁ የነበረን ሰው በድንገት ያገኘ ንጉሥ ምን እንዳለው እንይ፡፡ “አስታወስከኝ ወይ ንጉሥ ሆይ፤ የዱሮ ጓደኛህ ነኝኮ?” ይለዋል ወዳጁ፤ ንጉሡ “እውነት ነው ጓደኞች ነበርን፡፡ ያ ጓደኝነታችን ግን የተመሠረተው በነበረን ሥልጣን ላይ ነበር… ለዓላማዬ፣ ለጥቅሜ ስል ነበር የተወዳጀሁህ፡፡ እንጂ ማንም መናጢ ደሀ የሀብታም ጓደኛ አይሆንም፡፡ ማንም ጅል የብልጥ ጓደኛ አይሆንም፡፡ ማንም ፈሪ የጀግና ጓደኛ ሊሆን አይችልም” ብሎታል፡፡ ጊዜና ሁኔታ ባላንጦችን ባንድ አልጋ ሊያስተኛ እንደሚችል (Strange Bed-fellows) እንዲሉ ታሪክ ይነግረናል፡፡ ለአገር ሲባል የማይቆራኙ ሲቆራኙ፣ የማይወዳጁ ሊወዳጁ ይችላሉ እንደ ማለት ነው፡፡ ዋናው ሀብትን መምራት፣ ዕውቀትን ማዳረስና በጥበብ ላይ የተመሠረተን ዕሳቤ ማዕከል ማድረግ ነው፡፡
ሌላው ዋንኛ ጠላታችን ቂምና በቀል ነው፡፡ “ሰዎች ውለታን ከመክፈል ይልቅ ያቆሰላቸውን መበቀልን ይወዳሉ፡፡ ምክንያቱም ማመስገን ሸክም ነው፡፡ በቀል ግን መደሰቻ ነው” ይለናል ታኪታስ የተባለው ፈላስፋ፡፡ መልካም ለሠራ ማንም ይሁን ማን ምስጋናን መስጠት መልመድ አለብን፡፡ አዎንታዊና ተመስጋኝ ማህበረሰብ ለመገንባት መጣር ይኖርብናል፡፡ (Positivist and meritorious እንዲሉ) ከመቋሰልና ከመጠላለፍ የፀዳ የፖለቲካ አካሄድ ለማሰልጠን፤ ሌላውን ለመተንኮስ ለማናደድ፣ አንጀቱን ለማሳረር ከሚል እሳቤ ነፃ መንገድን ለመቀየስ፤ “ላናድህ ያለ እሳት ሲጭር፣ እሳት ፍለጋ አትሂድ፡፡ ማገዶውን አርጥብ” የሚለውን ተረት እናስታውስ፡፡ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ንጉሥ ሶስት ልጆቹን ጠርቶ፣
“በጣም ከማርጀቴ በፊት ካለኝ ነገር ሁሉ የምትመርጡትን ላወርሳችሁ እፈልጋለሁና ምርጫችሁን አሳውቁኝ፡፡ በኋላ ግን የወረሳችሁትን ነገር የት እንዳደረሳችሁት ትነግሩኛላችሁ” ይላቸዋል፡፡
የመጀመሪያው ልጅ፤
“አባቴ ሆይ፤ ለእኔ ገንዘብ ስጠኝ፡፡ በሀገሬ ላይ ትልቁ ባለፀጋ ሰው ተብዬ መኖር ነው የሚያስደስተኝ፡፡ ከዚያ ሌላ ምንም የምጠይቅህ ነገር አይኖርም” ይላል፡፡

ሌላው ዋንኛ ጠላታችን ቂምና በቀል ነው፡፡ “ሰዎች ውለታን ከመክፈል ይልቅ ያቆሰላቸውን መበቀልን ይወዳሉ፡፡ ምክንያቱም ማመስገን ሸክም ነው፡፡ በቀል ግን መደሰቻ ነው” ይለናል ታኪታስ የተባለው ፈላስፋ፡፡ መልካም ለሠራ ማንም ይሁን ማን ምስጋናን መስጠት መልመድ አለብን፡፡ አዎንታዊና ተመስጋኝ ማህበረሰብ ለመገንባት መጣር ይኖርብናል፡፡ (Positivist and meritorious እንዲሉ) ከመቋሰልና ከመጠላለፍ የፀዳ የፖለቲካ አካሄድ ለማሰልጠን፤ ሌላውን ለመተንኮስ ለማናደድ፣ አንጀቱን ለማሳረር ከሚል እሳቤ ነፃ መንገድን ለመቀየስ፤ “ላናድህ ያለ እሳት ሲጭር፣ እሳት ፍለጋ አትሂድ፡፡ ማገዶውን አርጥብ” የሚለውን ተረት እናስታውስ፡፡

Read 4613 times Last modified on Saturday, 12 November 2011 08:22