Friday, 06 January 2012 08:34

ለ28ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አዲስ ሻምፒዮን ይፈጠራል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ለ28ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አዲስ ሻምፒዮን ይፈጠራልከ2 ሳምንት በኋላ በጋቦንና ኢኪቶሪያል ጊኒ የሚዘጋጀው 28ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አዲስ ሻምፒዮን እንደሚያሳይ ተገመተ፡፡ በአፍሪካ ዋንጫው ላይ የአህጉሪቱ ታላላቅ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድኖች አለመገኘታቸው አንድ ልዩ ገፅታ ሲሆን ለፍፃሜው ማለፍ ከቻሉት 16 አገራት 5 ብቻ የዋንጫውን ድል በታሪካቸው ያስመዘገቡ ናቸው፡፡

የአፍሪካ  ዋንጫ ያመለጣቸው 5ቱ የእግርኳስ ሃያላን የሁለት ጊዜ ሻምፒዮኖቹ አረንጓዴዎቹ ንስሮች ናይጄርያ፤ የ4 ግዜ ሻምፒዮኖቹ የማይበገሩት አንበሶች ካሜሮን፤ ባፋና ባፋናዎቹ ደቡብ አፍሪካ፤ የ7 ግዜ ሻምፒዮኖቹ ፈርኦኖቹ ግብፅ እንዲሁም የበረሃ ቀበሮዎቹ አልጄርያ ናቸው፡፡ በ2012ቱ የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጆቹን ኢኳቶርያል ጊኒና ጋቦንን ጨምሮ ሴኔጋል፤ በምድብ ማጣርያው በመሪነት ያለፉት ቦትስዋና፤  ቡርኪናፋሶ ፤ኮትዲቯር ፤ማሊ ፤ዛምቢያ፤ ሞሮኮ፤ ጋና ፤አንጎላ ኒጀርና ጊኒ እንዲሁም በምርጥ 2ኛነት ማለፋቸው ያረጋገጡት ቱኒዚያ ፤ሊቢያና ሱዳን ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ ከእነዚህ ተሳታፊዎች ለዋንጫ ባላቸው እድል ጋና፤ ኮትዲቯርና ሴኔጋል ቅድሚያ ግምት ወስደዋል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የተሳታፊ ብሔራዊ ቡድኖች አጠቃላይ የቡድን ዝርዝር እንዲገባ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ከ4 ቀናት በኋላ ያበቃል፡፡  ለአፍሪካ ዋንጫው ታዋቂው የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ አዲዳስ “ኮሜክዋ” የተባለች ኳስ የሚያቀርብ ሲሆን ስያሜውን ሁለቱ አዘጋጅ አገራት ያሏቸውን ኮሞ እና ኢክዌተር የተባሉ ወንዞች የወከለ ነው፡፡ በማጣርያው ላይ በምድብ 2 ናይጄርያ፤ኢትዮጵያና ማዳጋስካርን ጥላ ያለፈችው ጊኒ ለዋንጫ ተቀናቃኝነት ግምት ከተሰጣቸው ቡድኖች ተርታ ተሰልፋለች፡፡ የአገሪቱ መንግስት ይህን ግምት በማሳካት ብሄራዊ ቡድኑ ታሪክ እንዲሰራ በማቀድ ለተለያዩ ወጭዎቹና የቦነስ ክፍያዎች እንዲሆን 7 ሚሊዮን ዶላር መበጀቱን ሱፕር ስፖርት ዘግቦታል፡፡28ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሊካሄድ ሁለት ሳምንታት ሲቀሩ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድኖች እርስ በራሳቸው የሚገናኙባቸውን የወዳጅነት ጨዋታዎች በማቀድ በየፊናቸው ዝግጅታቸውን አጧጥፈዋል፡፡ የቡድኖች የመጨረሻ ዝግጅት ላይ ምስራቅ አፍሪካን የወከለችው ሱዳን 3  ፤ሌላዋ አዘጋጅ ጋቦን፤አይቬሪኮስትና ሴኔጋል 2 ፤ ቱኒዚያ፤ አንጎላ፤ ቦትስዋና፤ ቡርኪናፋሶ፤ ዛምቢያ እያንዳንዳቸው 1 የወዳጅነት ጨዋታዎችን በማድረግ አቋማቸውን ይፈትሻሉ፡፡ ሊቢያ፤ ማሊ፤ ሞሮኮና ኒጀር ግን ለዝግጅት የወዳጅነት ጨዋታ ስለማድረጋቸው ለፊፋ ያሳወቁት ነገር የለም፡፡

 

 

 

Read 2727 times Last modified on Friday, 06 January 2012 08:37