Monday, 19 May 2014 07:51

የዘመናችን “ሚዳስ” - ዋረን ቡፌት

Written by 
Rate this item
(0 votes)

         የ80 ትልልቅ ድርጅቶች ባለቤት የሆነውና በግዙፍነቱ ከአለም አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው BERKSHIRE HATHAWAY ለዚህ ማዕረግ የበቃው በዋረን ቡፌት ነው። የዛሬ ሃምሳ አመት፤ አንድ ሰው የኩባንያውን አንድ አክስዮን በ10 ዶላር ቢገዛ፤ በየአመቱ አንድ ዶላር ትርፍ ይደርሰው ይሆናል። ነገር ግን፤ ኩባንያው በከፍተኛ ፍጥነት ስላደገ፣ የአክስዮኑ ዋጋ ዛሬ 170ሺ ዶላር ገደማ ይደርስለታል። አስሯን ዶላር በሃምሳ አመት ውስጥ ወደ 170 ሺ ዶላር መለወጥ ነው የዋረን ቡፌት ስራ።

ከሚዳስ አስደናቂ አፈታሪክ ጋር ይቀራረባል። ሚዳስ፤ እጁ የነካውን ነገር ሁሉ ወደ ወርቅ የመቀየር ችሎታ ነበረው። ደረጃው ይለያይ እንጂ፣ “ምርታማነት” ማለት ይሄው ነው - የዘመናችን “ሚዳስ” - ዋረን ቡፌት እፍኝ ከማይሞላ የእህል ዘር ኩንታል የሚሞላ አዝመራ ማምረት።

በተለያዩ ምክንያቶች የተዳከሙና የከሰሩ በርካታ ኩባንያዎች ዳግም ሕይወት የዘሩት በዋረን ቡፌት አስደናቂ ችሎታ ነው። በቅርቡ 83 አመታቸውን ያከበሩት ታታሪ የቢዝነስ ሰው፤ ዛሬ የ65 ቢሊዮን ዶላር ጌታ ናቸው። ትልቅ ሃብት ነው። በጥረታቸው ከፈጠሩት የሃብት መጠን ጋር ሲነፃፀር ግን ኢምንት ነው። በበርካታ የሃብት ፈጠራ አመታት ውስጥ ብዙዎችን ለሚሊዮነርነት አብቅተዋል። ባለፈው አመት ብቻ፣ የኩባንያው ባለአክሲዮኖች 20 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ትርፍ አግኝተዋል። ለሚሊዮኖች የስራና የገቢ እድል ፈጥረዋል።

Read 2718 times