Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 January 2012 12:03

የፍቅር ጥግ

Written by 
Rate this item
(10 votes)

ከሁሉም አይነት ልጃገረዶች ጋር በፍቅር ወድቄአለሁ፡፡ አሁንም ሙሉ በሙሉ በዚሁ አይነት ተግባሬ ለመግፋት አቅጄአለሁ፡፡

ቻርልስ - የዌልስ ልዑል

(1948-)

ፈፅሞ አፍቅራ የማታውቅ ሴት ጨርሶ በህይወት ኖራለች ማለት አይቻልም፡፡

ጆን ጌይ

(እንግሊዛዊ ገጣሚና ፀሐፊ ተውኔት)

ያፈቀረ ወንድ እስኪያገባ ድረስ ሙሉ አይደለም፡፡ ካገባ በኂላ ግን አለቀለት፡፡

ዛዛ ጋቦር

(ትውልደ ሃንጋሪ አሜሪካዊ የፊልም ተዋናይ)

እያፈቀሩ ብልጥ መሆን አይቻልም፡፡

ፍራንሲስ ቤከን

(እንግሊዛዊ ፈላስፋ፣ ፖለቲከኛና ጠበቃ)

አንዲት ሴት በህይወት ዘመኗ አንዴ ወይም ሁለቴ መጥፎ ወንድ ማፍቀር አለባት - አመለ ቀናውን እንድታመሰግን፡፡

ማጆሪ ራውሊንግስ

(አሜሪካዊ የረዥም ልብወለድ ደራሲ)

ሴት ልጅ የሚያፈቅራትን ወንድ እንጂ የምታፈቅረውን ወንድ ማግባት የለባትም፡፡ ያ ነው የዘላቂ ደስታ ምስጢሩ፡፡

ማርያማ ባ

(ሴኔጋላዊት ደራሲና የሴቶች መብት ተሟጋች)

የሴት ልብ ሁልጊዜ የቃጠሎ ምልክት አለበት፡፡

ሉዊስ ላቤ

(ፈረንሳዊ ገጣሚ)

መኖር አልፈልግም - መጀመርያ ማፍቀር ነው የምሻው፡፡ ከዛም እግረ መንገዴን ብኖር አልጠላም፡፡

ዜልግ ፊትዝገራልድ

(አሜሪካዊ ፀሐፊ)

እያንዳንዱ ወንድ የሚኖረው ለራሱ በሚያደርገው እን

 

ክብካቤ ሳይሆን በፍቅር እንደሆነ ተገንዝቤአለሁ፡፡

ሊዮ ቶልስቶይ

(ሩሲያዊ ደራሲ)

ስትስመኝ ነበር የተወለድኩት፡፡ በህይወት የኖርኩትም ስታፈቅረኝ በነበረበት ጥቂት ሳምንታት ያህል ነው፡፡ ትታኝ ስትሄድ ሞትኩኝ፡፡

ሃምፍሬይ ቦጋርት

(አሜሪካዊ አክተር)

 

 

 

Read 12885 times Last modified on Saturday, 14 January 2012 12:07