Saturday, 31 December 2011 11:44

ሆንሪ ኤምሬትስ ደጃፍ ላይ ነው

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(1 Vote)

የቲዬሪ ሆንሪ ወደ አርሰናል በ2 ወራት የውሰት ውል የሚመለስበት ሁኔታ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አርሴን ቬንገር ገለፁ፡፡ ለተጨዋቹ ዝውውር እውን መሆን በአርሰናል እና በሬድ ቡልስ ክለብ መካከል በዋስትና የሚደረገው ስምምነት ወሳኝ እንደሚሆን ቤንገር ተናግረዋል፡፡በአሜሪካ ሜጀር ሶከር ሊግ ተወዳዳሪ በሆነው የኒውዮርኩ ሬድ ቡልስ የሚጫወተው ሆንሪ 34 አመቱ ነው፡፡

ሆንሪ በአርሰናል ከ1999 እስከ 2007 በተጫወተባቸው 369 ጨዋታዎች 226 ጎሎች በማስመዝገብ ወርቃማ ታሪክ እንዳለው ይታወቃል፡፡ የሆንሪ አርሰናልን በውሰት መቀላቀል እውን ከሆነ ክለቡ ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል ዘገባዎች እያወሱ ሲሆን ተጨዋቹ በኒውዮርኩ ሬድ ቡልስ ክለብ በ29 ጨዋታዎች 15 ጎሎች በማስመዝገብ የያዘው ወቅታዊ ብቃት እማኝ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡ በአርሰናል ክለብ ስታድዬም ኤምሬትስ ከወራት በፊት ሃውልት የቆመለት ቲዬሪ ሆንሪ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ከክለቡ ጋር ልምምድ እየሰራ የቆየ ሲሆን የውሰት ውሉ ከተሳካ በፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን የሚለብሰውን 12 ቁጥር ማልያ እንደሚታጠቅም እየተነገረ ነው፡፡ አርሰናል ሆንሪን በውሰት ውል ከወሰደ በሬድ ቡልስ የሚከፈለውን የ70ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ እንዲከፍል የሚገደድ ይሆናል፡፡ ተጨዋቹ 2012 ከገባ ከ9 ቀናት በኋላ አርሰናል በኤፍ ኤ ካፕ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር በሚያደርገው ግጥሚያ በመሰለፍ ለቀድሞ ክለቡ መልሶ መጫወት እንደሚጀምርም ይገለፃል፡፡

ሆንሪና ባንፕርሲ በአርሰናል

ሆንሪ በ2003/04ቫንፒርሲ በ2011

ተጫወተ   5141

አገባ  39 38

1 ጐል  114.15ደቂቃ 87.97ደቂቃ

 

 

Read 2946 times Last modified on Saturday, 31 December 2011 11:47