Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 17 December 2011 11:28

የማሪያም ስእል ከእርግዝና ምርመራ ጋር

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ከመጪው የገና በአል ጋር ተያይዞ የተሰራ ቢልቦርድ ነው። ከስያሜ በቀር ምንም ፅሁፍ የለውም። ማርያም፤ በግራ መዳፏ አፏን ከድናለች። በድንጋጤ  ምክንያት ይመስላል። በቀኝ እጇ የያዘችው የእርግዝና መመርመሪያ፤ ቀላ ያለ ምልክት ያሳያል - በሃምራዊ ቀለም። “ማሪያም በሃምራዊ” የሚል ስያሜ የተሰጠው፤ በኒውዝላንድ በቅዱስ ማቴዎስ ቤተክርስቲያን የተዘጋጀው ቢልቦልድ፤ በቢልቦርድ ጎዳና ላይ ይታያል። መቼም የፈረንጅ ጉድ አያልቅም እንበል?
ቤተክርስቲያኑ፤ እንዲህ አይነት ያልተለመደና ለየት ያለ ማስታወቂያ ሲያዘጋጅ የመጀመሪያው እንዳልሆነ ዘግቧል - ቲቪ3 የተሰኘ የኒውዝላንድ ጣቢያ። ለምሳሌ ከሁለት አመት በፊት ማሪያምና ዮሴፍ አብረው ሲኖሩ የሚያሳይ ማስታወቂያ ነበር የተዘጋጀው - “Poor Joseph, God was a hard act to follow” ይላል ርእሱ። “ምስኪኑ ዮሴፍ፤ አምላክን መከተል ፈታኝ ነበር” እንደማለት።
“የተለመደው አይነት ሆደ ቡቡ ስሜታዊነትና የተሰለቸ አስተሳሰብን ማስወገድ  እንፈልጋለን” በማለት የተናገሩት የቤተክርስቲያኗ ሃላፊ፤ አላማችንም ማስታወቂያውን የሚያዩ ሰዎች እንዲያስቡና እንዲወያዩ ማነሳሳት ነው፤ ማስታወቂያዎቹ ከስያሜ በስተቀር ሌላ ማብራሪያ ፅሁፍ እንዳይኖራቸው ያደረግነውም በዚህ ምክንያት ነው ብለዋል። ለአንዲት እናት ከህፃን ልጇ ጋር ሁኔታው ምን ይመስል እንደነበር እንድናስብ ያደርጋል የሚሉት የቤተክርስቲያኗ ሃላፊ፤ “ጉዳዩ የምር እርግዝና ነው፤ የምር እናትነት፤ የምር ህፃን ልጅ ...የምር ጭንቀት፣ ፅናትና ተስፋ” ብለዋል።

Read 7327 times

Latest from