Friday, 06 January 2012 12:24

መንግስት ቤታችንን ከቀማን መውደቂያ የለንም

Written by  ሰላም ገረመ
Rate this item
(0 votes)

መንግስት ድህነት ይጥፋ አለ እንጂ ድሃ ይጥፋ አላለም …

ከ30 ዓመት በፊት በውጭ መንግስት የተሰራልን ቤት እየተወሰደብን ነው …

ህገ ወጥ ግንባታ ነው የተባልነው ቤት ለሌላ እየተከራየ ነው …

አቶ ጽባየሁ ሽኩር የዛሬ 30 ዓመት ግድም ከአሜሪካ ግቢ የተፈናቀሉት በጐርፍ ምክንያት ነበር፡፡ የውጭ አገር ኤምባሲ ቤት ሰርቶ እንደሰጣቸው የሚናገሩት አቶ ፅባየሁ፤ ለሰባት ዓመት በየወሩ 18 ብር ክፈሉና ቤቱ የራሳችሁ ይሆናል፤ ካርታም ይሰጣችኋል ተብለን ነበር፤ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ግን መኖሪያ ቤታችንን እየነጠቀን ነው ሲሉ ያማርራሉ፡ በግቢያቸው ውስጥ ሰርተው የሚያከራዩዋቸው ሁለት ክፍል ቤቶች እንደነበሩ የተናገሩት አቶ ፅባየሁ፤ ህገወጥ ግንባታ ፈፅመሃል በሚል በመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ መነጠቃቸውን ይገልፃሉ - ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩት በኪራይ ከሚያገኙት ገቢ እንደነበር በመጠቆም፡፡ ይሄ ብቻ ግን አይደለም፡፡ 18 ብር እየከፈሉ ሲኖሩበት የነበረው ቤታቸው አዲስ የኪራይ ዋጋ እንደተተመነለት የሚናገሩ በርካቶች ናቸው፡፡ሙሉ ዘገባውን ቶ ጽባየሁ ሽኩር የዛሬ 30 ዓመት ግድም ከአሜሪካ ግቢ የተፈናቀሉት በጐርፍ ምክንያት ነበር፡፡ የውጭ አገር ኤምባሲ ቤት ሰርቶ እንደሰጣቸው የሚናገሩት አቶ ፅባየሁ፤ ለሰባት ዓመት በየወሩ 18 ብር ክፈሉና ቤቱ የራሳችሁ ይሆናል፤ ካርታም ይሰጣችኋል ተብለን ነበር፤ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ግን መኖሪያ ቤታችንን እየነጠቀን ነው ሲሉ ያማርራሉ፡ በግቢያቸው ውስጥ ሰርተው የሚያከራዩዋቸው ሁለት ክፍል ቤቶች እንደነበሩ የተናገሩት አቶ ፅባየሁ፤ ህገወጥ ግንባታ ፈፅመሃል በሚል በመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ መነጠቃቸውን ይገልፃሉ - ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩት በኪራይ ከሚያገኙት ገቢ እንደነበር በመጠቆም፡፡ ይሄ ብቻ ግን አይደለም፡፡ 18 ብር እየከፈሉ ሲኖሩበት የነበረው ቤታቸው አዲስ የኪራይ ዋጋ እንደተተመነለት የሚናገሩ በርካቶች ናቸው፡፡ መገናኛ ሀያ አራት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሰፈሩ ነዋሪዎች ከአሜሪካን ግቢ፣ ከፍልውሃ፣ ከእስጢፋኖስና ከቤተመንግስት በ1973 ዓ.ም በጎርፍ ተፈናቅለው የመጡ ናቸው፡፡ የሰፈሩበት አካባቢ ጎርፍ አስወጋጅ ተብሎ ይጠራል፡፡ በጐርፍ ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች የመኖርያ ቤት እንዲሰራ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው የስውዲን ኤምባሲ እንደነበርና ቤቶቹን ህብረተሰቡ በጉልበቱ እንደሰራው የሚያስታውሱት ነዋሪዎች፤ ለቤቶቹ ተወካይ (ሞግዚት) መንግስት እንደሆነ ቢነገራቸውም ‹‹በዋናነት ቤቱ የእናንተ ስለሆነ ጠብቁት›› እንደተባሉ ይገልፃሉ - በደርግ ዘመን፡ ለአንድ ዓመት የኖሩትም በነፃ እንደነበር ያወሳሉ- ነዋሪዎቹ፡፡ ከአመት በኋላ ግን ኪራይ ቤቶች ውል እንዳስፈረማቸውና ቤቱን ለማደሻ በሚል   እንደ ቤቶቹ ክፍል ብዛት ከ3ብር - 18ብር በወር ማስከፈል እንደጀመረ ፤አቅም የሌላቸውም በነፃ እንዲኖሩ ተወስኖ ሶስት አስርት አመታትን እንዳሳለፉ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡  ጎርፍ አስወጋጅ ሰፈር አስደንጋጭ ወሬ የተሰማው አዲሱን የተከራይ አከራይ መመሪያ ተከትሎ እንደሆነ የሚናገሩት ነዋሪዎች፤ ለሚኖሩበት ቤት አቅምን ያላገናዘበ የኪራይ  ክፍያ እንደተተመነባቸው ይገልፃሉ፡ በግቢያቸው ውስጥ የሰሩትን ትርፍ ቤት ለመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ እንዲያስረክቡ፤ ያለበለዚያ ግን ውላቸው እንደሚፈርስ ስጠንቀቂያተሰጥቷቸዋል፡ ‹‹እኛ የምናውቀው የራሳችን ቤት መሆኑን ነው፤  የምንከፍለውም ክፍያ የቤት ማደሻ እንጂ ኪራይ አይደለም፤ ኪራይ ላሻሽል የሚባለው  ለተከራየ ነው፡፡” ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡ባለፈው እሁድ የ24 አካባቢ ነዋሪዎች በቀበሌያቸው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የተሰበሰቡት ይሄንኑ አስደንጋጭ ጉዳይ ለመወያየት ነበር፡፡ ጐርፍ አስወጋጅ ተብሎበሚጠራውአካባቢ520አባወራዎችየሰፈሩሲሆንበችግሩዙሪያየሚወያዩዋቸውኮሚቴዎችእንደመረጡም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዓላማቸው የመንግስትን ፖሊሲ መቃወም እንዳልሆነ የሚናገሩት የኮሚቴው ሰብሳቢዎች፤ የመንግስት ቤቶችኤጀንሲባወጣው መመሪያ መሰረት እንዲያስተናግዳቸውና ያነሱትም የመብት ጥያቄ እንደሆነ አስረግጠው ይናገራሉ፡፡  የአምስት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ ወሰንየለሽ አበራ አካባቢው ምድረ በዳ በነበረበት ወቅት በጐርፍ ተፈናቅለው ወደዚህ ሥፍራ እንደመጡ ይናገራሉ - መብራትና ውሃ የሌለበትና ጅብ የሚፈነጭበት አካባቢ እንደነበር በማስታወስ፡፡ ቀድሞ ከሚከፍሉት 18 ብር ወርሃዊ ክፍያበተጨማሪ540ብርኪራይንደተተመነባቸው የሚናገሩት ወ/ሮ ወሰንየለሽ፤ ነዋሪዎች የሰሩት ትርፍ ቤቶች ተወስዶባቸው ለሌላ እየተከራየ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ መንግስት ቤቱን አልሰራልንም የውጭ መንግስት እንጂ ያሉት ወ/ሮዋ፤ ክፍያውን ያልፈፀመ በአምስት ቀን ይወጣል መባሉንም ተናግረዋል፡፡ መንግስት ድህነት ይጥፋ አለ እንጂ ድሃ ይጥፋ አላለም ሲሉም ገልፀዋል - ወ/ሮ ወሰን የለሽ፡፡   በደርግ መንግስት ከ10 ዓመት በላይ በአካባቢው ላይ ኖረናል የሚሉት ነዋሪዎች፤ የቀድሞ መንግስት ቤቶቹ ይሰጣችኋል በማለት አታሎናል ሲሉ ይወቅሳሉ፡ “ይሄ መንግስት መሀሪ በመሆኑ ችግሮቻችንን እንዲፈታልን ነው ጥያቄያችን” ሲሉም ተማፅነዋል፡ በደርግ ዘመን ጉዳዩ  ይመለከታቸው የነበሩትን ግለሰብ በቅርቡ አግኝተው ማናገራቸውን የገለፁ የኮሚቴውሰብሳቢዎች፤ግለሰቡ ማስረጃው የት እንዳለ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ነግረውናል ብለዋል፡፡ በደርግ ዘመን ቤቱ እንዲሰጠንና ካርታ እንዲሰራልን የተፃፈ መመሪያ ነበር የሚሉት ሰብሳቢዎቹ፤ ሆኖም መመሪያው ተግባራዊ ሳይሆን ደርግ እንደወቀደ ይናገራሉ፡፡ ቤቶች ኤጀንሲ አሁን የተመነው የኪራይ ክፍያ ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ይታይልን  ሲሉ የጠየቁ አንዳንድ ነዋሪዎች፤ ቤቱን የሰራልን የስዊዲን ኤምባሲ ነበር፤ ነገር ግን ከመመሪያ ውጪ መኖር ስለማይቻል ተከራዩ ከተባልን እንቀበላለን፤ ሆኖም መክፈል የምንችለው ቀድሞ የምንከፍለውን መጠን ነው ብለዋል፡፡ የንግድ ቤቶችን ለሶስተኛ ወገን ያከራዩ ነዋሪዎች ቤቶቹን ተወርሰዋል ያሉት ነዋሪዎች፤ ነገ መኖሪያ ቤቶቻችን ላለመወሰዳቸው ምን ማረጋገጫ አለን ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡  አከራይተውት የነበረ አንድ ክፍል ቤት መወረሱን የተናገሩት የ70 ዓመቱ ጐልማሳ አቶ ባዩ ዘለቀ፤ መንግስት ህገወጥ ከሆነ አፍርሱ ይላል እንጂ እንዴት ከኛ ተረክቦ መልሶ ያከራያል ሲሉ ግራ በተጋባ ስሜት ይጠይቃሉ፡፡  “የእኛ ትልቁ ጥያቄ የልጅ ልጅ ያየንበት ቦታ የባለቤትነት ማረጋገጫ  ይሰጠን የሚል ነው፤ ኮሚቴው ከመንግስት አካላት ጋር ተነጋግሮ የባለቤትነት ደብተር ካገኘን በኋላ ቀጥሎ ስለተሰራው ቤት እንወያያለን፤ ከዚህ በኋላ ደግሞ የትም ልንሄድ አንችልም” የሚሉት ነዋሪዎች፤ ቤት አለን ብለን ኮንዶሚንየም እንኳን አልተመዘገብንም፤ በዚህ የኑሮ ውድነት የት እንወድቃለን ብለዋል፡፡ “ወፍ እንኳን ቤት አላት፤ እኛ ህጋዊ ነገር ነው የጠየቅነው፤ ለጨረቃ ቤት እንኳን እየተሰጠ ነው፤ እኛም ኢትዮጵያዊያኖች ስለሆንን ሊሠጠን ይገባል” ሲሉ   ባለፈው እሁድ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል፡፡ ከ30 ዓመት በላይ ኖረንበታል የሚሉትን ቤት እንደማይወሰድብን ማረጋገጫ የለንም በሚል ክፉኛ የሰጉት የ24 ጐርፍ አስወጋጅ ሰፈር አንዳንድ ነዋሪዎች፤ ካርታ ይሰጠን የሚል ጥያቄ በማንሳታችን ሌላ ችግር ይከሰት ይሆን የሚል ፍራቻም አለን ይላሉ፡፡ “ስለዚህም አዲስ የተተመነውን ክፍያ የመክፈል አቅም የለንም ብለን መከራከር እንጂ ኪራይ ቤቶች አይመለከተውም የሚል ነገር ማንሳት የለብንም” የሚል ከስጋት የመነጨ አስተያየት ሲሰነዝርም ተሰምቷል፡፡ የሚበዙት ግን ድምፅቸው ተመሳሳይ ይመስላል፡፡ለቤትነት ደብተር ይሰጠን ነው የሚሉት፡፡ “የእኛ ጥያቄ የቤት ኪራይ ይቀነስልን አይደለም ቤቱ ይሰጠን ነው” ያሉት ነዋሪዎች፤ ያለፈውመንግስትያጠፋው ጥፋት በዚህ መንግስት እንዲስተካከልልን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ “የቀድሞው መንግስት አታሎናል፤ ውሉ ላይ  የሚለው ስንከፍል የኖርነው ለቤት ማደሻ እንጂ ለኪራይ አይደለም፡፡  ለአራት ክፍል 18 ብር ነበር የምንከፍለው፤ ጡረታ ወጥተን የእድሜያችን መገባደጃ ላይ ሳለን ከቤታችን ውጡ መባላችን አግባብ አይደለም ያሉት አንድ ነዋሪ፤ ግን እየተከፋፈልን ነው ያለነው፤ ሁላችንም አንድ አይደለንም ሲሉ በመሃላቸው ያለውን ልዩነት ተናግረዋል፡፡  ሌላ ነዋሪ ደግሞ ቅሬታቸውን ሲናገሩ፡- “እኛ እንደ ውሻ ነው የምንታየው፤ አንድም ጥያቄያችንን የተቀበለን የለም፡፡ አሁን በኪራይ ቤቶች በኩል ተስፋ ቆርጠናል፡፡ ፓርላማም ሄደን ነበር፤ በቂ መልስ አላገኘንም፡፡ የምንበላው እና የምንጠጣው ይሄንን ቤት አከራይተን ነበር፡፡ በመንግስት በኩል ችላ መባላችን እያሳሰበን ነው” ብለዋል፡፡   ቤቱ ይሸጥልን ብለን የምንጠይቀው በምናችን ልንገዛው ነው ያሉ አንድ ነዋሪ በበኩላቸው፤  የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ይሰጠን ነው ጥያቄያችን፤ መንግስት መሀሪ ነው፤ ይቅር ባይ ነው በማለት ጠይቀዋል፡፡ እስካሁን ለቤቱ ማደሻ የሚሆን ገንዘብ ስንከፍል የቆየነው ልጆቻችን ባዕድ አገር ሰርተው በሚልኩብን ገንዘብ ነበር፤ አሁን ግን እነሱም ሰልችቷቸው ስለተመለሱ ሜዳ እንዳንወድቅ ሲሉ ሌላ ነዋሪ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡  ቤቱ ሲሰራ ከህዝብ 10 ሳንቲም እየሰበሰብኩ ነው የኖርኩት የሚሉት ነዋሪ ደግሞ የቤት ኪራይ የምከፍለው አንድ ሳንቲም የለኝም ብለዋል፡፡ ከ74 ዓ.ም ጀምሮ የነበረው አሰራር አሁን መለወጡ አግባብ አይደለም ሲሉም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲን አዲስ መመሪያ ተቃውመዋል፡፡ “እኔ ስመጣ ሶስት ብር ነበር የምከፍለው፤ በወቅቱ ባለሁለት ክፍል ቤት ነበረኝ፤  ቤተሰብሽ ብዙ ነው ባለአራት ክፍል ውሰጂና ለማደሻ ሀያ ብር ክፈይ ስባል አልከፍልም የለኝም ስላልኩ በነፃ ትኑር ተብዬ ነበር፤ አሁን ደግሞ ውጪ ተባልኩኝ ፡፡ ሁላችንም አንድ አይነት ሀሳብ ነው ያለን፤ መንግስት ችግራችንን ተረድቶ ቤታችንን አይቀማን” ብለዋል፡፡ ይሄንንም ስንል የነገ አገርተረካቢ ልጆቻችንን፣ የሚጦሩ አዛውንትንና፣ ፍሬያማ ወጣት ዜጎቹን አስቦ መንግስት ቤት አልባ አያድርገን ማለቴ ነው ሲሉ ተማፅነዋል፡፡

 

 

 

Read 12845 times Last modified on Friday, 06 January 2012 12:30