Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 January 2012 10:19

ሳያት በጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን ላይ የመሰረተችው ክስ በሽምግልና እንዲያልቅ ተወሰነ

Written by 
Rate this item
(7 votes)


XXድምፃዊት ሳያት ደምሴ በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 “ታዲያስ አዲስ” አዘጋጅ ላይ የመሰረተችውን ክስ በሽምግልና እንዲጨርሱ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በትላንትናው ዕለት ፍ/ቤት የቀረቡት ባለጉዳዮች ሽማግሌዎች እያሰባሰብን ነው በማለታቸው ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ተገለፀ፡፡
ሳያት ደምሴ በአሜሪካን አገር ያቀረበችውን የሙዚቃ ኮንሰርት አስመልክቶ የሸገር ኤፍ ኤም “ታዲያስ አዲስ” ፕሮግራም አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን ከስፍራው ባስተላለፈው ዘገባ መልካም ስሜና ዝናዬ ተነክቷል ስትል ሳያት ክስ መስርታ እንደነበር ይታወቃል፡ክሱን ሲመረምር የቆየው የመናገሻ ፍ/ቤት ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን ባቀረበው የእርቅ ጥያቄ መሰረት ፍ/ቤቱ  ጉዳዩን በሽምግልና እንዲጨርሱ አዝዞ ነበር፡፡

በትላንትናው ዕለት የሽምግልናውን ሂደት አስመልክቶ ለፍ/ቤት ያስረዱት ባለጉዳዮቹ ሽማግሌ በማሰባሰብ ላይ መሆናቸውን በመግለፃቸው ፍ/ቤቱ ለጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ተወካይ የሆነችው እህቷ ቤተልሄም ደምሴ ለአዲስ አድማስ ተናግራለች፡፡ የሽምግልና ሂደቱ ትላንት ከፍ/ቤት እንደወጡ መጀመሩን የገለፀችው ተወካዩዋ፤ እርቁ በካሳ ይሁን ወይም ማስተባበያ በመስራት የሚለው ጉዳይ ገና አለመወሰኑን  ተናግራለች፡፡ የሽምግልና ሂደቱ ምንእንደሚመስል የጠየቅነው ጋዜጠኛ ሰይፉ በበኩሉ፤ ጉዳዩ በፍ/ቤት የተያዘ በመሆኑ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን ገልጿል፡፡ ጋዜጠኛ ሰይፉ ከአሜሪካ ባስተላለፈው ዘገባ ድምፃዊት ሳያት ባቀረበችው ኮንሰርት፤ መድረክ ላይ በድምጿ መዝፈን አቅቷት ከመድረክ ጀርባ በቴፕ ዘፈኗ ይጫወት እንደነበር ጠቁሞ በዚህም ታዳሚዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውን መግለፁ ይታወሳል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሳያት ማስተባበያ እንዲሰራላት ጠይቃ የፕሮግራሙ አዘጋጆች ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው የጣቢያው ባለቤቶች ድምፃዊቷን ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡

 

 

 

 

Read 26176 times Last modified on Saturday, 14 January 2012 13:32