Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 March 2012 11:02

የህፃናት ጥግ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ውድ እግዚአብሔር፡-
ወንድሜን ጆሲን በጣም ነው የምወደው፡፡ ስነግረው ግን ገፍትሮ ጣለኝና አስለቀሰኝ፡፡ እናቴ እሱም ሊወደኝ እንደሚገባ ነግራኛለች፡፡ አንተስ ምን ይመስልሃል?
-ሳሚ -
ውድ እግዚአብሔር፡-
ጓደኛዬ ሮዝ ጫማ ተገዝቶላታል፡፡ እኔ ደሞ ጫማውን ፈለኩት፡፡ መፈለጌ መጥፎ ነው እንዴ? ልሰርቃት ወይም ሌላ ነገር ላደርግ አልፈለኩም፡፡ ግን አንተ የእሷ ዓይነት ጫማ ትልክልኛለህ?
-ዴቭ-
ውድ እግዚአብሔር፡-
ባቢ ቢራ ጠጥቶ ሲመጣ ያስጠላኛል፡፡ አቤት አፉ ሲሸት! በቃ ደስ አይልም፡፡ ደሞ ተኝቶ ሲነሳ ይጮህብኛል፡፡ ግን ቢራውን የምትሰራው አንተ ነህ እንዴ? ለምን?
-ሃኒ-
ውድ እግዚአብሔር፡-
ትልቋ አያቴ ልትሞትብኝ ነው፡፡ እሷ እግዚአብሔር ጠርቶኛል ትላለች፡፡ እኔ ግን እዚህ ከኛ ጋር እንድትሆን እፈልጋለሁ፡፡ አንተ እኮ የፈለከውን ሰው መውሰድ ትችላለህ፡፡ እኔ ግን እሷ ብቻ ናት ያለችኝ፡፡ ስለዚህ እንዲሻላት አድርግልኝና ከእኔ ጋር ትቆይ …
-ሶፊ-
ውድ እግዚአብሔር፡-
ህፃኑ ኢየሱስ ሁልጊዜ ያለቅሳል እንዴ? አዲስ የተወለደው ወንድሜ ግን ሲያለቅስ ነው የሚውለው፡፡ እናቴ ህፃናት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ አንቺም ትንሽ ሆነሽ ታለቅሺ ነበር ብላኛለች፡፡ አሁን ስድስት ዓመቴ ነው፡፡ ሳስበው ግን ህፃኑ ኢየሱስ አልቅሶ የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ ልጅህ አይደል? መልሱን ታውቀዋለህ ማለት ነው፡፡ በናትህ ስለተወራረድን መልሱን ፅፈህ ላክልኝ፡፡
-ሊዛ-
ውድ እግዚአብሔር፡-
ለምንድነው ሸረሪትና እንሽላሊትን የፈጠርከው? እኔ እኮ በጣም ነው የምፈራቸው፡፡
-ጄሪ-
===============================================================
የፍቅር ጥግ
አሁን እነዚህን ቃላት ለነፋሱ አንሾካሹክለታለሁ፡- “የምወድሽ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ብቻ ነው”
በፍቅር ለሚወድቁ ሰዎች ስበት ተጠያቂ አይደለም፡፡
አንቺን ከመውደድና ከመተንፈስ የግድ መምረጥ ቢኖርብኝ፣ በመጨረሻዋ ትንፋሼ “እወድሻለሁ” እልሽ ነበር፡፡
ፍቅር እንደ ምርጥ ወይን ጠጅ ነው፡፡ መጀመሪያ ላይ ጣፋጭ፤ በመጨረሻ ግን መራራ!
ሁለት ከናፍሮች ሲገናኙ ፍቅር ሙሉ ይሆናል፡፡
ፍቅር ውሃ ቢሆን ኖሮ ባህሩን እጠጣው ነበር፡፡ ፍቅር ህልም ቢሆን ኖሮ መንግስተ ሰማያት እገባ ነበር፡፡ ፍቅር ዛፍ ቢሆን ኖሮ ጫካ ውስጥ እሸሽግ ነበር፡፡ ፍቅር ግን ምን እንደሆነ ታውቃለህ? እኔና አንተ ማለት ነን!
ውበት ቀልብን ብቻ ይስባል፡፡ ሰብዕና ግን ልብንም ይማርካል፡፡
በተሰበረ ልብ ስታልም አስቸጋሪው ነገር ምን መሰለህ? ከእንቅልፍህ መንቃት!
እያንዳንዱ የፍቅርህ ጠብታ ለዓለሜ ዕፁብ ድንቅ ሙቀት ያጐናፅፈኛል፡፡ ማንም ሊሰጠኝ የማይችለውን አንዳች ነገር ይሰጠኛል፡፡ ልቤን ለመክፈት በቂ ምክንያት የሚሆነኝም እሱ ነው፡፡
ምንጭ፡- (ኢንተርኔት)

=====================

Read 4910 times