Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 28 January 2012 13:12

አፋጣኝ......ቅድ...... (PMTCT Emergency Plan )…

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ኢትዮጵያ ውስጥ ፡-

በዚህ አመት ወደ 2.9 ሚሊዮን የሚሆኑ እናቶች እርግዝና ላይ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

ወደ 90.000 የሚሆኑት ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ናቸው ተብሎ ይገመታል፡፡

በዚህ አመት ወደ 14.000 የሚሆኑ ሕጻናት ኤችአይቪ ቫይረስ ከእናታቸው ይወርሳሉ የሚል ግምት አለ ፡፡

“በአለም ላይ የህጻናትን የኤችአይቪ ስርጭት በሚመለከት ይበልጡን ድርሻ የሚይዘው ከእናት ወደልጅ በሚኖረው መተላለፍ መሆኑ ተረጋግጦአል፡፡ ቀደም ሲል የወጣ አንድ መረጃ እንደሚጠቁመው በአለም ላይ በየቀኑ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ህጻናት በኤችአይቪ ቫይረስ ይያዛሉ፡፡ ሕጻናት በኤችአይቪ ቫይረስ የሚያዙበት ምክንያትም ይበልጡኑ በእርግዝና ፣በወሊድ ወቅት እና በጡት ማጥባት ጊዜ እንደሆነም ይታወቃል፡፡ በቫይረሱ ከተያዙት ህጻናት መካከልም አብዛኞቹ የአምስት አመት እድሜያቸውን የልደት በአል ሳያከብሩ ይሞታሉ፡፡

ሕጻናትን ከኤችአይቪ ስርጭት መታደግ ማለት የወደፊቱን ትውልድ ከኤችአይቪ ቫይረስ ነጻ ማድረግ መቻል ስለሚሆን ጠንክረን መስራት አለብን፡፡ ጠንክረን ከሰራን የምንፈልገውን ውጤት እናገኛለን፡፡”

የቀድሞው የአሜሪን ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ጁን 19/2002

በዘንድሮው   የአፍሪካውያን የኤችአይቪ ስብሰባ ከተነሱት አበይት ነጥቦች መካከል አንዱ ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ በየህክምና ተቋማቱ የሚሰሩት ስራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ አፋጣኝ የሆነ ፕላን ቂስቈሸስቃሰቨ ሓቁሮቃ  ያስፈልጋል የሚል ይገኝበታል፡፡

ኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ፡-

ቀደም ሲል የነበረው ስርጭቱን የመከላከል ስራራ ምን ይመስል ነበር ?

ይህ አፋጣኝ እቅድ ለምን አስፈለገ?

አፋጣኙ የ ፒኤምቲሲቲ እቅድ በምን መልክ ተግባራራዊ ይሆናል?

ከህብረተሰቡስ ምን ይጠበቃል...ወዘተ

ከላይ የተነሱትን ሀሳቦች እንዲያብራሩ የተጋበዙት ዶ/ር ታደሰ ከተማ በኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የእናቶች ጤና አማካሪ ናቸው፡፡

ኤችአይቪ ኤይድስና የአባላዘር በሽታዎች እንዲሁም ኤችአይቪ ኤይድሰ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ (PMTCT) እንዲሁም ከእናቶችና ከህጻናት ጋር የተያየዙ በሽታዎችን በሚመለከት በርካታ ጥናታዊ ስራዎች እና ተሞክሮዎች በስብሰባው እንደቀረቡ የገለጹት ዶ/ር ታደሰ በተለይም ከኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ PMTCT ን በሚመለከት በአፋጣኝ ግብን ለመምታት የሚያስችል ፕላን ተቀርጾ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የአለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች በተገኙበት ይፋ ሆኖአል፡፡

አፋጣኙ ፕላን የታቀደው በኢትዮጵያ ውስጥ ከፕሮግራሙ ጋር በተያያዘ ከሚነሱ ችግሮች ነው፡፡ በእርግጥ ኢትጵያ ውስጥ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም በ2015/ ከሚጠበቀው የጤና ልማት መርሀ ግብር ከእናት ወደልጅ ቫይረሱ እንዳይተላለፍ 80 ለሚሆኑት እናቶች የህክምና አገልግት መስጠት የሚል እቅድ ተይዞአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአለም አቀፍ ደረጃ በሕጻንነት የሚኖረውን Syphilis የተሰኘውን ሕመም ለማጥፋት እቅድ የተያዘ ሲሆን ኢትዮጵያም የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥላ ስር እንደመሆንዋ እቅዱን ተቀብላለች፡፡ ስለዚህ እነዚህን ትልልቅ ግቦች ለማሳካት አሁን ካለንበት ሁኔታ ሲነጻጸር በጣም ብዙ ነገር መስራት ስለሚጠበቅብን ይህ አሁን የወጣው አፋጣኝ ፕላን አስፈላጊ ሆኖአል ብለዋል ዶ/ር ታደሰ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በዚህ አመት 2004 ዓ/ም ወደ 2.9 ሚሊዮን የሚሆኑ እናቶች እርጉዝ እንደሚሆኑና ከነዚህም ውስጥ ወደ 90.000 የሚሆኑት ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ናቸው ተብሎ ይገመታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በ2004/ዓም ወደ 14.000 የሚሆኑ ሕጻናት ኤችአይቪ ቫይረስ ከእናታቸው ይወርሳሉ የሚል ግምት አለ፡፡ ከላይ የተጠቀሰውን በኤችአይቪ ምክንያት የሚከሰት ችግር ለማስቀረት ከእናት ወደልጅ ቫይረሱ እንዳይተላለፍ ለማድረግ የተነደፈው መርሀ ግብር በብዙ ጤና ተቋማት ውስጥ መድሀኒቱ እንዲሰጥ ተደርጎአል፡፡ ነገር ግን እስከአሁን ከተደረገው እንቅስቃሴ ውጤቱ ሲለካ ከእናት ወደልጅ ኤችአይቪ ቫይረስ እንዳይተላለፍ ለማድረግ መድሀኒቱን ያገኙ እናቶች ቁጥር ከአጠቃላዩ ሲታይ 9.3  ብቻ ናቸው፡፡ ስለዚህ በ2015/ ተጠቃሚዎቹን 80  ለማድረስ በጣም ከፍተኛ የሆነ እሩጫ ያስፈልገዋል፡፡ የአገልግሎ ቱን በስፋት ያለመዳረስ ሁኔታ ምክንያቱ ምንድነው የሚለውን ለማጥናት ተሞክሮ ከተገኘው ውጤት አንዱ ሁሉም የህክምና ተቋማት አገልግሎቱን አለመስጠታቸው ነው፡፡ እንደ ዶ/ር ታደሰ በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ሁለት ሺህ ስድስ መቶ ስድሳ አምስት 2665 የሚሆኑ የጤና ጣቢያዎችና ወደ አንድ መቶ ሀያ ሁለት 122 የሚሆኑ ሆስፒታሎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የ PMTCT አገልግሎት የሚሰጡት ግን አንድ ሺህ አራት መቶ አርባ አምስት 1445 ብቻ ናቸው፡፡ ስለዚህ፡-

1/ አገልግሎቱ በሌለበት ቦታ ላይ ስራውን በፍጥነት መጀመር አንዱ የአፋጥኝ እቅዱ ትኩረት ነው፡፡

2/ አገልግሎቱ በሚሰጥበት ቦታም የተጠቃሚዎች ሁኔታም አጥጋቢ አለመሆኑ መፈተሸና መስተካከል የሚገባው መሆኑን ነው ፕላኑ የሚያመላክተው፡፡ በጤና ተቋማት መጥተው የህምና አገልግሎቱን የማያገኙ እናቶች አሉ፡፡ በአንድ አመት ውስጥ ወደ ጤና ተቋማት መጥተው አገልግሎቱን ያላገኙ እናቶች ወደ 300.000 ይደርሳሉ፡፡

አገልግሎቱን መውሰድ ጀምረው በመሀል የሚያቋርጡ እናቶች በጣም በርካታ ናቸው፡፡በእርግዝና ጊዜ መመርመር ፣ከተመረመሩ በሁዋላ በጊዜው መድሀኒት መውሰድ፣ በወሊድ ጊዜ የሚደረግ ጥንቃቄ፣ ለሕጻኑ የሚደረግለት ክትትል...ወዘተ ከላይ የተጠቀሰውን ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ አፋጣኝ እቅድ የሕክምና አገልግሎቱን ጥራት እንዲሻሻል እና ለሚፈልጉ ሁሉ እንዲዳረስ እንዲሁም አገልግሎቱን አቋርጠው የሚመለሱትን እናቶች አፈላልጎ በማግኘት ወደአገልግሎቱ እንዲመለሱ ለማድረግ የሚያስችል የጥራት ማሻሻያ ወይንም የማጠናከሪያ ስራ አገልግሎቱን በሚሰጡት ተቋማትና ባለሙያዎች ላይ መስራት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል ፡፡

3/   ህብረተሰቡ ከግንዛቤ ማጣት እንዲሁም ከተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ የጤና ተቋማትን ያለመጠቀም ሁኔታ ይታይበታል፡፡፡፡ ከዚህ አኩዋያም የጤና ተቋምን አገልግሎት ፍላጎት መጨመር የሚያስችል የግንዛቤ ማስፋት ስራ አስፈላጊ ነው፡፡ይህም የሚሰራው የጤና ልማት ሰራዊት በሚባሉት ባለሙያዎች ሲሆን እነርሱ የጤና ተቋም አጠቃቀምን ፍላጎት የሚጨምር ስራዎችን እንዲሰሩ በማድረግ የተጠቃሚዎችን ቁጥር እንዲጨምሩ ለማድረግ የታቀደ አሰራር ነው፡፡

4/  አገልግሎቱ ከተሰጠ በሁዋላ የክትትልና ድጋፍ ስራ ያስፈልጋል፡፡ በአጠቃላይ የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎት በትክክል መመዝገብና ሪፖርት ማድረግ እንዲሁም ከላይ ወደታች ድጋፍ የሚሰጥበትን ሁኔታ እንዲጠናከር ማድረግ አስፈላጊነቱ ስለታመ ነበት በአፋጣኝ ጊዜ ፕላኑ ተነድፏል፡፡ዶ/ር ታደሰ ከተማ በኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የእናቶች ጤና አማካሪ በስተመጨረሻው እንደገለጹት ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የአለም ጤና ድርጅትን የሓልማ ን አዲስ አሰራር የተቀበለች ሲሆን ይህም የአፋጣኝ ጊዜ እቅድ (Emergency Plan )  አብሮ ተቀናጅቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሁሉም በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የጤና ተቋማት እንዲተገበር ለማድረግ ጥረቱ ይቀጥላል፡፡

 

 

Read 2770 times Last modified on Saturday, 28 January 2012 13:19