Saturday, 10 March 2012 10:15

በወንድሜ የተፈፀመብኝ አስገድዶ መድፈር ፍትህ ሣያገኝ በማላውቃቸው ወንዶች ተደፈርኩ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(46 votes)

ቀትር ላይ ነው፡፡ ባለፈው ማክሰኞ ዕለት፡፡ ፀሐዩ አናት ይበሣል፡፡ በዚህ ሰዓት ነው  አንዲት ወጣት ዝግጅት ክፍላችን የመጣችው፡፡ ዕድሜዋ ሃያዎቹ መጨረሻ ግድም የምትሆነዋ ወጣት የለበሰችው ነጭ የአገር ልብስ ቁመናዋን ያጐላላት ይመስላል፡፡ ወጣትዋ በተደጋጋሚ ተፈፅሞብኛል በምትለው ተደራራቢ በደል የተነሳ አዕምሮዋ መነካቱን ብትናገርም ከአንደበቷ የሚወጡት ቃላት ያንን አመላካች አልነበሩም፡፡ ግልፅና የማያደናግር ነበር ንግግሯ፡፡ ሆኖም ከእንባዋ ጋር መታገል ነበረባት፡፡ እሱን በጥንካሬና በብርታት ተወጥታ ወደኛ ቢሮ ያመጣትን ዋና ጉዳይ በዝርዝር ነገረችን፡፡ የበደልዋ ታሪክ የዛሬ 10 ዓመት ይጀምራል፡፡

“ከ10 ዓመት በፊት ገና የአስራ ዘጠኝ ዓመት ልጅ እያለሁ በታላቅ ወንድሜ ተደፈርኩ፡፡ በወቅቱ እኔ በአንድ ካፌ ውስጥ ተቀጥሬ እሰራ ስለነበር ሥራዬን ጨርሼ ካሣንቺስ አካባቢ ከሚገኘው የሥራ ቦታዬ ማዕከላዊ አካባቢ ወደሚገኘው የመኖሪያ ቤቴ እየሄድኩ ነበር፡፡ ፒያሣ ደርሼ ከታክሲ ከወረድኩ በኋላ ወደ ሰፈሬ የሚያደርሰኝ ታክሲ ለመያዝ እየሄድኩ ሣለ ከኋላዬ ጥሪ ሰማሁና ዞርኩ፡፡ የአባቴ ልጅ የሆነው ታላቅ ወንድሜ ከጓደኛው ጋር ነበር፡፡ ቦታው ጨለማ ስለነበር ስላገኘኋቸው በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ ሻይ እንጠጣ አለኝና ሰሜን ሆቴል አካባቢ አንድ ቤት ገባን፡፡ ለእናቴ ስልክ ደወለና ከእሱ ጋር እንደሆንኩና እንሽ እንደምቆይ ነገራት፡፡ ወንድሜ የኢኮኖሚ አቅም ስለነበረው ወደ አረብ አገር እንዲልከኝ ስለምፈልገ የመገናኘታችንን አጋጣሚ ወድጄዋለሁ፡፡ እዛው አካባቢ ያሉ ቤቶችን እያቀያየርን ቆየን፡፡ በዚህ መካከል እናቴ ደወለችና “አልመሸም ወይ?” አለችን፡፡ “ከወንድሟ ጋር ነች፤ ምን ትሆናለች? ትመጣለች!” አላት ወንድሜ፡፡ ብቻዬን ወደቤት እንዳልሄድ ጨለማውን ፈራሁ፡፡ እንዳልቆይ ደግሞ የወንድሜ ሁኔታ አላምር ብሎኛል፡፡ ኧረ ባክህ በቃ እንሂድ እያልኩ ውትወታዬን ቀጠልኩ፡፡ “እሺ ጓደኛዬን እንሸኘውና እቤት አደርስሻለሁ” አለኝ፡፡ ተያይዘን ወጣን፡፡ ሾላ አካባቢ ስንደርስ ወንድሜ መሣሪያ አውጥቶ ጆሮዬ ላይ ደገነብኝና ስልኩን ሰጠኝ፡፡ “እናትሽን አድሬአለሁ በያት፤ ከዚህ ውጪ አንድ ነገር ብትናገሪ ግን አጠፋሻለሁ” አለኝ፡፡ በጣም ደነገጥኩ፡፡ “እማ አድሬአለሁ” ብዬ ስልኩን ዘጋሁ፡፡ ከዛ በኋላ እዛው ጓደኛው ቤት ጓደኛው ቁጭ ብሎ እያየን ወንድሜ የሴትነት ክብሬን አሣጣኝ፡፡ በአሰቃቂ ሁኔታ ደፈረኝ፡፡ በማግስቱ ጠዋት ልብሴን እንድለብስ አስገደደኝና ከቤቱ አስወጣኝ፡፡ እቤት እንዲያደርሰኝ ጠየኩት፡፡ ሃሣቤ ቤታችን ማዕከላዊ አካባቢ ስለነበር እዛ ስደርስ ለመጮህ ነበር፡፡ ወንድሜ ግን ከእኔ በፊት ሃሳቤ ገብቶት ነበርና “አንድ ነገር ለማድረግ ከሞከርሽ ግን አጠፋሻለሁ” አለኝ፡፡ ምንም ሣልናገር እቤት አደረሰኝ፡፡ ከዛም ለእናቴ አስረክቦኝ 20 ብር ሰጥቶኝ ሄደ፡፡ ሽንቴን መሽናት እንኳን እያቃተኝ ህመም ሲያሰቃየኝ ሁኔታውን ደውዬ ነገርኩት፡፡ “የራስሽ ጉዳይ ነው” አለኝ፡፡ በቃ ሁኔታውን ለቤተሰቦቼ መንገር አለብኝ ብዬ ወሰንኩና ነገርኳቸው፡፡ ቤተሰቦቼ ግን ሚስጢሩ እንዲወጣባቸው አልፈለጉም፡፡ ሥቃዩ ከቁጥጥሬ ውጪ ሲሆን ራሴን ለማጥፋት መድሃኒት ጠጣሁና ዘውዲቱ ሆስፒታል አስገቡኝ፡፡ ዶክተሩ “ምን ሆና ነው መድሃኒት የጠጣችው?” ብሎ ሲጠይቅ ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ “ተደፍራ ነው” አሉት፡፡ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ሪፈር ፃፈልኝ፤ ሳይካትሪስት እንዲያየኝ፡፡ እዛም ዶክተሯ “ያለ እኮ ነው መደፈር፤ አባት በልጁ ይደፈራል፤ ወንድም እህቱን ይደፍራል” እያለች ስታፅናናኝ በቃ ተስፋ ቆረጥኩ፡፡ ሞራሌ ወደቀ፡፡ ህክምናዬንም አቋረጥኩ፡፡ በ15ኛው ቀኔ መንገድ ላይ ወድቄ ያየኝ አንድ ሰው ስለ ሁኔታዬ ሲጠይቀኝ የደረሰብኝን ሁሉ ነገርኩት፡፡ በጣም አዘነና እስቲ የሴቶች ጉዳይ ሂጂ አለኝ፡ ቦሌ ማተሚያ ቤት አካባቢ ወደነበረው ቢሮአቸው ሄጄ፣ ላገኘኋት የቢሮው ሠራተኛ (ባለሙያ) ስለደረሰብኝ በደል በዝርዝር ነገርኳት፡፡ ሁሉን ከአሰማችኝ በኋላ “ብዙም አትዘኚ፡፡ የህጉም ጉዳይ ብዙ የሚያስኬድሽ አይደለም፤ ባትደክሚ ጥሩ ነው፤ ስትለኝ ተስፋ ቆረጥኩና ሁሉንም ተውኩት፡፡ ይህ በገዛ ወንድሜ የተፈፀመብኝ ወንጀል ግን እስከዛሬም ድረስ ህሊናዬን እጅግ ጐድቶት፣ ወጣትነቴን ሣላውቀው እጅግ አሣዛኝ የሆነ ህይወት እንድመራ አድርጐኛል፡፡ እኔ ውስጤ የተነካና አዕምሮዬ የቆሰለ ሰው ነኝ፤ የተፈፀመብኝ በደል በህሊናዬ ላይ ያደረሰውን ቁስል እንደማከም አዕምሮዋን ታማለች ብለው አማኑኤል ሆስፒታል ወሰዱኝ፤ እኔ ግን ያጣሁት ፍትህን ነው፡፡ ፍትህ ቢሰጡኝ ከህመሜ እድናለሁ፡፡ እኔ እብድ አይደለሁም፡፡ ትክክለኛ መድሃኒቴ ፍትህ ነው፡፡”

ከ10 ዓመት በፊት ተፈፀመብኝ ስላለችው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከቤተሰቦቿ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ እናቷን ስልክ ደወልን፡፡

የብዙ ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን የገለፁት እናቷ፤ በልጃቸው ላይ ተፈፀመ በተባለው ንጀል እጅግ መጐዳታቸውን ይናገራሉ፡፡ “ልጆቼ ሁሉ ራሣቸውን እንዲጠብቁ፣ በጊዜ ወደቤታቸው እንዲገቡና በትምህርታቸው እንዲበረቱልኝ ነበር የእኔ ጥረትና ድካም፡፡ ድርጊቱ ተፈፀመብኝ በምትለው ዕለት ይኸው የአባቷ ልጅ የሆነው ወንድሟ አብራው እንዳደረች ገልፆ ጠዋት ይዟት መጣ፡፡

በወቅቱ ይህ በደል እንደተፈፀመባት አልነገረችኝም፤ ነግራኝ ቢሆን ኖሮ እዛው ኡኡ ብዬ አስይዘው ነበር ቢገለኝም ለልጄ ብሞት አይቆጨኝም ነበር፡፡ እንዲህ በሽተኛ ሆና ከማያት የኔ ሞቼላት ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ እናም በዕለቱ አልሰማሁም፡፡ ጊዜው ካለፈ በኋላ ግን ነገረችኝ፡፡ ምን ዋጋ አለው፡፡ ለማንስ እነግረዋለሁ እኔ የልጆቼን ጉሮሮ ለመሙላት ጠዋት ማታ ደፋ ቀና እያልኩ የምውል ደካማ ምን አቅም አለኝ፡፡ ከዛ በኋላ ግን ልጄ በቃ በሽተኛ ሆነችብኝ፡፡ አንዳንዴ በጣም ያማታል፡፡ ከሥራ ቦታዬ ተጠርቼ ሁሉ የምሄድበት ጊዜ አለ፡፡ ምን ላድርግ ልጄ ጤና ሆናልኝ ሠርታ ብትበላ ነበር የኔ ምኞት፡፡” አናት በልጃቸው ላይ በደረሰው በደል ልባቸው እንደተሰበረ ድምፃቸው ይናገራል፡፡ ግን ተስፋና ምኞት አላቸው፡፡ ልጃቸው ወደቀልቧ ተመልሳ ራሷን ሆና ራሷን ችላ እንድትኖር፡፡

የናርዶስ በደል በዚህ ብቻ ግን አላበቃ፡፡ ከ10 ዓመት በኋላ በደሉ ተደገመብኝ ትላለች፡፡ በማላውቃቸው ሁለት ወንዶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈፀመብኝ ብላለች - ወጣቷ፡፡

የካቲት 10/2004 ዓ.ም ምሽት ላይ ስትዝናና እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ በሁለት የማታውቃቸው ወጣቶች በአንድ ፔንሲዮን ውስጥ ተደፍራለች፡፡

ይህን ወንጀል ግን ለፖሊስ አመልክታለች፡፡ የቦሌ ክፍለከተማ ፖሊስ መምሪያ በወንጀል ድርጊቱ ላይ ምርመራ እያካሄደ ነው፡፡ ከጋንዲ ሆስፒታል የምስክር ወረቀትና የጣት አሻራን የሚያሳዩ መረጀዎች ተገኝተዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ሁለቴ የጊዜ ቀጠሮ ከተሰጠባቸው በኋላ ፍ/ቤቱ የዋስ መብት በመፍቀዱ ምክንያት ከእስር ተለቀዋል፡፡ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ ዝርዝር መረጃ መስጠት እንደማይችሉ የገለፁት ምክትል ሣጅን ሰናይት፤ ክሱ በምርመራ ላይ እንደሆነ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡

ናርዶስ ለሁለተኛ ጊዜ ስለተፈፀመባት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ስትናገር ስሜቷ ክፉኛ እንደተጐዳ ያስታውቃል፡፡ “ያኔ የሴቶች ጉዳይ ሄጄ አትድከሚ ስላለችኝ ደክሜ ተውኩት፤ ዛሬ ግን ህፃን አይደለሁም፡፡ መተው አልችልም፡፡ እጮሃለሁ ሰሚ እስከማገኝና በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ላይ ፍትህ እስኪሰጠኝ ድረስ መጮኼን አልተውም፡፡ ለመሆኑ መንግስት ምን እየሰራ ነው አሁን ለሁለት አስገድደው የደፈሩኝን ወንዶች ፖሊሶች ይቅርታ አድርጊላቸው ይሉኛል ያኔ የልጅነት ህልሜን ያመከነውን ወንድሜን ቤተሰቦቼ ሸፋፍነው አልፈውብኛል፡፡ እናስ እኔ ከየት ነው ፍትህ የማገኘው ሴቶች ጉዳይ አትድከሚ ተይው ብላ፣ ወንዶች ጉዳይ ሆነችብኝ4 እኔ ታዲያ የት ልሂድ ይህ ጥሪዬ የድረሱልኝ ጥሪ ነው፡፡ ህዝብ በደሌን ይስማና ዳኝነቱን ይስጠኝ፡፡

የዛሬ 10 ዓመት ስደፈር ኢህአዴግ ነበር፡፡ ዛሬም በድጋሚ ስደፈር ያለው ይኸው መንግስት ነው፡፡ እናስ እኔ ለማን ልጩህ መንግስት በሴቶች ጥቃት ላይ እየሰራ ያለው ምንድነው እኔ የምሻው ፍትህን ነው፤ ፍትህን ካገኘሁ እፈወሳለሁ፡፡ መድሃኒቴ እሱ ብቻ ነው፡፡”

ሀዘን በተሞላው ስሜት በደሏን ዘርዝራ ስታበቃ ተንፈስ አለች፡፡ ኑሮን ለማሸነፍ ጠንክራ እየሰራች እንደሆነ የምትናገረው ናርዶስ፤ ጐተራ አካባቢ በ2500 ብር ተከራይታ በምትኖርበት ኮንዶሚኒየም ቤት ዶሮ ወጥና የተለያዩ ምግቦችን እየሰራች በአካባቢው ለሚኖሩ ሰዎችና ለሱፐር ማርኬቶች እንደምትሸጥ ገልፃለች፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለሁለተኛ ጊዜ በተደፈረችበት ጊዜ ላደረገላት የሞራል ጥገናና ወንጀሉን ለመመርመር ለሚያደርገው ጥረትም ምሥጋናዋን ያቀረበችው ወጣቷ በአፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጣት እየተማፀነች ነው፡፡

የተፈፀመብኝ በደል በህሊናዬ ላይ ያደረሰውን ቁስል እንዶማከም አዕምሮዋን ታማለች ብለው አማኑኤል ሆስፒታል ወሰዱኝ፤ እኔ ግን ያጣሁት ፍትህን ነው፡፡ ፍትህ ቢሰጡኝ ከህመሜ እድናለሁ፡፡ እኔ እብድ አይደለሁም፡፡ ትክክለኛ መድሃኒቴ ፍትህ ነው፡፡”

ከ10 ዓመት በፊት ተፈፀመብኝ ስላለችው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከቤተሰቦቿ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ እናቷ ስልክ ደወልን፡፡

የብዙ ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን የገለፁት እናቷ፤ በልጃቸው ላይ ተፈፀመ በተባለው ወንጀል እጅግ መጐዳታቸውን ይናገራሉ፡፡ “ልጆቼ ሁሉ ራሣቸውን እንዲጠብቁ፣ በጊዜ ወደቤታቸው እንዲገቡና በትምህርታቸው እንዲበረቱልኝ ነበር የእኔ ጥረትና ድካም፡፡ ድርጊቱ ተፈፀመብኝ በምትለው ዕለት ይኸው የአባቷ ልጅ የሆነው ወንድሟ አብራው እንዳደረች ገልፆ ጠዋት ይዟት መጣ፡፡ በወቅቱ ይህ በደል እንደተፈፀመባት አልነገረችኝም፤ ነግራኝ ቢሆን ኖሮ እዛው ኡኡ ብዬ አስይዘው ነበር ቢገለኝም ለልጄ ብሞት አይቆጨኝም ነበር፡፡ እንዲህ በሽተኛ ሆና ከማያት ያኔ ሞቼላት ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ እናም በዕለቱ አልሰማሁም፡፡ ጊዜው ካለፈ በኋላ ግን ነገረችኝ፡፡ ምን ዋጋ አለው፡፡ ለማንስ እነግረዋለሁ እኔ የልጆቼን ጉሮሮ ለመሙላት ጠዋት ማታ ደፋ ቀና እያልኩ የምውል ደካማ ምን አቅም አለኝ፡፡ ከዛ በኋላ ግን ልጄ በቃ በሽተኛ ሆነችብኝ፡፡ አንዳንዴ በጣም ያማታል፡፡ ከሥራ ቦታዬ ተጠርቼ ሁሉ የምሄድበት ጊዜ አለ፡፡ ምን ላድርግ ልጄ ጤና ሆናልኝ ሠርታ ብትበላ ነበር የኔ ምኞት፡፡” እናት በልጃቸው ላይ በደረሰው በደል ልባቸው እንደተሰበረ ድምፃቸው ይናገራል፡፡ ግን ተስፋና ምኞት አላቸው፡፡ ልጃቸው ወደቀልቧ ተመልሳ ራሷን ሆና ራሷን ችላ እንድትኖር፡፡

የናርዶስ በደል በዚህ ብቻ ግን አላበቃ፡፡ ከ10 ዓመት በኋላ በደሉ ተደገመብኝ ትላለች፡፡ በማላውቃቸው ሁለት ወንዶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈፀመብኝ ብላለች - ወጣቷ፡፡

የካቲት 10/2004 ዓ.ም ምሽት ላይ ስትዝናና እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ በሁለት የማታውቃቸው ወጣቶች በአንድ ፔንሲዮን ውስጥ ተደፍራለች፡፡

ይህን ወንጀል ግን ለፖሊስ አመልክታለች፡፡ የቦሌ ክፍለከተማ ፖሊስ መምሪያ በወንጀል ድርጊቱ ላይ ምርመራ እያካሄደ ነው፡፡ ከጋንዲ ሆስፒታል የምስክር ወረቀትና የጣት አሻራን የሚያሳዩ መረጃዎች ተገኝተዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ሁለቴ የጊዜ ቀጠሮ ከተሰጠባቸው በኋላ ፍ/ቤቱ የዋስ መብት በመፍቀዱ ምክንያት ከእስር ተለቀዋል፡፡ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ ዝርዝር መረጃ መስጠት እንደማይችሉ የገለፁት ምክትል ሣጅን ሰናይት፤ ክሱ በምርመራ ላይ እንደሆነ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡

ናርዶስ ለሁለተኛ ጊዜ ስለተፈፀመባት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ስትናገር ስሜቷ ክፉኛ እንደተጐዳ ያስታውቃል፡፡ “ያኔ የሴቶች ጉዳይ ሄጄ አትድከሚ ስላለችኝ ደክሜ ተውኩት፤ ዛሬ ግን ህፃን አይደለሁም፡፡ መተው አልችልም፡፡ እጮሃለሁ ሰሚ እስከማገኝና በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ላይ ፍትህ እስኪሰጠኝ ድረስ መጮኼን አልተውም፡፡ ለመሆኑ መንግስት ምን እየሰራ ነው አሁን ለሁለት አስገድደው የደፈሩኝን ወንዶች ፖሊሶች ይቅርታ አድርጊላቸው ይሉኛል ያኔ የልጅነት ህልሜን ያመከነውን ወንድሜን ቤተሰቦቼ ሸፋፍነው አልፈውብኛል፡፡ እናስ እኔ ከየት ነው ፍትህ የማገኘው፤ ሴቶች ጉዳይ አትድከሚ ተይው ብላ፣ ወንዶች ጉዳይ ሆነችብኝ እኔ ታዲያ የት ልሂድ? ይህ ጥሪዬ የድረሱልኝ ጥሪ ነው፡፡ ህዝብ በደሌን ይስማና ዳኝነቱን ይስጠኝ፡፡የዛሬ 10 ዓመት ስደፈር ኢህአዴግ ነበር፡፡ ዛሬም በድጋሚ ስደፈር ያለው ይኸው መንግስት ነው፡፡ እናስ እኔ ለማን ልጩህ መንግስት በሴቶች ጥቃት ላይ እየሰራ ያለው ምንድነው እኔ የምሻው ፍትህን ነው፤ ፍትህን ካገኘሁ እፈወሳለሁ፡፡ መድሃኒቴ እሱ ብቻ ነው፡፡”

ሀዘን በተሞላው ስሜት በደሏን ዘርዝራ ስታበቃ ተንፈስ አለች፡፡ ኑሮን ለማሸነፍ ጠንክራ እየሰራች እንደሆነ የምትናገረው ናርዶስ፤ ጐተራ አካባቢ በ2500 ብር ተከራይታ በምትኖርበት ኮንዶሚኒየም ቤት ዶሮ ወጥና የተለያዩ ምግቦችን እየሰራች በአካባቢው ለሚኖሩ ሰዎችና ለሱፐር ማርኬቶች እንደምትሸጥ ገልፃለች፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለሁለተኛ ጊዜ በተደፈረችበት ጊዜ ላደረገላት የሞራል ጥገናና ወንጀሉን ለመመርመር ለሚያደርገው ጥረትም ምሥጋናዋን ያቀረበችው ወጣቷ በአፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጣት እየተማፀነች ነው፡፡

 

 

 

Read 107539 times Last modified on Saturday, 10 March 2012 12:41