ማሃትማ ጋንዲ
(የህንድ መሪ የነበሩ)
እግዚአብሔር የላቀ ደረጃ ያለው የሂሳብ ሊቅ ነው፡፡ ዩኒቨርስን ለመገንባት በጣም የተራቀቀ ሂሳባዊ ስሌት ተጠቅሟል፡፡
ፓውል ዳይራክ
(የብሪቲሽ ሃኪም እና የኖቤል ሎሬት ተሸላሚ)
እግዚአብሄር የበቃ የጂኦሜትሪ ባለሙያ ነው፡፡
ቶማስ ብራውኔ
(እንግሊዛዊ ሃኪምና ፀሃፊ)
ተጣልተን እንደነበር አላውቅም እኮ፡፡
ሄነሪ ዴቪድ ቶሩ
(አሜሪካዊ ፀሐፊ - ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም እንዲፈጥር ሲመከር የመለሰው)
እግዚአብሔርን ሁሉ ነገር ላይ አየዋለሁ - የሩጫ ጫማም ሆነ ዓሳ ነባሪ ላይ!
ኬ.ዲ ላንግ
(ካናዳዊ ዘፋኝና የዜማ ደራሲ)
ጥቁር አገልጋዮችን እንዲሁም ጥቁር ህዝቦችን ጭምር ላስታውሳቸው የምፈልገው ፤ እግዚአብሄር የሰዎችን ችግር ለመፍታት ከመንግስተ ሰማያት ወደ ምድር የመምጣት ልማድ እንደሌለው ነው፡፡
ስቲፈን ቢኮ
(ደቡብ አፍሪካዊ ፖለቲከኛ)
እግዚአብሄር ባይኖር ኖሮ እኛ እንፈጥረው ነበር፡፡
ቮልቴር
(ፈረንሳዊ ፀሃፊና ፈላስፋ)
አስቡት ጌታ ፈረንሳይኛ ሲናገር! ከአንዳንድ የሂብሩ ቃላት በቀር እግዚአብሄር ፈፅሞ ሌላ ቋንቋ ተናግሮ እንደማያውቅ እርግጠኛ ነኝ - እጅግ ከተከበረው እንግሊዝኛ በቀር!
ክላራንስ ጄፓርድ ዴይ
(አሜሪካዊ ፀሐፊ)
የእግዚአብሄርን ተፈጥሮ ለማወቅ ራሱን እግዚአብሄርን መሆን ይጠይቃል፡፡
ጆሴፍ አልቦ
(ስፔናዊ የጁዳይዝም ፈላስፋ)