Saturday, 09 March 2013 11:06

የአረጋውያን የአዕምሮ ሕሙማን ማዕከል 500ሺ ብር አገኘ

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ሳምንት እሁድ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን ማዕከል በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም 510ሺህ ብር መገኘቱን ድርጅቱ አስታወቀ፡፡ የኤግዚቢሽን ማዕከል ግቢውን ከነአዳራሹ በነፃ እንድንጠቀም በማድረጉ እናመሰግናለን ያሉት የማዕከሉ መስራች አቶ ቢኒያም በቀለ የቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ ክቡር አቶ ብርሃነ ዴሬሳ በ10ሺህ ብር፣ አቢሲኒያ ዱቄት ፋብሪካ ደግሞ 104ሺህ ብር እንዳበረከቱ ተገልጿል፡፡ ከስፖንሰር ሺፕ 180ሺህ ብር፣ ከቲኬት ሽያጭ 120ሺህ ብር፣ ከጨረታ 50ሺህ ብር፣ በጥሬ ገንዘብና ቃል የተገባ 160ሺህ ብር በአጠቃላይ 510ሺህ ብር መገኘቱን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ የዕለቱ ፌስቲቫል የተሳካ እንዲሆን አዲካ፣ ቢጂ አይ (ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ)፣ ሞሃ ለስላሳ ፋብሪካ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ፣ ሴፍዌይ ሱፐርማርኬት፣ ዲ ኤች ገዳ ፋብሪካ፣ ብሔራዊ አረቄ ፋብሪካና ሌሎችም ስፖንሰር ማድረጋቸውም ተጠቅሷል፡፡

Read 2370 times