Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 21 April 2012 16:29

አምለሰት ስለ ፍቅር

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ቅዳሜ መስከረም 22 ቀን 1997

የተማሪ ፍቅር

ቅዳሜ መስከረም 22 ቀን 1997

የተማሪ ፍቅር

ሃይ ፍሬንዶቼ፡፡ አዳሜ ወንዴና ሴቴ ሰዌ ሁሉ ምን ያለው ፈጣጣ ሆኗል? እኔ መቼም አይን ቀቅሎ የበላ ለጉድ ሞልቷል ነው የምለው፡፡  “ምን ሆና ነው?” ብላችሁ ማሰባችሁን ወድጄላችኋለሁ፡፡ ልነግራችሁ አይደል? ዝም በይ ካላላችሁኝ እኮ ዝም አልልም፡፡ በያኔና በዛሬ መሃል ነው፡፡ ከአንዲት የት/ቤት ጓደኛዬ ጋር ፍጹም አንድ አይነት የሆነ የፍቅር ደብዳቤ ደረሰን፡፡ ሰምታችሁኛል? አቦ እንደማመጣ! - ስነስርአት ይኑራችሁ፡፡ ለሁለታችንም ከተለያዩ ልጆች አንድ አይነት ደብዳቤ፤ ሆ! ለካስ ነገሩን ስንሰማ... ማለቴ መቼም ሾካካ አይጠፋም፡፡ እንደተንሿከከልን ከሆነ ገንዘብ እየተከፈላቸው የሚያማምሩና የሴትን ልብ ሊማርኩ በሚችሉ ቃላት ያበዱ የፍቅር ደብዳቤዎችን ፈው የሚሸጡ ልጆች (“ደራሲዎች”) እንዳሉ ሰማን፡፡ እናንተም ስሙ - ከኛ፡፡ ያው እንግዲህ ለኔና ለዚያች ጓደኛዬ የደረሰን ደብዳቤም  “ከደራሲዎቹ “ የተገዛ መሆኑ ነው፡፡ ይሄ የታሪካችን መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ እንዳይመስላችሁ፡፡

አንድ ሃሳብ መጣልኝ፤ ደብዳቤውን ወደላከልኝ ልጅ መሄድ፡፡ የሷንና የራሴን ሁለቱንም ደብዳቤዎች ወሰድኩና አንድ ላይ አድርጌ፤  “ኦርጂናሉ ሌላ ሰው ጋር ደርሷል፡፡ ለኔ የደረሰኝ ኮፒው ይሆን? “ ብዬ መለስኩለት፡፡ ከዚያስ አትሉም? ከዚያማ መልሱ በሌላ ደብዳቤ መጣልኝ፡፡ መጀመሪያ ላይ እንዲያ በውብ ቃላት ያበደ የፍቅር ውዳሴ፤ በቆንጆ የእጅ ሁፍ ተከሽኖ፤ በሚያምር ነጭ ፖስታ እንዳልተላከልን፤ አሁን በተቦጫጨቀ አሮጌ ፖስታ ዶሮ የሞነጫጨረችው በሚመስል የእጅ ሁፍ መልስ መጣልን፡፡ እስቲ ከመጀመሪያው የፍቅር ደብዳቤ በጥቂቱ፤ በጣም በጥንጡ ልንገራችሁ፡፡  “የልቤ ንግስት ሆይ፤ ከወገቤ ጎንበስ ከአንገቴ ዘንበል በማለት በቅድሚያ ሰላምታዬን አደርስሻለሁ፡፡ ልእልት ሆይ፤ ልቤ በፍቅርሽ ጦር ተወግቶ መድማት ከጀመረ ወራቶች ተቆጠሩ፡፡ ዛሬ ግን ልቤ ሲፈራና ሲቸር እፎይ ማለት ቢያምረው በድፍረት ለመተንፈስ ቆረጠ፡፡ ውበትሽ ብርሃን ሆነና ያላንቺ ቀንና ሌቱ አልለይ አለኝ፡፡ የፍቅር ንግስት ሆይ፤ የሴቶች ቁንጮ መሆንሽን ታውቂያለሽ? አንቺ ለኔ በእሾሃማ አጥር የተከበበች እንቡጥ ጌሬዳ ነሽ፡፡ ዝምታሽና ብዙ ጊዜ ብቻሽን የመሆንሽ ነገር፤ ሰው እንዳይደፍርሽ... በቃ ላንቺ ታማኝ ዘቦችሽ ይመስሉኛል፡፡ ከሁሉም የሚገርመኝ... አምላክ በቀን መቶ ሴት እንዳላመረተ አንቺን ግን አመቱን ሙሉ “ምን ጎደላት?” እያለ ተጨንቆ መሥራቱን ሳስበው ግርም ይለኛል፡፡ የልቤ ናፍቆት ሁሌም አከብርሻለሁ፡፡ ስተኛም ስነሳም ለአምላኬ ፀሎቴን የማደርሰው ባንቺው አማላጅነት ነው፡፡ ግን ሰምተሽኝ ይሆን? የምሬን እኮ ነወ፡፡ አንቺኮ ለማሪያም ሩብ ጉዳይ ነሽ...” ...ምናምን እያለ ሲያንቆለጳጵሰኝ ሲያንቆለጳጵሰኝ... ምን ማለቂያ አለው? የእጅ ሁፉም የፖስታው ንጣቱም ያምር ነበር - የተገዛ የፍቅር ደብዳቤ ቢሆንም፡፡

በተጨረማመተ ፖስታ፤ በሙንጭርጭር ሁፍ ከመጣው ደብዳቤ ደግሞ ትንሽ ላቅምሳችሁ፡፡ “ማነሽ? እንትና! መቼም ስም አይገዛ? ረቂቅ አሉሽ? አንቸን ብሎ ረቂቅ! ትንቅንቅ ቢሉሽ አይሻልም ነበር? ስሚ፤ ቀን ካየሁሽ ማታ ስቃዥና ስበረግግ ማደሬን ላንቺ አልነግርሽም፡፡ ምክንያቱም ምን ያህል እንደምታስፈሪ ታውቂዋለሽ፡፡

የምትገርሚው አማረብኝ እያልሽ በዚያ ጭራሮ እግርሽ ሚኒ አድርገሽ ውንጥ ውንጥ ስትይ፡፡ ልብስ ጣል ተደርጎበት ተገልብጦ የቆመ የባላ እንጨት ትመስያለሽ - የምር፡፡ ከድንበሩ አፈንግጦ እንደፀበል ዕቃ ውጪ የሚያድረውን ጉጥር ሆድሽን ሳይ ደግሞ፤ እንዴ ትልቅ ዕንቁራሪት በሁለት እግሯ ቆማ ስትሄድ እዩ እያልኩኝ ለሰው አሳያለሁ፡፡

የምር በጣም ትመሳሰላላችሁ፡፡ እኔ ምለው ወገብሽና መቀመጫሽኮ ተለይቶ አይታወቅም፡፡ ኧረ ያንቺስ ይገርማል፡፡ ተፈልፍሎ የወጣ ወጥ ድንጋይ አይደል እንዴ የምትመስይው፡፡ ስለመቀመጫሽ ግን አይነሳ፡፡ እንዴ ኧረ አይነሳ፡፡ ልክ የተላገ ጣውላ - በቃ፡፡ መቼም ጉድሽ አያልቅም፡፡ በፈረስ ጭራ የተቀጣጠለው ፀጉርሽ ደግሞ አኪሩ የወደቀ ያረጀ አንበሳ አስመስሎሻል፡፡ የምር የጓደኝነቴን ልምከርሽና ስሚ፤ ተደበቂ፤ ሰው እንዳያይሽ ተደበቂ”... እያለ እያለ ይቀጥላል፡፡ እኛም እያነበብን እያነበብን... አቤት የሳቅነው ሳቅ፤ መቼም ደግሜ አልስቀውም፡፡ ቢሆንም ግን አላስቻለኝም፤ ማለቴ እግሬን፣ ፀጉሬን፣ ሆዴን እየተዟዟርኩ ለማየት መስታወት ፊት ተገትሬ መክረሜ አልቀረም፡፡ አሁንም ደብዳቤውን ባስታወስኩት ቁጥር አያስችለኝም ማለቴ ወደ መስታወት...፡፡ እስቲ ደግሞ ሳምንት እመጣለሁ፡፡ ዝም በይ ካላላችሁኝ፤ ዝም አልወድም አይደል?ነ

ጥቅምት 13 1997ዓ.ም

ሰባት A

መቼም ደንብ ነውና ዘው ተብሎ አይገባም፡፡ ዛሬም እንደትናንቱ ሰላምና ጤና ይበርክትላችሁ ይባላል፡፡ እኔም “እንዴት ሰነበታችሁ” በማለት በመልካም ምኞት እና በሰላምታ ወጌን ልጀምራ፡፡ ይሄውላችሁ አስራ ሁለተኛ ክፍል ደረስን፡፡ ጊዜዉ ይሮጣል ... የረፈደበትን አያሳውቅ የተኛን አይቀሰቅስ ... በቃ ቀርፋፋውን ትቶ እንደጉድ ይበራል፡፡ አዲሱ የትምህርት ፖሊሲ ሳይደርሰን ወይም ሳይደርስብን ማትሪክ የምንፈተን የመጨረሻዎቹ ተማሪዎች እኛው ነን፡፡ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ለመግባት (በሌላ አነጋገር ለከፍተኛ የትምህርት ገበታ ለመታጨት) ጥረታችን ተጧጡፏል፡፡ ለፍቅር ብዙም ትኩረት የምንሰጥበት ጊዜ አይደለም፡፡ “ምክንያትስ?” ብትሉ፤ ጠንክረን ካልሰራንና ውጤታችን ካላማረ “ድጋሚ ማትሪክ ልፈተን” የሚባል ነገር አይኖርም፡፡ እንደ ዲቪ ደጋግሞ መሞከር፤  ውጤት አሻሽላለሁ ብሎ ማሰብ ድሮ ቀረ - መጀመሪያውኑ ራስን አሻሽሎ ማቅረብ ሆነ ሚያዋጣው፡፡ በቃ፤ አዳሜ ተደፍታ መጮምጮሟን ተያያዘችው፡፡ ቢሆንም የለመድኩት አላጣሁም፡፡ የኔ ስም “ውበትሽ”፤ የአባቴ ስም “ብርሃን” ሆነ መሰለኝ፤ ደብተሩን ትቶ “የውበትሽ ብርሃን” ብሎ የሚጠራ አልቀረብኝም፤ አልቀረልኝም፡፡ ሰምታችሁኛል? እንደማመጣ፤ ስነስርአት ይኑራችሁ፡፡ ምን ታከብዳለች ስትሉ ሰማሁ መሰለኝ፡፡ ብቻ “የውበትሽ ብርሃን” የምትባይው፤ ከመብራት ሃይል(ኤልፓ) ጋር ለመወዳደር ነው ወይ እንዳትሉ፡፡ እስቲ ስሙኝ፡፡ በቼም ዝም በይ ካላላችሁ ዝም አልልም አይደል? እናላችሁ የማትሪክ ፈተና በተቃረበበት ቀውጢ ግዜ ምን ሆንኩ መሰላችሁ? ምን ልበላችሁ፤ በቃ ተወደድኩኝ፤ የምር ተፈቀርኩኝ፡፡ ደግሞ ከጩጬነት ፍቅር ከፍ የሚል የፍቅር አይነት ነው፡፡ ለምን? ብትሉ “እኔ እኮ ለቁም ነገር ነዉ ምፈልግሽ” የሚል ነዋ ጥያቄው፡፡ የጩጬነት ፍቅርኮ፤ ቦርሳችንን እንዳነገትን በእረፍት ሰአት እጅ ለእጅ ተያይዞ በቀስታ መራመድ ብቻ ነው፡፡ ግን ቀላል እንዳይመስላችሁ፡፡ አይ አያ ፍቅር፤ በስንቱ ጩጬ ልብ ውስጥ ጐጆውን ቀልሶ የቤት ባላባት ሆነ!  ልንገራቹሁማ፤ ወሬ ትወዱ የለ? በመፈቀሬ ካልቀናችሁ በቀር ስሙኝ፡፡ የክፍሌ ልጅ ነው ሚስኪኑ ተማሪ - መልከመልካም፡፡ በቃ አለቀለት፤ በፍቅሬ ወጥመድ ውስጥ ገብቶ አረፈው፡፡ “ምስኪን”፤ የኔን “ብርሃን” ፍለጋ አይኑ ሲንከራተት፤ ልቤ ያዝንለታል፡፡ ጐበዝ ተማሪ አይደል? አንዳንድ ጥያቄዎችን አብረን ስለምንሰራ የእጅ ሰላምታ አለን፡፡ እሱ ከፊት ወንበር ይቀመጣል፡፡ እኔ ደግሞ ከጓደኞቼ ጋር ሶስተኛ ዴስክ ላይ ነኝ፡፡ ድሮኮ አይኖች ከብላክቦርድና ከደብተር ተነቅለው አያውቁም፡፡ አሁን ግን ትምህርቱን መከታተል ትቶ ከአንደኛው ፔሬድ እስከመጨረሻው አንገቱን ጠምዝዞ እኔን ሲያይ ይውላል፡፡ አንገቱ አለመቀንጠሱ ቢገርመኝም ልቤ ብቻ ሳይሆን ሆዴና ኩላሊቴም ያዝንለታል፡፡ ለጓደኞቼ ግን መቀለጃ ሆኗቸዋል፡፡ እየዞረኮ አያይሽም፤ ሲፈጠር አንገቱ ዞሮ ነው የተሰካው ይላሉ፡፡ መቼም መፈቀር ቀላል እድል አይደለም፡፡ ሲያሸማቅቅስ ብታዩ? ልንገራችሁ አይደል፤ አስተማሪ እያለም አስተማሪ ሳይኖርም ሁሌ እየዞረ ሲያየኝ (ይቅርታ ሲያፈጥብኝ) ቀላል አያሸማቅቀኝም፡፡ በመሸማቀቅ ቢያልፍልኝስ ጥሩ አልነበር? የትምህርት ቤቱ ወሬ ሆነ፡፡ የተማሪና የአስተማሪ መጠቋቆሚያ ሆኜ አረፍኩት፡፡ የምገባበት አጥቼ፤ ጨነቀኝ ጠበበኝ እላችኋለሁ፡፡ ጭንቀት በጭንቀት ስሆን አላሳዝንም? እስከዛሬ የማውቀው “የወደደ አበደ” ሲባል ነው፡፡ በኔ ላይ የደረሰው ግን “የተወደደ አበደ” የሚል ሆነ፡፡ እኔ አልወደድኩትም አላልኳችሁም፡፡ እንዴት መሰላችሁ? ከአፍቃሪዬ የደረሰኝን የመጀመሪያውን  የፍቅር ደብዳቤ ብታዩ ነበራ፡፡ እኔ አድንቄዋለሁ፡፡ የደብዳቤዉ ይዘት ልብወለድ ቢመስልም ልብን የሚነካ ነው፡፡ ልጁ የሴትን ፍላጐት በሚገባ ያወቀ፤ ሰውን እንደየባህሪው የመቅረብ ተሰጥኦ ያለው መስሎ ሳይሆን ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ እሱነቱን ለማወቅ መመራመር አላስፈለገኝም፤ አይኑን ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡ ያው እንደምታውቁት፤ ልቤ ደንዳና ሆነና በቀላሉ ለፍቅር አይንበረከክም፡፡ እንደውም የቅርብ ጓደኞቼ የረቂቅ ልብ እንደ ኢትዮጵያ መሬት በቅኝ ግዛት ያልተገዛ፤ ድንበሩ የማይደፈር እያሉ ያወራሉ - ለጨዋታ ያህል ቢሆንም፡፡ የልጁ የደብዳቤ አፃፃፍ ግን፤ ከገዳም ያስመንናል፡፡ ከኔ ጋር ገጥሞ አልሆነለትም እንጂ፤ ሚስኪን! እሱም ሳይታወቀው አልቀረም፤ ደብዳቤዎቹን “ከርታታዉ” በሚል ርእስ ነው የሚፍልኝ፡፡ ግን ተስፋ አይቆርጥም፡፡ ልሳቅ ልዘን አላውቅም እንጂ አንድ ገጠመኝ ልንገራችሁ፡፡ ታዲያላችሁ፤ አካፑልኮ የተሰኘው ተከታታይ የፍቅር ፊልም በኢቲቪ ይተላለፍ ነበር፡፡ ሁለት ዋና ገፀባህሪያት ቶኒና ሪቼ፤ ማለት በቃ በፍቅር የቀለጡ፤ ነገር ግን በመሀከላቸው እንከን የተጋረጠባቸው ናቸው፡፡ ፊልሙ ውስጥ የቶኒ ዘበኛና ተላላኪም አለ - መርቲን የተባለ ሕንዳዊ ተቀጣሪ፡፡ አንድ ቀን “ከርታታው” ወዳጄ ከቦታው ተነስቶ ወንበሬ ድረስ በመምጣት ስለታሪኩ በጥቂቱ አወራልኝ፡፡ ጎበዝ ተራኪ ነው፡፡ ታሪኩን ከጨረሰ በኋላ፤ “አንቺ ሪቼን ትመስያለሽ፤ እኔ ማንን እመስላለሁ?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡ አሰብኩና እሱን የሚመስል ሰው ፊልሙ ውስጥ አጣሁ፤ ግን ጠይምነቱ ወደ ህንዳዊው ማሪቲን ስላደላብኝ “ማርቲንን” አልኩት፡፡ እውነቴን ነው ተንኮል አስቤ አይደለም፡፡ እሱ ግን አውቄ ዝቅ ያደረግሁት መሰለው፡፡ ለምን፤ “የሪቼ ፍቅረኛ ቶኒን ትመስላለህ አላለችኝም?” በማለት ተከፋብኝ፡፡ ጭራሽ ወሬውን የሰሙ ልጆች አሾፉበት፡፡ ምን ይሄ ብቻ? ከዚያን ቀን ጀምሮ ቅጽል ስሙ መርቲን ሆነ፡፡ የሚገርመው “ከርታታው” እያለ ደብዳቤ መፃፉን አላቆመም፡፡ እንዲያውም ከቀን ወደ ቀን እየባሰበት ሄደ፡፡ እየዞረ ማየቱም እንዲሁ፡፡ የሱን ጭቅጨቃ ማስተናገድ፤ የተማሪና የአስተማሪ መጠቋቆሚያ መሆን ቢያስጨንቀኝ፤ ዘዴ ፈለግኩኝ፡፡ ለኔም ለሱም ይበጃል፡፡ ልጁም “የውበትሽ ብርሃን” እያለ የወደፊት ሕይወቱ ቢጨልም ጥሩ አይደለም፡፡ ዘዴ አላጣሁም፡፡ መቼም እራሴው ሄጄ ላነጋግረዉ እንደምፈልግ ስገልለት እንዴት በደስታ እንደፈነጠዘ አትጠይቁኝ፤ ዝም ብሎ ይስቃል፤ የእጁን ጣቶች ያፋትጋል፡፡ ግራ ገብቶኝ፤ ልታነጋግረኝ አትፈልግም? ብዬ ጠየኩት፡፡ “እንዴ እፈልጋለሁ” አለ እንደምንም - ቆይቶ “በጣም” ሲል አከለበት፡፡

“ስማኝ፤ የማትሪክ ፈተና የምንወስድበት ጊዜ ተቃርቧል፡፡ አንተ

 

 

Read 7685 times Last modified on Saturday, 21 April 2012 16:58