Monday, 25 May 2015 08:59

የፀሐፍት ጥግ

Written by 
Rate this item
(6 votes)

(ስለ ምርጫ)

ሰዎች ፖለቲካን የሚጠሉበት አንዱ ምክንያት የፖለቲከኞች ዓላማ እውነት ላይ ያነጣጠረ ባለመሆኑ ነው፡፡ የእነሱ ዓላማ ምርጫና ሥልጣን ነው፡፡
ካል ቶማስ
እንግሊዞች ነፃ ነን ብለው ያስባሉ፡፡ ነፃ የሚሆኑት ግን በፓርላማ አባላት ምርጫ ወቅት ብቻ ነው፡፡
ዣን ዠኪውስ ሩሶ
ይሄ አስደንጋጭ መረጃ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ከአሜሪካ ምርጫ ይልቅ ለ“አሜሪካ አይዶል” ድምፃቸውን ይሰጣሉ፡፡
Rush Limbaugh
ሰዎች ከአደን በኋላ፣ በጦርነት ወቅትና ከምርጫ በፊት የሚዋሹትን ያህል መቼም አይዋሹም፡፡
ኦቶ ቦን ቢስማርክ
አሸነፍንም ተሸነፍንም ከምርጫው በኋላ ለሸመታ ገበያ እንወጣለን፡፡
ኢሜልዳ ማርቆስ
ከሰዎች በሚሰበሰበው አስተያየት ሁልጊዜም ምርጫውን እሸነፋለሁ፤ በምርጫው ቀን ግን ሁልጊዜም አሸናፊው እኔ ነኝ፡፡
ቤንጃሚን ኔታንያሁ
የምርጫ ዓላማ ሲጠቃለል የህዝብን ፍላጎት መስማት እንጂ ድምፆችን (Votes) መፈብረክ አይደለም፡፡
ሊንከን ድያዝ - ባላርት
ሁላችንም ምርጥ ለምንለው ሰው ድምፃችንን መስጠት እንፈልጋን፤ ነገር ግን ፈፅሞ በእጩነት አልቀረበልንም፡፡
ኪን ሁባርድ
የነፃ ምርጫ ችግሩ ማን እንደሚያሸንፍ ፈፅሞ አለመታወቁ ነው፡፡
ሊኦኒድ ብሬዠኔቭ
መጥፎ ባለሥልጣናት የሚመረጡት ድምፅ በማይሰጡ መልካም ዜጎች ነው፡፡
ጆርጅ ዣን ናታን
እውነት በአብላጫ ድምፅ አይወሰንም፡፡
Doug Gwyn
በአሜሪካ በሁለቱም ፓርቲዎች ውስጥ በርካታ የመርህ ሰዎች አሉ፤ በመርህ የሚመራ ፓርቲ ግን የለም፡፡
አሌክሲስ ዲ ቶኪውቪሌ
ዲሞክራሲ ለሁሉም ሰው የራሱ ጨቋኝ የመሆን መብት ያጎናፅፈዋል፡፡
ጄምስ ራስል ሎዌል
ድምፅ መመዘን እንጂ መቆጠር የለበትም፡፡
ፍሬድሪክ ሺለር
ከተመረጥኩ ደስተኛ እሆናለሁ፤ ባልመረጥም እንደዛው ነው፡፡
አብርሃም ሊንከን

Read 3046 times