Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 07 April 2012 07:52

“ድንጋይ ...ዘመዷ... ጉዋደኛዋ ይሆናል”

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“የፌስቱላ መሰረቱ ዋናው ድህነት ነው፡፡ ድህነት በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብም ጭምር ነው፡፡ አንዲት ሴት ገና በህጻንነት እድሜዋ ተለምና ከተገባች በሁዋላ የፌስቱላ ሕመም ሲያጋጥማት ባልዋ ወደቤተሰቦችዋ ይመልሳታል፡፡ ቤተሰቦችዋ ደግሞ በሚኖሩበት ግቢ ውስጥ ነጠል ያለች መኖሪያ ያመቻቹና በዚያ እንድትቀመጥ ካደረጉ በሁዋላ የሚያገኙዋት ምግብና ውሀ በሚሰጡዋት ወቅት ብቻ ነው፡፡ ታማሚዋ ሽንቱዋን መቆጣጠር ስለማትችል የምትለብሰው... የምትተኛበት እንዲሁም የምትኖርበት ሁሉ ስለ ሚበላሽና ስለሚሸት ውሃ መጠጣትዋን ታቆማለች፡፡ ምግብ መውሰዱዋንም ትቀንሳለች፡፡ በዚህም ሰውነቷ እየደረቀ ይመጣል፡፡ ከዚህም በላይ በውስጧ ያለው ፈሳሽ በሚፈስበት ጊዜ አካባቢዋን እንዳያበላሸው በአቅራቢያዋ ካለ ድንጋይ ተቀምጣ መዋልን ትመርጣለች፡፡ ድንጋይ ስለማይበሰብስና ስለማይርስ ዘመዷ...ጉዋደኛዋ ይሆናል፡፡ ይህች ልጅ በዚህ ሁኔታ ስትቆይ ሰውነቷ የመድረቅ ... የመቀጨጭ ... ጅማቶችዋ የመኮማተር ችግር ስለሚያጋጥማት ለከፍተኛ ሕመም ትጋለጣለች፡፡ በጊዜው እርምጃ ካልተወሰደም ለሕልፈት ልትዳረግ ትችላለች...”

ዶ/ር መላኩ አብርሀ በመቀሌ የፌስቱላ ከፍተኛ ቀዶ ሕክምና ባለሙያ በሁለት ብልቶች መካከል ወይንም በብልትና በቆዳ መካከል... በበሽታ ...በጉዳት ወይንም በተፈጥሮ አጋጣሚ ክፍተት ወይንም ቀዳዳ ሲከሰት ፌስቱላ ይሰኛል፡፡ በዚህ እትም ለንባብ ያበቃነው ፊስቱላ ግን በወሊድ ምክንያት በማህጸንና በአካባቢው የሚፈጠረውን ቀዳዳ የሚመለከት ነው፡፡ ታሪክን ወደሁዋላ መለስ ብለን ስንመለከት በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የፌስቱላ ሆስፒታል የተከፈተው በአዲስ አበባ ሲሆን የከፈቱትም (Dr Catherine Hamlin & her late husband, Dr Reg Hamlin) ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን እና ባለቤታቸወ የነበሩት ዶ/ር ሬግ ሐምሊን ናቸው፡፡ እነዚህ የህክምና ባለሙያ  የሆኑ ባልና ሚስቶች ይህንን ሆስፒታል በአዲስ አበባ ሲከፍቱ እሳቤው በመውለድ ምክንያት በማህጸንና በአካባቢው በፌስቱላ ሕመም ለሚሰቃዩ ሴቶች መድህን እንዲሆን ነው፡፡

በማህጸን አካባቢ የሚከሰተው የሰውነት ክፍል መቀደድ የሚፈጠረው በተራዘመ ምጥ ምክንያት ነው፡፡ ሴቶች ቀናትን በፈጀ ምጥ ምክንያት መሰቃየት እጣ ፈንታቸው በሆነ ቁጥር ምናልባትም የራሳቸው ሕይወት ቢተርፍ እንኩዋን የሚወልዱት ልጅ ሕይወት የሌለው እንደሚሆን በተደጋጋሚ የተስተዋለ ነው፡፡ ውሎ እያድር ደግሞ የሽንት መቋጠር ችግር ይደርስባቸዋል፡፡ በአዲስ አበባ ወደሚገኘ ፊስቱላ ሆስፒታል በመሄድ ለህክምና ከተለያየ አካባቢ የመጡ ሴቶችን የአምዱ አዘጋጅ አነጋግራለች፡፡

...መልኩዋ ቀይ ነው፡፡ ጸጉርዋ ሐር የመሰለ ጥቁር... ዞማ...ሰውነቷ ቀጠን ያለ...ቆንጆ ከሚባሉ የምትመደብ ነች...፡፡

.. እኔ የመጣሁት ከሸዋ ሮቢት ነው፡፡ ሸዋ ሮቢት በእርግጥ ስሙ ነው እንጂ ወደገጠር ይገባል፡፡በምጥ ስያዝ ሕክምናው ወዳለበት ማድረስ አልቻሉም፡፡ መጉዋጉዋዣውም ችግር ነው፡፡ እናም ለሶስት ቀን ያህል በምጥ ስሰቃይ ከቆየሁ በሁዋላ እንደምንም ብለው ወደሐኪም ሲወስዱኝ ከመንገድ ላይ ወለድኩኝ፡፡ በቃ ከተገላገለች ብለው ወደቤ መለሱኝ፡፡ ወደቤ ከተመለስኩ በሁዋላ ውዬ ሳድር ግን የተለየ ነገር አየሁኝ፡፡ ለካንስ ሽንን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ በቃ... በቤተሰቤ ዘንድ ሐዘን ሆነ፡፡ ባለቤም በጣም አዘነ፡፡ ቀደም ሲል ሁለት ልጆች የወለድኩ ሲሆን እነሱን ሳላሳድግ ...በቃ...ተበላሸሁ በሚል እጅግ በጣም አዘንኩኝ፡፡ ሌት ተቀን እንባዬ ይፈስ ጀምር፡፡ ሁኔታውን ሰዎች ሲሰሙ... ይርቃል...አዲስ አበባ ነው እንጂ ሕክምና እኮ አለ...ማለትን ሲሰማ ...በቃ ... ባለቤ አንጠልጥሎ ወደሐኪም አመጣኝ...አሁን እዚህ ከመጣሁ በጣም ተሸሎኛል፡፡ ...ድኛለሁ... ብዬ አስባለሁ፡፡..

በእርግጥም ከላይ ሀሳብዋን የገለጸችልን የሸዋ ሮቢቷ የፊስቱላ ታማሚ ሕመሙዋ የተሸላት ይመስላል፡፡ ምክንያቱም በምትናገርበት ወቅት ፊቷ ላይ የደስተኛነት ስሜት ይነበብባት ነበር፡፡ በሆስፒታሉ የመኝታ ክፍል ዞር ዞር ባልንበት ወቅት ሌላ ታካሚ አይናችንን ሳበች፡፡ ጠይም ...ቁመናዋ ረዘም ቀጠን ያለ ለግላጋ ነች፡፡ አይኑዋ ከብለል ከብለል ሲል ያሳዝናል፡፡ በእርጋታ የተሞላች ናት፡፡ አልጋዋ ላይ ሆና መጽሐፍ ታነባለች፡፡ እድሜዋን ስንጠይቃት አስራ ስምንት አመት እንደሞላት ገልጻልናለች፡፡ ቀሪውን ከእሱዋ አንደበት እናስነብባችሁ፡፡

.. ..እኔ የመጣሁት ከአፋር አካባቢ ነው፡፡ በእርግጥ የምኖረው በደቡብ ነው፡፡ በደቡብ ስኖር አንድ ቀን እናና ቤት ውስጥ ያሉ ሰዎች ወደገበያ ሲሄዱ አጎ በድንገት ደፈረኝ፡፡ እና ጽንሱን ለማስወረድ ብዙ ሞክራ ነበር፡፡ ነገር ግን ቀኑ ስለገፋ አልተቻለም፡፡ ከዚያ በሁዋላ ወደአክስ ጋ ወደአፋር ሄድኩ፡፡ በዚያም ከሁለት ቀን በላይ እያማጥኩኝ ነገር ግን ሊወለድ አልቻለም፡፡ ሕክምና አለ በተባለበት ቦታ ሁሉ ተሞክሮ አልሳካ ያለ ሲሆን በመጨረሻ ግን ወደ ናዝሬት መጥቼ ተገላግያለሁ፡፡ ሕጻኑም ሞቶአል፡፡ በሁዋላም ለአንድ ወር ቆይቼ ከተኛሁበት ስነሳ የሽንት መቆጣጠር ችግር አጋጥሞኛል፡፡ ቦታውን በማጠያየቅ በብዙ ችግር ወደአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል ለመድረስ ችያለሁ፡፡ አሁን እግዚአብሔር ይመስገን...ድኛለሁ፡፡ ..

ይህች ከሕጻንነት እድሜ ለመውጣት ጥቂት ቀናት የቀሩዋት ወጣት የምትድነው በምን ደረጃ እንደሆነ የሚታወቀው ሕክምናውን ስትጨርስ ነው፡፡ እንደ መረጃዎች እማኝነት በፌስቱላ ሆስፒታል የሚሰጠው የቀዶ ሕክምና 93 ያህሉን ሕመሞች ሙሉ በሙሉ ያድናል፡፡ በተከታይነት ስለሆስፒታሉ ስራ የሚያብራሩት ወ/ሮ ፌቨን ሐዲስ በሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ናቸው፡፡

”የሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ውጭ አምስት ተጨማሪ ሆስፒታሎችን በተለያዩ መስተዳድሮች እንዲቋቋሙ አስችሎአል፡፡ የአዲስ አበባው ዋናው ሆስፒታል ሲሆን በመቀሌ ፣ባህርዳር፣ ሐረር፣በመቱና በይርጋአለም የተቋቋሙት ሆስፒታሎች በሐምሊን ሆስፒታል ስር እንደቅርንጫፍ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡የእነዚህ አምስት ቅርንጫፍ ሆስፒታሎች መከፈት ምክንያትም ታካሚ የሆኑ ሴቶች የሚመጡት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደመሆኑ መጠን የሚደርስባቸውን የመጉዋጉዋዣ ፣የገንዘብ እና ሌሎችም እንግልት ለመቀነስና ጤንነታቸው እንዳይስተጉዋጎል በማሰብ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል የአልጋ ቁጥር አንድ መቶ ሀምሳ ብቻ ሲሆን አንድ ታካሚ በአማካኝ ከሶስት እስከ አራት ሳምንት ድረስ አልጋ ሊይዝ ይችላል፡፡ በአመት በአጠቃላይ ከሶስት ሺህ በላይ ኦፕራሲዮኖች የሚደረጉ ሲሆን ቅርንጫፍ ሆስፒታሎቹ ባይከፈቱ ኖሮ በአዲስ አበባው ብቻ ማስተናገድ አይቻ ልም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፊስቱላን በመከላከል ደረጃ የጤና መኮንኖች በአም ስቱም ሆስፒታሎች በአካባቢው ባሉ ወረዳዎች በመዝለቅ ታካሚዎችን ወደሆስፒ ታል እያመጡ እንዲታከሙ ስለሚያደርጉ ወደ አንድ ሺህ አምስት መቶ ያህሉን በክልሎች ማከም ተችሎአል፡፡

የህክምናውን አሰጣጥ ስንመለከት በሁሉም ቅርንጫፍ ሆስፒታሎች በቂ ችሎታ ያላቸው ባለሙያዎች ያሉ ሲሆን ነገር ግን በሆስፒታሎቹ አደረጃጀት እና በሙያተኞች መሟላትም የአዲስ አበባው ሆስፒታል ስለሚበልጥ አንዳንድ ከፍ ባለ ደረጃ መታከም የሚገባቸውን ታካሚዎች ወደ አዲስ አበባው እንዲያስተላልፉ ይደረጋል፡፡ በአመት ኦፕራሲዮን ከሚደረጉት ታካሚዎች ወደ 1 የሚሆኑት የሽንት ፊኛቸው በጣም ስለሚጎዳ እና ከተፈጥሮአዊው መንገድ ውጭ በሆነ መንገድ በፕላስቲክ ከረጢት ፈሳሽን የመቀበል ሕክምና ስለሚያስፈልጋቸው ከየትኛውም ቅርንጫፍ ሆስፒታል ወደ አዲስ አበባው ሐምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል ይላካሉ”ብለዋል፡፡

ከቅርንጫፍ ፊስቱላ ሆስፒታሎች በመቀሌ የሚገኘው ፊስቱላ ሆስፒታል በከፍተኛ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት የሚሰጡት የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር መላኩ አብርሀ እንደሚሉት...

“በ2005 ዲኤችኤስ ጥናት መሰረት በትግራይ ከፍተኛ የሆነ የፊስቱላ ታማሚዎች የሚገኙ በመሆኑ ቅርንጫፍ ሆስፒታሉ በሀገራችን በሁለተኛ ደረጃነት ካለ ፉት አምስት አመታት ወዲህ ለመከፈት ችሎአል፡፡ ትግራይን ጨምሮ በአካባቢው ባሉ ህብረተሰብ ክፍሎች መካከል  የኑሮ ደረጃ ዝቅ ማለት፣ የትምህርትና የስራ እድል አለመ ኖር የሚስተዋል ሲሆን ከዚህም የተነሳ ያለእድሜ ጋብቻ  እንዲተገበር ምክንያት ይናል፡፡ ያለእድሜ ጋብቻ ጥንቃቄ ለጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት ስለሚያልጥ ሴቶቹ ሰውነታ ቸው ሳይደረጅ እርግዝና ይከሰታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የህክምና ተደራሽነት... የመጉ ዋጉዋዣ ችግር ...ወዘተ ሴቶቹ በምጥ በሚያዙበት ጊዜ ፈጥነው ወደሆስፒታል እንዳ ይሄዱ ምክንያት ይሆኑዋቸዋል፡፡ በትግራይ ወደ 88  የሚሆኑት ሴቶች የሚወልዱት በቤታቸው ውስጥ ነው፡፡ በቤታቸው ከሚወልዱት ውስጥ አንዳንዶቹም በተራዘመ ምጥ ምክንያት ለፊስቱላ ሕመም ይጋለጣሉ” እንደ ዶ/ር መላኩ እማኝነት፡፡

ይቀጥላል

 

 

Read 2596 times Last modified on Saturday, 07 April 2012 07:57