Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 17 December 2011 08:10

ሰው ይጫኑብህ ግንድ ቢሉት፤ ግንድ ከተጫነኝ ሰው ያነሳልኛል ሰው ከተጫነኝ ግን ማን ያነሳልኛ፤ አለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“ደህና ነን እናንተስ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ከጫካ እኛ የምንኖርበት ድረስ እንዴት መጣችሁ? ምን እግር ጣላችሁ?” ሲሉ ይጠይቃሉ ውሾች፤ በጥርጣሬ መንፈስ፡፡

ተኩላዎቹም፤
“አመጣጣችን ግር ቢላችሁ አይገርምም፡፡ ሠፈራችንም አኗኗራችንም የተለያየ ስለሆነ ነው፡፡ ሆኖም ዛሬ እዚህ የተገኘነው ለእኛም ለእናንተም የጋራ ጥቅም ስንል ነው”
ውሾቹም፤ ትንሽ በመረጋጋት ስሜት፤
“የጋራ ጥቅም ማለት ምንድን ነው?” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ከተኩላዎቹ አንደበተ-ቀና የሆነው ጮሌ እንዲህ ይላል፡፡ “በመጀመሪያ እኛና እናንተ ለምን እንደጠላት እንተያያለን? በደንብ አስተውላችሁ ካያችሁ ከአካላዊ አቋማችን ጀምሮ ብዙ የሚያመሳስሉን ነገሮች አሉን፡፡ በእኛ መካከል ያለ አንድ ልዩነት የሥልጠና ልዩነት ነው፡፡ በህይወት ያለን ልምድም የተለያየ መሆኑ ነው፡፡”
ውሾቹ የበለጠ ለማወቅና ለመመካከር ዝግጁ እየሆነ መጡ፡፡
“የኑሮና የሥልጠና ልምዳችሁ ምንድን ይመስላል?” ሲሉ ተኩላዎችን ጠየቁ፡፡
አንደበተ - ቀናው ተኩላም፤ “መልካም፡፡ እናስረዳችኋለን፡፡ ዋናው ግልፅ ሆነን መረዳዳት ነው፡፡ አያችሁ እኛ በዱር ውስጥ በነፃነት የምንኖር ነን፡፡ እንደልባችን እንንሸራሸራለን፡፡ እንደልባችን እንበላለን፡፡ እንደልባችን እናመሻለን፡፡ አገር-ምድሩ የእኛ ነው፡፡ እናንተስ? እናንተ የሰው ባሪያ ናችሁ፡፡ የምትኖሩት የሰው እጅ እያያችሁ ነው፡፡ እንደፈለገ ይደበድባችኋል፡፡ ይቀጠቅጣችኋል፡፡ አንገታችሁ ላይ ሠንሠለት አሥሮ የፈለገው ቦታ ያስቀምጣችኋል፡፡ ሲፈልግ ደግሞ ሳጥን ውስጥ ይቆልፍባችኋል፡፡ ከብትና መንጋ እንድትጠብቁ ያስገድዳችኋል፡፡ እንቅልፋችሁን አሳጥቶ ከሌባ ጋር እንድትታገሉ ያደርጋችኋል፡፡ እሱ ለጥ ብሎ የሞቀ አልጋ ላይ ይተኛል፡፡ እናንተ ብርድ ይፈደፍዳችኋል፡፡ ድንገት ሌባው አምልጦ አንድ ነገር ቢሰረቅ የእሱ ማንቀላፋት ሳይሆን የእናንተ ንዝህላልነት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ይሄን ሁሉ ውለታ እየሰራችሁ የሚሰጣችሁ ምንድን ነው? ከሱ የተረፈ የተጋጠ አንጥት! ከእንግዲህ ይሄ አኗኗር ማክተም አለበት፡፡ በቃችሁ፡፡ መንጋዎቹን ለእኛ አሳልፋችሁ ስጡን፡፡ ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ፡፡ ምድሩን እንቆጣጠረዋለን፡፡ አጥንት ሳይሆን ጮማ ትበላላችሁ፡፡ ወተት ትጠጣላችሁ ዋናው ነገር እናንተ ከእኛ ጋር ሁኑ፡፡ እኛ የምንላችሁን ብቻ ፈፅሙ! ዓለም በሙሉ የእኛና የእናንተ ብቻ ትሆናለች፡፡ ሰው በሰፈረው ቁና ይሰፈራል!”
ውሾቹ በንግግሩ ተማርከው አጨበጨቡ! የተለየ ዓለም ውስጥ ሲኖሩ ካሁኑ ታያቸው! ወደ ተኩላዎቹ ጎሬ ሄደው የተኩላዎቹን ኑሮ ለመኖር ተስማሙ፡፡ ተያይዘው ወደ ዱር ሄዱ፡፡ ተያይዘው ወደ ጎሬው ገቡ፡፡ ውሾቹ ገና ጎሬው ውስጥ ገብተው አረፍ አረፍ ብለው መኖሪያውን አድንቀው ሳያበቁ ተኩላዎች እየዘለሉ ሰፈሩባቸው! ቦጫጭቀው ተቀራመቷቸው፡፡

“ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ” ማለት ይሄ ነው፡፡ ለጋራ ጥቅማችን ብሎ ለራሱ ከሚጠቀምብን ያድነን፡፡ ከሃዲዎች የዕጣ-ፈንታቸዉን ያገኛሉ” ይለናል ኤዞፕ፡፡ ታዋቂው ፀሐፌ-ተውኔትና ገጣሚ ፀጋዬ ገ/መድህን ደግሞ፤
“…እኛማ መቼ ሰው ፈጠርን፣ ከብት እንጂ መንጋና ጌኛ
እንደ ወዶ-ገባ ኮርማ
ተነስ ሲሉት የሚነሳ፣ ተኛ ሲሉት የሚተኛ …” ይለናል፡፡ ዞሮ ዞሮ ወዶ-ገባ ያሉትን መፈፀም ግዴታው ነው፡፡ ወዶ-ገባ ዝርያው ብዙ ነው፡፡ የፖለቲካ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ፖለቲካው ምንም ይሁን ምንም ለጥቅሜ እገባበታለሁ ይላል፡፡ የኢኮኖሚ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ኢኮኖሚው ምንም ይሁን ምን ሆዴን እሞላበታለሁ ይላል፡፡ የማህበራዊ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ከማናቸውም ማህበራዊ ቀውስ እኔ ጥቅሜን ካካበትኩ ያሉኝን አደርጋለሁ ባይ ነው፡፡ ብልህ ሰው የውሾቹን ዓይነት ዕጣ-ፈንታ ያስተውላል፡፡ አበሻ፤ “አብዶም ሠግዶም ውሉን አይስትም” የሚል አባባል አለው፡፡ ይሄንንም ልብ-ልንበል፤ የህግ-ወዶ-ገባም አለ፡፡  በፍትሕ ሽፋን ጥቅሙን የማያጋብስ፡፡
አንድ የሮማውያን ጭቅጭቅ ተብሎ የሚጠቀስ ወግ አለ፡፡ በጌታ ሥቅለት ወቅት “እኛ ድንጋይ ነው ያቀበልነው” ይላሉ አንደኛዎቹ ወገኖች፡፡ ሌላኞቹ ወገኖች ደግሞ “እኛ ሚሥማር ነው ያቀበልነው” ይላሉ፡፡ ማን የበለጠ ጥፋት ሠርቷል ዓይነት ነው፡፡ ዋናው ነጥብ ግን “ጌታ ተሰቅሏል” አገርን የሚያጠፋ ማንኛውም ጥፋት ጥፋት ነው፡፡ ሚሥማርም አቀበልን ድንጋይ ያው ነው፡፡ በወገናዊነት ላንድ ቡድን መጠቀሚያ አመቻቸንም፣ በሙስና ውስጥ ተዘፈቅንም፤ ዞሮ ዞሮ “ጌታ ተሰቅሏል”፡፡ አገርና ህዝብ በድለናል፡፡ እገሌ አድርግ ብሎኝ ነው እንጂ እኔ በራሴ አላደርገውም ነበር ማለት የኋላ ኋላ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ በሥርዓቱም ማሳሰብ በግልና በቡድን ከሠራነውና አንዱን የእናት ልጅ፣ አንዱን የእንጀራ ልጅ አድርገን ካጠፋነው ጥፋት ተጠያቂነት አያድንም፡፡ አንድ ፀሐፊ እንዳለው “በካፒታሊዝም ሰው ሰውን ይበዘብዛል፡፡ በኮሙኒዝም ደግም ተበዝባዡ በዝባዡን ይብዘብዛል” ይለናል፡፡ ዞሮ ዞሮ ሰው ሰውን መበዝበዙ ነው ሀቁ፡፡ ፊት ለፊቱም ግልባጩም ያው ነው እንደ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሥርዓት ሰበብ አይሆንም፡፡ ዕውነቱ ሰው ሰውን መበዝበዙ ነው፡፡ ሊበራል፣ ኒዮ ሊበራል፣ አብዮታዊ፣ ኮሙኒስታዊ፣ ፋሽስታዊ፣ ቦናፓርቲዝማዊ፣ ልማታዊ፣ ሉአላዊ፣ ፀረ-ሽብራዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ኢጋዳዊ፣ … ሁሉም የሰውና ሰው ተቃርኖና ፍጭት መልኮች ናቸው፡፡ ዋናው ከህዝብና ከሀገር ጥቅም አኳያ ምን ይመስላሉ ተብሎ መመርመር ያለባቸው ናቸው፡፡ የሰውና ሰው ግንኙነት የጨቋኝና ተጨቋኝ፣ የወገናዊና ኢወገናዊ፣ የፍትሐዊና ኢፍትሐዊ፣ ወይስ ቡድናዊና ኢቡድናዊ? ምን ይመስላል፡፡ የሳንቲሙ ገፅ ምን ዓይነት ነው? ዘውድ? ጎፈር? ወይም በሠያፍ የቆመ? መፈተሽ አለበት፡፡ አንዱ ለአመራሩ ሚሥጥር ቅርብ በመሆኑ አስቀድሞ ኢንፎርሜሽን ያገኛል፡፡ ቤቱን ከውርስ ያድናል፡፡ ሌላው ለኢንፎርሜሽኑ እሩቅ ነውና ላዩ ላይ ይታወጅበታል፡፡ ለብዙሃኑ ጥቅም ሲባል ጥቂቶቹ ቢጎዱም ምንም አይደለም የሚለውም አስተሳሰብ መመርመር ይኖርበታል፡፡ የአብዮቱ ጦስ ይሁን የካፒታሊዝም ጦስ ባልለየበት አገር አዋጆችና መመሪያዎች ሲከለሱ ማየት ቢያንስ ያስገርማል፡፡ አቀንቃኙ (Protagonist) እና ተቃራኙ (antagonist) በቀላሉ አይለዩም፡፡ ቴያትሩ ይቀጥላል፡፡ “የማታ ማታ መጋረጃው ሲዘጋ መልበሻ ክፍል ይገናኛሉ” እንደሚባሉት ተዋንያን ይሆናሉ፡፡ “በአደባባይ ይሰዳደባሉ እንሰት ጓሮ ይታረቃሉ” እንደሚባለው የጉራጊኛ ተረት መሆኑ ነው፡፡ አንዳንዴ ከሥልጣን ይባረራሉ፡፡ ተባራሪዎቹ ያወጡት ህግና መመሪያ ምን እንደሚሆን ዕጣ-ፈንታው አይታወቅም፡፡ ከሁሉም ይሰውረን! ህዝብ ብቻ ግራ እንደተጋባ ይቀጥላል፡፡ “ሰው ይጫኑብህ ግንድ? ቢሉት፤ ግንድ ከተጫነኝ ሰው ያነሳልኛል፣ ሰው ከተጫነኝ ማን ያነሳልኛል፤ አለ” የሚባለው ግራ-ገብ ዘመንን የሚያመላክተን ነው፡፡ ከዚህም ይሰውረን! ከሚጫነን ይገላግለን፡፡ ከወዶ-ገባነት ይቅር ይበለን!!

ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላዎች ወደ ውሾች ዘንድ ይመጣሉ አሉ፡፡ “እንደምን ከርማችኋል?” ይላሉ ተኩላዎቹ፡፡

  • 

Read 4089 times Last modified on Saturday, 17 December 2011 08:18

Latest from