መፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ እንዳለው ሰውዬ 900 ዓመት መኖር እፈልጋለሁ፡፡ እወድሃለሁ!
ኤልያስ
ውድ እግዚአብሔር፡-
እኔ አሜሪካዊ ነኝ፡፡ አንተ ምንድነህ?
አሌክስ
ውድ እግዚአብሔር፡-
ብርሃን የፈጠረው ቶማስ ኤዲሰን ነው የሚል አንብቤአለሁ፡፡ ት/ቤት ደግሞ አንተ ነህ የፈጠርከው አሉን፡፡ ከዛም ሃሳብህን ሰርቆሃል ብዬ ተወራረድኩኝ፡፡
ሩት
ውድ እግዚአብሔር፡-
ስቴፕለር ከታላላቅ ፈጠራዎችህ አንዱ ይመስለኛል፡፡ ልክ ነኝ?
ሩት
ውድ እግዚአብሔር፡-
ቀናተኛ አምላክ ነህ ማለት ምን ማለት ነው? ሁሉ ነገር አለህ አይደለም እንዴ?
ጆኒ