Saturday, 10 May 2014 12:34

በህክምናና በመድሃኒት ዘርፍ ላይ የሚሰራ ጀርመናዊ ድርጅት በኢትዮጵያ ሥራ ጀመረ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ህገወጥ መድሃኒቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሣሪያ ለጤና ጥበቃ ሚ/ር አበርክቷል
በህክምና፣ በመድሃኒትና በኬሚካል ዘርፍ አዳዲስ ምርቶችን በማቅረብ የሚታወቀውና ዋና መ/ቤቱ በጀርመን አገር የሆነው መርክ የተሰኘው ድርጅት በኢትዮጵያ ሥራ ጀመ፡፡ ይህ በአዲስ አበባ ከተማ የተከፈተው አዲስ ድርጅት ሱዳንን፣ ኢትዮጵያንና ፈረንሳይኛ ተናጋሪ የሆኑ የአፍሪካ አገሮችን የሚየገለግልና በቀጠናው የመጀመሪያው ማዕከል ነው ተብሏል፡፡
ድርጅቱ በትሮፒካል አካባቢዎች እምብዛም ትኩረት ባልተሰጣቸውና እንደ ቢልሀርዚያ ያሉ አደገኛ በሽታዎችን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም የድርጅቱ ሃላፊዎች ከትናንት በስቲያ በሸራተን አዲስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል፡፡
ድርጅቱ በመሠረተው የዓለም አቀፍ ፋርማ ሄልዝ ፈንድ ፕሮግራም ስር ሁለት አነስተኛ ላብራቶሪዎች ለጤና ጥበቃ ሚ/ር ያበረከተ ሲሆን መሣሪያዎቹ ህገወጥና የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ መድሃኒቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡
መርክ በጀርመን አገር በ1968 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰራ በህክምና፣ በመድሃኒትና በኬሚካል ዘርፍ የተሰማራ አንጋፋ ኩባንያ ነው፡፡

Read 3101 times