በሃይማኖት አክራሪነቱ ምክንያት ተቃውሞ የገጠመውን “የሙስሊም ብራዘርሁድ መንግስት” በመገልበጥ ስልጣን የያዙት ጄ/ል አልሲሲ፣ በግብፅ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያለ ብዙ ፉክክር በሰፊ ልዩነት ያሸንፋሉ ተብሏል።
በእርግጥ ምርጫው የሚጀመረው ሰኞ ነው። ነገር ግን፤ በውጭ የሚኖሩ ግብፃዊያን ከወዲሁ ድምፅ ሰጥተው ቆጠራ ተካሂዷል። በዚሁ ቆጠራ፤ ጄ/ል አልሲሲ፣ 94.5% ድምፅ ሲያገኙ፣ ወደ ሶሻሊዝም የሚያዘነብሉ ተቀናቃኛቸው 5.5% ድምፅ ማግኘታቸውን ዎልስትሪት ጆርናል ዘግቧል።
ሰኞ በሚጀመረው የአገር ውስጥ ምርጫም አልሲሲ አብዛኛውን ድምፅ እንደሚያገኙ ከመራጮች የተሰበሰበሰ አስተያየት ይጠቁማል። በእርግጥ፤ በጭራሽ ድምፅ ላለመስጠትና ላለመምረጥ የወሰኑ ግብፃዊያን ብዙ ናቸው። ከፊሎቹ ጄነራሉን በጠላትነት የሚቃወሙ የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎች ናቸው። ከፊሎቹ ደግሞ፤ የተሻለ አማራጭ የያዘ ደህና ፓርቲና ደህና ፖለቲከኛ በማጣት ከምርጫው ራሳቸውን አግልለዋል። ከእነዚህ ውጭ የሆነው አብዛኛው ግብፃዊ መራጭ፤ ለጊዜው ለአገሪቱ የሚበጃት ጄነራል አልሲሲን የመሰለ ጨከን ያለ መሪ ነው ብለው ያምናሉ።
በሌላ በኩል፤ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ይዘው ከሰላሳ አመት በላይ ግብፅን የገዟት ሆስኒ ሙባረክ፣ 3 ሚሊዮን ዶላር ገደማ የመንግስት ገንዘብ አጭበርብረዋል በሚል ሰሞኑን የሶስት አመት እስር ተፈርዶባቸዋል። ልጃቸው ደግሞ የአራት አመት እስር። ከዚሁም ጋር የ14 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ተወስኖባቸዋል።
Published in
ከአለም ዙሪያ
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል