Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 19 November 2011 14:37

ቢሊ ክሪስታል የኦስካር ምሽትን ለ9ኛ ጊዜ ይመራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ2012 መግቢያ ላይ የሚካሄደውን የኦስካር ምሽትን እንዲያስተናብር የ63 ዓመቱ ቢሊ ክሪስታል መሾሙ ታወቀ፡፡ ቢሊ ክሪስታል የኦስካር አስተናጋጅ ሆኖ ሲሾም ዘንድሮ 9ኛው ነው፡፡ በ2012 መግቢያ ላይ የሚዘጋጀው 84ኛው የኦስካር ሽልማት ስነስርዓት በአስተናባሪው ኤዲ መርፊና በፕሮዲውሰሩ ከሃላፊነት መልቀቅ ጋር በተያያዘ በገቢው ላይ መቀዛቀዝ እንደተፈጠረበት ያወሳው ኒውዮርክ ታይምስ ደግሞ በማስታወቂያ ዋጋው ላይ ከዓምናው በ25 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን ገልጿል፡፡ የኦስካር ምሽትን በቀጥታ የማሰራጨት መበት ያለው ኤቢሲ ጣቢያ ለ30 ሰከንድ ማስታወቂያ 1.7 ሚሊዮን ዶላር ይጠይቃል፡፡ ባለፈው ዓመት “ዘኪንግ ስፒች” የተባለው ፊልም ትልቁን የኦስካር ሽልማት የወሰደበትን ምሽት በአሜሪካ ብቻ 41.7 ሚሊዮን ተመልካች ታድሞታል፡፡ አንድ የኦስካር ምሽት በቴሌቭዠን ስርጭቱ በሚያገኘው ትኩረት ከማስታወቂያው ብቻ እስከ 90 ሚሊዮን ዶላር ይገኝበታል፡፡

Read 3998 times Last modified on Saturday, 19 November 2011 14:39