አንድ ፅሁፍ ያለልፋት በቀላሉ ከተነበበ፣ ሲፃፍ በእጅጉ ተለፍቶበታል ማለት ነው፡፡
ኤንሪክ ጃርዴይል ፓንሴላ
እውነተኛ ፀሐፍትን ተስፋ ማስቆረጥ አይቻልም፡፡ ምንም ብትሏቸው ደንታ ሳይሰጣቸው ይፅፋሉ፡፡
ሲንክሌይር ልዊስ
በእጄ ላይ ብዕር ይዤ እንቅልፍ ከጣለኝ ብዕሬን አትንኩብኝ፣ በእንቅልፍ ልቤ ልፅፍ እችላለሁ፡፡
ቴሪ ጉሌሜትስ
የመፃፍ ተሰጥኦ እንደሌለኝ ለማወቅ አሥራ አምስት ዓመት ፈጅቶብኛል፡፡ ፅሁፍን ማቆም ግን አልቻልኩም፡፡
ምክንያቱም ያኔ ዝነኛ ፀሃፊ ሆኛለሁ፡፡
ሮበርት ቤንችሌይ
የምንፅፈው አሁናችንን በኋላ ለማስታወስ ነው፡፡
ቴሪ ጉሌሜትስ
ማንም ሰው የፃፈውን ነገር ለሴት ሳያነብ መፅሃፍ ማሳተም የለበትም፡፡
ቫን ዊክስ ብሩክ
ሃኪሜ የምትኖረው ለስድስት ደቂቃ ብቻ ነው ቢለኝ በፍርሃት አልርድም፤ ፍጥነቴን
ጨመር አድርጌ እፅፋለሁ እንጂ፡፡
አይሳክ አሲሞቭ
Published in
የግጥም ጥግ
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል