ከሆሊውድ ፊልም ሰሪ ኩባንያዎች በዘንድሮው የዓለም ገበያ 19.2 በመቶ ድርሻ በመያዝ በአድቬንቸር ፊልሞቹ ስኬታማ የሆነው ፓርማውንት ፒክቸርስ እንደሚመራ ያመለከተው ቦክስ ኦፊስ ሞጆ በ2011 የወጡ ፊልሞች አጠቃላይ ገቢ 8.57 ቢሊዮን መድረሱን አመልክቷል፡፡ ዋርነር ብሮስ 17.8 ፤ቡዌና ቪስታ 13.2 ፤ሶኒና ኮሎምቢያ 12.7 እንዲሁም ዩኒቨርሳል ፒክቸርስ 11.5 በመቶ የገበያ ድርሻ ኖሯቸው እስከ 5 ያለውን ተከታታይ ደረጃ አግኝተዋል፡፡ ዘንድሮ 19 ፊልሞችን በዓለም ዙርያ ለእይታ ያበቃው ፕርማውንት ፒክቸርስ ገቢው 1.56 ቢሊዮን ዶላር ተመዝግቧል፡፡በሆሊውድ ፊልም ሰሪ ኩባንያዎች በዓመቱ የተሰሩ ፊልሞች 1.05 ሚሊዮን ትኬቶች በ7.97 ዶላር አማካይ ዋጋ እንደተሸጠላቸው ያሳየው የቦክስኦፊስ ሞጆ መረጃ ከዓመቱ ጠቅላላ ገቢ 34 የአድቬንቸር ፊልሞች 2.05 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማስመዝገብ ከፍተኛውን ድርሻ መያዛቸውን ጠቅሷል፡፡