Saturday, 14 April 2012 12:04

ፌስቱላ ...ቢያገልም ...ወዲያውን ይገልም...

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

ሴቶች በተለይም በገጠሩ ክፍል ከአርባ አመት በላይ የፌስቱላን ሕመም በመታመም ሳይፈወሱ፣ ከሰው ሳይደባለቁ ፣ወደ እምነት ተቋማት ሳይሄዱ ፣በሚያሳዝን ሁኔታ ተገልለው የሚኖሩበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ለዚህ ሕመም ብዙዎች የሚሰጡት ምክንያት ከባእድ አምልኮ ጋር የተያያዘ መሆኑን ወይንም እግዚአብሔር እንደተቆጣ እና የእድል፣ የኃጢአት ጉዳይ ተደርጎ ስለሆነ መዳን ወይንም መታከም የሚባለው ነገር እንደማይታሰብ ነው.....
ዶ/ር መላኩ አብርሀ...
ሐምሊን ፌስቱላ ኢትጵያ ከአዲስ አበባ ውጭ በአምስት ክልል መስተዳድሮች ቅርንጫፍ ሆስፒታሎችን የከፈተ ሲሆን ከአምስቱ መካከል የትግራይ ፌስቱላ ሆስፒታል አንዱ ነው፡፡ በትግራይ ፌስቱላ ቅርንጫፍ ሆስፒታል ከፍተኛ የቀዶ ሕክምና ባለሙያና የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር መላኩ አብርሀ እና የፌስቱላ ኢትጵያ የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ ወ/ሮ ፌቨን ሐዲስ እንዲሁም ታማሚዎ ችና በሆስፒታሉ  ለታካሚዎች የሙያ ስልጠና የሚሰጡ ባለሙያ ለዚህ እትም እንግዶች ናቸው፡፡ በቅድሚያ ዶ/ር መላኩ አብርሀ ስለሆስፒታሉ አገልግሎትና ስለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት የነገሩንን እናስነብባችሁ...
.. የ2005 /የዲኤችኤስ ጥናት እንደሚያሳየው 1.6 ማለትም ከአንድ ሺህ ወላ ዶች ወደ 16/ የሚሆኑት ፌስቱላ እንደሚያጋጥማቸው ነው፡፡ ይህ መረጃ የሚያሳየው በትግራይ አካባቢ ችግሩ ምን ያህል ስፋት እንዳለው ሲሆን ከዚህ ባሻገርም ትግራይ ለአፋር ፣ለአማራ ክልልና ለኤርትራ አዋሳኝ አካባቢዎች ቅርብ በመሆኑ የፌስቱላ 10 የሚሆኑት ታካሚዎች ከእነዚህ አጎራባች አካባቢዎች የሚመጡ ናቸው ፡፡ ቅርንጫፍ ሆስ ፒታሉ ሲከፈት ለትግራይ ብቻ ተብሎ ሳይሆን ለአጎራባች ክልሎችም ተብሎ ስለሆነ እየዋለ እያደረ ወደ 20  የሚሆነው ታካሚ ከወደአማራው ክልል ማለትም ...ደሴ ወልድያ ፣ቆቦ ፣አገው ምድር ፣ሰቆጣ ከመሳሰሉት አካባቢዎች ወደ መቀሌወ ፌስቱላ ሆስፒታል ይመጣሉ፡፡
በትግራይ ፌስቱላ ሆስፒታል በአንድ አመት ጊዜ በቀዶ ሕክምና ማገልገል የሚጠበቅብን ወደ 400/ ለሚሆኑ ሴቶች ሲሆን እስከአሁን የደረስነው ግን ወደ 280/ ገደማ ብቻ ነው፡፡ በእርግጥ የገንዘብም ሆነ የማሪያል ድጋፍ ችግር የለብንም ፡፡ሕክም ናውም በነጻ ይሰጣል ፡፡የመጉዋጉዋዣ አገልግሎትም በነጻ እንሰጣለን፡፡ 24 ሰአት ማገል ገል የሚችሉ ባለሙያዎችም በሆስፒታሉ ይገኛሉ፡፡ነገር ግን ሕክምናውን በሚመለከት ሕብረተሰቡ ጋ ያለው ግንዛቤ አናሳ በመሆኑ ተገልጋዩ ገና በተገቢው ሁኔታ ወደሕክም ናው እንዲቀርብ ግንዛቤው አላደገም፡፡
የሶስት እና አራት አመታት ሪፖርት እንደሚያሳየው ወደ 70  የሚሆኑት የፌስቱላ ታማሚዎች እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች ሲሆን ወደ 26  የሚሆኑት ደግሞ ከአስራ ስምንት አመት በላይ ነው፡፡ በህብረተሰቡ እንደሚገመተው ለፌስቱላ ምክንያት ከሚሆኑት የልጅነት ጋብቻ አንዱ ቢሆንም በአጠቃላዩ ግን በመው ለድ ጊዜ የሚፈጠር አስቸጋሪ ምጥ የሚባለው ፌስቱላን በገጠርም ይሁን በከተማ እንዲከሰት የሚያደርገው ዋነኛው ችግር ነው፡፡ አስቸጋሪ ምጥ ሲባል የልጁና የሴትየዋ ማህጸን ያለመመጣጠን አንዱ ምክንያት ሲሆን ልጁ የመቀርቀር ባህርይ ሲኖረው በወቅቱ በኦፕራሲዮን ካልተወለደ እና ለብዙ ሰአታት ከቆየ በአካባቢው ያለውን የደም ዝውውር ስለሚቀንስ ሴሎቹን በመግደል ከፊት ለፊት የሽንት ፊኛ ከበስተሁዋላ ደግሞ የሰገራ መውጫ ጫፍ ላይ ጫና በማድረግ የደም ዝውውሩ እንዲቆምና ሴሎቹ እንዲሞቱ ያደርጋል፡፡ በዚህን ጊዜ በማህጸንና ሽንት ፊኛ ወይንም በማህጸንና ሰገራ መውጫ መካከል ቀዳዳ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ ሲሆን በማህጸን በኩል ያለምንም ቁጥጥር ሽንት እና ሰገራ እንዲፈስ ስለሚያደርግ አስከፊ የሆነ ሽታን ይፈጥራል፡፡ በዚያም ሳቢያ የማህበራዊና ስነልቡናዊ ጫናን ከማስከተሉም በላይ ከፍተኛ የጤና ችግር እንዲከሰት ደርጋል፡፡፡፡..
-----------------////--------------
በአዲስ አበባ የሚገኘውን ሐምሊን ኢትዮጵያ ፌስቱላ ሆስፒታልን በጎበኘንበት ወቅት ታማሚዎችን አነጋግረናል፡፡ አንዱዋ እግርዋ እየተጎተተ ከፊት ለፊት ክብ የሆነ ብረት በግራና በቀኝ እጅዋ በመያዝ እየገፋች ትሄዳለች፡፡ እንዲህ አለች...
.. እዚህ የመጣሁት የፌስቱላ ታማሚ ሆኜ ነው፡፡ እድሜዬ አስራ ስድስት አመት ነው፡፡ መሔድ የማልችለው እግሬ ተሳስሮ አልሄድ ብሎ ነው፡፡ የመጣሁት ከጎንደር ሲሆን የህመሜ ምክንያት ወሊድ ነው፡፡ ምጥ ያመመኝ ለአራት ቀን ነው፡፡ በአካባቢዬ ያለው ሆስፒታል ሳይሆን ጤና ጣብያ ነው፡፡ እነርሱ ሊያዋል ዱኝ ስላልቻሉ ወደቤት እንድመለስ ተደረገ፡፡ በእርግጥ ጤና ጣቢያዎቹ ያማከሩን ሻል ወደአለ ሕክምና አገልግሎት እንድወድ ነበር፡፡ ነገር ግን ስለአልተቻለ ቤተ ሰቡ እያዘነ ወደቤት መልሰውኝ ...ያው...በአራት ቀኑ በግድ ሕይወት የሌለውን ልጅ ተገላገልኩ፡፡ ከዚያ በሁዋላ ግን እግሬ መቆም አልቻለም፡፡ እንደገናም ሽንቱ እየፈሰሰ አስቸገረ፡፡ ቤተሰቦቼ ወደዚህ ያመጡኝ እግርዋ እንኩዋን ቢሄድ ብለው እንጂ ሽንቱስ ይድናል ብለው አይደለም፡፡ አባ ሕክምና አለ ሲሉት ወደባህር ዳር ሆስፒታል ይዞኝ ሲሄድ የባህርዳር ሆስፒታል ደግሞ ወደዚህ አመጣኝ፡፡ ...ለካንስ ሕክምና ኖሮአል....
-----------------////--------------
ሌላዋ ታማሚ በጣም ቀጭን ትንሽ ቀይ ልጅ ናት ፡፡ፊቷ ላይ፣ ግንባ ርዋ፣ አገጩዋ ሁሉ በመስቀል ቅርጽ እና ክብ ቅርጽ ንቅሳት ተጊጣለች ፡፡ በንቅ ሳት ያስጌጧት ጉዋደኞቿ መሆናቸውን ነግራናለች፡፡ እድሜዋ አስራ ስድስት ነው፡፡ የመጣችው ድሀና ከሚባል ከወሎ አካባቢ ነው፡፡ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ ጨርቅ ላይ ጥልፍ ትሰራለች፡፡ ወደፌስቱላ ሆስፒታል የመጣችው በምጥ ምክን ያት ሽንትዋን መቆጣጠር ስላቃታት ነው፡፡ ምጥ በያዛት ጊዜ ወደሆስፒታል ለመ ውሰድ ቤተሰቦችዋ ቢሞክሩም አልተቻለም፡፡ገንዘቡም ውድ ከመሆኑም ሌላ የሚለ መንም አልተገኘም፡፡ ከአራት ቀን ምጥ በሁዋላ ግን እንደምንም ሕይወት የሌለው ልጅ ተገላግላለች፡፡ በዚያ ሳቢያ ግን የተከሰተውን ሕመም ለመግለጽ በጣም ትቸገ ራለች፡፡ በአጠቃላይም ...እግዚሐር ፈርዶብኝ እንጂ... የሚል ስሜት አላት... አንገ ቷን በምትሰራው ጥልፍ ላይ አቀርቅራ...፡፡..
-----------------////--------------
በሐምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ ለሕክምና የሚመጡትን የተለያዩ የእጅ ስራዎች ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኙት ወ/ሮ እጅጋየሁ እንደሚገልጹት ...
..ታካሚዎች ለሕክምና ወደ ሆስፒታሉ ሲመጡ ምንም እውቀት የሌላቸው ሲሆኑ የተለያየ የስልጠና ድጋፍ እየተደረገላቸው የተማሩትን የተለያዩ የእጅ ስራዎች ...ዳንል...የአንገት ሻርፕ...የጨርቅ ጥልፍ...ወዘተ በጥሩ ሁኔታ ይሰ ራሉ፡፡ የሰሩዋቸው የእጅ ስራዎችም በተለያዩ ጊዜያት ለሚመጡ እንግዶች በሽ ያጭ ላይ ስለሚውል የተሸጠበት ገንዘብ ተመልሶ የእጅ ስራውን ለሰሩት ልጆች ይሰጣል፡፡ ገንዘቡን የፌስቱላ ታማሚዎቹ የሚፈልጉትን ነገር ለመግዛት ያውሉ ታል፡፡ ገንዘቡን ከመጠቀም ባሻገር ግን ልጆቹ በጋራ ተቀምጠው ስለአካባቢያቸው እና ስለመሳሰሉት ሁኔታዎች በመወያየት ሕመማቸውን ሳያሰላስሉ በሰላም እንዲ ውሉ ይረዳ ቸዋል፡፡ከዚህም በላይ ድነው ወደየአካባቢያቸወ በሚመለሱበት ጊዜ እውቀቱን በዘላቂነት የሚጠቀሙበት ይሆናል፡፡..
በስተመጨረሻ ሀሳባቸውን የገለጹት የሐምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙ ነት ሓላፊ ወ/ሮ ሐዲስ ፌቨን እንደሚገልጹት ...
.. ፌስቱላ ከማህበረሰቡ ቢያገልም ነገር ግን ወዲያውን የማይገል ሕመም ነው፡፡ ስለዚህ ለሕክምና የሚመጡት ታካሚዎች እንደ ቲቪ ወይንም ወባ የመሳሰሉት ሕመ ሞች ቢኖርባቸው በፌስቱላ ሆስፒታል የሚቻል ከሆነ ሕክምናው ይሰጣቸዋል፡፡ የማይ ቻል ከሆነ ደግሞ ወደሌላ ሆስፒታል ሄደው መጀመሪያ ታክመው እንዲመጡ ከተደረገ በሁዋላ ነው ፌስቱላውን የሚታከሙት፡፡ ከዚህም በላይ እራሳቸውን እንዴት መርዳት እንዳለባቸው እንዲሁም የተለያዩ እውቀቶችን እንዲጨብጡ የተለያዩ ስልጠናዎች ይሰጣ ቸዋል፡፡ በስተመጨረሻም የፌስቱላው ሕክምና ተሰጥቶአቸው ከዳኑ በሁዋላ ወደ የአገራ ቸው ሲሄዱ የትራንስፖርት ክፍያ የሚሰጣቸው ሲሆን በአጠቃላይ በፌስቱላ ሆስፒታል የሚሰ ጠው ማንኛውም አገልግሎት ለሁሉም ተገልጋዮች በነጻ ነው፡፡ ሆስፒታሉ የሚፈ ልገው አገልግሎቱን የሚሹ ሁሉ ሕመሙ ሳይጠናባቸው በፍጥነት እንዲመጡ ብቻ ነው፡፡ ሲታከሙ ይድናሉ ፡፡..

Read 3716 times Last modified on Saturday, 14 April 2012 12:10