ባለፈው ማክሰኞ የ18 ዓመት የልደት በዓሉን ያከበረው ወጣቱ አሜሪካዊ አቀንቃኝ ጀስቲን ቢበር፤ ለልደቱ ከ100 ሚ ብር በላይ የሚያወጣ ቪላ ከቤተሰቡ በስጦታ እንደተበረከተለት ታውቋል፡፡ ዴይሊሜል እንደዘገበው፣ ቪላው የሚገኘው በሆሊዉድ ኮረብታ ላይ ሲሆን ባለአምስት መኝታ ክፍሎች ያሉትና የተንጣለለ ግቢ ውስጥ የተገነባ ነው፡፡ ጀስቲን ቢበር በቪላው ውስጥ ከ19 ዓመቷ ጓደኛው ሴሊና ጎሜዝ ጋር የፍቅር ህይወቱን ማጣጣም እንደሚፈልግ ለዴይሊሜል ገልጿል፡፡ ወጣቱ አቀንቃኝ ከቪላው በተጨማሪ ከ1ሚ. ብር በላይ የምታወጣ ዘናጭ መኪና የተበረከተለት ሲሆን ይሄን ስጦታ አባቱና ማኔጀሩ ተመካክረው እንደሰጡት ታውቋል፡፡