Saturday, 05 October 2013 10:49

በአፍሪካ ያሉ እናቶችን ጤና ለማሻሻል …”

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ (ከኢሶግ)
Rate this item
(0 votes)

በአለምአቀፍ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ፌደሬሽን FIGO የአፍሪካ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ፌደሬሽን AFOG የመጀመሪያው አህጉራዊ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡

ረቡእ እ.ኤ.አ/ October 2/መስከረም 22/2013 የተጀመረው የፊጎ አፍሪካ አህጉራዊ ስብሰባ ለአራት ቀናት ያህል በተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረቱን በማድረግ ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 25/2013 ተጠናቆአል ፡፡ 

የፊጎ አለም አቀፍ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ስለስብስባው መጀመር በሰጡት መግለጫ .....በአፍሪካ ያሉ እናቶችን ጤና ለማሻሻል እንዲረዳ የአፍሪካ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ፌደሬሽን በመቋቋሙ አድናቆት አለኝ፡፡ አፍሪካ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የጤና መጉዋደል አሉባቸው ከሚባሉ ሀገራት አንዱዋ ናት፡፡ የአፍሪካ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ፌደሬሽን አባላት የሆኑ ሀገራት ባለሙያዎች በተቻለ መጠን በየሀገሮቻቸው ያሉትን እናቶች ጤንነት ለማሻሻል ጥረት በማድረግ ላይ ቢሆኑም ብዙ ሀገራት ያሉትን የጤና ችግሮች ለመፍታት እንደሚቸገሩ ግልጽ ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም የታቀፉ አባል ሀገራት ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ልምዳቸውን ለሌሎች እንደሚያካፍሉ እሙን ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ልንመለከታቸው የሚገቡ ችግሮች አሉ፡፡ እነርሱም...
እንዴት ጤናማ የሆነ የሕይወት ዘመንን እውን ማድረግና ድክመትን መቀነስ እንደሚቻል?
ህመምተኞች ለራሳቸው የሚሰጡትን ግምት ከማሳደግ አንጻር ታካሚን ማእከል ያደረገ አገልግሎት እንዴት መስጠት እንደሚቻል እና እርካታን እንዲያገኙ ማድረግን፣
የህክምና ባለሙያዎች ሕጋዊ በሆነ መንገድ እና የሙያው ስነምግባር በሚፈቅደው መሰረት መስራት የሚችሉበትን ማመቻቸት...ወዘተ/
ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የአፍሪካ የጽንስና ማህጸን ሕክምና ባለሙያዎች ፌደሬሽን ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል የሚል እምነት አለኝ። ብለዋል የአለምአቀፉ የጽንስና ማህጸን ሕክምና ባለሙያዎች ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት፡፡
ፕሮፌሰር ይርጉ ገ/ሕይወት የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ፋክልቲ መምህር እና የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ባወጡት መግለጫ፡-
“…የፊጎ አፍሪካ የመጀመሪያው አህጉራዊ ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄዱ በቅድሚያ በመላው የአገሪቱ ሕዝብ ስም ደስታዬን መግለጽ እወዳለሁ፡፡ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካም ዋና ከተማ ናት፡፡ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ላለፉት 3ሺህ/ዘመናት በነጻነት የኖረች እንዲሁም ለጥንታዊ ስልጣኔና ለሰው ዘር መገኛ ነች፡፡ ተፈጥሮአዊውን ቅርስ በሚመለከትም ከ3.2 ሚሊዮን አመታት በላይ የሆናት እና የሰው ልጅ እናት የሚል ስያሜ የተሰጣት ሉሲ የተገኘችው በኢትዮጵያ ነው፡፡ ኢት ዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ላለፈው አስር አመት ቀጣይ የሆነ የኢኮኖሚ እድገት በማሳ የት ላይ ያለች አገር ነች፡፡ ኢትዮጵያ የፊጎ አፍሪካን የመጀመሪያ አህጉራዊ ስብሰባ በማድረግዋ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል... ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት የምእተ አመቱን የልማት ግብ ከማሳካት አንጻር ያልተሟሉ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ግልጽ ነው፡፡ በእነዚሁ አገራት የእናቶችንና የህጻናቱን ጤንነት በማሻሻል ረገድ በ2015/ እንዲ ደርስ ከሚጠበቅበት ደረጃ ለማድረስ ጥንቃቄና ጥራት የተሞላበት ስራ መስራት አስፈላጊ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ይህ በኢትዮጵያ የተካሄደው የፊጎ አፍሪካ አህጉራዊ ኮንፍረንስ በአ ፍሪካ ባሉ የጋራ ችግሮች ላይ ለመነጋገር የሚያስችል የተለየ መድረክ በመሆኑ ባለሙያ ዎች አስተሳሰባቸውን አቀናጅተው የጋራ መፍትሄ ሊያመጡ የሚችሉበትን እድል ይፈጥ ራል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከሌሎች የአለም ክፍሎች ተወክለው በስብሰባው ከሚሳተፉት ልምድን ለመቅሰም እና የነበረውን አሰራር ለማሻሻል የሚያስችል እድልን ለአፍሪካ የጽን ስና ማህጸን ሐኪሞች ፌደሬሽን አባል አገራት ይፈጥራል የሚል እምነት አለኝ... ብለዋል ፕሮ/ይርጉ ገ/ሕይወት፡፡
በመጀመሪያው የፊጎ አፍሪካ አህጉራዊ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት አንግዶች ወደ 715/ሰባት መቶ አስራ አምስት የሚገመት ሲሆን ተሳታፊዎችን የላኩ ሀገራት ብዛት 67/ስድሳ ሰባት ናቸው። ከነዚህ ሀገራት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተሰብሳቢዎች የላከች ሀገር ናይጄሪያ ናት፡፡
በመጀመሪያው እለት ረቡእ መስከረም 22/2013 ስብሰባው ከመከፈቱ በፊት በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ አውደጥናቶች የተካሄዱ ሲሆን ስፍራውም በሂልተን ሆል ፣በጥቁር አንበሳና በጳዎሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ነበር፡፡ በአውደጥናቶቹ ላይ ከተለያዩ ሐገራት የመጡ እንግዶችም ተሳትፈዋል፡፡ እስከቅዳሜ የቆየው ስብሰባ መጀመሩ ይፋ የሆነው ረቡእ ከምሽቱ 12፡30 ነበር፡፡

Read 2052 times