የሆሊውድ ፊልሞች የቻይና ገበያ በዓመት 2 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የዘገበው ቻይና ዴይሊ ኒውስ፤ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የገቢ መጠኑ ወደ 5 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያድግና በዓለም አቀፍ ገበያ ሁለተኛ ደረጃን እንደሚይዝ ጠቁሟል፡፡ በእስያ አህጉር ከ650 በላይ ዓመታዊ የፊልም ኤግዚቢሽኖችና ፌስቲቫሎች የሚደረጉ መሆናቸውም ለሲኒማ ኢንዱስትሪው ገበያ እንደፈጠረ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የሆሊውድ ፊልም ሰሪዎች ለሚሰሯቸው ትላልቅ ፊልሞች የቻይና ኩባንያዎችን የበጀት ድጋፍ እየጠየቁ ሲሆን ከቅርብ ዓመት ወዲህ በተሰሩት እንደ “ዘ ዳርክ ናይት”፤ “ኢንሰፕሽን” እና “ሃንጎቨር” ፊልሞች ላይ የቻይና ኩባንያዎች 45 በመቶ የሚደርስ የበጀት ድጋፍ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡