Monday, 05 March 2012 13:08

የራፕ ሙዚቃ እንደ ቢዝነስ መመሪያ

Written by  አልአዛር ኬ
Rate this item
(0 votes)

ስለአሜሪካ ዝነኛ የሂፕ ሆፕ ሙዚቃ አቀንቃኞች ስታስቡ ድፍን አለሙን ሁሉ በአድናቆት እንዲያብድላቸው ያስገደዱበት ተወዳጅ የጥበብ ስራቸው ወደ አዕምሮአችሁ መምጣቱ አይቀርም፡፡ ከዚያ በመቀጠል ደግሞ ሥራቸው ያቀዳጃቸው ዝናና ባለጠግነታቸው ቢታሰባችሁ ጨርሶ የሚገርም አይደለም፡፡ ለምን ቢባል? የባለጠግነታቸው ነገር እንዲሁ ለወሬ ማጣፈጫ የሚቀርብ ሳይሆን አለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ስለሆነ ነው፡፡

እነዚህ የጥበብ ሰዎች ከዝነኝነታቸውና ከቱጃርነታቸው ጋር በተያያዘ በአለምአቀፍ ደረጃ ታዋቂ ያደረጋቸው አንድ ሌላ ባህርይ ደግሞ አላቸው፡፡ ምርጥ የጥበብ ስራ ለህዝብ በማቅረብ ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙትን ያህል፣ ያገኙትን ከፍተኛ ገንዘብ እንዲሁ ሜዳ ላይ የሚበትኑት እስኪመስል ድረስ ያሻቸውንና ያማራቸውን ማድረግ መውደዳቸው ነው፡፡ የእነዚህን ዝነኛ አሜሪካዊ የጥበብ ሰዎች ልክ የለሽ የገንዘብ አወጣጥ በተመለከተ ሁለት አይነት አስተያየቶች ይሰነዘራሉ፡፡
አንደኛው ስለ ነገ የማይጨነቁ፣ ጥሪታቸውን የትም የሚያባክኑ “አባ ዝራው” ናቸው የሚል ሲሆን ሌላኛው ሠርተው ያገኙትን ገንዘብ ለተሠራበት አላማ የሚያውሉ አሪፍ ሰዎች ናቸው የሚል ነው፡፡
በዝነኞቹ ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶች ቢሰነዘሩም ሁለት ነገሮች ግን ሳይለወጡ የሰዎቹ መገለጫ እንደሆኑ ቀጥለዋል፡፡ አርቲስቶቹ በጥበብ ችሎታቸው ምርጥ ስራዎችን አበርክተው አለማቀፋዊ ዝና ለመጐናፀፍና የከፍተኛ ሀብት ማማ ላይ ለመውጣት ችለዋል፡፡ ያገኙትንም ሀብት የእኛን የተለያየ አስተያየት ለእኛው ለራሳችን ብቻ ትተው፣ እነሱ ለወደዱት ጉዳይ በወደዱት መጠን እያወጡ ይጠቀሙበታል፡፡
በእርግጥም የእነዚህን ዝነኛ የሂፕ ሆፕ ሙዚቃ አቀንቃኞች የገንዘብ አወጣጥ ጉዳይ በዋናነት የሚመለከተው እነሱን ስለሆነ ነገርዬውን ማንሳትና መጣሉን ትተን አንድ አሪፍ ጥያቄ በመጠየቅ ስለአንድ ትልቅ ጉዳይ መነጋገር እንጀምር፡፡
ለመሆኑ ዝነኞቹ አርቲስቶች ስለስራና ሠርቶ ስለመክበር ለእኛ ብርሃን ሊሆነን የሚችል አንዳች አይነት ትምህርት ሊያስተምሩን ይችሉ ይሆን? “እንዴታ! ለዚያውም በተግባር የተፈተነ ምርጥ ትምህርት ያስተምሩናል” የሚል፡፡
የሙዚቃ ስልቶችን በተመለከተ እኛ የራሳችንን የሙዚቃ ስልቶች አምባሰል፣ ባቲ፣ አንቺ ሆዬ ወዘተ… እያልን  እንደምንጠራው ሁሉ አሜሪካኖችም ብሉዝ፣ ሀገረሰብ፣ ፖፕ፣ ሂፕ ሆፕ ወዘተ… እያሉ የሙዚቃ ስልታቸውን ይጠራሉ፡፡
ከተፈጠረበት ጊዜ አንፃር ሲታሰብ እንደ አፍላ ጐረምሳ ይቆጠራል የሚሉትን የራፕ የሙዚቃ ስልት አንዳንድ የሙዚቃ ባለሙያዎች፤ ራሱን እንደቻለ ሙሉ ስልት ሲቆጥሩት አንዳንዶች ደግሞ ዘሩንና ቤቱን ሂፕ ሆፕ ከሚሉት የሙዚቃ ስልት ይመድቡታል፡፡
የራፕን ሙዚቃ አሜሪካኖች በተለያየ ስልት እንደመደቡት እኛም ከፈለግን ከአሜሪካኖች ጋር በመስማማት፣ ካልፈለግን ደግሞ የራሳችንን ውሳኔ በመወሰን ካሻን የሙዚቃ ስልት ውስጥ ልንመድበው እንችላለን፡፡ ይህ ጉዳይ ጨርሶ ሊያጨቃጭቀን አይችልም፡፡
የራፕን የሙዚቃ ስልት የመውደድና ያለመውደድ ጉዳይም እንደዚሁ ነው፡፡ ወይ እንወደዋለን አለበለዚያ ደግሞ አንወደውም፡፡ አለቀ፡፡ ይሄ ምርጫችን እንደተጠበቀ ሆኖ የራፕ ሙዚቃዎችን በጥሞና እያዳመጥን፣ በየዘፈኖቹ የቀረበውን መልእክት በጥሞና ከመረመርን ስለቢዝነስና ሰርቶ ስለመክበር መሠረታዊ የስኬት እውቀት መጨበጥ እንችላለን፡፡
ይህ ጉዳይ የማይመስልና ተራ ግምት ከመሠላችሁ በእርግጥ ተሳስታችኋል፡፡ እንዴት ብትሉ… በርካታ የቢዝነስ ባለሙያዎች የመሠከሩለት ሃቅ ነውና፡፡
አብዛኞቹ የራፕ ዘፈኖች የቢዝነስና የፉክክር መልእክቶችን ያያዙ እንደሆኑ የራፕ ሙዚቃ አፍቃሪዎች ይመሰክራሉ፡፡ በአብዛኞቹ የራፕ ዘፈኖች ውስጥ ስለ ስሜትና ይህንን ስሜት መፍጠር ስለሚችለው ነገር የሚያስገነዝቡ የተለያዩ ጉዳዮች ይነሳሉ፡፡ ቢዝነስንና የቢዝነስ አሠራርን በተመለከተ በተለይ ደግሞ ከፍተኛና ስትራተጂካዊ የቢዝነስ ውሳኔዎችን በመወሰን በኩል ወሳኙን ሚና የሚጫወተው ከአመክንዮአዊ (logical) አስተሳሰብ ይልቅ በጉዳዩ ላይ ያለን ስሜት ነው፡፡
ሙዚቃ በየትኛውም ስልት ቢቀርብ አድማጩ ቀልቡን ሰብስቦ በአዕምሮው ጓዳ ያለውን የተለያየ ሀሳብ መልክ ባለው ሁኔታ እንዲያቀናጅና እንዲያሰናዳ፣ ተቀናጅቶ የተሠናዳውን ሀሳብም በወጉ በጽሑፍ ማስፈር እንዲችልና ተገቢ ነው ብሎ የመረጠውን ውሳኔም እንዲወስን በሚገባ እንደሚያግዙት በዘርፉ ጥናት ያደረጉ የስነልቦና ምሁራን ይገልፃሉ፡፡
የዚህን ጉዳይ እርግጠኛነት ግሩፓን እና ስካይፕ በተባሉ ኩባንያዎች ውስጥ ገንዘቡን ኢንቨስት በማድረግ፣ ቢጠሩት የማይሰማ ሚሊዬነር ቀጭን ጌታ መሆን የቻለው የአንደርሰን ሆሮዊትዝ ኩባንያ ተባባሪ መስራችና ባለቤት አሜሪካዊው ቤን ሆሮዊትዝ ሲናገር፤ “ከፍተኛ ስትራተጂካዊ የቢዝነስ ውሳኔዎችን እንዴትና በምን ሁኔታ መወሰን እንዳለብኝ የሚያነቃቃኝና ትክክለኛውን አቅጣጫ የሚያስይዘኝ አንድ ምርጥ የቢዝነስ አማካሪ አለኝ፡፡ እሱም ሌላ ሳይሆን የራፕ/የሂፕሆፕ ሙዚቃ ብቻ ነው” ብሏል፡፡ በኮሎራዶ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ አሜሪካውያን ስነጽሑፍ ተባባሪ ፕሮፌሰር አቶ አዳም ብራድሊ ደግሞ “የራፕ ሙዚቃዎች በቢዝነስ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የማይሰጡ የተለያዩ ድንቅ የቢዝነስ የስራ አመራር ትምህርቶችን ይዘዋል” በማለት የራፕ ሙዚቃ በቢዝነስ ጉዳይ ላይ ያለው ጠቃሚ መልእክት የዋዛ አለመሆኑን እማኝነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ከዚህ በላይ የቀረቡት ገለፃዎች የሚያስገነዝቡንና የሚያረጋግጡልን አንድ እውነት አለ፡፡ ይኸውም ከራፕ ሙዚቃ የቢዝነስን አመራር ወይንም ሠርቶ መክበርን በተመለከተ ለእኛ ብርሀን ሊሆኑን የሚችሉ የተለያዩ ጠቃሚ የስኬት ትምህርቶችን ልንማር እንደምንችል ነው፡፡
እንግዲህ ትልቁ ቁምነገር በእለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡልን ወይም ህይወታችንን እስከ ወዲያኛው ድረስ በበጐ መልኩ ሊለውጡልን የሚችሉ የቢዝነስ ትምህርቶችን ከራፕ ሙዚቃዎች መማር የመቻላችን ጉዳይ የተረጋገጠ ከሆነ ቀጣዩ ጥያቄአችን እንዲህ የሚለው ነው፡፡ የቢዝነስ አሠራርን በተመለከተ ከራፕ ሙዚቃ መማር የምንችላቸው የተለያዩ ጠቃሚ የስኬት ትምህርቶች ለመሆኑ እንዴት ያሉት ናቸው? ለዚህ ጥያቄ መልሱ ደግሞ በጥቂቱ አምስት አይነት ትምህርቶች ናቸው የሚል ነው፡፡
ለተሳካ የቢዝነስ አሠራርና አመራር ቁልፍና ወሳኝ ነው የሚባለውን የቢዝነስ ስምምነትና ውሳኔ አሰጣጥን አንድ ብለን ዝርዝራችንን እንጀምር፡፡ ከዚያ የዝነኛውን አሜሪካዊ የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ የፊፍቲ ሴንትን “I Get Money” የሚለውን ተወዳጅ የራፕ ዘፈኑን እናዳምጥ፡፡
ፊፍቴ ሴንት ከሚያቀነቅነው ከዚህ የራፕ ሙዚቃ ግጥሞች (ግጥም ከተባሉ) ውስጥ አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ የትርጉም መዛባት ኖሮ ጉዳያችን ፉርሽ እንዳይሆን ግጥሙን በተገጠመበት ቋንቋ እንደወረደ እናቅርበው:-
I take quarter water sold it in bottles for two bucks,
Coca – Cola came and bought it for billions, what the…
እንዲህ እያለ የራፕ ርግረጋው ይቀጥላል፡፡
ራፐርነት ዋነኛ መለያው የሆነውና መላው አለም “50 cent” በሚለው የቅጽል ስሙ የሚያውቀው አፍሪካ አሜሪካዊው ካርቲስ ጃክሰን፤ ከዝነኛ የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኝነቱ በተጨማሪ በሂፕሆፕ የሙዚቃ ስልት የተጨበጨበለትና ምላጭ የሆነ ነጋዴ ነው፡፡
ኮርቲስ ጃክሰን ወይም ፊፍቲ ሴንት ለሁለተኛ ጊዜ ባሳታመው የሙዚቃ አልበሙ ውስጥ በሚያቀነቅነው በዚህ “I Get money” በተሰኘው ዘፈኑ፣ በቫይታሚን የበለፀገ ውሃ አምራች ለሆነው “ግላሴው” ለተሰኘው ኩባንያ የውሃ ምርቱን ለማምረት የሚያስችለውን አራት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ዶላር ከከፈለው የኮካኮላ ኩባንያ አስር በመቶ የአክሲዮን ድርሻ መግዛት ስለመቻሉና በዚህም ከፍተኛ ገንዘብ ማግኘቱን በኩራት ይገልፃል፡፡
ፊፍቲ ሴንት ከኮካ ኮላ ኩባንያ ጋር ያደረገው ይህ የቢዝነስ ስምምነት ከመቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ሲያስገኝለት ጠቅላላ አንጡራ ሀብቱ ደግሞ ወደ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ገደማ አሻቅቦለታል፡፡
ራፐሩ ፊፍቲ ሴንት በየጊዜው ከሚያቀርባቸው ተወዳጅ የራፕ ዘፈኖቹ ከሚሰበስበው ከፍተኛ ገቢ በተጨማሪ በተሠማራባቸው የተለያዩ የቢዝነስ ኢንቨስትመንቶች እያካበተው ያለው መጠነ ሰፊ ሃብት በቀጣዮቹ ጥቂት አመታት ብቻ ከአሜሪካም ሆነ ከአለም የቢሊዬነሮች ተርታ መሠለፍ የሚችል የመጀመሪያው የሙዚቃ አቀንቃኝ እንደሚሆን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
“I Get money” እያለ በሚያቀነቅነው ዘፈን ውስጥ “Quarter water” እያለ የሚገልፀው ከዛሬ ሃያ አምስት አመት በፊት ኒውዮርክ ውስጥ በሚገኘው ጐስቋላ የድሆች ሠፈር (ጌቶ) ውስጥ ህፃናት ሳሉ እሱና ጓደኞቹ በስሙኒ እየገዙ ይጠጡት የነበረውን በፕላስቲክ የታሸገ የቫይታሚን ውሃ ለማስታወስ ነው፡፡
ፊፍቲ ሴንት በዚህ ዘፈኑ ብቻ ሳይሆን “Get Rich or Die Trying” በሚለው ዝነኛ የራፕ አልበሙ 3.8 ሚሊዮን ለሚገመቱ አድናቂዎቹ ኢንቨስተርና ባለአክሲዮን በሆነበት ኩባንያ ውስጥ ከአክሲዮን ሽያጭ እንዴት ያለ ጥቅም ማግኘት እንደሚችሉ በትዊተር በጠቆመበት አልበም ስለቢዝነስ አሰራር የሚያስተምር ሲሆን ዘፈኑ በአሁኑ ወቅት አወዛጋቢ የመነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ ተደጋጋሚ ጥያቄ የቀረበለት እሱም ሆነ አድናቂና ተከታዮቹ “አሹ አበጀን” ብለዋል - እሱ እነሱን ለመጥቀም ማሠቡን፣ እነሱም መጠቀማቸውን በይፋ በመግለጽ፡፡
ወደ ሁለተኛው ቁልፍ ትምህርት ስንሻገር የምናገኘው “ጠንክረህ ስራ፤ የወጪህንም ጉዳይ በአንክሮ ተከታተል” የሚለውን የቢዝነስ ጥብቅ መመሪያ ነው፡፡ ሌላኛው ዝነኛ አሜሪካዊ የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ድሪ የሚያዜመውን “Get Your Money Right” የሚለውን ዘፈን ካዳመጥን የተጠቀሰውን ዋነኛ የቢዝነስ ቁልፍ መመሪያ እናገኘዋለን፡፡ ከዚህ የራፕ ሙዚቃ ግጥም ጥቂቱ እንዲህ ይላል:-
Get your money right, be an international player,
Don’t be scared to catch those red eye flights,
You better get your money right
Because when you out there on the streets,
ጽou gotta get it, get it…
እንደ ፊፍቲ ሴንት ሁሉ ዶክተር ድሪ እየተባለ በቅጽል ስሙ የሚጠራው አንድሬ ያንግ ከባለፀጋ ራፐሮች አንዱ ነው ተብሎ በፎርብስ መጽሔት የተመዘገበ ሲሆን 250 ሚሊዮን ዶላር አንጡራ ሀብት ያለው ዘመናይ ቱጃር ነው፡፡ አንድሬ ያንግ ዝነኛ ራፐር ብቻ ሳይሆን ብልጥ ነጋዴና ኢንቨስተር ነው፡፡ ባለፈው አመት የጆሮ ማዳመጫ አምራች ኩባንያ ከሆነው ቢትስ ኤሌክትሮኒክስ ውስጥ ያለውን ድርሻ ሀምሳ በመቶውን ለገበያ በማቅረብ 175 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን አንጡራ ሀብቱንም ወደ 425 ሚሊዮን ደላር አሳድጓል፡፡
ዶክተር ድሪ በ2007 ዓ.ም “Get your money Right” የተሰኘውን አልበሙን ካወጣ በኋላ እንደሱው ዝነኛ ራፐር ከሆነው ጄይ ዚ ጋር አነስተኛና ጥቃቅን ቢዝነሶችን እንዴት መጀመር እንደሚቻል የሚያስተምር ሴሚናር ለመስጠት ህብረት ፈጥሯል፡፡
በቅርቡ ከባለቤቱና ከዝነኛዋ የሂፕ ሆፕ አቀንቃኝ ከቢዮንሴ የሴት ልጅ አባት ለመሆን የበቃው ጄይ ዚ፤ ችሎታውና ተሰጥኦው ራፕ ሙዚቃ ማቀንቀን ብቻ ነው ብለን ካሰብን በእርግጥ ተሳስተናል፡፡ ጄይ ዚ በቢዝነስ አሠራርና አመራር ያለው ችሎታ ከመዚቃ ችሎታው በእጅጉ የላቀ እንደሆነ የሚያውቁት ይመሰክሩለታል፡፡ ጄይ ዚ በራፕ ሙዚቃ ቢዝነስ ውስጥ ካለፉት አራት አመታት ጀምሮ በየአመቱ ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ገቢ በማግኘት የዘፋኞቹን ጐራ እየመራ እንደሚገኝ ፎርብስ መጽሔት ይፋ አድርጓል፡፡
ባለፈው አመት ብቻ እንኳ 37 ሚሊዮን ዶላር ወደ ካዝናው ማስገባት ችሏል፡፡ ጄይ ዚ በቢዝነሱ አለም ያለው ችሎታ ድንቅ ነው እየተባለ የሚመሰከርለትም ያለምክንያት እንዳይመስላችሁ፡፡ ሰውየው በእርግጥም የዋዛ አይደለም፡፡ ከሙዚቃ ስራው በተጨማሪ በ450 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል የሚያንቀሳቅሰው የሬስቶራንቶችና የፋሽን አልባሳት ድርጅቶች ሲኖሩት በስፖርቱ አለምም ኒውጀርዚ ኔትስ ከተሰኘው የአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ቡድን የአክሲዮን ባለድርሻ ነው፡፡
ጆይ ዚና ዶክተር ድሪ ለእጩ ነጋዴዎች ወይም አነስተኛ ቢዝነስ ለመጀመር ለተዘጋጁ ሰዎች በተሰናዳ ወሳኝ የስልጠናና ምክር ፕሮግራም ላይ በተገኙበት ወቅት ምርጥ ተሞክሯቸውን አበርክተው ነበር፡፡ “ስለሚቀጥለው ሰው ወይም ስለተፎካካሪያችሁ ጨርሶ አትጨነቁ፡፡ ኧረ እንዲያውም ደንታ አይስጣችሁ፡፡ የጀመራችሁትን ቢዝነስ ግን በፍቅርና በትጋት አጥብቃችሁ ያዙት፤ ለመጠናችሁት ግብ ተሟሟቱ፤ ገንዘብ ለማግኘት አቅዳችሁ ገንዘብ ለማግኘት የማትሠሩ ከሆነ ከጨዋታው ውጡ፡፡”
በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ በሚገኙ ታላላቅ የቢዝነስ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ስትሄዱ በተለያየ አገላለጽና አቀራረብ የጄይ ዚና የዶክተር ድሪን ምክር ለተማሪዎቻቸው ሲያስተምሩ ታገኟችሁዋላችሁ፡፡ የተለያዩ የቢዝነስ አሰራርና አመራር መጽሐፍቶችን ብታገላብጡም እንዲሁ ነው፡፡ አሁን ወደ ሶስተኛው አብይ ነጥብ እንመለስ፡፡ እዚህ ላይ የምናገኘው ቁልፍ የስኬት መመሪያ የራስህ አለቃ ሁን የሚለውን አቻ የለሽ የቢዝነስ ስኬት መመሪያ ነው፡፡
ይህ ቁልፍ መመሪያ በራፕ ሙዚቃ የበለጠ እንዲብራራልን ከፈለግን ደግሞ “A Job Ain’t nothing But work” የሚለውን የቢግ ዳዲ ኬንን የራፕ ሙዚቃ ማድመጥ እንችላለን፡፡ አሜካዊው ተደናቂ ራፐር ቢግ ዳዲ ኬን፤ በዚህ ሙዚቃው ወሳኙ ነገር ስራ መያዛችን ሳይሆን ራሳችን የራሳችን አለቃ በመሆን፣ ስራችን ለሚጠይቀን ስነምግባር ተገዥ ሆነን፣ በጥንካሬና በትጋት መስራትና የሚገጥሙንን ፈተናዎች ለማለፍ የማያቋርጥ ትግል ማድረግ መቻላችን እንደሆነ ያስገነዝበናል፡፡ የኮሎራዶ ዩኒቨርሲቲው ተባባሪ ፕሮፌሰር አዳም ብራድሊ “The poetics of hip hop” በሚል ርዕስ ጽፈው ባሳተሙት መጽሐፍ ውስጥ ቢግ ዳዲ ኬን በዘፈኑ ያነሳውን ቁምነገር የበለጠ አብራርተውታል፡፡
የቢዝነስ መስራቾች የተሻሉ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች መሆን ይችላሉ የሚለው ሌላኛው ቁልፍ የቢዝነስ የስኬት መመሪያ ደግሞ በአራተኛ ደረጃ የምናገኘው ቁምነገር ነው፡፡ ይህን ምርጥ ቁምነገር በሚያቀነቅነው የራፕ ሙዚቃ የሚያስረዳን ደግሞ ተወዳጁ አሜሪካዊ ራፐር ራኪም ነው፡፡ ራኪም “Follow the Leader” በሚለው የራፕ ዘፈኑ እንዲህ ይላል:-
You’re just a rent. a - rapper, your rhymes are minute maid
I will be here when it fade to watch you flip like a renegade …
ከራፐሩ ራኪም ደስ የሚሉ ነገሮች አንዱ የመጀመሪያው ታላቅ ራፐር ከመሆኑ በተጨማሪ የራፕ ሙዚቃ ፈጣሪም መሆኑ ነው፡፡ የራፕ የሙዚቃ ስልትን ታሪክ ያጠኑት እንደሚናገሩት፤ ራፕ ሙዚቃ ሲጀመር በስኬት ለመዝለቁ ማንም እርግጠኛ አልነበረም፡፡ ይሁን እንጂ ራኪም በጀመረው ሙዚቃ በጥንካሬና በእምነት በመጓዙ ራሱን ለታላቅ ስኬት ያበቃ ሲሆን የጀመረው ራፕ ሙዚቃም መሠረቱ የጠናና ራሱን የቻለ የሙዚቃ ስልት ለመሆን በቅቶ ለሌሎች በርካታ አርቲስቶች የከፍተኛ ስኬት መሠረት ሆኗል፡፡ ራኪም “Follow the Leader” እያለ በሚያቀነቅነው የራፕ ዘፈኑ በቢዝነሱ መስራች ዋና ሥራ አስፈፃሚና በሌላው በተቀጣሪው ስራ አስፈፃሚ መካከል ያለውን ልዩነት ነው የሚያብራራው፡፡
ተቀጣሪው ስራ አስፈፃሚ በቦታው ላይ የሚገኘው የሚመራው ቢዝነስ ትርፍ እንዲያገኝ ብቻ ነው፡፡ በቢዝነሱ እንቅስቃሴና በተልዕኮው ውስጥ እንደ ቢዝነሱ ፈጣሪ በሙሉ ትኩረትና ስሜት አይሳተፍም፡፡ የቢዝነስ ፈጣሪ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ከሌሎች የተሻሉ ስራ አስፈፃሚዎች ናቸው የሚባሉበት ምስጢርም ሌላ ሳይሆን ይሄው ነው፡፡ ወደ አምስተኛው የቢዝነስ ስኬት ቁምነገር ስንሻገር የምናገኘው፣ ድክመትህን ለሌሎች አታሳይ የሚለውን ቁልፍ ምክር ነው፡፡ ይህንን ጉዳይ ደግሞ ዘ ጌም የተሰኘ የራፕ አቀንቃኝ ቡድን “Scream on Em” በሚል ርዕስ ባቀነቀኑት ዘፈን ውስጥ ገልፀውታል፡፡ የዚህ ዘፈን አንዱ ዘለላ እንዲህ ይላል:-
I’m runnin the buildin,
Don’t make me ran in  the buildin
No this ain’t the first time
I had my gun in the buildin’…
ለሻርክ ደም አታሳይ እየተባለ የሚመከረው ሻርክ ደም ካየ ባለ በሌለ ሃይሉ ስለሚተናኮል ነው፡፡ ቢዝነስ ደግሞ የፉክክር ጨዋታ ነው፡፡ ፉክክሩን በበላይነት ለመወጣት ከተፎካካሪዎች ልቆና ጠንክሮ መገኘት የግድ ነው፡፡ በቢዝነስ እንቅስቃሴ ውስጥ ድክመትን ማሳየት ማለት ለሻርክ ደም እንደማሳየት ማለት ነው፡፡
እንግዲህ ከዚህ በላይ ያየናቸው ነገሮች ሁሉ ማጠቃለያቸው አንድ ጉዳይ ነው፡፡ ራፕ ሙዚቃ ለቢዝነስ ስኬት የሚረዳ በርካታ ቁምነገሮችን ይዟል፡፡ በሚገባ ላዳመጠው፣ አዳምጦም ለተረዳው፣ ተረድቶም በተግባር ላዋለው - ለሁሉም!!

Read 3989 times Last modified on Monday, 05 March 2012 13:18