Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Monday, 07 November 2011 13:22

የድሪምዎርክስ ፊልሞች ገበያውን ተቆጣጠሩ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በድሪምዎርክስ የተሰሩት “ፑስ ኢን ዘ ቡትስ” በሰሜን አሜሪካ፤ ስቴቨን ስፒልበርግ ዲያሬክት ያደረገው “ዘ አድቬንቸር ኦፍ ቲን ቲን” በመላው ዓለም በሳምንታዊ ገቢያቸው የቦክስ ኦፊስ ደረጃን እየመሩ ነው፡፡ በ130 ሚሊዮን ዶላር በጀት በዲጅታል 3ዲ የተሰራው “ፑስ ኢን ዘ ቡትስ” በታዋቂው የሽሬክ ፊልም ላይ ያለውን የድመት ገፀባህርይ ፕስ መሪ ተዋናይ አድርጓል፡፡ በኮምፒውተር አኒሜሽን የተፈረጀው ፊልሙን በድምፅ መሪ ተዋናይ ሆኖ አንቶኒዮ ባንደራስ ሰርቶታል፡፡ ሳልማ ሃይክ፤ ዛክ ጋልፊናኪስና ቢሊ ቦብ ቶርተንም ተሳትፈውበታል፡ ፑስ የተባለው ድመት በሽሬክ ፊልም ላይ ከሽሬክና ከዶንኪ ጋር ከመገናኘቱ በፊት በነበረው ጀብደኛ ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን ታሪክ ይዟል፡፡

ፑስ በሽሬክ ፊልሞች ከ2ኛው ክፍል ጀምሮ እየሰራ ያለና የመስከቲርስ ባህርይ ያለው ጀብደኛ ገፀባህርይ ነው፡፡ ሰሞኑን በሰሜን አሜሪካ 35 ሚሊዮን ዶላር ያስገባው “ፑስ ኢን ዘቡትስ” ቦክስ ኦፊስን የመራ የመጀመርያው የአኒሜሽን ፊልም ሆኗል፡፡  
ሌላው የድሪምዎርክስ ፊልም በስቲቨን ስፒልበርግ የተሰራው “ዘ አድቬንቸርስ ኦፍ ቲንቲን፡ ዘ ሴክሪት ኦፍ ዩኒኮርን” ሲሆን ባለፈው ሰሞን በመላውዓለም ሲታይ 56 ሚሊዮን ዶላር አስገብቶ የቦክስኦፊስን የሳምንታዊ ገቢ ደረጃ በበላይነት መርቷል፡፡ ስቴቨን ስፒልበርግ ዘንድሮ በሰበሰበው 107 ሚሊዮን ዶላር 
ከፍተኛ ገቢ ያገኘ የሆሊውድ ዲያሬክተር ሆኗል፡፡ በ175 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተሰራው ፊልሙ ለፕሮሞሽንና ለሌሎች 100 ሚሊዮን ዶላር የወጣበት ሲሆን ገቢው 500 ሚሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ተገምቷል፡፡

 

Read 3191 times Last modified on Monday, 07 November 2011 13:28

Latest from