Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 18 February 2012 10:26

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(13 votes)

ሐይቅ

(ዮሐንስ አድማሱ)

አለፈ ወጀቡ፣

ጸጥ ባለ ወጀቡ፣

ረጋ ባሕሩ …

ጥልቀቱን ደብቆ፣

ረጋ ባሕሩ …

ይሰፉበት ጀመር ዝይና ይብራው፡፡”

ባለጀልቦው መጣ፣ ጀልባ ላይ ቁጭ ብሎ፣

ቁጠኛውን ባህር እልከኛውን፣

እየኮረኮረው፣

እየሰነጠቀው እየቀዘፈው፡፡

ሄበሎው፣ ቄጠማው፣ ረዣዥም ሳር፣

መሰል ብለው ወጥተው፣

ይዘዋል ዝማሜ እጅግ የለዘበ፡፡

ይህ ሁሉ አንድነት፣

የድንገት ውበት፣

ድቅን ሲል ከፊት፣

ቋንቋም የለው ስሜት ከዝምታ ሌላ፣

አይቶ ዝም፣ ሰምቶ ዝም፣ ይህንን ትንግርት፡፡

 

=====================================

ትዝታ

(ጸጋዬ ገብረ መድኅን)

ዓይንህን በዓይኔ ፀንሼ፣ የቀስቱን ጮራ እንደቋጠርኩ

ሌሊት በሕልሜ አማምጨህ፣ ሕመምህን እየፈጠርኩ

ጥላህን እንደለበስኩ

የፍቅራችንን ነበልባል፣ በቁም ሰመመን እንዳቀፍኩ

ልብ ውስጥ እንዳዜሙት ሙሾ፣ የሲቃ ስልት እንዳቃጨልኩ

የነፍሴን የእሳት ዘለላ ጎዳናህ ላይ እንዳነጠብኩ

እንደ ገደል ዳር ቄጠማ፣ የስጋት እምባ እንደቃተትኩ

ሕይወቴን ላንተ እንዳሸለብኩ

ሕልምህን በጄ እንደዳሰስኩ

ያን የመጀመሪያ ሞቴን፣ በመሸ ቁጥር እንደሞትኩ

አለሁ፣ እንደብኩን መረብ፣ ትዝታህን እንዳጠመድኩ፡፡

 

 

 

Read 6615 times Last modified on Saturday, 18 February 2012 10:30