Saturday, 25 February 2012 14:34

ህያው ስብሃት

Written by  ከበደ ደበሌ ሮቢ
Rate this item
(0 votes)

“ኢትዮጵያ አንድ ታላቅ ደራሲዋን አጥታለች”

“The seventh Seal” (ሠባተኛው ማኅተም) የዝነኛው ስውዲናዊ ደራሲ ኢንግማን በርግማን መጽሐፍ ርዕስ ነው፡፡ በመጽሐፉ ላይ አንዱ (ምናልባትም ዋናው) ገፀባህሪ ቼዝ የሚጫወት ሰው ነው፡፡ ትረካው የሚቀጥለው ይህ ዋነኛ ገፀ ባህሪ ቼዝ በመጫወት ላይ እያለ ሞት ወደሱ መጥቶ ልወስድህ መጥቻለሁ ሲለውና ከሞት ጋር ፊት ለፊት መፋጠጣቸውን በመግለጽ ነው፤ ሰውዬው በድንጋጤ ተውጦ አንተ ልትወስደኝ ብትመጣም እኔ ግን ሥራዬን አልጨረስኩም ይለዋል ለሞት፡፡ ከዚያ የመጽሐፉ ዋነኛ ገፀ ባህሪና ሞት (ሁለቱ) ቼዝ መጫወት ይጀምራሉ፤ ጨዋታችንን እንደጨረስን እወስድሃለሁ…ብሎት፡፡
ከአውሮጳዊቱ ስዊዲን ወደ ላቲን አሜሪካ ስንመጣ ደግሞ አንድ ሌላ መጽሐፍ እናገኛለን፡፡ ከላቲን ስመ ጥር ደራሲያን በአንደኛው ሊቀ ጠቢብ አንድ ጽሑፍ ላይ ከአምላክ ጋር በመንፈስ ብርሃን የመገናኘታቸው ሂደት እንዳይቋረጥ እንዲፋጠንና እንዲሰፋ በቅድስና የሚተጉ ገፀ ባህሪ በእግራቸው ሲጓዙ እናያለን፡፡ እኒህ ሰው በጉዞ ላይ እያሉ ማን እንደወረወረው ባይታወቅም ጦር ወደሳቸው ይወረወራል፡፡ በአየር ውስጥ እየተምዘገዘገ ወደሣቸው የሚፈጥነውን ጦር ባዩ ጊዜ በለሆሳስ መፀለይ ጀመሩ፤ አምላኬ ሆይ:- በዚህች ምድር ላይ መከወን የሚገባኝን ሥራ አልጨረስኩምና እስክጨርስ ድረስ የሞት መውጊያ ለእኔ አይሁን፡፡ ፀሎታቸውን ጨርሰው ቀና ቢሉ ወደሳቸው በመምዘግዘግ ላይ የነበረው ጦር መምዘግዘጉ ተገትቷል፡፡ ጉዞአቸውን ቀጠሉ፡፡ ብዙ ምዕራፍ ከተጓዙ በኋላ መድረሻ ሥፍራቸው ጋ ሲደርሱ ጉዞአቸው ተጠናቀቀ፡፡ እናም ጊዜ ጅም (እብስ) እያለ በዚህች ምድር ላይ በአፀደ ሥጋ እያሉ መከወን የሚገባቸውን ተግባር አከናውነው ጨረሱ፡፡
በዚህ ጊዜ ወደ አምላካቸው በማሰላሰል ተጉና እንዲህ አሉት፤ አሁን ሥራዬን ጨርሻለሁ…የሞት መውጊያ ለእኔ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህቺ ቃል ከአንደበታቸው በወጣችበት ቅጽበት አየር ላይ መምዘግዘጉ ተገትቶ የነበረው ጦር ወደሳቸው መምዘግዘጉን ቀጠለ፡፡
ከጥቂት ቅጽበቶች በኋላ አካልና ጦር ሲገናኙ በቅድስና የሚተጉት በጐ ሰው ደም ዠረርር እያለ ወረደ፤ ነፍሳቸውም ወደ አምላካቸው መጣደፍን ናፈቀች…
ሁለቱንም የህልፈት (በአፀደ ሥጋ ከዚህች ዓለም የመለየት) ወጐች ከስዊዲንና ከላቲን አዋርሶ ባማረ ቃናና ለዛ ያጫወተኝ ታላቅ አእምሮ ያለው፤ በጣም ሩህሩህ አዛኝ፤ ሁሌም ጢም ባለ ፍቅርና መነካት የተሞላው፤ ትሁትና ጨዋ ነፃ ህፃን ነው፡፡ ዕድሜው ሰባ አምስት ዓመት ነው፤ ነገር ግን ህፃን ነው፤ ሁሌም ህፃን የትም ህፃን፤ ትልቅና ታላቅ አእምሮ ያለው አዛኝ ህፃን - ስብሃት ገ/እግዚአብሄር፡፡ ከአሥር ዓመት በፊት ይመስለኛል፤ እዚሁ እመዲናችን ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ውስጥ ደራሲያንና የጥበብ ቤተሰቦች ተሰባስበን መጽሐፍ ስናስመርቅ በታላቅ ግርማና በመነካት በስልሳ አምስት ዓመት አዛውንት አካልህ ውስጥ የአንድ ዓመት ህፃን ነፍስ ትታየኛለች፡፡
ከአሥራ ሁለት ዓመታት በፊት ግድም ላፍቶ አካባቢ ሲኖር ታምሞ ሰውነቱ ሳስቶብኝ ባይ በፍቅርና በርህራሄ በመንሰፍሰፍ አዝኜ ሥጋት ባዳመነው ፀጥታ ተዋጥኩ፤ ብዙም ወራት ሳይቆጠሩ ሰውነቱ ተመልሶ ጉድባ ለመዝለል እመር ሲል ሳይ ደግሞ ነፍሴ ተመልሶ ከአሁን በኋላ ባሉት ጊዜያት ሃያ እና ሰላሳ ዓመታት ወደፊት እያየሁ ልቤን ደስ አለው፡፡
የካቲት 12 ቀን 2004 ዓ.ም የጋሼ ስብሃት ሥርዓተ ቀብር በተፈፀመበት ዕለት ከሠላሳ ሺህ እስከ ሰማንያ ሺህ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በአዲስ አበባ ከተማ በግፍና በገፍ በተጨፈጨፉበት ዕለተ ሰማዕታት  ሰባ አምስተኛ ዓመት ላይ፣ ከአዲስ አድማስ ጊቢ ወደ ውጪ በመውጣት ላይ እያለሁ እፁብ የምላት ተወዳጅ ልጅ ጠራችኝና ቀብር ትሄድ እንደሆን ብዬ ነው አለችኝ፡፡ በተመስጥኦ ሳሰላስል ቆየሁና “ጋሼ ስብሃት በእግዚአብሔር የብርሃን እቅፍ ውስጥ ገብቷል” አልኳት፡፡ ስብሀት በእኔ ውስጥ ህያው ነው፤ በእኔ የልብ ጽላት ውስጥ ተቀብሮአል፤ የእርሱ አካል የሚገባበት አፈር እንኳን የተቀደሰ ነው፡፡ እኔ ቀብር አልሄድም፤ ህያው ስብሀት ለዘላለሙ በህያውነት በእኔ ውስጥ እስከወዲያኛው ይኖራል፡፡ ይልቅ “ህያው ስብሀት” የሚል ጽሑፍ እፅፋለሁ አልኩ፡፡
በጉርምሥናው ወራት የፃፋቸው ቄንጠኛና ያማሩ መጽሐፍቱ በተገለጠ ወሲብ የተሞሉ (Pornographic) ናቸው በሚል የህትመት ብርሃን ያገኙት ህፃኑ ታላቅ አእምሮ ከሸመገለ በኋላ ነው፡፡ መጀመሪያ ወሲባዊ መገለጣቸው ኤዲት ተደርጐ ቀጥሎ ደግሞ እንደወረዱ የታተሙት በቅርቡ ነው፤ ከዛሬ አሥራ ዘጠኝና ሃያ ዓመታት በፊት የስብሃት አንዱም መፃሕፍት ሳይታተም፤ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ “ፍኖት” በሚል መጽሔት “ፊሎ” በሚል ርዕስ የዝነኛው ኢትዮጵያዊ ደራሲ ስብሀት መፃሕፍት በተለያዩ ኢትዮጵያዊ ቋንቋዎች ሲታተሙ አሳይቷል፡፡ “ፍኖት” መንገድ ማለት ነው፤ ፍኖተ ጥበብ ፍኖተ ሠላም ፎኖተ ብርሃን…፤ ፊሎ ደግሞ ጥበብ ማለት ነው፤ ፊሎዞፊያ የጥበብ ፍቅር፡፡
ከጥቂት ዓመታት በፊት በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ኅብረ ቀለም የኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ የምትገኘዋን ኮከብ በመሳል ያሸነፈው፤ ብርሃን የፈነጠቀበት ስመ ጥሩው ወጣት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ፣ ባለቅኔና ገጣሚ መሥፍን ሀብተማርያም በአፀደ ስጋ ሲለየን ከጋሼ ስብሃት ለአብ ገብረ እግዚአብሔር ጋር በቀጨኔ መድኅኔዓለም ቤተክርስቲያን በሥርዓተ ቀብሩ ላይ ተገኘን፡፡ ከሥርዓተ ቀብሩ ገለል ብለን ስለ ህያውነትና በአካለ ሥጋ ስለመለየት ብዙ ተጫወትን፡፡ ይኸውም እንዲህ ነው፡- መስፍን በእኔ ውስጥ ህያው ነው፤ የእግዚአብሔር አካል የሆነች ነፍስ በውስጤ አለች፣ የመስፍን ነፍስ የዚህች ነፍስ አካል ነች፡- ይሄ እውቀት ነው፤ የመጀመሪያው (መሥፍን በእኔ ውስጥ ህያው መሆኑ) ደግሞ ስሜት ነው፡፡ መስፍን በእኔ ውስጥ ህያው እንደሆነ ይሰማኛል፤ ይታወቀኛል፤ ስሜት ልትለው ትችላለህ፤ አቅል ልትለው ትችላለህ፤ የደመ ነፍስ እውቀት ልትለው ትችላለህ፤ የመንፈስ እውቀት ልትለው ትችላለህ፡፡ መስፍን በእኔ ውስጥ ህያው መሆኑ መታወቁ ግን እውነት ነው፤ ለዘላለም በእኔ ውስጥ መኖሩና ህያውነቱ ይሰማኛል…፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ባነብ ባላነብ፤ ኪታብ አል አቅዳስ ባነብ ባላነብ፤ ከሀቫጋድ ጊታ ባነብ ባላነብ፤ ቅዱስ ቁርዓን ባነብ ባላነብ፤ ፒታካስ ባነብ ባላነብ… ከህፃንነቴ ጀምሮ የማውቀው አንድ ነገር የሰው ልጅ በውስጡ ዘላለማዊ የሆነ የማይሞት ማንነት ያለ መሆኑ ነው፡- ይህም የአምላክ ባህሪ መገለጫና የአምላክ ህልውና አካል የሆነ በበጐነትና በፍቅር፣ በቅድስናና በላቀው ከፍተኛው እውቀት፣ በርህራሄና በደግነት በንጽህና የተመላ (ሠብአዊ) ማንነቱ ነው፡፡ ይሄ እውቀትና “ስሜት” በኔ የልብ ጽላት ላይ በእግዚብሔር ጣቶች የተፃፈ እውነት ነው፡፡ ነፍስ ሣውቅና ትንሽ ከፍ ስል አስቀድሞ በልቤ ላይ የተፃፈውን በመጽሐፍ ቅዱስና በሌሎች ሃይማኖቶች ቅዱሳን መፃሕፍት ላይ ተጽፎ አገኘሁት፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት ሁለት ሰባት ላይ፤ እግዚአብሔር ሰውን ከጭቃ አፈር አበጀው በአፍንጫውም የህይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ህያው ነፍስ ያለው ሆነ ይላል፤ እንዲሁም በትንቢተ ኤርሚያስ አንድ አምስት ላይ፤ በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ በማህፀን ሳለህ ቀድሼሃለሁ ተብሎ ተጽፎአል፡፡ በኦሪትም ሆነ በኤርሚያስ ላይ የተፃፈው ሁለቱም ከባዮሎጂ ከፍ ያለና (ለየት ያለ) እውቀት ነው፡፡
ሠባት መቶ ሚሊዮን ምዕመን ያላቸው ኢንዱዎችና ሶስት መቶ ሚሊየን አማኝ ያላቸው ቡድሂስቶችም አቀራረቡ ይለያይ እንጂ ልክ እንዲህ እንደተወሳው ያምናሉ፡፡ አንድ ሰው ነፍሱ የመጨረሻው የአምላካዊ ባህሪው ብቃትና ፍጽምና [(ፍልቅቅ ፍንጥቅ ያለ ሀሴት) (NIRVANA)] ላይ እስክትደርስ ድረስ በሰው በእንስሳትና በዛፎች አማካይነት ከአንዱ አካል ወደ ሌላው አካል የምታደርገው የመተላለፍ ዑደት (ሪኢንካርኔሽን) ይቀጥላል፡፡ በሌሎች ፍልስፍናዎችም እንዲሁ ይሄን የመሰለ ሃሳብ አለ፡፡
ህያው ስብሀት፤ ህፃን ስብሀት ያደገ ነፍስና የበለፀገ አእምሮ፣ የሚያምር አካልና የዋህ ቅን አዛኝ ሩህሩህ ደግ ልብ ያለው፤ ከማናቸውም የአስተሳሰብ እሥራት የተፈታ የተለቀቀና የተላቀቀ (Released)…ትልቅና ታላቅ ሠብዕና ያለው በጐ ህፃን ነው፡፡  ቤቴ ውስጥ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ይሄ ሰው ሰይፍ ወይም ካራ ይዞ በበር ወይም በመስኮት ገብቶ አንገቴን ቢቀላውና አንድ ሰው አንገቱ ከተቆረጠ በኋላ ማሰብና መናገር የሚችል ቢሆን ይሄንን ታላቅ አእምሮ ያለው ህፃን የምለው አንድ ቃል “ምን ነካህ ጋሼ ስብሃት” የሚል (ቃል) ነው፡፡ በጭራሽ ልቀየመውም ሆነ ቅንጣት ታህል ቅር ልሰኝበት አልችልም፡፡ ለምን ቢሉ፤ ለምን እንደሆነ እኔም አላውቀውም፡፡
ህያው ስብሀት መቼም የትም ለእግዚአብሔር የቀረበ ባህሪ ያለው ህፃን ነው፤ ትልቅና ታላቅ አእምሮ ያለው አዛኝ ህጻን፡፡ ሥልጡን ደግ አዋቂ ሊቀ ጠቢብ የሆነ ልቡን ግንባሩ ላይ የምታየው በጐ ህፃን፡፡ በፍቅር የተመላ ግልጽና ነፃ ህፃን፡፡ የእግዚአብሔር ብርሃን በህፃን ውስጥ ካለአንዳች ሁከትና ታክል እየተንፎለፎለ ያልፋል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅጽበት እንኳ ዓይኖቹን ከእግዚአብሔር አብ ዓይኖች ላይ የማያነሳ መልአክ የህፃናት መልዐክ መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በግልጽ ተናግሮአል፡፡ ስብሀት እንደ ህፃን ሳይሆን ህፃን ነው፡፡ እንደ ህፃን መሆንም አንድ ፀጋ ነው፤ እንደ ህፃን ሳይሆን ህፃን መሆን ደግሞ ከዚያም የሚበልጥ ትፍሥህት ነው፡፡
ያንን ህፃን ታላቅ አአምሮ ያለው ባለሙሉ ችሎታ ደራሲና ጋዜጠኛ፣ አሰላሳይና የራሱ ጌታ ብርቱ ኤዲተርና ተርጓሚ፣ ተዋናይና መምህር ዛሬ አጥተነዋል፡፡ ኢትዮጵያ አንድ ታላቅ ደራሲዋን አጥታለች፡፡ አፍሪቃውያን ከሚወድዷቸው ምሣሌያዊ ንግግሮቻቸው አንዱ “አንድ አዛውንት የሆነ ሰው ሲሞት ሀዘንና ጉዳቱ አንድ ቤተ መፃሕፍት የተቃጠለ ያህል ነው” የሚል፡፡ በዚያ ሽማግሌ አእምሮ በአንድ ቤተ መጻሕፍት በሚገኙ መጽሐፎች ውስጥ ካለው እውቀት ጋር የሚተካከል የተከማቸ እውቀት አለ ለማለት ነው፡፡
ህያው ስብሀት (የሰባ አምስት ዓመቱ አዛውንት፤ ታላቅ አእምሮ ያለው ህፃን ስብሀት) ደግሞ ከዚህ መወሳት እጅግ በላይ ነው፡፡
“ዴሊታንት” ነው ያለው ዘነበ ወላ “ማስታወሻ” ላይ፤ በሁሉም ነገር የተሟላና የላቀ ሠብዕና ለማለት፡፡ ስብሀት ለእኔ ከዚህም በላይ ነው፡፡ ትልቅና ታላቅ እእምሮ ያለው ህፃን፡፡ ከሁሉም ይልቅ ለእግዚአብሔር ባህሪ የቀረበ ነው፡፡ እግዚአብሔር በእውቀቱ እጅግ የላቀ፤ በፍቅሩ ሙላት በቅንነቱ በበጐነቱና በርህራሄው (በልቡ) የዋህ ነው፡፡
አብርሃም ከሰዶምና ጐሞራ ጥፋት በኋላ እግዚአብሔርን ሃምሳ ሰው ቢፀልይ ኖሮ ይሄ የቁጣ ቅጣት ላይደርስ ይችል ነበር ወይ ብሎ ጠየቀው፤ አዎን አለ እግዚአብሔር፤ አርባ አምስት ሰው ቢፀልይስ፤ አዎን ይሄ ጥፋት አይደርስም ነበር አለ እግዚአብሔር፤ አርባ ሰው ቢፀልይስ፤ …ሠላሣ አምስት ሰው… ሠላሳ ሰው… ሃያ አምስት ሰው… ሃያ ሰው… አሥራ አምስት ሰው… አሥር ሰው …አምስት ሰው…እያለ ቀጠለ አብርሃም፡፡ እግዚአብሔር ለነዚህ ተከታታይ ጥያቄዎች ለአብርሃም የሰጠው መልስ አንድ ዓይነት ነው ፅንሠ ሃሳቡ፤ አዎን አልቆጣም ነበር የሚል፡፡ እግዚአብሔር በጣም ያልተወሳሰበ (ቀላል) እና ቅርብ ከመሆኑ የተነሣ ወደ ግብጽ ውረድ እኔ አብሬህ እወርዳለሁ ይላል መጽሐፍ ቅዱሥ ላይ፡፡ ስትታመም እግዚአብሔር አልጋህን ያነጥፍልሃል ይላል መዝሙረ ዳዊት ላይ፡፡ እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ሌላኛው ሥፍራ እግዚአብሔር ራሱ እኔ እንደናንተው መፃተኛ ነኝ ይላል፡፡
ህያው ስብሀት (ህፃን ስብሀት) አንዱ ባህሪው ሲምፕሊሲቲ ነው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ ሶስት የሩቅ ምሥራቅ ሰዎች ህፃኑን በአራስነቱ ሊያዩት ወደ መሀከለኛው ምሥራቅ ቤተልሄም መጡ፡፡ በህፃን መታቀፊያ ውስጥ ተኝቶ አገኙት፤ አይተው ጠግበው ተመልሰው ሲሄዱ እርስ በርሳቸው ማውራት የጀመሩት ስለ ህፃኑ ፊት ነው፤ አንደኛው የጐልማሳ ፊት ነው ያየሁት አለ፤ ሁለተኛው የህፃን ፊት ነው ያየሁት አለ፤ ሶስተኛው የሽማግሌ ፊት ነው ያየሁት አለ፡፡ ስለዚህ እውነቱን ለማጣራት በዳዊት ከተማ ወደተወለደው ህፃን ኢየሱስ ክርስቶስ ተመለሱ፡፡ ሶስቱም በድጋሚ የህፃኑን ፊት ትክ ብለው መመልከት ጀመሩ፡፡ እና ሲበቃቸው ወደመጡበት የመልስ ጉዞ ያደርጉ ያዙ፤ ትንሽ ቆይተው አሁንም ስለ ህፃኑ ፊት ማውራት ሲጀምሩ አንደኛው የህፃን ፊት ነው ያየሁት አለ፤ ሁለተኛው የሽማግሌ ፊት ነው ያየሁት አለ፤ ሶስተኛው የጐልማሳ ፊት ነው ያየሁት አለ፡፡ ስለዚህ ለመጨረሻ ጊዜ ለማጣራትና እርግጠኛ ለመሆን አሁንም ህፃኑ ወደተወለደበት የከብቶች ማደሪያ በረት ተመለሱ፡፡ ሶስቱም ለሶስተኛ ጊዜ ህፃኑን ትክ ብለው ለደቂቆች ሲመለከቱ ቆዩ፡፡ አይተው ሲበቃቸው የመልስ ጉዞ ማድረግ ጀመሩ፡፡ በመልስ ጉዞው ሂደት መወያየት ሲጀምሩ አንደኛው (የህፃን ፊትና የጐልማሣ ፊት ነው ያየሁት ብሎ የነበረው) የሽማግሌ ፊት ነው ያየሁት አለ፡፡ ሁለተኛው (የህፃን ፊትና የሽማግሌ ፊት ነው ያየሁት ብሎ የነበረው) የጐልማሳ ፊት ነው ያየሁት አለ፤ ሶስተኛው (የሽማግሌ ፊትና የጐልማሳ ፊት ነው ያየሁት ብሎ የነበረው) የህፃን ፊት ነው ያየሁት አለ፡፡
ህፃን ስብሀት ፡- መልኩ የሚያምር፤ እጅ ጽሑፉ የሚያምር፤ አነጋገሩ የሚያምር፤ አስተሳሰቡ የሚያምር፤ አፃፃፉ የሚያምር፤ መለቀቁና መላቀቁ የሚያምር፤ ነፃነቱና ግልጽነቱ የሚያምር፤ …አዛኝና ደግ ታላቅ አእምሮ ያለው ህፃን፤ ሁሉነገሩ የሚያምር ህያው እና ታላቅ ሰብዕና ነው፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ታላቁ ፐርሺያዊ ባለቅኔ ጀላሉዲን ሩሚ ያጫወተኝ ይሄ ትልቅና ታላቅ አአምሮ ያለው ህፃን ነው፡፡ ጀላሉዲን ሩሚ እንዴት ታላቅ ባለቅኔ እንደሆነ ነው የነገረኝ፡፡ ከዘጠኝ መቶ ዓመታት በፊት በሰሜን አፍሪካ ስደተኛ የነበረው ማይሞኒደስ ከታልሙድ ቀጥሎ ያለውን የአይሁድ ቅዱስ መጽሐፍ እንደፃፈ ሁሉ፤ ሩሚ ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት በጥንታዊ ፋርስ የኖረ ከቅዱስ ቁርዓን ቀጥሎ ያለውን የተቀደሰ ኢስላማዊ መጽሐፍ የፃፈ ኢራናዊ ባለቅኔና ደራሲ፣ ፈላስፋና ቅዱስ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔርን ካለ ነቢይ ማግኘት ይቻላል እግዚአብሔርን አታስቸግሩት የሚሉት ሱፊዎች የሱፊው ቅዱስ ይሉታል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን እቤቱ ውስጥ ተቀምጦ ግጥም ሲጽፍ ሩሚ የሚል የጥሪ ድምጽ ሰማ፡፡ ወደ ውጪ ሲወጣ ነጭ ሀር የመሰለ ፂማቸው ዠቅ ያለ፣ የፀዳ ነጭ ጀለቢያ የለበሱ፣ የተወለወለ ዘንግ የያዙ ደስ የሚሉ ባለግርማ ሽማግሌ በራፉ ላይ ቆመዋል፤ አያውቃቸውም፡፡ እስኪ ግጥሞችህን አምጣቸው አሉት፤ አመጣቸው፡፡ አንተ ከዚህ ለሚበልጥ ክብር ነው ወደ ምድር የተጠራኸው አሉና ቀዳደህ ጣላቸው አሉት፤ ግጥሞቹን ቀዳዶ ጣላቸው፡፡ ተከተለኝ አሉና አቀኑ፡፡ ተከተላቸው፡፡ ሩሚ በድጋሚ ወደ ቤቱ አልተመለሰም፤ ታላቅ ያሰኙትን ታላላቅ ሥራዎች የሰራው ግን ከዚህ በኋላ ባሉት ጊዜያት ነው፡፡
ሩሚ፤ እግዚአብሔርን ፈልጐ በመጨረሻ አገኘሁት የሚለው በማደሪያው በፀባኦቱ (በልቡ ውስጥ) ነው፡፡
ህያው ስብሃት፤ ለዘላለም በእኔ ልብ ውስጥ በህያውነት ፀንቶ ይኖራል፡፡ እንዲሁም በሌሎች የጥበብና የልቀት ቤተሰቦች ልብ ውስጥ፡፡ ይሄ ጽሑፍ ለዚያ ታላቅ አእምሮ ላለው በጐ ህፃን ወዳጆችና ቤተሰቦች መዘክርታ ቢሆን፤ በብዙ ፍቅር በከበረ ክብርና እጅግ ከፍ ባለ ትህትና እነሆ፡፡
ሠላምዎ ይብዛ! በፍቅር!
Soli. Deo.Gloria!

Read 18978 times Last modified on Saturday, 25 February 2012 15:32