Saturday, 17 December 2011 09:56

ምነ... ባግዛት ብዬ ነው”

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

እውን ወንዶች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቱ ላይ ሙሉ ተሳትፎ ያደርጋሉን? ይህ ጥያቄ የብዙዎች ሲሆን ለመልሱ የተለያዩ ሰዎችን አነጋግረናል፡ ሰዎቹ አንድ ወንድና የተቀሩት ሴቶች ናቸው፡ ስለወንዶች ተሳትፎ ሴቶችን ማነጋገር ለምን አስፈለገ? የሚሉ አንባቢዎች ሊኖሩ ይችላሉ ፡፡
ሴቶቹ የቤተሰብ  እቅድ አገልግሎቱን ሲጠቀሙ ምንም እንኩዋን መብታቸው ቢሆንም ከባሎቻቸው ጋር ግን መግባባት ይኖርባቸዋል፡፡
ወንዶቹ እራራሳቸው የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቱን ተግባራራዊ ሲያደርጉም የግል መብታቸው ቢሆንም አሁንም ከሚስቶቻቸው ጋር መስማማት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ዞሮ ዞሮ በጋር ሊመሩት የጀመሩትን ትዳር እና ያፈሩትን ቤተሰብ በተገቢው መንገድ የማስተዳደር ኃላፊነት እንዲወጡ ሴትና ወንድ የትዳር አጋሮች ተግባብተው የሚበጀውን ማድረግ ካልቻሉ ውጤቱ አጉዋጉል ነው፡፡
በኢንጀንደር ሔልዝ “አብሪ”ፕሮጀክት በእንግሊዝኛው (access for better  reproductive health ) በአማርኛው የወጣቶችን እንዲሁም የእናቶችን ጤና በማሻሻል ብሩህ ሕይወትን እንዲያገኙ ጥረት ማድረግን የሚመለከት ነው፡፡ የአብሪ ፕሮጀክት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጀማል ካሳው እንደገለጹት አብሪ ፕሮጀክት በሰባት ክልሎች በቁጥር ወደ 238 /ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት የሚሆኑ ማለትም የጤና ጥበቃ ሚኒስር ፣የክልል ጤና ቢሮዎች ፣እንዲሁም የጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች የቤተሰብ እቅድ እና ንጽህናውን የጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎትን እንዲሁም ሌሎች የስነተዋልዶ አካላት ጤና አጠባበቅን በሚመለከት የክኒክና የአቅም ግንባታንና ባለሙያዎችን በአዳዲስ ዘዴዎች ላይ ክህሎትን እንዲያዳብሩ የማድረግ ስራ ይሰራል፡፡ በህብረተሰቡም በኩል ከአገልግሎቱ ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ግንዛቤ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸትና እራሳቸውም አገልግሎቱን እንዲፈልጉ የሚያስችል አቅም መፍጠር የአብሪ ፕሮጀክት ከሚያተኩርባቸው መካከል ናቸው፡፡
በኢንጀንደር ሔልዝ አብሪ ፕሮጀክት በተለይም የወንዶችን የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተሳትፎ በሚመለከት ምን በመስራት ላይ እንደሆነ ለመመልከት ከሚሰራባቸው አካባቢዎች ወደ ደብረብርሀን እና አካባቢዋ ዘልቀን ተመልክተናል፡ ያነጋገርናቸው ሰዎች የሚከተሉትን ሀሳቦች ሰንዝረዋል፡፡
“እኔ እድሜዬ ወደ 38 አመት ይሆነኛል፡፡ የምኖረው በቀይት ነው፡፡ አራት ልጆች ወልጃለሁ፡ ባለቤ.. ከዚህ በሁዋላ ልጅ መውለድ የለብንም ...እነዚህኑ የወለድናቸውን በወግ በማእረግ ማሳደግ ይጠበቅብናል ብሎኛል፡፡እኔ በእርግጥ እስከአሁን ድረስ የምጠቀመው መርፌውን ነበር፡ ነገር ግን በስራ ምክንያት እንዲሁም በተለያየ ጉዳይ በትክክል ቀኑን ባለማስታወስ ብዙ ጊዜ ችግር ይገጥመኛል፡፡ ደግነቱ ባለቤት የሚኖረው በስራ ምክንያት በአዲስ አበባ በመሆኑ እንጂ እስከአሁን ወደ ስድስት የሚደርስ ልጅ ልወልድ እችል ነበር፡፡ ስለዚህ በአካባቢዬ ያሉ የጤና ሰራተኞች እስከአሁን የወለድነው ልጅ ይበቃናል ...ሁለተኛ ልጅ መውለድ አንፈልግም ካላችሁ ለዘለቄታው መውለድ የማያስችል የህክምና አገልግሎት አለ ...ስላሉኝ አሁን ወስኜ ለህክምናው ቀርቤአለሁ፡፡ የእኔ ጉዋደኞች እስከ ስምንት ልጅ ወልደዋል፡፡ ልጅ የሚወልዱት የወሊድ መከላከያውን በትክክል ባለመጠቀማቸው እንጂ ይህን ሁሉ ልጅ ፈልገውት አይደለም፡፡ ስለዚህ ይህንን ቢጠቀሙ እመክራለሁ” ከቀይት
በመቀጠል ሀሳብዋን የምታካፍለን ጉዶበረት ከሚባለው አካባቢ ያኘናት እናት ናት፡፡ የአንድ አመት እድሜ ያለው ሕጻን ልጅ ታቅፋለች፡፡ ለሚመለከታት ጎስቋላ ናት፡፡ እድሜዋ 28 አመት ነው፡፡
“እኔ ትውልዴ ወደ ወላይታ ነው፡፡ ባል አግብቼ ነበር ወደ ጉዶበረት የመጣሁት፡፡ ነገር ግን ባለቤ ሶስት ልጅ ካስወለደኝ በሁዋላ ሌላ ሴት አግብቶ ከእኔ ጋር መኖሩን አቆመ፡፡ በሕግ ጠይቄው ለልጆቹ ማሳደጊያ ቢወሰንልኝም ገንዘቡን ግን አይሰጠኝም ፡ በቃ... እኔ ሽሮ እየቆላሁ ሌላ ሌላ የጉልበት ስራ እየሰራሁ ስለምኖር ልጆቼን በትክክል ማሳደግ አልቻልኩም፡ ስለዚህ ሌላ እረዳሻለሁ የሚል ሰው ደግሞ አንድ ልጅ አስወልዶ ዞር በይ አለኝ፡፡ እንግዲህ አራተኛ ልጅ ነው አሁን የያዝኩት፡፡ ስለዚህ ምንም እንኩዋን እድሜዬ ልጅ ቢሆንም አራት ልጅ ከበቂዬ በላይ ስለሆነ ዳግመኛ ልጅ የሚባል ነገር አልፈልግም፡፡ እነዚህ የተወለዱትም ቢሆኑ በየሰው ቤት በታትኜአቸዋለሁ፡፡ ምክንያቱም ልረዳቸው አልቻልኩም፡፡ ስለዚህ ቋሚ የወሊድ መከላከያውን ለማድረግ ወስኜ ይኼው ተሰርቶልኛል፡፡ በተለይም እንደእኔ ላሉት የምመክረው ሕመም የማያስከትል... አስታወስኩት... እረሳሁት... የማይባለውን ዘለቄታ ያለውን ሕክምና ቢወስዱ ይሻላል እላለሁ” ከጉዶበረት፡፡
በሰሜን ሸዋ በተገኘንበት ወቅት በተለይም ወንዶች ቋሚ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ ቀጠሮ ስለተያዘላቸው ይመጣሉ ቢባልም በደብረብርሀን ሆስፒታል የተገኙት አንድ አባወራ ብቻ ነበሩ፡፡ ሌሎቹ በምን ምክንያት እንደሆነ ባይታወቅም ቋሚውን የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ለማሰራት አልመጡም ነበር፡፡
“እኔ የምኖረው በአንኮበር ነው፡፡ አምስት ልጆች አሉኝ፡፡ በእድሜዬ ወደ አርባው የምደርስ ስሆን ባለቤ ግን ገና የሰላሳ አምስት አመት ሴት ነች፡እስከዛሬ አብረን ስንኖር የወሊድ መከላከያውን በተለያየ መልክ የምትወስድ ሚስ ነበረች፡፡ ነገር ግን በኑሮም ይሁን ልጆችን በመውለድ በጤናዋ ብዙም ደስተኛ ስላልሆነች መፍትሔ መሻት ነበረብን፡፡ እንግዲህ ሲያስተምሩን ...እንዲያው ለዘለቄታው ልጅ የማያስወልድ መፍትሔ አለ ስላሉን ...እኔ ፈቃደኛ ሆኜ ይኼው አገልግሎቱን ተጠቅሜአለሁ፡ እንግዲህ የተለያዩ ሰዎች የማይሆን ነገር ቢናገሩም እኔን የመከረኝ ግን ለእራሱ የተሰራለት ሰው ስለሆነ አምኜዋለሁ፡፡ ለሌሎች የምነግረው ...የወለድኩዋቸው ልጆች ይበቁኛል ከሚል ደረጃ ከተደረሰ በማይሆን ወሬ ከመሸበርና ወደሁዋላ ከማለት ይልቅ ቢጠቀሙ ጥሩ ይመስለኛል፡ እኔ እኮ ሚስ ስላሳዘነችኝ እንጂ ለሴቶቹም አገልግሎቱ እንደሚሰጥ አውቃለሁ፡ ነገር ግን እሱዋ በመውለዱም ሆነ ቤተሰብን በማስተዳደሩ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ስለተጎዳች ...ምነ... ባግዛት ብዬ ነው” ከአንኮበር
በዘለቄታው የቤተሰብ እቅድ የወንዶች ተሳትፎ ምን ይመስላል? ብለን የጀመርነው ጽሁፍ ከባለሙያዎች አንደበትም ለአንባቢ የምናካፍለው ቁም ነገር ይኖረናል፡፡ እሱን በቀጣዩ እትም የምናስነብባችሁ ሲሆን የዘላቂውን የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት በሚመለከት የተሳሳቱ አስተሳሰቦችን ወደሚጠቁመው ጽሁፍ እንመ ራችሁዋለን፡ጽሁፉን ያቀረበችላችሁ አዲስ አለም ብርሀኔ የኢሶግ የመገናኛ ብዙሀን ስራ ተባባሪ ነች፡፡
Vasectomy  ለወንዶች ብቻ ሳይሆን ለሴቶችም የሚሰጥ የህክምና አይነት ነው፡፡ በእርግጥ በቃል አጠቃቀም በተለይም ለሴቶች sterilization  ሲባል ይሰማል፡፡ ይህ የቤተሰብ እቅድን ለዘለቄታው ለመወሰን የሚያስችል የህክምና አይነት በተለይም ልጅ መውለድ ይበቃናል ብለው ለተማመኑና ለወሰኑ ሰዎች የሚሰጥ ሲሆን በአኑዋኑዋራቸው ላይ ምንም ተጽእኖ የማያሳድር እንዲያውም ለሚያደርጉት የግብረስጋ ግንኙነት ነጻነትን የሚያጎናጽፍ ነው፡ምክንያቱም በጊዜያዊነት የሚወሰዱት ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ በትክክል ወቅትን መጠበቅን የሚሹና ጥንቃቄን የሚፈልጉ ሲሆን Vasectomy  ግን ለዘለቄታው ያለምንም ሀሳብ ሊጠቀሙበት የሚችሉ በመሆኑ ነው፡፡
Vasectomy  በተለይም ለወንዶች የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ብዙ የተሳሳቱ አስተያየቶች የሚሰጡበት በመሆኑ እስከአሁን በጣም ብዙ ወንዶች ሊደፍሩት ያልቻሉት አገልግሎት ነው፡፡  ከሚሰጡት የተሳሳቱ አስተያየቶች መካከል ...
ከቀዶ ሕክምናው በሁዋላ የወንዶች ብልት ወደተፈጥሮአዊው ሁኔታ ስለማይመለስ ወሲብ ለመፈጸም አይችሉም፡፡
ለካንሰር ሕመም፣ ለእግር ጠረን መበላሸት ፣ለጸጉር መነቃቀል ይዳርጋል፡፡
ለጭንቀት ዳርጋል... አለአግብብ ያከሳል...ወዘተ... እውነቱ ግን ይህ አይደለም፡፡
ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎች የተሳሳቱ አስተያየቶች የሚሰጥበት ይህ ዘላቂ እና ቋሚ የሆነው የቤተሰብ እቅድ ማስፈጸሚያ Vasectomy  የተባለው የህክምና አገልግሎት በተለይም በአገራራችን በብዙ ወንዶች የሚተገበር አይደለም፡፡
ወንዶች በቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ ምን ሚና አላቸው?
ወንዶች በቤተሰብ እቅድ ተሳትፎ ማድረጋቸው ለምን ያስፈልጋል?
በአገራራችን ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?
ይቀጥላል

እውን ወንዶች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቱ ላይ ሙሉ ተሳትፎ ያደርጋሉን? ይህ ጥያቄ የብዙዎች ሲሆን ለመልሱ የተለያዩ ሰዎችን አነጋግረናል፡ ሰዎቹ አንድ ወንድና የተቀሩት ሴቶች ናቸው፡ ስለወንዶች ተሳትፎ ሴቶችን ማነጋገር ለምን አስፈለገ? የሚሉ አንባቢዎች ሊኖሩ ይችላሉ ፡፡ ሴቶቹ የቤተሰብ  እቅድ አገልግሎቱን ሲጠቀሙ ምንም እንኩዋን መብታቸው ቢሆንም ከባሎቻቸው ጋር ግን መግባባት ይኖርባቸዋል፡፡ ወንዶቹ እራራሳቸው የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቱን ተግባራራዊ ሲያደርጉም የግል መብታቸው ቢሆንም አሁንም ከሚስቶቻቸው ጋር መስማማት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ዞሮ ዞሮ በጋር ሊመሩት የጀመሩትን ትዳር እና ያፈሩትን ቤተሰብ በተገቢው መንገድ የማስተዳደር ኃላፊነት እንዲወጡ ሴትና ወንድ የትዳር አጋሮች ተግባብተው የሚበጀውን ማድረግ ካልቻሉ ውጤቱ አጉዋጉል ነው፡፡ በኢንጀንደር ሔልዝ “አብሪ”ፕሮጀክት በእንግሊዝኛው (access for better  reproductive health ) በአማርኛው የወጣቶችን እንዲሁም የእናቶችን ጤና በማሻሻል ብሩህ ሕይወትን እንዲያገኙ ጥረት ማድረግን የሚመለከት ነው፡፡ የአብሪ ፕሮጀክት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጀማል ካሳው እንደገለጹት አብሪ ፕሮጀክት በሰባት ክልሎች በቁጥር ወደ 238 /ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት የሚሆኑ ማለትም የጤና ጥበቃ ሚኒስር ፣የክልል ጤና ቢሮዎች ፣እንዲሁም የጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች የቤተሰብ እቅድ እና ንጽህናውን የጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎትን እንዲሁም ሌሎች የስነተዋልዶ አካላት ጤና አጠባበቅን በሚመለከት የክኒክና የአቅም ግንባታንና ባለሙያዎችን በአዳዲስ ዘዴዎች ላይ ክህሎትን እንዲያዳብሩ የማድረግ ስራ ይሰራል፡፡ በህብረተሰቡም በኩል ከአገልግሎቱ ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ግንዛቤ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸትና እራሳቸውም አገልግሎቱን እንዲፈልጉ የሚያስችል አቅም መፍጠር የአብሪ ፕሮጀክት ከሚያተኩርባቸው መካከል ናቸው፡፡ በኢንጀንደር ሔልዝ አብሪ ፕሮጀክት በተለይም የወንዶችን የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተሳትፎ በሚመለከት ምን በመስራት ላይ እንደሆነ ለመመልከት ከሚሰራባቸው አካባቢዎች ወደ ደብረብርሀን እና አካባቢዋ ዘልቀን ተመልክተናል፡ ያነጋገርናቸው ሰዎች የሚከተሉትን ሀሳቦች ሰንዝረዋል፡፡ “እኔ እድሜዬ ወደ 38 አመት ይሆነኛል፡፡ የምኖረው በቀይት ነው፡፡ አራት ልጆች ወልጃለሁ፡ ባለቤ.. ከዚህ በሁዋላ ልጅ መውለድ የለብንም ...እነዚህኑ የወለድናቸውን በወግ በማእረግ ማሳደግ ይጠበቅብናል ብሎኛል፡፡እኔ በእርግጥ እስከአሁን ድረስ የምጠቀመው መርፌውን ነበር፡ ነገር ግን በስራ ምክንያት እንዲሁም በተለያየ ጉዳይ በትክክል ቀኑን ባለማስታወስ ብዙ ጊዜ ችግር ይገጥመኛል፡፡ ደግነቱ ባለቤት የሚኖረው በስራ ምክንያት በአዲስ አበባ በመሆኑ እንጂ እስከአሁን ወደ ስድስት የሚደርስ ልጅ ልወልድ እችል ነበር፡፡ ስለዚህ በአካባቢዬ ያሉ የጤና ሰራተኞች እስከአሁን የወለድነው ልጅ ይበቃናል ...ሁለተኛ ልጅ መውለድ አንፈልግም ካላችሁ ለዘለቄታው መውለድ የማያስችል የህክምና አገልግሎት አለ ...ስላሉኝ አሁን ወስኜ ለህክምናው ቀርቤአለሁ፡፡ የእኔ ጉዋደኞች እስከ ስምንት ልጅ ወልደዋል፡፡ ልጅ የሚወልዱት የወሊድ መከላከያውን በትክክል ባለመጠቀማቸው እንጂ ይህን ሁሉ ልጅ ፈልገውት አይደለም፡፡ ስለዚህ ይህንን ቢጠቀሙ እመክራለሁ” ከቀይት

በመቀጠል ሀሳብዋን የምታካፍለን ጉዶበረት ከሚባለው አካባቢ ያኘናት እናት ናት፡፡ የአንድ አመት እድሜ ያለው ሕጻን ልጅ ታቅፋለች፡፡ ለሚመለከታት ጎስቋላ ናት፡፡ እድሜዋ 28 አመት ነው፡፡

“እኔ ትውልዴ ወደ ወላይታ ነው፡፡ ባል አግብቼ ነበር ወደ ጉዶበረት የመጣሁት፡፡ ነገር ግን ባለቤ ሶስት ልጅ ካስወለደኝ በሁዋላ ሌላ ሴት አግብቶ ከእኔ ጋር መኖሩን አቆመ፡፡ በሕግ ጠይቄው ለልጆቹ ማሳደጊያ ቢወሰንልኝም ገንዘቡን ግን አይሰጠኝም ፡ በቃ... እኔ ሽሮ እየቆላሁ ሌላ ሌላ የጉልበት ስራ እየሰራሁ ስለምኖር ልጆቼን በትክክል ማሳደግ አልቻልኩም፡ ስለዚህ ሌላ እረዳሻለሁ የሚል ሰው ደግሞ አንድ ልጅ አስወልዶ ዞር በይ አለኝ፡፡ እንግዲህ አራተኛ ልጅ ነው አሁን የያዝኩት፡፡ ስለዚህ ምንም እንኩዋን እድሜዬ ልጅ ቢሆንም አራት ልጅ ከበቂዬ በላይ ስለሆነ ዳግመኛ ልጅ የሚባል ነገር አልፈልግም፡፡ እነዚህ የተወለዱትም ቢሆኑ በየሰው ቤት በታትኜአቸዋለሁ፡፡ ምክንያቱም ልረዳቸው አልቻልኩም፡፡ ስለዚህ ቋሚ የወሊድ መከላከያውንለማድረግ ወስኜ ይኼው ተሰርቶልኛል፡፡ በተለይም እንደእኔ ላሉት የምመክረው ሕመም የማያስከትል... አስታወስኩት... እረሳሁት... የማይባለውን ዘለቄታ ያለውን ሕክምና ቢወስዱ ይሻላል እላለሁ” ከጉዶበረት፡፡

በሰሜን ሸዋ በተገኘንበት ወቅት በተለይም ወንዶች ቋሚ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ ቀጠሮ ስለተያዘላቸው ይመጣሉ ቢባልም በደብረብርሀን ሆስፒታል የተገኙት አንድ አባወራ ብቻ ነበሩ፡፡ ሌሎቹ በምን ምክንያት እንደሆነ ባይታወቅም ቋሚውን የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ለማሰራት አልመጡም ነበር፡፡

“እኔ የምኖረው በአንኮበር ነው፡፡ አምስት ልጆች አሉኝ፡፡ በእድሜዬ ወደ አርባው የምደርስ ስሆን ባለቤ ግን ገና የሰላሳ አምስት አመት ሴት ነች፡እስከዛሬ አብረን ስንኖር የወሊድ መከላከያውን በተለያየ መልክ የምትወስድ ሚስ ነበረች፡፡ ነገር ግን በኑሮም ይሁን ልጆችን በመውለድ በጤናዋ ብዙም ደስተኛ ስላልሆነች መፍትሔ መሻት ነበረብን፡፡ እንግዲህ ሲያስተምሩን ...እንዲያው ለዘለቄታው ልጅ የማያስወልድ መፍትሔ አለ ስላሉን ...እኔ ፈቃደኛ ሆኜ ይኼው አገልግሎቱን ተጠቅሜአለሁ፡ እንግዲህ የተለያዩ ሰዎች የማይሆን ነገር ቢናገሩም እኔን የመከረኝ ግን ለእራሱ የተሰራለት ሰው ስለሆነ አምኜዋለሁ፡፡ ለሌሎች የምነግረው ...የወለድኩዋቸው ልጆች ይበቁኛል ከሚል ደረጃ ከተደረሰ በማይሆን ወሬ ከመሸበርና ወደሁዋላ ከማለት ይልቅ ቢጠቀሙ ጥሩ ይመስለኛል፡ እኔ እኮ ሚስ ስላሳዘነችኝ እንጂ ለሴቶቹም አገልግሎቱ እንደሚሰጥ አውቃለሁ፡ ነገር ግን እሱዋ በመውለዱም ሆነ ቤተሰብን በማስተዳደሩ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ስለተጎዳች ...ምነ... ባግዛት ብዬ ነው” ከአንኮበር

በዘለቄታው የቤተሰብ እቅድ የወንዶች ተሳትፎ ምን ይመስላል? ብለን የጀመርነው ጽሁፍ ከባለሙያዎች አንደበትም ለአንባቢ የምናካፍለው ቁም ነገር ይኖረናል፡፡ እሱን በቀጣዩ እትም የምናስነብባችሁ ሲሆን የዘላቂውን የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት በሚመለከት የተሳሳቱ አስተሳሰቦችን ወደሚጠቁመው ጽሁፍ እንመ ራችሁዋለን፡ጽሁፉን ያቀረበችላችሁ አዲስ አለም ብርሀኔ የኢሶግ የመገናኛ ብዙሀን ስራ ተባባሪ ነች፡፡

Vasectomy  ለወንዶች ብቻ ሳይሆን ለሴቶችም የሚሰጥ የህክምና አይነት ነው፡፡ በእርግጥ በቃል አጠቃቀም በተለይም ለሴቶች sterilization  ሲባል ይሰማል፡፡ ይህ የቤተሰብ እቅድን ለዘለቄታው ለመወሰን የሚያስችል የህክምና አይነት በተለይም ልጅ መውለድ ይበቃናል ብለው ለተማመኑና ለወሰኑ ሰዎች የሚሰጥ ሲሆን በአኑዋኑዋራቸው ላይ ምንም ተጽእኖ የማያሳድር እንዲያውም ለሚያደርጉት የግብረስጋ ግንኙነት ነጻነትን የሚያጎናጽፍ ነው፡ምክንያቱም በጊዜያዊነት የሚወሰዱት ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ በትክክል ወቅትን መጠበቅን የሚሹና ጥንቃቄን የሚፈልጉ ሲሆን Vasectomy  ግን ለዘለቄታው ያለምንም ሀሳብ ሊጠቀሙበት የሚችሉ በመሆኑ ነው፡፡

Vasectomy  በተለይም ለወንዶች የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ብዙ የተሳሳቱ አስተያየቶች የሚሰጡበት በመሆኑ እስከአሁን በጣም ብዙ ወንዶች ሊደፍሩት ያልቻሉት አገልግሎት ነው፡፡  ከሚሰጡት የተሳሳቱ አስተያየቶች መካከል ...

ከቀዶ ሕክምናው በሁዋላ የወንዶች ብልት ወደተፈጥሮአዊው ሁኔታ ስለማይመለስ ወሲብ ለመፈጸም አይችሉም፡፡

ለካንሰር ሕመም፣ ለእግር ጠረን መበላሸት ፣ለጸጉር መነቃቀል ይዳርጋል፡፡

ለጭንቀት ዳርጋል... አለአግብብ ያከሳል...ወዘተ... እውነቱ ግን ይህ አይደለም፡፡

ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎች የተሳሳቱ አስተያየቶች የሚሰጥበት ይህ ዘላቂ እና ቋሚ የሆነው የቤተሰብ እቅድ ማስፈጸሚያ Vasectomy  የተባለው የህክምና አገልግሎት በተለይም በአገራራችን በብዙ ወንዶች የሚተገበር አይደለም፡፡

ወንዶች በቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ ምን ሚና አላቸው?

ወንዶች በቤተሰብ እቅድ ተሳትፎ ማድረጋቸው ለምን ያስፈልጋል?

በአገራራችን ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?

ይቀጥላል

Read 3776 times